ግለ ወሲብ ክብረ ንፅህናን ያሳጣል?
እንዲህ ከላይ እንደተገለፀው ግለ ወሲብ የሚፈፅም ሰው በልቡ እየተመኘ "ያመነዝራል" ብለናል። ይህን ካልን ግለ ወሲብ ክብረ ንፅህናን ማሳጣቱ "የግድ" ይሆናል ማለት ነው። ግለ ወሲብን የመፈፀም ፍላጎት የሚጀምረው በአዕምሮ ላይ በሚቀሰቀስ ክፉ የዲያቢሎስ ሀሳብ ነው። ዲያቢሎስ ይህንን ክፉ ስራ ለማሰራት በተለያየ መልኩ የሰው ልጆችን ይፈታተናል። በተለይም ደግሞ በጉርምስና እና በወጣትነት የእድሜ ክልል ላይ ያሉትን ግለሰቦች የወሲብ ፊልሞችን እንዲያዩ በመገፋፋትና ሁኔታወችን አስቀድሞ በማዘጋጀት በብርቱ ሀይሉ እየተፈታተነ ይህንን ክፉ ተግባር ያስፈፅማል።
ጌታችን በወንጌሉ ሲያስተምረን "ወደ ሴት ያየ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ አመንዝሯል" ብሎናል። ይህ ቃል አንድ ሰው ሀሳቡንና ምኞቱን ካልተቆጣጠረና የአይኖቹን የልቦናውን መንገድ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አድርጎ ካልተንቀሳቀሰ መዳረሻው ሀጢያት እንደሚሆን በግልፅ ይነግረናል። ክብረ ንፅህና ማለት ከተቃራኒ ፆታ ጋር ብቻ ግንኙነት ሳይፈፅሙ መቆየት ብቻ ነው ብለን ካሰብን ተሳስተናል። ትርጉሙ ከዚህም ከፍ ያለ ነው። ክብረ ንፅህና ማለት ዲያቢሎስ የሚቃጣብንን የሀሳብ ውጊያና ልዩ ልዩ ፈተናዎች እንቅስቃሴያችንን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ "ብቻ" በማድረግና የእግዚአብሔርን ሀሳብ "በማሰብ" በፅናትና በትዕግስት ማለፍ ማለት ነው።
የዲያቢሎስን ሀሳብ ላለመቀበላችን እና ፈተናውን ለማለፋችን አንዱ ማረጋገጫችን ክብረ ንፅህናችንን አስጠብቀን መቆየታችን ነው። ክብረ ንፅህና ሀሳባችንን የመቆጠጣጠር፣ ምኞታችንን ፈር የማስያዝ በአጠቃላይ ራሳችንን የመግዛት ልምምድ ነው። የክብረ ንፅህና ዋናው አላማውም ይህ ነው። ግለ ወሲብ ደግሞ በዚህ ረገድ ይህንን ልምምድ በጅምር የሚያስቀርብን ሀጢያት ሆኖ እናገኘዋለን። ስለዚህ ድንግልና/ክብረ ንፅህና ራስን የመግዛትና እርካታን የማቆየት ልምምድ እንደመሆኑ ግለ ወሲብ መፈፀም ይህንን ክብራችንንም ያሳጣናል ማለት ነው። ይህ በመሆኑም ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግንኙነት ስላልተፈፀመ ብቻ "ድንግል ነኝ" ብሎ መናገር ፈፅሞ የተሳሳተ እና ራሱን የቻለ ሌላ ሀጢያት ስለሚሆን በአንደበታችንም መጠንቀቅ ይገባናል።
በዚህ ምክንያት አንድ ግለ ወሲብ ሲፈፅም የነበረ ሰው በእግዚአብሔር እርዳታ ከዚህ ሀጢያቱ ቢላቀቅ በተክሊል ማግባት፤ ድቁናንና ክህነትን መቀበል፤ እንዲሁም ስርዓተ ተክሊልን መፈፀም አይችልም። ምክንያቱም እነዚህ የቤተ ክርስትያናችን ማዕረጋት ከሚፈልጓቸው መስፈርቶች ውስጥ አንዱ ክብረ ንፅህና ስለሆነ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ይህንን ተግባር ሲፈፅም የኖረ ሰው ሀጢያቱን ተናዞ በንስሃ ከነፃ በኋላ ስርዓተ ቁርባንን መፈፀም ይችላል።
ዲያቆን የነበረ ሰው ግለ ወሲብ ቢፈፅምና ቢፀፀት ተመልሶ ድቁናውን ሊያገኝ ይችላል ወይ?
እንግዲህ ግለ ወሲብ እንደማንኛውም ሀጢያት ከፈፀሙት በኋላ ፀፀት ላይ የሚጥል ሀጢያት መሆኑን አይተናል። ሆኖም ግን መፀፀት ማለት ሙሉ በሙሉ ከሀጢያት መንፃት ማለት አይደለም። ከተፀፅትን በኋላም በተደጋጋሚ የምንሳሳትበት ጊዜ ብዙ ነውና ለየትኛውም ሀጢያታችን ንስሃ ብንገባም እንኳን ሁልጊዜም ሀጢያተኛ መሆናችንን መርሳት የለብንም። ዲያቆን ማለት ደግሞ በደረጃ ከሚያንሱት የተሻለ እውቀት ሊኖረው ይገባል(ይኖረዋል ተብሎም ይታሰባል)። ባለው የተሻለ እውቀት ልቦናውን የመግዛት፤ ከዲያቢሎስ ጋር መዋጋትና መንፈሳዊ ህይወቱን ማስጠበቅ እንዲሁም ለሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ብርሃንን የመግለጥና ከዲያቢሎስ ጋር ለሚያደርጉት ውጊያ በተሰጠው የፀጋ መጠን ልክ የማገዝና የማገልገል መንፈሳዊ ግዴታ አለበት። እነዚህ ከእሱ የሚጠበቁ ሀላፊነቶች ሆነው ሳለ ግን እሱ ራሱ ለእንዲህ አይነቱ ሀጢያት እስራት ቢዳረግ በመጀመርያ ራሱን የማንፃት ስራ መስራት ስለሚኖርበት ድቁናውን ያጣል ማለት ነው።
በቀጣይ ...
ከዚህ ሀጢያት እንዴት ነፃ መውጣት እንደምንችል እንመለከታለን።
@orthodoxess