ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል አስራ ዘጠኝ
12.8 ሺርክ ህይወትና ገንዘብን ሀላል ያደርጋል
የአላህ መልክተኛﷺአንድ ሰው ገንዘቡ እና ህይወቱ በምን መንገድ ጥበቃ እንደሚነሳበት እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል ፦
“ሰዎችን እንድታገላቸው ታዝዣለሁ።ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ እውነተኛ አምላክ የለም ብለው እስኪመሰክሩ ድረስ።ይህን ካሉ ነፍሳቸው፣ገንዘባቸው የተጠበቀች ትሆናለች።የእስልምና መብት ሲቀር(የገደለ መገደልን ይመስል)...”
12.9 ሺርክ ምድርንያበላሻል፣ያወድማል
በዋናነት ምድር የምትበላሸው በሽርክ ነው።ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይለናል፦
وَلَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَٰحِهَا وَٱدْعُوهُ خَوْفًۭا وَطَمَعًا ۚ إِنَّ رَحْمَتَ ٱللَّهِ قَرِيبٌۭ مِّنَ ٱلْمُحْسِنِينَ
በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ፈርታችሁና ከጅላችሁም ተገዙት፡፡ የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና፡፡(አል አዕራፍ 56)
ምድር የምትስተካከለው ነብያት ይዘውት በመጡት መልክት ነው።ነብያት ይዘውት የመጡት መልክት ደሞ ተውሒድ ነው ። ዛሬ አለም ሰልጥኗል ይባላል ነገር ግን አብዛኛው ሰው ብቸኛው ፈጣሪ በብቸኝነት ያመልካል ወይ?ፈጣሪውን ይፈራል ወይ ? ብቸኛውን ሲሳይን እና ሌሎች ነገሮችን ለጋሽ የሆነውን ብቸኛ አምላክ ያመሰግነዋል ወይ ?ፈጣሪውን ያውቀዋል ወይ ? አላህ ለአለማት እዝነት አድርጎ በላካቸው ነብዩ ﷺ መልክት ይሠራበታል ወይስ ስሜቱን ተከትሎ ያልታዘዘውን ይሰራል ? እና የመሳሰለው ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ አሳዛኝ ነው ሚሆነው።ዝሙት፣ገብረሰዶም፣ቁማር፣ ወለድ መስፋፋታቸው ምድርን ካበላሸ፣በአላህ ላይ ማጋራት እማ የባሰ ምድርን ማበላሸት ነው የሚሆነው። አላህ ምድርን ከማበላሸት ይጠብቀን።
13. በችግር ጊዜ አላህን እያመለኩ በሰላሙ ጊዜ ማጋራት ተውሒድ አይባልም
ነብዩ ﷺ ጋር የተዋጉት የመካ አጋሪያን በችግር ጊዜ አላህን ብቻ የጠሩ ነበር ።ሆኖም ግን ይህ በችግር ጊዜ ብቻ እሱን (አላህን ብቻ) መለመናቸው አማኝ አላስባላቸውም።አላህ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦
فَإِذَا رَكِبُوا۟ فِى ٱلْفُلْكِ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمْ إِلَى ٱلْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ
በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡(አል ዐንከቡት 65)
በዘመናችን ሺርክ ላይ የወደቁ ሰዎች ግን ጥፋታቸው ቦታና ጊዜ እንኳን አይመርጥም። ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ በሰላሙም ጊዜ በችግርም ጊዜ ከአላህ ውጭ ላሉ አካላት አምልኮን ሲፈፅሙ ይታያሉ።ቀናትን ማምለክ አስመልክቶ እንደ አካባቢው ቢለያይም ዋና ዋና የሆኑት የሚከተሉት ናቸው። ለምሳሌ ፦ሰኞ እስነይን፣ማክሰኞ የመገርገቢያው ፣እሮብ የጄይላኒ፣ሃሙስ የነቢ እድሪስ፣ቅዳሜ የሰይድና ኸድር፣እሁድ የፈቂህ አሊ ሙዝ ወዘተ በማለት ያለገደብ ሺርክ ይፈፅማሉ።የተፈጠሩት ግን በሰላሙም በችግሩም ጊዜ አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ነው።
✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 38-40)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide