ETV_Zena_Entertainment🇪📺#


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


#https://t.me/Zadomuler

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Guysoch beklalu birr magengt kflgu awnunu linkun tchanut ewneteynow melachu mokurt kalwen tetawlachu
https://share.influencersearn.com/dashboard/register.php?referral=Mulualem


Addis መረጃ:
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 805 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,786 የላብራቶሪ ምርመራ 805 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 78 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 16,615 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 263 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,763 ናቸው።
👇👇👇👇👇
@addis_tv


ኢትዮ-መረጃ-NEWS:
#UPDATE

✅ሐምሌ 20/2012 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር መዋለቸውን BBC ዘገበ።

✅የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሃመድ እንደገለጹት ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በትላንትናው ዕለት ነው።

✅እንደ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገለፀ ከሆነ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከመፈጸማቸው በፊት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል እርምጃ እየወሰደባቸው ነበር።

✅እርምጃውን ተከትሎ ተበታትነው በመንቀሳቀስ 13 ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ጠቁመዋል።

✅ከጥቃቱ በኋላ በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ 20 ሰዎች ትናንት መያዛቸውን አቶ አብዱላዚዝ አስታውቀዋል። ግለሰቦቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 12 መሣሪያዎችም መያዙን ነው የተናገሩት

BBC
ethio_mereja_news

ethio_mereja_news


TIKVAH-MAGAZINE:
#DSTV
ኢ.ኤስ.ፒ,ኤን ወደ ዲኤስትቪ ተመልሷል ቻናል 218 / 219

ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት የገንዘብ እጥረት ገጠመው

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ)የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለስደተኞች አስፈላጊ የሆኑ የምግብ፣የትምህርት፣ የጤናና የመጠለያ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከሚያስፈልገው 385 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 72 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማግኘት መቻሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከፈረንጆቹ ሰኔ 30 ጀምሮ ኮሚሽኑ ከ766ሺ በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በኢትዮጵያ በስተኞች ካምፕና በስድስት ክልሎች ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ ቀጥሎ በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ - #AlAin

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች በብድር ለገዢዎች ሊቀርቡ ነው!

ለወጣቱ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል የተበረለ ባለሦስተ እግር ተሽከርካሪዎች በብድር ለማቅረብ ቫዮ ኦቶሞቢል የተባለ በሀገር ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን የሚገጣጥም ተቋምና ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ቫዮ ኦቶሞቢል በቀን 50 ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ የሚገጣጥም ሲሆን የወቅቱ ዋጋቸውም 175,000 ብር ተገምቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ 75,000 ብር ቅድሚያ በመክፈል መግዛት እንደሚቻልና ቀሪ 100,000 ብሩ በሁለት አመት ውስጥ እንዲከፍሉ ተመቻችቷል ተብሏል፡፡

አንድ የ7,000 ብር ደሞዝተኛ ለሁለት ገዢዎች ዋስ መሆን የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የመድን ዋስትናም ተገብቶላቸዋል፡፡ አገልግሎቱም በቅርቡ የሚጀመር መሆኑን ነው ሁለቱ ድርጅቶች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቁት፡፡

#ShegerFM
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ኢትዮ ቴሌኮም በጀት ዓመቱ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ አገኘ!

ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም ካገኘው ትርፍ ላይም 11 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ግብር መክፈሉም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል። ትርፉ ከቀዳሚው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ31 ነጥብ 4 ብልጫ እንዳለውም ተመላክቷል።

በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 46.2 ሚሊዮን ደርሷልም ብለዋል። የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 44.5 ሚሊዮን፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 23.8 ሚሊዮን፣ የብሮድባንድ ደንበኞች ብዛት 212.2 ሺ እንዲሁም የመደበኛ ስልክ 980 ሺ ደንበኞች አሉትም ተብሏል።

#አዲስማለዳ #EthioFM
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ከ4.1 ቢሊዮን ችግኞች በላይ መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታወቁ!

በዚህ ዓመት በአረንጓዴ አሻራ ሂደት አጋማሽ በሀገሪቱ ከ 4.1 ቢሊዮን ችግኞች በላይ መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። የአረንጓዴአሻራ ሂደት በኢኮኖሚው እና በሥራ ፈጠራ እንቅስቃሴው ላይም ቀጥተኛ ተፅዕኖ ስለሚኖረው የመንግሥት ዋነኛ የትኩረት እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡

@etv_zena @etv_zena


TIKVAH-MAGAZINE:
የክረምት የችግኝ ተከላ መርኃግብራት:-

- በድሬደዋ አስተዳደር በአንድ ጀንበር 2 መቶ ሺህ ችግኝ የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡ በድሬደዋ አስተዳደር ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ከተያዘው መርሀ ግብር በዛሬው እለት በአስተዳደሩ 2 መቶ ሺህ ችግኞች ተተክለዋል ተብሏል፡፡

- በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀንበር 304 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የችግኝ ተከላ ስራው በዛሬው ዕለት ተከናውኗል። በዛሬው ዕለት እየተተከለ ያለውን እና የተተከሉ የቡና ችግኞችን ሳይጨምር በክልሉ እስካሁን 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን የኦሮሚያ እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ የገለጹ ሲሆን በአጠቃላይ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች በክልሉ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

- የሶማሊ ክልል 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ለመትከል ማቀዱንና እሰከ አሁንም 2 ሚሊየን 358 ሺህ ችግኞች መተከላቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገልፀዋል። ቀሪ 1 ሺህ 441 ሺህ ችግኞችን በተቀመጠው ግዜ ሰሌዳ ዉሰጥ እንደሚተከሉም አሳውቀዋል።

- በሲዳማ ክልል ከ215 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝና እስካሁንም 147 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መስፋን ቀሬ ገልጸዋል።

#ENA #FBC #DW
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

"የማንነት ፓለቲካና የኢትዮጵያ ሚዲያ" ሚል ርዕስ ከጋዜጠኞች ጋር እና ከመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ጋር ዛሬ የተደረገውን ውይይት ተከታትለን ተከታዩን አሰናድተናል። ሊንኩን ተጭነው ማንበብ ይችላሉ
@etv_zana

tikvahethmagazine tikvahmagBot


እንግሊዝ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ የመሬት አስተዳደር ሥራዎችን ጨምሮ የሥራ ዕድል ለማስፋፋት የሚያግዙ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሞችን ለማስፈጸም የሚያግዝ 105 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ወይም 4.71 ቢሊዮን ብር ዕርዳታ መስጠቷን መንግሥት አስታውቋል፡፡

#Reporter
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

1441ኛው የዓረፋ በዓል የፊታችን ዓርብ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሀጂ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ በሰጡት መግለጫ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በመተጋገዝ እና በትብብር እንዲሁም ራሱን ከኮሮናቫይረስ በመጠበቅ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ኢትዮጵያ በሁለተኛነት በተፈለፈለው የአንበጣው መንጋ እየተቸገረች ነው

ኬንያ የበርሃ አንበጣን ለማጥፋት በሚያስችል አቋም ላይ እንደምትገኝ የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) አስታውቋል፡፡ በመንጋው ከተጠቁ 29 የሃገሪቱ አካባቢዎች 20ዎቹ ነጻ መሆናቸውን ነው የተነገረው፡፡ ሀገሪቱ በቀጣዩ ሦስት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ ከመንጋው ነጻ ልትሆን እንደምትችል ተገምቷል፡፡

የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ መከላከል (ሬዚሊዬንት) ቡድን መሪ ሲሪል ፌራንድ በናይሮቢ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ በሁለተኛነት በተፈለፈለው የአንበጣው መንጋ እየተቸገረች እንደምትገኝ የተናገሩ ሲሆን ከኬንያ በፈለሰው መንጋ በከፊል መቸገሯንም ገልጸዋል፡፡ - #AlAin

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የምስራቅ አፍሪካን  የምግብ  ቀውስ ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃ ያስፈልጋል ተባለ

(በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቀረበ )

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት ውስጥ በዚህ አመት ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ኢጋድ፣ ፋኦና የአለም ምግብ ድርጅት የምግብ ዋስትና በጋራ በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል።

እንደ መግለጫው በምስራቁ ክፍል ወደ 28 ሚሊዮን ዜጎች ለዚህ ችግር እንደሚጋለጡ እና በዓለም ዙሪያ ካለው ጠቅላላ የምግብ ዋስትና ችግር ካለባቸው ውሳጥ 20 በመቶውን እንደሚይዝ ነው የተነገረው።

ከሰኔ እስከ መስከረም ባሉ ወራት በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ምስራቅ ደቡብ ሱዳን፣ሱዳን ፣ምዕራባዊ ኬንያ እና ሰሜናዊ እና መካከለኛው ኡጋንዳ ለተጨማሪ የጎርፍ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው ሊጨምር እንደሚችል የአየር ሁኔታ ትንበያዎች እንደሚያሳዩ ኢጋድ አስታውቋል፡፡

በአባል አገራቱ እስካሁን ከ 47 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸው ነው የገለፀው፡፡ በቀጣይ ሰባት የኢጋድ አባል አገራትን የምግብ ደህንነት፣አኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል የሰብዓዊ ፍላጎቶች ድጋፍ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት መንግስት የሚያደርገው እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

Readmore https://telegra.ph/ENA-07-29

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ENA
የምስራቅ አፍሪካን  የምግብ  ቀውስ ለመከላከል አስቸኳይ እርምጃ ያስፈልጋል ተባለ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ሀገራት ውስጥ በዚህ አመት ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ በአካባቢው በቅርቡ የተከሰተው ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ ብቻ ሀገራቱን ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ቀውስ መዳረጉ ታውቋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ፤ፋኦ እና የአለም ምግብ ድርጅት  የምግብ ዋስትና ቀውሱን ለመከላከ...


በጉባ ወረዳ አቡጃር ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት 14 ሰዎች ተገደሉ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በትናንትናው ዕለት 14 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ። ሌሎች ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን የክልሉ ኮምዩንኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው የሐዘን መግለጫ አስታውቋል።

በመግለጫው መሠረት ግድያው የተፈጸመው ትናንት ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ አቡጃር ቀበሌ ከምሽቱ 2፡00 ገደማ ነው። 

ጥቃቱ በታጠቁ ሽፍቶች መፈጸሙን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ ኩምሳሪ እንደተናገሩ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል።

የአማራ ክልል መንግሥት ለጥቃቱ “ጽንፈኛ ኃይሉ ተልእኮ የሰጣቸው፤ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚንቀሳቀሱ ” ያላቸውን ኃይሎች ተጠያቂ አድርጓል - #DW

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች!

ተማሪዎች ወደ ሚማሩበት የትምህርት ተቋም መመለሻ ጊዜ ታውቋል በሚል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ስም (የዩኒቨርሲቲዎችን ሎጎ አስመስሎ) የተዘጋጁ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች /የትምህርት መርሃግብርን የሚያሳዩ ምስሎች/ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

እስካሁን የኢፌዴሪ ሳይንሳና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው የሚመለሱበትን ቀን ያላሳወቀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ወደፊት የምናገኛቸውን መረጃዎች እናካፍላችኃለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial

ዲኮደሮን ቤት ድረስ በነጻ እናደርሳለን
☎️ 6116

ውድ የፈረስ ደንበኞቻችን ወደ ቀድሞ ስራችን ተመልሰናል እርስዎም መተግበሪያውን ወይም በጥሪ ማዕከል ቁጥራችን 6090(በደቂቃ 50 ሳንቲም ብቻ) በመጠቀም ወደ አሻዎት ቦታ ይንቀሳቀሱ::

ለፕሌይስቶር ወይም ለአፕስቶር ይህን ሊንክ ይጠቀሙ👇
http://onelink.to/jzr2aq

ፈረስ ያደርሳል!

#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!

✍ቅንነት ይነገራል ፣ ቅኖች ይመሰገናሉ ፣ ምክንያታዊ ዳሰሳዎች በሀገርና በአለም ትዕይንቶች ላይ ይቀርባሉ፡፡
መነሻችንም መድረሻችንም ቅንነትን ያነገበ በምክንያታዊነት የሚመራ በሀገር ፍቅር የተሞላ ትውልድ ማፍራት ነው፡፡

# ቅንድል_ኢትዮጲያ

አውርደው ያንብቡ https://bit.ly/3f3uU57

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

በተለያዩ ፊልሞችና የዘፈን ክሊፓች ላይ የጸጥታ አካላትን መለዮ በመልበስ የተቀረጹ ቪዲዮችን ቆራርጦ በማውጣት ያልሆነ ስያሜ በመስጠት ለተለየ ዓላማ ማዋል ተገቢነት የለውም፡፡ በማህበራዊ ሚዲያው ላይም ከሚሰራጩ መልክ ቀይረው የሚሳሉ ሀሰተኛ ዘገባዎች አሉና ተጠንቀቁ፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የኮንሶና የአሌ ተፈናቃዮች የርዳታ ጥሪ!

( በጀርመን ድምጽ ራዲዮ የቀረበ )

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ክልል በኮንሶና በአሌ ማህበረሰብ አባላት መካከል የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አንገኛለን አያሉ ነው።

ተፈናቃዮቹ እንዳሉት በግጭቱ ከአካባቢያቸው በመሽሽ በተለያዩ ስፍራዎች ከተጠለሉ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። በግጭቱ የመኖሪያ ቤቶቻችንና የእህል ጎተራዎቻችን በአሳት በመውደማቸው በቂ ድጋፍ ባለማግኘታቸው በሜዳ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን የበና ፀማይ ወረዳ አመራሮች ግጭቱን ሸሽተው ወደ አካባቢው የገቡ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለበላይ አካላት ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የኮንሶ ዞን ባለስልጣናት በበኩላቸው አሁን በስፍራው አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነ በመምጣቱ የኮልሜ ክላስተር በተባለው አካባቢ ለተፈናቀሉት ጊዜያዊ የምግብ ድጋፍ ማቅረብ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

45 ሚሊዮን የሚጠጉ ደቡብ አፍሪካውያን ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ

45 ሚሊዮን የሚጠጉ ደቡብ አፍሪካውያን በድርቅ፣ በጎርፍና በኮሮናቫይረስ ምክንያት ረሃብ እንደተጋረጠባቸው 16 አገራትን የሚወክለው ቀጠናዊ ቡድን አስታወቀ።

በአገራቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ሥራ አጥነት እየጨመረ፣ ንግዶች እየተቀዛቀዙ እንዲሁም ከባህር ማዶ የሚላክ የውጪ ምንዛሬ እየቀጨጨ መሆኑም ተጠቅሷል።

ዜጎች መሰረታዊ የቤት እቃቸውን በመሸጥ ምግብ እየገዙ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጠናው ትምህርት ቤት በመዘጋቱ ምክንያት 20 ሚሊዮን ታዳጊዎች ከትምህርት ቤት ምገባ ቀርተዋል።

በተያያዘ ዜና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) 4 ነጥብ 2 ቢልዮን ዶላር ለደቡብ አፍሪካ ብድር አጽድቋል፡፡ ብድሩ በወረርሽኙ አመካኝነት ጫና ላረፈበት የአገሪቷ ኢኮኖሚ ማገገምያ፣ ደካማ የጤና ስርአትና ፊለፊት ቫይረሱን ለተጋፈጡት የጤና ባለሙያዎች መደጎምያ ይውላል ተብሏል፡፡ -#BBC

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#AddisAbaba

የፊታችን እሁድ ሐምሌ 26 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር ከሁለት ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡ በመርኃግብሩም ወጣቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም በከተማዋ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ እስካሁንም በከተማዋ ከ4.3 ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉ ነው የተነገረው፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#HappeningNow

"የማንነት ፓለቲካና የኢትዮጵያ ሚዲያ" ሚል ርዕስ ከጋዜጠኞች ጋርና ከመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ጋር በሂልተን ሆቴል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይቱም በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የመወያያ ጹሑፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot


||Markdawn|| dan repost
Temert endgemer
Sel ter astela'fwal temert menesteru
More manbebe kflgu@❤echanut


📌| አርሰናል የስፔናዊዉን የመሀል ስፍራ ተጫዋች የዉሰት ዉሉን በአንድ ዓመት ተጨማሪ የዉሰት ዉል ማቆየት ይፈልጋል።

👉| በማይክል አርቴታ የሚሰለጥነዉ የሰሜን ለንደኑ አርሰናል የስፔናዊዉን የመሀል ስፍራ ተጫዋች ዳኒ ሴባዮስን ዉል በአንድ ተጨማሪ ዓመት ማራዘም ይፈልጋል።

👉| ተጫዋቹ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ስፔን በመመለስ ለሪያል ቤቲስ በዉሰት ሊሰጥ ይችላል ተብሎ ሲነገር ነበር።

@SkysportEt @SkysportEt

የሚድልስብሮ ቀጣይ አሰልጣኝ ...

👉|የሚድልስብሮው ሊቀ መንበር ስቴቭን ጊብሰን ኒል ዋርኖክ ቀጣዩ የክለቡ አሰልጣኝ እንደሚሆን አረጋግጧል።

👉| ክለቡ በሻምፒዮንስ ሺፕ በዚህ አመት 17ኛ ደረጃ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

@SkySportEt @SkySportEt

🇪🇹ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታዮች ዛሬ ለቻናላችን አዲስ ሎጎ አሰርተናል። ለቻናላችን ይሄ ሎጎ ተስማሚ ነው ትላላችሁ? 👍👍👍

@SkySportEt @SkySportEt

📌|በዘንደሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ሬቲንግ በአንድ ጨዋታ ካስመዘገቡት መሀል ኬቭን ዲ ብሮይን ቀዳሚዉ ነዉ፦

👉| ቤልጄሚያዊዉ የማንችስተር ሲቲ የመሀል ስፍራ ሞተር ኬቭን ዲ ብሮይን ማንችስተር ሲቲ 8 - 0 ዋትፎርድን ሲያሸንፍ ያስመዘገበዉ ቁጥራዊ ማስረጃ፦


⏱️| የተጫወተዉ ደቂቃ ብዛት - 90
🔑| ቁልፍ ኩዋስ በማቀበል - 8
🅰️| አሲስት - 2
🏹 ሙከራ - 4
⚽️| ግብ - 1
📈| ሬት- 10.0

@SkysportEt @SkysportEt

🎽| ማንችስተር ዩናይትድ በ2019/20 የዉድድር ዓመት የሚለብሱት አዲሱን ማልያ ይፋ አድርገዋል።

@SkysportEt @SkysportEt

📝 DEAL DONE:

👉| ወደ ሻምፒዮን ሺፕ መዉረዱን ያረጋገጠዉ ኖርዊች ሲቲ ሴባስቲያን ሶቶን ከጀርመኑ ቡድን ማስፈረሙን ይፋ አድርጎዋል።

👉| ኖርዊች ሲቲ ተጫዋቹን ለረጅም ግዜ የፈለገ የነበረ ሲሆን ከቡድኑ ሃኖቨር ላይ በመጨረሻም ከስምምነት በመድረስ ተጫዋቹን ኢንግሊዝ እንዲያርፍ አድርገዋል።

👉| የሻምፒዮንሺፑ ቡድንም ከሴባስቲያን ሴቶ ጋር የሶስት ዓመት ዉል ተፈራርመዋል።

@SkysportEt @SkysportEt

📝| DEAL DONE:

👉| የሪያል ቫላዶሊዱ ተጫዋች ራዉል ካርኔሮ ከቡድኑ ጋር እስከ 2023 መጨረሻ ድረስ የሚያቆየዉን ዉል ተፈራርሞዋል።

👉| በሮናልዶ ትልቁ አስተዳዳሪነት የሚንቀሳቀሰዉ ቡድን በቀጣይም የሌሎች ተጫዋቾችን ዉል ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

@SkysportEt @SkysportEt


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ማስፈጸሚያ 62.7 ቢሊዮን ብር አጽድቋል፡፡ የተመደበው የበጀት መጠንም ከባለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ15.3 ቢሊዮን ወይም 32.4 በመቶ ብልጫ እንዳለው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የኮሪያ ጦርነት ያበቃበትን 67ኛ ዓመት በማስመልከት ንግግር ያደረጉት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ”በገነባነው አስተማማኝ እና ውጤታማ ራስን የመከላከያ ኒዩክለር ከዚህ በኋላ በዚህ ምድር ላይ ከማንም ጋር ጦርነት አይኖርብንም” በማለት ሀገራቸው ከየትኛውም ሀገር የጦርነት ሥጋት እንደማይኖርባት መግለጻቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ኮሪያ ሴንትራል ኒውስ ኤጅንሲ ዘግቧል፡፡ -#AlAin

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የክረምት የችግኝ ተከላ መርኃግብራት!

በደቡብ ክልል በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአንድ ጀንበር 60 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሀግብር ተካሂዷል፡፡ ዘንድሮ በክልሉ 1ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1ነጥብ 3 ቢሊየን ያህሉን ማሳካት መቻሉ ተነግሯል፡፡

በክልሉ በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ እንደገለፁት ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ 5ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት 3ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች መትከል ተችሏል፡፡

በተያያዘ ዜና በኦሮሚያ ክልል ነገ ሀምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም 304 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። ክልሉ እስካሁን ከ2.3 ቢሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ኃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

በባህር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የነበሩ 1ዐዐ ታራሚዎች በይቅርታ መፈታታቸው ተገልጿል!

በባህር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት መደበኛ የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ ወንድ 99 ሴት 1 በድምሩ 1ዐዐ ታራሚዎች በይቅርታ መፈታታቸው ተገልጿል፡፡ ታራሚዎቹ በይቅርታ መመሪያው መሰረት ተቋሙ የሚሰጠው እርምት፣ የትምህርት የስልጠና በአግባቡ የተከታተሉ ናቸው ተብሏል፡፡

በይቅርታ የተፈቱ ታራሚዎች በመደበኛ የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ የህግ ታራሚዎች ሲሆኑ በፍርድ ላይ ያሉ መመሪያ ቁጥር 32ዐዐዐ/ 2010 መሰረት ያደረጉ ታራሚዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ውብሸት መኮነን መግለጻቸውን የክልሉ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ካናል ፕላስ ከ50 በላይ ቻናሎችን ይዞ በኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው!

የካናል ፕላስ የቴሌቪዥን ቻናል ከኢውቴልሳት ኮሚይኒኬሽን ጋር በመተባበር በቀጥዩ የፈረንጆች አመት ለኢትዮጵያውያን ተጠዋሚዎች በመደበኛና በከፍተኛ ጥራት ደረጃዎች የሚቀርቡ 50 ያህል ቻናሎችን ለማድረስ ዝግጅት መጀመሩን ቢዝነስ ዋየር የተሰኘው መካነድር አስታውቋል።

በመጠነኛ ክፍያ ለተጠቃሚዎች ይቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁት ከ50 በላይ የሚደርሱት ቻናሎች ለኢትዮጵያ የብሮድካስቲንግ ኢንዱስትሪን እንደሚያሳድግ የታመነ ሲሆን የካናል ፕላስ ሊቀመንበር የሆኑት ዣክ ዱ ፑይ ድርጅታቸው ወደገበያው በሚገባበት ወቅት ድርጅታቸው ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የተሻለ አማራጭን ይዞ ይመጣል ሲሉ ገልጸዋል።

#AddisZeybe
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#UPDATE

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አቶ አረጋ ከበደን ለክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊነት በእጩነት አቅርበው ምክር ቤቱ በአንድ ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ የክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሾሙ ወስኗል።

አቶ አረጋ ከበደ ለጋስ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በልማት አስተዳደር፣ ሁለተኛ ድግሪያቸውን በንግድ ሥራ አመራር በከፍተኛ ማእረግ እንዳጠናቀቁ ግለታሪካቸው በቀረበበት ወቅት ተነግሯል።በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይም አገልግለዋል ተብሏል።

ምክር ቤቱ የዳኞችን ሹመትም አጽድቋል። ለጠቅላይ ፍርድ ቤት 14 ዳኞች በአንድ ተቃውሞ፣ አራት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በሙሉ ድምጽ፣ 166 አዲስ የወረዳ ዳኞች በሙሉ ድምጽ ተሹመው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።

#አብመድ
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot


ለኮሮና ቫይረስ ክትባቶች የመጨረሻ ሙከራ ተጀመረ።

ተስፋ ለተጣለበት የኮሮና ቫይረስ ክትባት የመጨረሻ ነው የተባለ ሙከራ ትናንት በአሜሪካ ተጀምሯል፡፡ ክትባቱ ሞደርና በተሰኘው የህክምና መድኃኒቶች አምራች ተቋም የሚዘጋ ሲሆን ሙከራው 30 ሺ በሚጠጉ በጎ ፍቃደኞች ላይ የሚካሄድ ነው፡፡

ሙከራው ክትባቱ በተጨባጭ ፈውስ መሆንና ቫይረሱን መከላከል ይችል እንደሆን በውል ለማረጋገጥ ያስችላል እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፡፡ ሞደርና ከሰሞኑ ተጨማሪ የ472 ሚሊዬን ዶላር ድጋፍ ከአሜሪካ መንግስት ማግኘቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ እንግሊዝና ቻይና ሌሎች ሃገራትም ጭምር ክትባቱን ቀድሞ ለማዘጋጀት በሚያስችል ጥድፊያ ውስጥ ስለመሆናቸውም ይነገራል፡፡

ምንጭ : አልአይን
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa


TIKVAH-MAGAZINE dan repost
ኢትዮጵያ በ10 ቀናት ውስጥ 15 ሚሊዮን ህፃናትን የኩፍኝ ክትባት መከተቧን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። በዘመቻው 15 ሚሊዮን ህፃናትን ለመከተብ የታሰበ ሲሆን ከዕቅዱም 14.4 ሚሊዮን በመከተብ 96% ማሳካት መቻሉንም ነው የገለጸው፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot


ከመላ አገሪቱ ለተውጣጡ የ12ተኛ ክፍል ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ!

ከመላ አገሪቱ ለተውጣጡ የ12ተኛ ክፍል ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና መስጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በስልጠናው ላይ ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ከ400 በላይ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እስካሁንም 250 ተማሪዎች ስልጠናውን መውሰድ መጀመራቸው ነው የተገለፀው።

ለ12ተኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች በኦንላይን ፈተና እንዲወስዱ የሚረዳው የተስማሚ ቴክኖሎጂ ስልጠና መረሃ ግብር ለ5 ሳምንታት የሚቆይ ነው፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 5 ኪሎ ቴክኖሎጂ ካምፓስ መስጠት እንደተጀመረ እና እስካሁን መረጃው ያልደረሳቸው ተማሪዎች በቦታው ተገኝተው ስልጠናውን መከታተል እንደሚችሉ ተገልጿል። -#EBC

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ለሁለት ቀናት በሚቆየው 5ኛ የምርጫ ጊዜ 5ኛ የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2012 በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲት ጽ/ቤት የ202 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲሁም የ2013 በጀት ዓመት ረቂቅ የበጀት አዋጅና ልዩ ልዩ ሹመቶችን ውሳኔዎች ቀርበው እንደሚፀድቁ ይጠበቃል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot


ስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ያለፈውን ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ ክንዋኔዎች የተገመገሙ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የበጎ ፈቃደኝነት ማስፋት፣ በጎ ፈቃደኝነትን ከቅጥር ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ማድረግ፣ የአውቶማቲክ ስልቶች ትግበራን ማበረታታት፣ የፋይናንስ ዘርፉን ለወጣቶች፣ ለአርሶ አደሮች እና አነስተኛ ትርፍ በሚያስገኙ ሥራዎች ለተሠማሩ ድጋፍ ለመስጠት በሚያስችል መልክ ማጠናከር ከተጠቀሱት አቅጣጫዎች መካከል ይገኙበታል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የታጁራን ወደብን በይፋ መጠቀም ጀምሪያለው ብሏል፡፡ የመጀመሪያዋ መርከብም የድንጋይ ከሰል ጭነት ጭና በወደቡ እያራገፈች ነው ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል ገልጸዋል፡፡

ወደቡ ለጥቅል ጭነት/ general cargo እንቅስቃሴ ማገልገል ቢችልም በጅቡቲ በኩል ያለው የመንገድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ ከ 3 አመት በፊት የተገነባው ወደብ ወደስራ መግባት ሳይችል ቆይቶ ነበር፡፡

ሆኖም ባለፈው ህዳር 120 ኪ.ሜ የሚረዝመው እና ታጁራን ከ ኢትዮጵያ ድንበር በበልሆ በኩል የሚያገናኘው የመንገድ ግንዳታ መጠናቀቁ ወደቡን ወደስራ እንዲገባ ማድረግ አስችሏል፡፡የ120ኪ.ሜትሩ የታጁራ በልሆነ መንገድ በኩዌት ፈንድ ድጋፍ በ156 ሚሊየን ዶላር የተገነባ ነው፡፡

#CAPITAL
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#AddisAbaba

በ2013 በጀት አመት ታክስ ካልሆኑ እና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ከቀደሙት አመታት በተሻለ ደረጃ ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ቢሮው የ2013 በጀት አመት ረቂቅ ለምክር ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርጓል።

በዘንድሮ በጀት አመት ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች፣ ከመንገድ ፈንድ፣ ከውጭ እርዳታና ብድር በተጨማሪ ከተራፊ በጀት 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል። ከተማ አስተዳደሩ በ2013 በጀት አመት በጠቅላላው 61 ነጥብ 34 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራ የልዑካን ቡድን ትናንት በጂቡቲ ታጁራ ክልል ተገንብቶ ስራ የጀመረውን ወደብ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የጂቡቲ ትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የጂቡቲ ወደብና ነጻ ቀጠና ሊቀመንበር እንዲሁም የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የወደቡ ስራ መጀምር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ተከትሎ እየጨመረ የመጣውን የወጪ ገቢ ምርት ፍሰት ለማስተናገድ ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም ባሻገር የሁለቱን ሃገራት የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል ተብሏል፡፡ -#FBC

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የዶሮ እርባታ ስራ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል!

የኮሮና ወረርሽኝ ባስከተለው ቀውስ ሳቢያ የዶሮ እርባታ ስራ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል ሲል የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቅራቢዎች ማህበር ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ወረርሽኙ አሁን ባለበት ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ዘርፉ ለከፋ አደጋ እንደሚጋለጥ የጠቆሙት የማህበሩ ሊ/መንበር ዶ/ር ምስጋናው ፍፁም በመጪዎቹ ወራት የእንቁላልና የዶሮ ዋጋ በእጅጉ ሊያሻቅብ ይችላል ብለዋል፡፡ መንግሥት ለዘርፉ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

በአሁኑ ወቅት የዶሮ ስጋ ክምችት ስላለ በትንሽ ትርፍ ለበላተኛው እንዲደርስ ከከተማ መስተዳድሮች፣ እንዲሁም ከሆስፒታሎች ማቆያ ጣቢያዎች ጋር በመነጋገር የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸውም ሊቀመንበሩ ጠይቀዋል፡፡ 

#አዲስአድማስ
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot


TIKVAH-MAGAZINE:
ውድ የፈረስ ደንበኞቻችን ወደ ቀድሞ ስራችን ተመልሰናል እርስዎም መተግበሪያውን ወይም በጥሪ ማዕከል ቁጥራችን 6090(በደቂቃ 50 ሳንቲም ብቻ) በመጠቀም ወደ አሻዎት ቦታ ይንቀሳቀሱ::

ለፕሌይስቶር ወይም ለአፕስቶር ይህን ሊንክ ይጠቀሙ👇
http://onelink.to/jzr2aq

ፈረስ ያደርሳል!

ሦስት ዓመታትን ከቤተሰቦቹ ጋር!

በቻናሉ ቤተሰባዊ ትስስርን በመፍጠር ሚዛናዊና ታማኝነት ያላቸው መረጃዎችን እርስ በእርስ በመለዋወጥ፣ ለውይይት የተመቸ መድረክ በማዘጋጀት እንዲሁም ሰብዓዊነትን በማጉላት በቅንነት ላይ የተመሰረተ የመረዳዳት ባህልን ለማሳደግ ጥረቶች ተደርገዋል።

• ምክንያታዊነት • ሚዛናዊነት • ቅንነት • ሰብዓዊነት • ቤተሰባዊነት

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ባለፉት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ የቆየው ጨፌ ኦሮሚያ 90 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2013 የኦሮሚያ ክልል መንግስት በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። ጨፌው የ2012 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀትን ከተመለከተ በኋላም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። በተጨማሪም የቀረቡለትን የተለያዩ አመራሮችም ሹመትም ተቀብሎ አጽቋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት፣ 15ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ይጀምራል

ሁለት ቀናት በሚቆየው መደበኛ ጉባኤው የ2012 ዓ.ም በጀት ሪፖርት ግምገማ፣ የሕግ የበላይነት እና በሰላም ማስከበር፣ ኮቪድ-19ን በዘላቂነት መከላከል እና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚመክር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መጥቀሳቸውን ገልጿል።

በተጨማሪም የዋና ኦዲተር የኦዲተሮችን መተዳደሪያ ደንብ፣ የ2012 ተጨማሪ በጀት፣ የካፒታል እና መደበኛ በጀት እንደሚያጸድቅ ተጠቅሷል። በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ልዩ፣ ልዩ ሹመቶች እንደሚጸድቁ እና የአረንጓዴ አሻራ ለማስቀመጥ ችግኝ ተከላ ይከናወናል ሲል አትቷል።

#EBC
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ከ330 ሺሕ በላይ ሥራዎች ከስመዋል!

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ3.3 ሚሊዮን በላይ ሥራዎች ሊፈጠሩ ችለው የነበር ቢሆንም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከ330 ሺሕ በላይ ሥራዎች መክሰማቸው እንደተረጋገጠ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህ የሥራ ዕድሎች ዘንድሮ ተፈጥረው ከሰባት ወራት ቆይታ በኋላ ለመክሰም የተገደዱ ናቸው፡፡

ይህ ይባል እንጂ እስካሁን የተፈጠሩት ሦስት ሚሊዮን የሥራ ዕድሎች ምንም እንኳ የታሰበውን አፈጻጸም ለማሳካት ቢያስችሉም፣ ከሚያስገኙት ገቢ መጠንና  ከሚሰጡት የሥራ ዋስትና አኳያ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው ነው የተነገረው፡፡

በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 14 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በአሥር ዓመታት ውስጥም ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እቅድ ተይዟል፡፡ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤፍሬም ተክሌ (ዶ/ር) ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል 384 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

#Reporter
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#UPDATE

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የመተማመኛ ድምጽ ባለማግኘት ከኃላፊነት በተነሱት የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስተር አሊ ካሕሬ ምትክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን ማህዲ ሞሐመድ ጉሊያድን መደበኛ ጠቅላይ ሚኒስትር እስኪሰየም ድረስ በጊዜያዊነት ሾመዋል፡፡ -#AlAin

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

አሜሪካ በቻይና የሚገኘው ቆንስላዋን ለቅቃ ወጣች

ባሳለፍነው ሳምንት አሜሪካ ሂውስተን የሚገኘውን የቻይና ቆንስላ ከዘጋች በኋላ በአጸፋኽ ቻይናም ቼንግዱ ከተማ የሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ አንዲዘጋ ያዘዘችው። እናም የአሜሪካ ቆንስላ ዲፕሎማቲክ አባላቱ የተቀመጠላቸው የ72 ሰአት ገደብ ከመጠናቀቁ በፊት ግቢውን ሲለቅቁ ታይተዋል።

የአሜሪካ ቆንስላ መዘጋቱን ተከትሎ በርካታ ቻይናውያን በአካባቢው በመሰባሰብ የአገራቸውን ባንዲራን ሲያውለብቡና ፎቶ ሲነሱም ተስተውዋል። በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ያለው ውጥረት በተለያዩ ምክንያቶች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እያየለ መጥቷል። -#BBC

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተበርክቶላቸዋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

በሚቀጥሉት አስር አመታት 4 ሚሊዮን 4መቶ ሺህ ቤቶች ለመገንባት ዕቅድ ተይዟል

በኢትዮጲያ ከተሞች እየታየ ያለውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት በሚቀጥሉት አስር አመታት 4 ሚሊዮን 4መቶ ሺህ ቤቶች ለመገንባት ዕቅድ መያዙን የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከዚህ ውስጥ የመንግስት ሚና 20 በመቶውን ሲወስድ 35 በመቶ ያህሉ ደግሞ ዜጎች በመሃበር ተደራጅተው የሚገነቡት ሲሆን 10/90፣ 20/80 እንዲሁም 40/60 ቤቶችም ግንባታቸው ይቀጥላል። ዜጎች በገቢ ልካቸው ሊከራዩ የሚችሏቸው ቤቶችም በመንግስት እንዲገነባ ይደረጋልም ተብሏል።

#አዲስዘመን #አዲስማለዳ
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#UPDATE

በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ ስር በሰደደ መልኩ የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ ያልቻሉ 1ሚሊዮን 890 ሺህ 985 የኅብረተሰብ ክፍሎች በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ በማድረግ እለታዊ የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ መቻሉን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ገልጸዋል፡፡

የግብርና ልማትን ለማፋጠን 458 ሺህ 185 የመሬት ባለይዞታዎች ሁለተኛ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ከማሳ ካርታ ጋር መሰጠቱን እንዲሁም የእርሻ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ተስጥቷቸው ወደ ሥራ ያልገቡ ባለሃብቶች ላይ በተወሰደው እርምጃ ሊያለሙ ለሚችሉ ለሌሎች ባለሃብቶች እንዲተላለፍ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል፡፡

#አብመድ
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

በአዲስ አበባ ሰሚት ጨርቆስ ኮንዶሚኒየም አከባቢ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ መንገዱን ስቶ ከጋራ መኖሪያ ህንጻ (ኮንደሚኒየም) ጋር ተጋጭቷል። በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ለጊዜው በውል አልታወቀም።

PHOTO: ከማህበራዊ ትስስር ገጽ የተወሰደ
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ለ2013 በጀት የቀረበውን ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ አአጽድቋል።የምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ የማሻሻያ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

ለበጀት ዓመቱ እንዲውል ከተያዘው በጀት ውስጥ 1 ቢሊዮን 9 ሚሊዮን 557 ሺህ 048 የሚሆነው በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ነው።

3 ቢሊዮን 50 ሚሊዮን 63 ሺህ 244 የሚሆነው ደግሞ ከማዕከላዊ መንግስት ግምጃ ቤት በድጎማ እና ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ ተቋማት የውስጥ ገቢ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ እንዲሁም ከውጪ ከሚገኝ ዕርዳታ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒ


Addis መረጃ™ dan repost
#COVID19

ሰሜን ኮሪያ ውስጥ የመጀመሪያ የተባለው በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተጠረጠረ ሰው መገኘቱ ተሰምቷል።

KCNAን ጠቅሶ BBC እንደዘገበው ከሆነ ቫይረሱ እንዳለበት የተጠረጠረው ግለሰብ ከ3 ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድቶ ሄዶ የነበረ ሲሆን በቅርቡ በድንበር በኩል ወደ ሰሜን ኮሪያ ከተመለሰ በኋላ የቫይረሱ ምልክቶች ታይተውበታል።

ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከፍተኛ በለስልጣኖቻቸውን ሰብስበው ከደቡብ ኮሪያ ጋር በምትዋሰነው የድንብር ከተማዋ ኬሶንግ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አድገዋል።

@Addis_merejas


TIKVAH-MAGAZINE:
#ችሎት

ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ ወንጀል በተከሰሱ በእነ ሻምበል ማማር ጌትነት መዝገብ የሚገኙ 49 ተከሳሾች በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሽታ ምክኒያት ከሰኔ 22 ቀን 2012ዓ.ም ጀምሮ አስከ ሐምሌ 17 ቀን 2012ዓ.ም በተለያዩ የስራ ቀናት በመነጣጠል ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

ሃምሌ 17 ቀን 2012ዓ.ም በዋለው ችሎት የምስክር አሰማምን በተመለከተ የትኛው ምስክር በየትኛው ተከሳሽ ላይ እንደሚመሰክር በመለየት ለፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 24 ቀን 2012ዓ.ም እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በእነ ሻምበል ማማር ጌትነት መዝገብ የሚገኙ አጠቃላይ ተከሳሾች 55 ሲሆኑ ከስድስቱ ተከሳሾች ወስጥ አራቱ ተከሳሾች ላይ የጋዜጣ ጥሪ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ANRSAG-07-25

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

10ሺህ የሚደርሱ ወገኖችን ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ ነው!

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ግርግር ለተፈናቀሉ 7 ሺህ 800 ሰዎች የዕለት ደራሽ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አቶ ዳመነ ዳሮታ አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ ድጋፉን እያደረገ ያለው ምግብና ምግብ ነክ ድጋፎችን ሲሆን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀትም እስከ 10ሺህ የሚደርሱትን ወገኖች ለመደገፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን ተነሱ!

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ካይሬ ከስልጣን ተነስተዋል፡፡ ካይሬ ከስልጣን የተወገዱት የሀገሪቱ የታችኛው ፓርላማ አባላት ጠቅላይ ምኒስትሩን ከሥልጣን ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በ170 ድጋፍ በ8 ተቃውሞ በመጽደቁ ነው፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ መሐመድ ሙርሳል "ጠቅላይ ምኒስትሩ ለፌድራል እና የክልል መንግሥታት የጸጥታ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅ ብሔራዊ የጸጥታ ኃይል ሳያዋቅሩ ቀርተዋል" ሲሉ ከሥልጣን የተነሱበትን ምክንያት አብራርተዋል።

ጠቅላይ ምኒስትሩ ከሥልጣን መነሳታቸው ከተረጋገጠ በኋላ መጪው የሶማሊያ ምርጫ በሚካሔድበት የጊዜ ሰሌዳ ጉዳይ በምክር ቤቱ ውዝግብ ተነስቷል። ሐሳን አሊ ኻይሬ የሶማሊያ ጠቅላይ ምኒስትር ሆነው ሥልጣን የጨበጡት የካቲት 2009 ዓ.ም ነበር። -#AlAin -#DW

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot


TIKVAH-MAGAZINE:
ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ጉባኤው ዛሬ እና ነገ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡

በሁለት ቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም የሚገመገም ሲሆን የ2013ን በጀት ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ጠቁመዋል። እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ 11ኛ ቃለ ጉባኤ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የክልሉ የውሃና ፍሳሽ አዲስ ደንብ ማጽደቅም የጉባኤው አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የሕግ ማርቀቅ እና በተጓደሉ አመራሮች ቦታ ሹመት ያጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡

#FBC
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#HERQA

ፓራዳይም ዩኒቨርስቲ በሚል እራሱን ሰይሞና ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ፈቃድ እንደተሰጠው በማስመከል እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ቢገልጽም በኤጀንሲው በኩል ምንም እውቅና እንዳልተሰጠውና ተማሪዎችና ወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተገልጿል፡፡ ጉዳዩን በህግ አግባብ እንዲታይ እንደሚያደርግም ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

ከአንዲት ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በቀዶ ህክምና ተወገደ!

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን 6 የእንስሳት ሃኪሞች ከአንዲት ላም ሆድ ውስጥ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ በቀዶ ህክምና አስወገዱ። ከጤና ባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ፍራኦል ዋቆ፤ “ላሚቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች” ሲሉ ከቀዶ ህክምናው በኋላ #ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፍራኦል “ከብቶች የሚግጡት ሳር ሲያጡ ወይም በሰውነታቸው ውስጥ የንጥረ ነገር እጥረት ሲያጋጥማቸው ፕላስቲክ ሊበሉ ይችላሉ” ያሉ ሲሆን ጨምረውም፤ ሰዎች ፕላስቲክ የሚያስወግዱበት መንገድ ለቁም እንስሳት ጤና ችግር እየሆነ ነው” ብለዋል።

50 ኪሎ ግራም ፕላስቲክ የተወገደላት ላም ባለቤት የሆኑት አቶ አሬሪ ጨሪ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደምም ፕላስቲክ የተመገበች ሌላ ላም ወደ ጤና ባለሙያዎቹ አምጥቶ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፕላስቲክ ከሆዷ ወጥቶ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

"ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም"- ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- " ግልጽ መሆን ያለበት መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያየ ዝም አይልም ፡፡ ይህን ማስቆም በህገመንግስቱ የተሰጠው ኃላፊነት ነው ። የሰራዊቱም ተልዕኮ ይሄ ነው፡፡ መንግስትም ቢሆን የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ፤ ግዴታም አለበት"

- የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያውያንን እኩል ሊያገለግል የሚችል ተቋም ሆኖ እየተገነባ መሆኑን አመልክተው፣ የጸጥታ ተቋማት የማንም ፓርቲ ዕሴት ወይም ሀብት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ሀብት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ሊቀረጽና ሊገነባ የማይገባው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

- ኢትዮጵያን እኔ ከሌለሁ ትፈርሳለች ወይም እኔ ካልተጠቀምኩ እናፍርሳት የሚለው አካል ሁል ጊዜ ቢናገርም፤ በእኔ በኩል ኢትዮጵያን የምትፈርሰው መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ላይ የሚያምኑት ሕዝቦቿ እና መሪዎቿ ከሌሉና ከሌሉ ብቻ ነው ፡፡ ከዛ በላይ ኢትዮጵያ የምትፈርሰው የመከላከያ ኃይላችን፣ የፀጥታ ኃይላችን፣ የደህንነት ኃይላችን ሲፈርስ፤ ወይም እሱ መስዋዕት ሆኖ ሲሸነፍ ብቻ ነው::"

Readmore https://telegra.ph/ENA-07-25

#ENA
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ENA
"ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም"- ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደሌላቸው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ። የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመለከቱ።  ጄኔራል አደም መሐመድ በተለይ ከአዲስ ዘመ...


TIKVAH-MAGAZINE dan repost
አቶ ደጀኔ ጣፋ ኤካ ኮተቤ መግባታቸውና የነአቶ ጃዋር መሃመድ ቅሬታ!

እስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» ባለስልጣናት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸዉ አራት ተጠርጣሪዎች እስር ቤት የሚገኙበት ሁኔታ ለጤናቸዉ አስጊ የሆነ ነዉ ሲሉ ጠበቃጠዉ ተናገሩ።

የታሰሩበት ክፍል መብራት የሌለዉ መብራት ሲጠፋም ሻማ እንደማይገባላቸዉ፤ ብሎም እርስ በርስ እንዳይገናኙ ተለያይተዉ መታሰራቸዉን ጠበቃዉ አክለዋል።

በሌላ ከኩል በቁጥጥር ስር የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ደጀኔ ጣፋ በኮሮና መያዛቸዉ መመረጋገጡ ወደ ኤካ የኮሮና ማገገሚያ መዛወራቸዉ ተነግሮአል - #DW

@tikvahethiopiaOfficial @tikvahethmagazins


Moreee
👇👇👇👇
@Addis_tv
@Addis_tv
@Addis_tv
@Addis_tv

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

783

obunachilar
Kanal statistikasi