#እርቅ በወንጀል ጉዳዮች ያለው ፋይዳ!
#አገራችን ኢትዬጲያ የበርካታ ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፤ ቋንቋዎች ፣ ባህሎች እና ወጎች ፣ ያላት ሀገር ነች፤የሀገራችን ህዝቦች የየራሳቸውን የሆነ ባህል /ወግ፣ አለባበስ እንዲሁም አገር በቀል የሆነ የዕርቅ፣ የሰላም መጠበቂያ እና የሰላም ግንባታ ስነ-ዘዴዎችም ያሏቸው ህዝቦች ናቸው፤ሀገር በቀል የሰላም መስሪያ ፣ የሰላም መጠበቂያና የሰላም ግንባታ ዘዴ የምንለው ኢ-መደበኛ የሆነው እና ማህበረሰቡ ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰው ሰነ-ዘዴ ነው፡፡
#በመሆኑም በእንግሊዘኛው አጠራር non-state based customary institutions የሚያመላክት ሆኖ በዚህ የሰላም እና የፍትህ ስርዓት በዳኝነት የሚቀመጡት መንግስት የሾማቸው ዳኞች ሳይሆኖ ማህበረሰቡ አምኖና ተቀብሎ ለዳኝነት የሾማቸው ባለ ልዪ ተስጦኦ የሆኑ የዕድሜ ባለፀጋ ሽማግሌዎች፤ባህላዊ መሪዎች እና ሀይማኖት አባቶች ሲሆኑ በዚህ ሂደት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ይህ መልካም የሆነ ታሪክ እና ባህል በቂ ነው ባይባልም በህጉም እውቅና ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን በፍርድ ቤቶችም ጭምር በወንጀል አድራጊው እና ተበዳይ መካከል እርቅ ሲበረታታ ይታያል፡፡ በሁሉም የወንጀል አይነቶች እርቅ መታረቅ ያልተከለከለ ሲሆን ነገር ግን እንደወንጀሉ አይነት እና በጠቅለላዉ እርቁ ፍትህን የማያረጋግጥ በሆነ ጊዜ ከሆነ እርቁ ተፈጻሚ የማይደረግ ሲሆን ነገር ግን ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንጻር ፍ/ቤቶች ፍርድ ከሰጡ በኀላ ለቅጣት ማቅለያነት ይጠቀሙታል፡፡
#በወንጀል ህጉ በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ ወንጀሎችን በአፈፃፀሙ እና ቅጣቱ ቀላል በመሆኑ የህብረተሰቡን ሰላም እና መልካም ግንኙነት ተጠብቆ ለማቆየት እንደሚጠቅም ተመልክተዋል፡፡
ሌላው በወንጀል ጉዳይ የመታረቅ ጥቅሙ፡ -የመዝገብ ክምችትን ይቀንሳል፣ ከእስራት ይልቅ በእርቅ ማለቁ ለሁለቱም ወገን ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ በወንጀል አድራጊው ላይ የባህሪ ለውጥ ሊመጣ ስለሚችል፣ እንዲሁም የፍርድ ቤቶችን የስራ ጫና እና የተከራካሪዎችን ግዜ ፣ ወጭ እና ጉልበት ያቀላል፡፡
#ከዚህም ባሻገር እርቅ ቀጣይነት ያለውን ሰላም በማስፈን፣የተጎዳን በመካስ ብሎም ሁለንተናዊ የሆነ ማህበራዊ ተግባቦትን በመመለስ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ነገር ግን እርቅና የተለያዩ አማራጭ የግጭት መፍቻ ሀገር በቀል እውቀቶችና ስርዐቶች እየተረሱና እየተሸረሸሩ በመሄዳቸው በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች ምክንያት በርካታ ዜጎች ለመፈናቀል ለሞት እና ለንብረት ውድመት ሰለባ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች ተከስተዋል፡፡
#በመሆኑም በአገር በቀል የግጭት አፈታት እና የዕርቅ ሥርዓቶች ላይ ትኩረት በማደረግ ወደ ቦታቸው መመለስ እንዲሁም በህግ ማዕቀፎቻችንም በሰፊው እንዲካተቱና እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ህብረተሰቡን በሰፊው የሚጠቅም ከመሆኑም በላይ በፍትህ ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመሠረታዊነት የሚፈታ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏