በፍትሀብሄር ክርክር የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
ሰዎች በእለት ተእለት በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በራሳቸው መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው በየእለቱ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከክስ አቀራረብ ጀምሮ የክርክር ሂደቱ የሚመራበት ሥነ ሥርአት አለው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ በሚያቀርብበት ወቅት ሊቀርብ የሚችልን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምንነት እንዲሁም የሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ እንመለከታለን።
የመጀመሪያ ደርጃ መቃወሚያ ምንነት
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የቀረበው ክስ ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆን በማንኛውም ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ መቃወሚያ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(1) መረዳት ይቻላል።
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምክንያቶች
አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አመልክቷል፡፡ ይኸውም፡-
• ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ስልጣን የሌላው ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ ከሆነ
• አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ
• ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ
• ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ
ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል።
ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም ወገን ከላይ ከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው። አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀር መቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠር በድንጋጌው ንኡስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔና ውጤቱ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማስረጃ እንዲቀርብለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(1) መሰረት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ በመሆኑ ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ በመሆኑ እንደሆነ የቀረበውን ክስ በመዝጋት ባለጉዳዮችን ያሰናብታል። የቀረበው መቃወሚያ ከእነዚህ ውጭ ሆኖ መቃወሚያው ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን በመዝጋት ተገቢ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።
ሌላው የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ በዚያው ጉዳይ መጀመሪያ ክስ ላቀረበበት ፍርድ ቤትም ይሁን ለሌላ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና የማቅረብ መብቱ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት ከሳሽ እንደገና ክስ የማቅረብ መብት እንዳለው በትእዛዙ ላይ መግለፅ እንደሚችል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(3) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋው ‘ፍርድ ቤቱ ነገሩን የማየት ስልጣን የለውም’ በሚል መቃወሚያ መሰረት ሲሆን ከሳሽ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ የሚቀነሰው ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ እንደሚመለስለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(4) ላይ በግልፅ ተደንግጓል።
በአጠቃላይ የፍትሐብሔር ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ወደ ዋናው ክርክር ከመግባቱ በፊት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244 ሥረ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባሉ ጊዜ ይህንኑ በመጥቀስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ይህም ወዲያውኑ መቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ሰላም ለሀገራችን 🙏