Al Qalam - القلم


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Al - Qelem Online Arabic and Quran Institute
አል ቀለም የቁርአን እና የአረብኛ ቋንቋ ተቋም

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የአረብኛ ቋንቋ ጥንታዊ ከሆኑና የሴሜቲክ ዝርያ ካላቸው ቋንቋዎች ይመደባል። ይህ ረዥም እድሜ ቋንቋው በሂደት እንዲዳብርና ሰፊ መዝገበ ቃላት እንዲያካትት ረድተውታል።

💡 የሚደንቀው ነገር ቋንቋው ከአንድ ሺህ አመታት በፊት የሚገለገልባቸው ቃላት አሁንም ድረስ በነበሩበት ትርጉም አገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። በሌሎች ቋንቋዎች ግን ከትውልድ መቀያየር ጋር በተያያዘ ቃላት ከበኩር ትርጉማቸው ሲያፈነግጡ እንዲያውም ቀጥተኛ ተቃራኒ ትርጉምን መወከል ሲጀምሩ ይስተዋላሉ።

🔖 ለምሳሌ በእንግሊዘኛ ቋንቋ “Wicked” ብሎ ማለት ከጥቂት አመታት በፊት “መጥፎ” ማለት የነበረ ሲሆን አሁን ግን በተቃራኒው “ጥሩ” የሚል መልእክትን ለማስተላለፍ ሊገባ ይችላል። አረብኛ ቋንቋን ከዚህ መሰሉ የመዝገበ ቃላት መሸርሸር የታደገው ምን እንደሆነ በስፋት የምናየው ይሆናል።

@alqalamarabic
@alqalamarabic
@alqalamarabic


የአረብያው ባህረሰላጤ በ1930ዎቹ ገደማ ከበረሀው በታች ለዘመናት ቢቀዱት የማያልቅ የነዳጅ ክምችት እንዳቆረ ከመታወቁ በፊት አካባቢው ለምንም ነገር የማይጋብዝ ከባድ ሀሩር ነበር

በተለይም ደግሞ በቅድመ ኢስላም ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሮም እና ፋርስን የመሰሉ ግዙፍ ኢምፓየሮች ልክ በሌሎች ግዛቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ በመካ ዙሪያ ያለውን ህዝብ ለማስገበር እምብዛም ጦር አልሰበቁም።

የረባ አልነበረምና ነው፥ እንዲያውም ጦር ለማዘጋጀትና በረሀው ላይ ቋሚ ሰራዊት ለማኖር የሚወጣው ወጪ በኢምፓየሩ ላይ ከባድ የኢኮኖሚ ጠባሳ በጣለ ነበር።

በመሆኑም የአረብያ ህዝብ በራሱ በሆነ ብልሀትና ጥንካሬ ሳይሆን ተፈጥሮ በቸረችው ለኑሮ የማይመች በረሀ ምክንያት ከቀኝ ወራሪዎች ተጽእኖ ለዘመናት ተጠብቆ ኖሯል። ለንግድ ልውውጥም ቢሆን ያን ያህል አጓጊ መድረክ ስላልነበረ በበረሀው ወበቅ ለመጠበስ ፍቃደኛ ሆኖ የሚመላለስ ነጋዴ አልነበረም። በሌሎች ክፍላተ አለማት ከሚስተዋለው የገበያና የገበያተኛ ቅይጥ አንጻርም የአረብያው በረሀ አንድ አይነት ህዝብ ብቻ የተከማቸበት ድፍን ከባቢ ነበር። ይህ ህዝብ በሌሎች ተጽእኖ ለመጠቃት የማይመች፥ በራሱ ለማጥቃት ደግሞ ጉልበት የሌለው፥ የተነጠለ ህዝብ ነው።

@alqalamarabic
@alqalamarabic
@alqalamarabic


ኢብን ሀዝም እንዳሉት የቋንቋዎች ሁሉ ምርጥ ቋንቋ የሚባለው በገለጻው ሁሉን ነገር ማጠቃለል የሚችል፥ ግልጽና ቀላል በሆነ መልኩ የሚዋቀር፥ አሻሚ ቃላት የማይበዙት፥ እጥር ምጥን ያለና በርካታ መዝገበ ቃላት ያሉት ሊሆን ይገባል ይላሉ።

💡 የአረብኛ ቋንቋ ደግሞ እነዚህን መስፈርቶች ከማሟላት ባለፈ እያንዳንዱን ነገር በስእላዊ መልክ በመሰየም ጭምር ንግግርን ከሚደመጥ ወሬ ወደ ሊመለከ ቱት የሚችል ምስላዊ ትእይንት የመቀየር ጉልበት አለው።

@alqalamarabic


Al - Qalam Online Arabic and Quran Institute
አል ቀለም የቁርአን እና የአረብኛ ቋንቋ ተቋም

@alqalamarabic


Al - Qalam Online Arabic and Quran Institute
አል ቀለም የቁርአን እና የአረብኛ ቋንቋ ተቋም

@alqalam

🔎https://t.me/joinchat/RepHc9OIib34qGfi

5 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

94

obunachilar
Kanal statistikasi