ስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ያለፈውን ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ ክንዋኔዎች የተገመገሙ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የበጎ ፈቃደኝነት ማስፋት፣ በጎ ፈቃደኝነትን ከቅጥር ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ማድረግ፣ የአውቶማቲክ ስልቶች ትግበራን ማበረታታት፣ የፋይናንስ ዘርፉን ለወጣቶች፣ ለአርሶ አደሮች እና አነስተኛ ትርፍ በሚያስገኙ ሥራዎች ለተሠማሩ ድጋፍ ለመስጠት በሚያስችል መልክ ማጠናከር ከተጠቀሱት አቅጣጫዎች መካከል ይገኙበታል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም ጀመረች
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የታጁራን ወደብን በይፋ መጠቀም ጀምሪያለው ብሏል፡፡ የመጀመሪያዋ መርከብም የድንጋይ ከሰል ጭነት ጭና በወደቡ እያራገፈች ነው ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል ገልጸዋል፡፡
ወደቡ ለጥቅል ጭነት/ general cargo እንቅስቃሴ ማገልገል ቢችልም በጅቡቲ በኩል ያለው የመንገድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ ከ 3 አመት በፊት የተገነባው ወደብ ወደስራ መግባት ሳይችል ቆይቶ ነበር፡፡
ሆኖም ባለፈው ህዳር 120 ኪ.ሜ የሚረዝመው እና ታጁራን ከ ኢትዮጵያ ድንበር በበልሆ በኩል የሚያገናኘው የመንገድ ግንዳታ መጠናቀቁ ወደቡን ወደስራ እንዲገባ ማድረግ አስችሏል፡፡የ120ኪ.ሜትሩ የታጁራ በልሆነ መንገድ በኩዌት ፈንድ ድጋፍ በ156 ሚሊየን ዶላር የተገነባ ነው፡፡
#CAPITAL
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
#AddisAbaba
በ2013 በጀት አመት ታክስ ካልሆኑ እና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ከቀደሙት አመታት በተሻለ ደረጃ ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ቢሮው የ2013 በጀት አመት ረቂቅ ለምክር ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርጓል።
በዘንድሮ በጀት አመት ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች፣ ከመንገድ ፈንድ፣ ከውጭ እርዳታና ብድር በተጨማሪ ከተራፊ በጀት 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል። ከተማ አስተዳደሩ በ2013 በጀት አመት በጠቅላላው 61 ነጥብ 34 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራ የልዑካን ቡድን ትናንት በጂቡቲ ታጁራ ክልል ተገንብቶ ስራ የጀመረውን ወደብ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የጂቡቲ ትራንስፖርት ሚኒስትር፣ የጂቡቲ ወደብና ነጻ ቀጠና ሊቀመንበር እንዲሁም የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የወደቡ ስራ መጀምር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ተከትሎ እየጨመረ የመጣውን የወጪ ገቢ ምርት ፍሰት ለማስተናገድ ተጨማሪ አቅም ከመፍጠሩም ባሻገር የሁለቱን ሃገራት የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል ተብሏል፡፡ -#FBC
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
የዶሮ እርባታ ስራ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል!
የኮሮና ወረርሽኝ ባስከተለው ቀውስ ሳቢያ የዶሮ እርባታ ስራ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል ሲል የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቅራቢዎች ማህበር ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
ወረርሽኙ አሁን ባለበት ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ ዘርፉ ለከፋ አደጋ እንደሚጋለጥ የጠቆሙት የማህበሩ ሊ/መንበር ዶ/ር ምስጋናው ፍፁም በመጪዎቹ ወራት የእንቁላልና የዶሮ ዋጋ በእጅጉ ሊያሻቅብ ይችላል ብለዋል፡፡ መንግሥት ለዘርፉ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
በአሁኑ ወቅት የዶሮ ስጋ ክምችት ስላለ በትንሽ ትርፍ ለበላተኛው እንዲደርስ ከከተማ መስተዳድሮች፣ እንዲሁም ከሆስፒታሎች ማቆያ ጣቢያዎች ጋር በመነጋገር የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸውም ሊቀመንበሩ ጠይቀዋል፡፡
#አዲስአድማስ