Eff sprisonpomi


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


"ከህይወት ውሀ የጠጣ ሁሉ ራሱ ምንጭ ይሆናል"
If you have any
comment use
👉 📫 @effisspbot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


𝔻𝕚𝕕𝕚 - ℬ𝒶𝓈𝓈 𝒫𝓁𝒶𝓎ℯ𝓇 🎸 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
New music❗❗❗
I've been blessed with such opportunities. 🙏🏽🙏🏽🙏🏽 I didn't take it for granted and I won't ever take it lightly. God just keep blessing me. Always grateful. 🙏🏽🙏🏽🙏🏽
Fam Be blessed with this amazing song.
Singers 🎙 Mussie Fisseha
🎙 Meskerem Getu
Music Production 🎹 💻Ermias M Alemu
Bass 🎸 @DidiBass8
Guitars 🎸 Kalab Tekil
Mixing 🎛 Robel Dagne
Video Production 💻🎥 Naod Ahavah
🎧HEADPHONES RECOMMENDED!!!🎧

Full Video on YOUTUBE
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
👉🏾 https://youtu.be/WQTKYX-IpJk 👈🏾
☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾☝🏾

FOLLOW ME!!!👇🏾👇🏾👇🏾
FACEBOOK
➡️ https://www.facebook.com/didi.k.wolde.48

FACEBOOK PAGE
➡️ https://www.facebook.com/Didi.K.Wolde.Page/

INSTAGRAM ACCOUNT
➡️ https://www.instagram.com/didi_k_wolde__

TWITTER
➡️ https://twitter.com/Didi_K_Wolde?s=09

MY YOUTUBE CHANNEL
➡️ https://www.youtube.com/c/DidiKWoldeETHIOPIANBASSPLAYER


"፤ ኢየሱስም፦ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤"
(የሉቃስ ወንጌል 19: 9)


ኤደን ብርሀኑ dan repost
#ማሰብና #መደሰት

#እግዚአብሔርን ማሰብ

"እግዚአብሔርን #አሰብኩት #ደስም አለኝ"መዝ.77:3

ደስታም ሆነ ሀዘን የማሰብ ውጤት ነው፡፡
ለመደሰት ከፈለግን ማሰብ አለብን፡፡

ሲያስቡት የሚያስደስት እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
እራሳችንን እንኳ ያለ እግዚአብሔር #ካሰብነው አስደሳች አይደለንም፡፡

እግዚአብሔር ደስታ የምናይበት መልካም መነፅር ነው፡፡
ቀኑን በጌታ ስናየው ያስደስታል፡፡
ሰዎችን በጌታ ስናያቸው ያስደስታሉ፡፡

እግዚአብሔር በማድረጉ ብቻ አይደለም #በመታሰቡ #ደስታ ነው

እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በማሰብ የደስታ #ሰንበት ይሁንልን🙏

መልካም ሰንበት


Dr. Eyob dan repost
ጥያቄ፡-
ሰላም ዶ/ር ለእድሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ እኔ ብዙ ጊዜ ነገሮች ሳይሳኩልኝ ሲቀሩ ወደ እደለቢስነት እቀይረዋለሁ በእርግጥም እድለቢስ የሚያስብል እድል አለኝ፡፡ ለኔ ሲሆን በህሩ ደርቆ አፈር ይሆናል ለኔ ሲሆን ምርኩዜ ይቀልጣል ግን የእውነት እድል አለ? እድለ ቢስነት አለ? ወይስ በተግባር ስሳት ስያሜ እየሰጠሁት ነው የእውነቴን ነው ምልህ ለኔ ሲሆን አይሳካም ሌሎች ያደረጉትን ባደርግ እንኳ በእኔ ግዜ አዲስ ህግ ይወጣል እስኪ ምን ትለኛለህ?

መልስ፡-
“ነገሮች ሳይሳኩልህ ሲቀሩ ትርጉሙን ወደ እድለ ቢስነት ለምትቀይረው”፡-

“እድል” የሚባለው ሃሳብ የብዙ መከራከሪያ ነጥብ ነው፡፡ ከሁለት ጽነፎች እንድትጠበቅ ልምከርህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች “እድል የሚባል ነገር ፈጽሞ የለም” ይላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ “እድል የሚባል ነገር አለ፣ ምንም ብንለፋ እድለኞች ካልሆንን የትም አንደርስም” ይላሉ፡፡ ከእነዚህ ሁለት አመለካከት መካከል ላይ ሚዛናዊ አመለካከት አለ ብዬ አምናለሁ፡፡ “እድል” የሚባል ነገር አለ፣ ነገር ግን እድል የሚባለው ነገር ሲመጣ እድሉን የሚመጥን ዝግጁነት ከሌለ ግን የትም አንደርስም፡፡

ከዚህ በፊት ለአንድ ጥያቄ ስመልስ “የፖሰትኩትን” ላስታውስህ፡- አጋጣሚን የሚመጥን ዝግጁነት ያለመኖር ችግር፡- ይህ ብዙ ሰዎች “እድል” ብለው የሚጠሩት ጉዳይ ነው፡፡ አንድ አጋጣሚ ሲገኝ አንዳንዶች ዝግጁ ስለሆኑ ይዘውት ሲሮጡ ሌሊች ግን ያልፋቸዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹን በልማድ እድለኞች፣ እነዚያኞቹን ደግሞ እድለ-ቢሶች እንላቸዋለን፡፡ አጋጣሚ ሲመጣ እንዳያመልጥህ ዝግጁ ሁን፡፡
አንተ ያለህበት አመለካከት አደገኛነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ አንድ ሰው እድለቢስ ነኝ ብሎ ካሰበ በሄደበት ቦታ ሁሉ የሚያየው ያልተሳካውን፣ ያልሆነውንና የተሰናከለውን ነው፡፡ እሱን ከማየቱ የተነሳ ሌላኛውን የሚጓጓ ነገር ለማየት የሚያበቃ ሁኔታ አይኖረውም፡፡

ለአንተ ሲሆን ባህሩ ከአንተ በፊት እኮ ለእኔ ሲሆን ደረቁ መሬት በውኃ ተሞላና ባህር ሆነብኝ ብሎ ራሱን እንደ እድለ ቢስ የቆጠረ ሰው እንደነበር አትጠራጠር፡፡ አሁን ደግሞ ባህሩ ደርቆ አፈር ሲሆን ያኛው ሰው እኔ ስፈልገው ያልመጣ ባህ አሁን መጣ ብሎ ሊያማርር ይችላል፡፡ በእነዚህ በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጠ ግን ደረቅ መሬት ሲሆን ለደረቅ መሬት የተዘጋጀ እቅድ፣ ባህር ሲሆን ደግሞ በውኃ ላይ የሚሰራ ነገር እቅድ ይዞ የተዘጋጀ ሰው በሁለቱም ሁኔታ የሚሰራው አያጣም፡፡

ነገሮች አልሳኩ ብለውና ጠማማ ሆነው እንዳስቸገሩህ በሚገባ ተገንዝቤያለው፡፡ ብዙ አንባቢቼና እኔንም ጨምሮ ለሰዓታት ተሰልፈን የጠበቅነው ተራችን ሲደርስ ቢሮው ተዘግቷል የተባልንባቸውን ጊዜያት አንረሳውም፡፡ በመዘጋቱ ውስጥ ልናደርግ የምንችለውን ነገር አስበን ከሁኔተዘው ዘወር ከማለትና ሲከፈት ከመመለስ ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ እድለቢስ ነኝ ብልን ብንሄድ ግን ጉዳያችን ይቀራል እንጂ ምንም አናመጣም፡፡

ስለዚህ አይዞህ፣ በርታና ተዘጋጅ፣ አዎንታዊ ሁን፣ አንኳኳ፣ ሞክር፣ አትማረር . . . አንተና ዓላማህ መገናኘታችሁ አይቀርም፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623




Dr. Eyob dan repost
ለማን ምን ሰጠህ?

“በምናገኘው ነገር እንኖራለን፣ በምንሰጠው ነገር ደግሞ ሰውን እናኖራለን” - Winston Churchill

በአሁን ጊዜ በእጅህ ካለው መልካም ነገር አንዱም እንኳን ከሰዎች መዋጮ ውጪ እጅህ እንዳልገባ እንዳስታውስህ ፍቀድልኝ፡፡ የአንድ ሰው የመወለድ፣ የማደግ፣ የመማርና ሰርቶ የማደር ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር የተሳሰረ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች በሌሎች እርዳታ ኖሩ፣ ተደራጁ፣ ተሻሻሉ፤ ከዚያም በእነሱ እርዳታ ደግሞ ሌላውን አኖሩና አለፉ፡፡ ተተኪዎቹም እንዲሁ ከሌላው የተረከቡትን ይዘው ቀጠሉና ለሌላው አቀበሉ፡፡ ይህ የኑሮ ዑደት ቀጣይና የማያቋርጥ ነው፡፡

እውነታው ሲሰበሰብ፣ ከሌሎች በተቀበልነው ነገር ለመኖር የመቻላችንን ያህል፣ እኛ ደግሞ በምንሰጠው ለሌሎች ሰዎችን እናኖራለን፡፡ ጊዜው መጥቶልን ራሳችንን እስከምንችል ድረስ ለሕልውናችን የተደገፍንበት ሰው እንደነበረ እሙን ነው፡፡ ራሳችንን ቻልን ባልንበት ጊዜ እንኳ አሁም ከሌላው ሰው መዋጮ ውጪ ማድረግ የማንችላቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ አሁን ደግሞ በእኛ ሁኔታ ላይ የሚደገፉ ሰዎች መኖራቸውን ማስታወስ የእኛ ተራ ነው፡፡ በሌላው ሰው ድጋፍ ኖረን በእኛ ድጋፍ ደግሞ ሌላውን የማኖርን ምስጢር እንግፋበት፡፡

ትናንት ለማን ምን ሰጠህ? ባለፈው ሳምንት ለማን ምን ሰጠህ? ባለፈው ወር ለማን ምን ሰጠህ! ባለፈው ዓመት ለማን ምን ሰጠህ? ዛሬ ለማን ምን ትሰጣለህ?

ስጥ! ስትሰጥ ግን ምስጋናን ፈልገን አትስጥ! ስጥ! ስትሰጥ ግን ምላሽን ጠብቀህ አትስጥ! ስጥ! ስትሰጥ ግን ዛሬ መስጠትህ ነገ ትርፍ እንደሚያመጣልህ አስበህ አትስጥ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623


ኤደን ብርሀኑ dan repost
የእግዚአብሔር ባህሪ

👉የአንድን ሰው ፀባይ(ባህሪ) ማወቃችን ለእኛ ጠቃሚ ነው፡፡ከዛ ሰው ጋር ለመቆየት ይጠቅመናል እንዲሁም አብሮ ብዙ እርምጃዎችን ለመጓዝም ይረዳናል፡፡ከሰው ባህሪ ጥሩም መጥፎም እናገኛለን፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንደው ፤ውይ የእገሌ ፀባይ እንዴት ደስ ይላል ፥ውይ የእገሌ ፀባይ እንደት ይከብዳል....
እንላለን፡፡.......


ግን አንድ ስለተማረኩበት ባህሪ ልንገራችሁ፡፡

💢እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው፡፡

..............እግዚአብሔር ፍቅር ነውና 1ዩሐ4:8
እግዚአብሔር ማፍቀር ባህሪው ነው፡፡

♨️ቅዱስ አምላክ ነው፡፡

ሁሉን የምትገዛ አምላክ ሆይ ስራህ ታላቅና ድንቅ ነው ጌታ ሆይ የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማነው?አንተ ብቻ #ቅዱስ ነህና.....ራዕይ15:3-4

♨️እውነተኛ አምላክ ነው፡፡

እርሱ አምላክ ነው ስራውም ፍፁም ነው መንገዱም የቀና ነው የታመነ አምላክ ክፋትም የሌለበት እርሱ #እውነተኛና ቅን ነው፡፡ዘዳ32:3-4

♨️የምህረት አባት ነው፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር #በምህረቱ ባለ ፀጋ ስለሆነ ፥ኤፌ2:4

♨️ታማኝ አምላክ፡፡

መዝሙር 89:33
ኤር 3:22-23

♨️ብርቱ አምላክ ነው፡፡

የማይታየው ባህሪ እርሱ የዘላለም #ሐይሉ ደግሞ አምላክነቱ...
ሮሜ1:20

♨️ለሙሴ ሲገለፅ፡፡

እግዚአብሔርም አልፎ ፦እግዚአብሔር እግዚአብሔር #መሐሪ ፥ሞገስ ያለው ፥#ታጋሽም ፥ባለብዙ #ቸርነትና #እውነት እስከ ሺ ትውልድም የሚጠብቅ አበሳን መተላለፍን ሐጥያትንም #ይቅር የሚል በደለኛውን ከቶ የማያነፃ የአባቶችንም ሐጥያት በልጆች እስከ ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች የሚያመጣ አምለክ ነው ሲል አወጀ፡፡

☑️የእግዚአብሔር ባህሪ ማወቃችን ብዙ እርምጃዎችን ከአምላካችን ጋር እንድራመድ ይረዳናል፡፡

☑️በዚህ ምድር ላይ ክርስቶስን መስሎ ለመኖርም ይጠቅመናል፡፡እንዲሁም እንደ ባህሪው #ለመመላለስ ይረዳናል፡፡

☑️በታማኝነት ፥ በፍቅር ፥በምህረት #በብዙ #ባህሪያቶች በሰዎች ተቸግረን ከሆነ ወደ አምላክ ባህሪ እንዙር፡፡የእርሱ ባህሪ #የማይቀያየሩ ናቸውና፡፡




Dr. Eyob dan repost
የስኬት ቁልፎች፡- ስኬትን የማይመኝ ሰው የለም፡፡ የስኬት ትርጉም ግን አወዛጋቢ የሆነበት ወቅት ላይ ነን ያለነው፡፡ ስኬት ለሚለው ቃል ሰዎች እንደ መነሻ ሃሳባቸውና እንደምኞታቸው ትርጉሙን ይለዋውጡታል፡፡ የስኬትን ትክክለኛ ትርጉምና 25 መሰረታዊ የስኬት ጎዳናዎችን ለመገንዘብ ይህ መጽሐፍ የግድ ነው፡፡ በ25 አስገራሚ ታሪኮች ላይ የተደገፈ አስገራሚ መጽሐፍ ነው፡፡

ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . .

የሆነልህን እንጂ የሆነብህን አትቁጠር

ሳታሸንፍ በፍጹም እዚህ አልደረስክም፡፡ አንተ የአሸናፊዎች ምሳሌ እንጂ በፍጹም የተሸናፊዎች ምልክት አይደለህም፡፡ የአየሩን መለዋወጥ፣ የኢኮኖሚውን ከፍና ዝቅ ማለት፣ ከሰዎች የሚሰነዘርብህን ደስ የማያሰኙ ሁኔታዎች … አልፈህ እዚህ ደርሰሃል፡፡ ከአሁን ወዲያ ደግሞ ከተሳሳትካቸው ነገሮች ትምህርትን፣ ከተሳኩልህ ጉዳዮች ደግሞ ድፍረትን በመያዝ ወደፊት የመሄድ ሃላፊነት አለብህ፡፡

ማታ እቤት ስትገባ በሰላም መግባትህን አስብ እንጂ ከኪስህ የጠፋውን ገንዘብ ወይም የሞባይል ቀፎ በማሰብ፣ ወይም በመንገድ ላይ ያበሳጨህን ሰው በማሰላሰል አእምሮህን አትሙላው፡፡ ውስጥህን በይሆናልና በይቻላል መሙላት ከአንተ በፊት ያለፉ ሰዎችን አስደናቂ ፈለግ የመከተል አስገራሚ እርምጃ እንጂ የቅዠት ምልክት አይደለም፡፡ የሆነልህን መልካም ነገር አእምሮህ ውስጥ ስፍራን ስጠውና በመኮትኮት አሳድገው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ጤና ቢሱን ሃሳብ ስፍራ በመንፈግ አስርበውና እንዲሞት አድርገው፡፡

“ከሃዘኖችህ ይልቅ ሃሴቶችህን፣ ከጠላቶችህ ይልቅ ደግሞ ወዳጆችህን ቁጠር” - Irish Proverb

ስለሚወዱህ ሰዎች ከማሰላሰልና ስለሚጠሉህ ሰዎች ከማሰብ የትኛው ጥሩ ስሜት ይሰጥሃል? የሚወዱህ ሰዎች የነገሩህን የፍቅርና የአክብሮት ቃል ከማሰብና የሚጠሉህ ሰዎች የነገሩህን ስሜትን የሚወጋ ቃል ከማሰላሰል የቱ ይሻልሃል? ምርጫው የአንተ ነው፡፡

ቁጭ ብለህ የማይቀበሉህ ሰዎች ማን ማን እንደሆኑ ከመቁጠር፣ የሚወዱህንና የሚቀበሉህን ሰዎች መቁጠር በስኬትህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ አለው፡፡ ጨለማን በብርሃን አሸንፍ እንጂ በጨለማ አትሸነፍ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623


🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻️🌹⁣🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊





https://t.me/joinchat/AAAAAEfX223-mkRE5vFvWA


ኤደን ብርሀኑ dan repost
🕺🚶‍♀🚶#እንሻገር

ደሞ ወዴት?

👉በጎም ሆነ ክፉው የሕይወት ገጠመኝ #በቀን ውስጥ የሚፈፀም ነው፡፡

ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙሩን ፦"እንሻገር"አላቸው፡፡

👍በመሻገር የበለጠ ሊያሳያቸው፡፡

#ማቲዎስ "እንሻገር የሚለውን ቃል አልመዘገበውም ፤ተአምራቱን ግን መዝግቦታል፡፡#ማርቆስ ግን ፦"በዚያን ቀን በመሸ ጊዜ ፦ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው" (ማር 4:35)በማለት ፅፎልናል፡፡

🌧በክረምት ማንም ሰው መሻገር አይፈልግም ፥በምሽትም ባሉበት መቅረት እንጂ መሻገር ማንም አይሻም፡፡ ጌታችን ግን".........ወደ ማዶ እንሻገር" አላቸው፡፡

☀️ከቀን ምሽት የዘመን ምሽት ይከብዳል፡፡
መኖር አያስመኝም ፡፡ምንም ዘመን ቢከፋ ከጌታ ጋር መሻገር ግን ብዙ ተአምር ያሳያል፡፡

🌊መሻገር መርጠው በታንኳ እንደ ተሳፈሩ ብርቱ #ማዕበል ገጠማቸው፡፡ማቲ 8: 23-27

🌚ከታንኳም እንደወረዱ በአስከፊ ሁኔታ በአጋኒት የተያዘ ሰው አገኙ፡፡(ማር 5:1-20)

☀️ለሐኪም ገንዘቧን የጨረሰችው ክርስቶስን በእምነት መንኳቷ እሷም ተፈወሰች፡፡ (ማር 5:21-34)

☀️ወደ እያሮስ ቤት ሲገቡ ልጅቷ ሞታ አልቃሿች እየተቀባበሉ ያሟሹ ነበር፡፡የሞተችዋን እንደ እንቅልፍ ቀስቅሶ ዝማሬ ሰጣተው፡፡(ማር 5:35-43)

🌑ደቀ መዛሙርቱ ፦እንሻገር ሲላቸው አይ "ምሽት"ነው ቢሉ ኖሮ ይህን ሁሉ ተአምር ለማየት ባልታደሉ ነበር፡፡

💦ከጌታ ጋር መሻገር በመፍቀዳቸው ግን ማዕበል ሲታዘዝ ፥የመቃብሩ እብድ ከሰው ሲደመር ፥ዐስራ ሁለት አመት የፈሰሰው ደም ሲቆም ፥የሞተችው ብላቴና ስትነሳ አዩ፡፡

🌎እኛስ ዘመኑን በመፍራት ሞትን እየለመንን ይሁን ?በማያቋርጥ የሕይወት ትግል የተነሳ በሞቱት ወገኖቻችን ቀንተን ይሁን?

👉ያሳለፍነው ቀንና አመት ትዝታ ምንም ይሁን፡፡
ብዙ ለመስራት ከእግዚአብሔር ጋር እንሻገር፡፡
ያቀድነው እቅድ የእውነት እንዲሳካልን ከአንተ ጋር መሻገር እፈልጋለሁ እንበለው፡፡

🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀🚶‍♀🚶ከጌታ ጋር እንሻገር ብዙ ድንቅ እናያለን፡፡
አዎ ችግሮች ያልፋሉ፡፡ጠንካራ ሰዎች ግን አያልፉም፡፡

💢💢እንሻገር💢💢
💢💢ከጌታ ጋር 💢💢


Emory Horne dan repost


የማለዳ ጣፋጭ መልዕክት
ከወንድም Emory Horne

👇👇👇👇👇


♨️ስለ መገረዝ
. . . . . . . . . . . . . ,

መገረዝ ያማል ምክንያቱም ከራስ ሰውነት ላይ ስለሚቆረጥ፡፡ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር የሚያሶግደው ፥አገልጋዮችና እራሳችን ናቸው፡፡

1,እግዚአብሔር ብቻ የሚያከናውነው መገረዝ፡፡
....................................
"በሕይወት እንድትኖር አምላክህን እግዚአብሔርን በፍፁም ልብህ በፋፅም ነፍስህ እንድትወድድ አምላክህ እግዚአብሔር ልብህን የዘርህንም ልብ #ይገርዛል፡፡ዘዳግም 30:6

👉በአገልጋይነት ሕይወት የነገሰ ነውር ጌታ በመንፈስ ቅዱስ ቆርጦ ካላወጣው በስተቀር ምንም ነገር አይበግረውም፡፡
.....................................
2ሌሎች ሊያከናውኑት የሚችሉት መገረዝ፡፡

ይህ ሐሳብ በእያሱ ምዕራፍ አምስት ውስጥ የተፃፈውን በመደገፍ እንመልከት

እያሱ 5:9 ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናተ ላይ አንከባልያለሁ ብሎ ተናገራቸው ይህ ነውር እንዲከባለል ግርዛቱን እያሱ ማከናወን ነበረበት፡፡በእኛም ህይወት ጌታ በአጠገባችን ባቆመልን አገልጋዮች አማካኝነት ሊገረዙ የሚችሉ ነውሮች ቢኖሩጌታ በእነሱ ተጠቅሞ እንዲገርዝልን ልንፈቅድ ይገባናል፡፡
.......................................
3,እራሳችን ልናከናውነው የሚገባ ን መገረዝ፡፡

👉እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ ታላቅ አምላክ ኃያል የሚያስፈራ በፍርድ የማያዳላ ማማለጃ የማይቀበል ነውና እናተ የልባችሁ ሸለፈት ግረዙ ... ዘዳግ 10:16

ሰው ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ በፊት በልብ ያለውን ቂም ማስወገድ አለበት ማቲ5:23

©ኤደን ብርሃኑ



https://t.me/joinchat/AAAAAEfX223-mkRE5vFvWA


ቀጠሮ የለውም
ዛሬም የይቅርታ ቀን ነው….

መጽሐፍ ቅዱስ ጸሀይ ሳትጠልቅ በፊት ይቅር መባባል እንዳለብን ቢነግረንም በዓመት አንድ ቀን ጠብቀን ‹ያስቀየምኩት ካለ› ተብሎ እርስ በእርስ ይቅር መባባሉ ሌላ ይቅርታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው ባይ ነኝ::በመጀመሪያ ይቅር ከመባባላችን በፊት የበደልነውን/የበደሉን ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን ሲቀጥል ደግሞ ሁኔታውን ማየት አለብን ይህም ጥፋቱ ሰው የሚያውቀው ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ያለብን በሰው ፊት ነው በግል ከሆነም እንዲሁ::ያጠፋነውን ጥፋት ስም ጠርተን መናገር አለብን እንጂ ያስቀየምኩት ካለ በሚል ስልክ ላይ ብቻ ያሉ ሰዎችን ይቅርታ መጠየቅ የዓፍ ወለምታ በድሊት አይታሽም ነው ነገሩ::ደግሞ ለክርስቲያን የይቅርታ ቀን ጳጉሜ 1 ብቻ ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ ነው!
‹እውነተኛ ኑዛዜ ሁል ጊዜ ጠቅለል ተደርጎ የሚቀርብ ሳይሆን እያንዳንዷን ሐጥያት በዝርዝር ማውሳት ይጠይቃል::ምናልባትም የሰራነው ሀጥያት በእግዚአብሔር ፊት ብቻ መቅረብ ያለበት ሊሆን ይችላል::ሰውን ጎድተን ከሆነ ወደዚያ ሰው ቀርበን ድርጊታችንን ማመን ተገቢ ነው::በህዝብ ፊት መናዘዝ የሚያስፈልገው ሀጢያት ሰርተንም ከሆነ በድረክ ላይ መናዘዝ ተገቢ ነው::ይሁን እንጂ የትኛዉም ዓይነት ኑዛዜ ግልጽና ቀጥተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ በደለኛ የሆንበት ጥፋት የቱ እንደሆነ የሚገልጽ መሆን አለበት››ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ ገጽ 36




https://t.me/joinchat/AAAAAEfX223-mkRE5vFvWA


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


መግዛት የምትፈልጉ እዘዙን






#ጥጃ_ሰሪ_አገልጋይ

የጌታ ሰላም እና ጤና በያላችሁበት ይሁን እያልሁ ጌታ ወዳካፈለኝ ሀሳብ ላምራ::ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ከእግዚአብሄር ጋር ሲነጋገር እንደዘገየ ባዩ ጊዜ እስራኤላውያን አሮንን ‹በፊታችን የሚሄድ አማልክት ስራልን›አሉት ሙሉ ሀሳቡን ዘጸዓት ምዕራፍ 32 ላይ ስታነቡ ታገኙታላችሁ::እናም አሮን ወርቅ አሰባስቦ ቀጥቅጦ አስተካክሎ ጥጃ አድርጎ ህዝብ ሁሉ እንዲያመልኩ በፊታቸው አቆመ::በጣም የገረመኝ ሙሴ ሲጠይቀው ቁጥር 24 ላይ‹እኔም። ከእናንተ ወርቅ ያለው ሰው ከእርሱ ሰብሮ ያምጣልኝ አልኋቸው ሰጡኝም በእሳትም ላይ ጣልሁት፥ ይህም ጥጃ ወጣ።› አለ።ወርቁን ቀጥቅጬ እሳት ውስጥ ስጨምር በሚገርም ሁኔታ አንድ ምታታዊ በሆነ ታላቅ ሀይል miracle የሆነው "ወርቅ እሳት ውስጥ ጨመርኩ ጥጃ ሆነ" ማለቱ ነው ይህም የግል performance እያሳየ መሆኑ ነው።አሮን ጥጃ ሰርቶ ተዓምር ነው የተከሰተው እያለ ለሙሴ ይመሰክራል::

ራሳቸው ቀጥቅጠው አበጅተው አንድ ታላቅ ተዓምር ተደርጓልና ኑ አምልኩ የሚሉ ጥጃ ሰሪ አገልጋዮች በበዙበት ጊዜ ላይ አለን።እነርሱ የሚያስመልኩት የሰሩትን አማልክት ነውና እንጠንቀቅ።




https://t.me/joinchat/AAAAAEfX223-mkRE5vFvWA

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

580

obunachilar
Kanal statistikasi