ናሁ ሰማን ዜማ(Nahu seman zema)


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




መልከ ጼዲቅ

     የበረታ ፃድቅ ኢትዮጵያዊ
     የታመነ ቅዱስ ባሕታዊ
     መልከ ጼዴቅ የጽድቅ ወታደር
     አክብሮሀል ቅዱስ እግዚአብሔር
     አዝ...

በገድልና በትሩፋት
ተመስክሯል የአንተ እምነት
ከከዋክብት በላይ ደምቀህ
በመንግስቱ በክብር ያለህ
መልከ ጼዴቅ ዛሬም ታበራለህ
     አዝ...
እንባ የለም ከፊቴ ላይ
በመውደቄ ከደጅህ ላይ
አለበስከኝ ነጩን በፍታ
እንቆቅልሼም ተፈታ
መልከ ጼዴቅ አማልደህ ከጌታ
     አዝ...
ስለምታውቅ የልቤን
ትሞላለህ የሃሳቤን
ቀድመኸልኝ በህይወቴ
ተፈፀመ ፍላጎቴ
መልከ ጼዴቅ ሆነኸኝ አባቴ
     አዝ...
በተከዝኩኝ ባዘንኩኝ ሰሀት
ነፍሴን ቀርበህ አፅናናሀት
ወደ ጌታ አቀረብከኝ
ከውድቀቴ አነሳኸኝ
መልከጼዴቅ ጎኔ ቅምኩልኝ


     ዘማሪት ፍሬሰላም ጌቱ
  ግጥምና ዜማ  መ/ር ሲሳይ ወ/አረጋይ


       ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥

╭✥◉●•┈•✨◍❀◍●✨◉●•┈•✥╮
/╭✧✞ @Nahuseman256✞ ✧╮\
\╰✧ ✞ @Nahuseman256 ✞✧/
╰✥◉●•┈•🌿◍❀◍●🌿◉●•┈•✥




ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ ✞

ንሴብሖ ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ(፪)
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
               
ለምስጋና ቀሰቀስከኝ በእኩለ ሌሊት
በተመስጦ ስለፍቅርህ ልጀምር ማኅሌት
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
      
ስመለከት ወደ ሰማይ በጨረቃ ብርሃን
ግርማ ለብሶ አስገረመኝ የአምላኬ ዙፋን
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን በመንፈስ እንዘምር
እልል እንበል በምስጋና ጸጋውን እንጀምር
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ

አእዋፉ በማለዳ መዝሙር ሲጀምሩ
በቋንቋቸው የአንተን ክብር በምስጢር ሲያወሩ
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ
      
ከበሮ ሆይ ጸናልናል ሆይ ለምስጋና ተነስ
በማለዳ ለጌታችን ምስጋና እናድርስ
ንሴብሖ ለአምላከ እዝራ

✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥

╭✥◉●•┈•✨◍❀◍●✨◉●•┈•✥╮
/╭✧✞ @Nahuseman256✞ ✧╮\
\╰✧ ✞ @Nahuseman256 ✞✧/
╰✥◉●•┈•🌿◍❀◍●🌿◉●•┈•✥




✞ ንሴብሆ ✞

ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 
       አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
       አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

 ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥

╭✥◉●•┈•✨◍❀◍●✨◉●•┈•✥╮
/╭✧✞ @Nahuseman256✞ ✧╮\
\╰✧ ✞ @Nahuseman256 ✞✧/
╰✥◉●•┈•🌿◍❀◍●🌿◉●•┈•✥

6 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

3

obunachilar
Kanal statistikasi