በይቱል መቅዲሥ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ
ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት በመካህ አገር ውስጥ ይገኛል፥ ይህም የአሏህ ቤት “በይቱል ሐረም” بَيْت الْحَرَام ማለትም “የተቀደሰው ቤት” ወይም “የተከበረው ቤት” ይባላል፦
3፥96 “ለሰዎች መጸለያ መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክ እና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው”፡፡ إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ
14፥37 «ጌታችን ሆይ! እኔ *"አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤትክ አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ"*፡፡ رَّبَّنَا إِنِّي أَسْكَنتُ مِن ذُرِّيَّتِي بِوَادٍ غَيْرِ ذِي زَرْعٍ عِندَ بَيْتِكَ الْمُحَرَّمِ
ይህንን ቤት መሠረት ጥሎ የመሠረተው ኢብራሂም ነው፥ ይህ ቤት ያለበትን አገር መካን የቀደሰውም እርሱ ነው፦
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም* «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ *"ከቤቱ መሠረቱን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ለእርሷ፦ *"የአንቺ ሕዝብ(ቁረይሽ) ከዕባህን ሲገነቡ በኢብራሂም በተመሠረተው እንዳልገነቧት ታውቂያለሽ? አሏት። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنهم ـ زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ لَهَا " أَلَمْ تَرَىْ أَنَّ قَوْمَكِ لَمَّا بَنَوُا الْكَعْبَةَ اقْتَصَرُوا عَنْ قَوَاعِدِ إِبْرَاهِيمَ ".
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 521
ጃቢር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ኢብራሂም መካን ቀድሷል፥ እኔም መዲናን ቀድሻለው”። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم “ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ حَرَّمَ مَكَّةَ وَإِنِّي حَرَّمْتُ الْمَدِينَةَ
"ቀዋዒድ" قَوَاعِد ማለት "መሠረት" ማለት ሲሆን ኢብራሂም የዚህ ቤት መሥራች መሆኑን ፍትው እና ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ በተጨማሪም “ሐረመ” حَرَّمَ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! “ሐረመ” حَرَّمَ ማለት “ቀደሰ” ወይም “አከበረ” ማለት ሲሆን ይህም ቤት “በይቱል ሐረም” بَيْت الْحَرَام ይባላል። ከዚያም አምላካችን አሏህ ኢብራሂምን በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር ወደ ሻም ወሰደው፦

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” "ማምለኪያ" ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው፥ የጥንት ሰዎች መሥጂድ አርገው የሚሠሩት ድንኳን ነበር። በኢብራሂም መካህ የተመሠረተው የመጀሪያው መሥጂድ “አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام ማለትም “የተከበረ ወይም የተቀደሰ መሥጂድ” ሲሆን ሁለተኛው መሥጂድ ደግሞ በሻም ምድር በኢብራሂም የተመሠረተው “አል-መሥጂዱል አቅሷ” الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى ማለትም “የሩቅ መሥጂድ” ነው። በሁለቱ መሣጂድ ምሥረታ መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
አቢ ዘር ሰምቶ እንደተረከው፦ “እኔም፦ ”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በምድር ላይ መጀመሪያ የተመሠረተው የትኛው መሥጂድ ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል ሐረም” አሉ። እኔም፦ “ከዚያስ ቀጥሎ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል አቅሷ” አሉ። እኔም፦ “በሁለቱ መካከል ምን ያህል የጊዜ ልዩነት አለ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አርባ ዓመት” አሉ”። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ مَسْجِدٍ وُضِعَ فِي الأَرْضِ أَوَّلُ قَالَ ” الْمَسْجِدُ الْحَرَامُ ”. قَالَ قُلْتُ ثُمَّ أَىٌّ قَالَ ” الْمَسْجِدُ الأَقْصَى ”. قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَهُمَا قَالَ ” أَرْبَعُونَ سَنَةً،
“ዉዲዐ” وُضِعَ ማለት “ተመሠረተ” ማለት ነው፥ ከዚያም አምላካችን አሏህ ዙሪያውን በባረከው በሁለተኛው የሩቁ መሥጂድ ላይ ሱለይማን ሕንጻ አል-በይቱል መቅዲሥ ገነባ፦
34፥13 ”ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል”፡፡ አልናቸውም፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ
ቻናላችን ይቀላቀሉ ⬇️⬇️⬇️ ioin
⬇️⬇️ join ⬇️⬇️⬇️
https://t.me/Reslan1