ለምን ?
Hook...1
ፍታ ፍታ አቁም ጦርነቱን
የደም የቂም ''የቂም በቀል'' አታርገው መሬቱን
አዉርድ ጠመንጃህን -ሄይ-
እራቅ ጦርነትን -ሄይ-
ለእህት ወንድምችህ -ሄይ-
አሳያቸው ፍቅርን።
ጥላቻና ቂምን አርቀህ ከወገን
ጣላቸዉ እባክህ መግባታቸው ፍቅርን
በአለም በዚህች ምድር በምንኖር ጊዜ
ችግርና ማጣት ~ መራብ መንከራተት ~አያጣን ሁል ጊዜ
ጥላቻና ክፍ በህይወትህ ቢስፋፉ
ችግርና ማጣት አያድርግህ መጥፎ
መሣርያህን ጣለዉ አዉርድ ፍቅር ሰላም
ድንበርና መሬት ከወገን አያጣላም
-ሄይ-
ከወገን አያጣላም
''ድንበር ቢለያየን'' -ሄይ- ''ጥላቻ ነግሦብን'' -ሄይ-
''ይህ ራስ ወዳድነት'' -ሄይ- ''ነግሶ በላያችን'' -ሄይ-
ለምን ለምን ?
ለምን ለምን ?
ዝም አልነው ጥላቻን
ክፋትና መራራቅን ሲያመጣ መሀላችን
አሁን ዘመን ተለወጠ
ፍቅራችን ከሁሉም በለጠ
ጥላቻና ቂምን ቆርጦ '' ቀይ ባህርንም አቋርጦ
ገባ ሰላም በመሃላችን ''ኤርትራ ሆነች ''ሀገራችን''
እዚህም እዛም ነው ቤታችን
አምላክ ምህረትን ሲሰጠን
እርቅ እንዲሆን በመሀላችን
ፍቅርን በእዉነት ሊያስተምረን
እንድንኖር ''ተደምረን''
አምላክ አንድን ሰዉ ላከልን...
አምላክ አምላክ አንድን አንድን ሰው ሰው ላከልን 2x
2.በሀይማኖት በዘር በጎሳ በቀለም
የሚነሳን እሳት የሚያስቆመዉ የለም
እንካ ተቀበለኝ ይህ መልእክት ላንተ ነዉ
ልንገርህ ደግሜ ሚያዋጣህ ሰላም ነዉ።
''በእናትህ በሀገርህ በተወለድክበት
ሰርተህ ጥረህ ግራህ እንዲያልፍልህ በእዉነት
እህት ወንድምችህ ሲስቁ ለማየት
የህፃናትን ለቅሶ ሲቃ ላለመስማት
ተነስና ጀምር አዲስ የህይወት ምዕራፍ
ጣለዉ አሮጌዉን
የክፋትን በትር
ሰላምን አንግበዉ -ሄይ- የስልጣኔን በር
ለምን ለምን ?
ለምን ለምን ?
ዝም አልነዉ ጥላቻን
ክፋትና መራራቅን ሲያመጣ መሀላችን
አሁን ዘመን ተለወጠ ፍቅራችን ከሁሉም በለጠ
3.ክፍት አይኑር በኛ ደግነት ይብዛልን
በምንኖር ጊዜ በዚህች ጠባብ ምድር
ተባብረን ካልሆነ እጅ ለእጅ ተያይዘን
መአበሉ ሲመጣ ሊጠርገን ሊያጠፋን
መዉደማችን አይቀር መጥፊያችን ያን ጊዜ
መሰረት ካልያዝን አንድ ላይ በጊዜ
''የዘርና የጎሳ'' የቆዳ ልዩነት
በመካከላችን አይፈጥርም ልዩነት
መደመር አለብን ለሀገራችን አድነት
ተጣምረን እንኑር አይግባ ድህነት።
ኢትዮጵያ ፧ሄይ፦ ኢትዮጵያ
@Kanni27_officialለምን ? #Lyrics