ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


እንኳን ወደ ኤፍሬም ስዩም እና የሌሎች ግጥም ባለቤቶች ተቀላቀሉን
እንዲለቀቅ ምትፈልጉት የማንኛውም ገጣሚ ግጥሞች ካሏችሁ እንዲሁም ለአስተያየት ያናግሩን 👉🏽 @ethiel_etoyope

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


#የማርያም_ንግስ_እለት
.
አዳፋ ነጠላ በቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ. ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፥ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች .........
ከቤተክርስቲያን አፀድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት .....ትለማመን ነበር
,
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል።
,
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
ከቤተክርስቲያን ጓሮ ቆማ ከዋርካ ስር።
,
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምዕመን ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል።
,
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደመወዝ ሊጨመር ግድ ይላል
3
ደጀ ሠላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ......
.
እናም.......
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እጃቹ የት - አለ?
እያለ።.....
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል።......
ለንግሱ የመጡ.....
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች....
ጥለት የለበሱ ፥ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ....እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሠላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በሺ .....የሚቆጠሩ
ብሮች ወረዋሩ....
.
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ውዛ
የሚወረወረው ብሩም በጣም በዛ።
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካ ስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር::
,
ኣደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል
አንቺ ነሽ ተስፋዬ የኔስ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች።
,
,
ግና ግን ለዛሬ ፥ ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጂ አምሃዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የኣንገት ሃብሌን::

ምንጭ "ኑ ግድግዳ እናፍርስ''

//ኤፍሬም ስዩም//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


እኔስ ስምየለኝም አንተው ነህ ማእተቤ
አክትቤ የያዝኩህ በአፍም በልቤ

ታየውም የለ ወይ መች ይቀርልሀል
እንቢ ብትል እንኳን ከኔ ተቀመጠሀል
ውበትስ የጋራ እንጂአይደለም ከኔ ዘንድ
ካንተው ጋር ሲሆን ነው ሁሉም የሚዛመድ


@efremsyum
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢


#መለያየት_ማለት

ይኸው ትላንትና ከትላንትም በስትያ
ያዩሽ ሰዎች ሁላ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ አለም!! ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው።

ለኔ ና ላንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት... ያለመተያየት
መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ህይወት
ዘወትር....
ዘወትር ምናልባት.........
ምናልባት እያለች የምትኖር ህይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት

በታስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው....
ልቤና ልቦናው ተጣብቀዋል በያችቸው
እንጂ በኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት....
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት

//ኤፍሬም ስዩም//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#ውሸት_ነው

ፍቅሬ አንዳንድ ግዜ አመሌን የማጣው
በንፁህ ጨዋታሽ የምነጫነጨው
በጥርስሽ ብርሀን ፊቴን የማጠቁረው
ምነው ሆዴ ስትይ ብወድሽ የምለው
እውነት እንዳይመስልሽ አይደለም ውሸት ነው።
.
ደግሞም አንዳንድ ቀን
እኔ አንቺ አብረን ሆነን
የምለይሽ በሰመመን።
ከሰመመን መልሰሽኝ
ምንው ሆዴ ስትይኝ
ሀሳብ የከተተኝ
ፍቅርሽ ነው ያልኩትኝ
እውነት ይሁን ውሸት እኔንም አልገባኝ።
.
ሌላም በሌላ ቀን አዱኛ ስተርፈን
አድባር ሲቀርበን ፍቅር በልተን
ፍቅር ሰርተን እንዳበቃን
ታፈቅረኛለህ ስትይኝ ከእኔ በላይ ያልኩትኝ
በእውኔ አይሆንም በህልሜ መሰለኝ።
.
ደግሞም ሌላ ጊዜ
ከሀገር ምድር ተገልለን
እኔ ባንቺ አንቺ በእኔ ተጠልለን
ምሽት ደርሶ ሲለያየን
ጀንበር ዘቀዘቀችች መለየት ሊሆን ነው
ነግቶ እስከማይሽ ናፍቆት ብዙ ነው
ብዬ ያወራሁሽ እኔ ልሙት ብዬሽ
እውነት እውነት ስልሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት ነው ልንገርሽ
በፈጠረሽ አምላክ ይሄን ሁሉ እውነት
አሁን የነገርኩሽ እራሱ ውሸቱን እውነት
እንዳይመስልሽ።
.
እውነት ግን አለሜ
ውሸት ይመስልሻል አንቺን ባላፈቅር
ይሄ ሁሉ ይወራል ውሸቴን ነው ተብሎስ
ከወደዱት ሌላ ለጠላት ይፃፋል
እውነቱን ልንገርሽ ሊፃፍም ይችላል
እውነት ነው ብሎ ማታለል ይቀላል።
.
እኔ ግን ልንገርሽ
እውነት ነው ስልሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት እንዳይመስልሽ........

//ኤፍሬም ስዩም//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


★★★"ደሃራ ሲሆን ቆላ"★★★

//ኤፍሬም ስዩም//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


Ezedin Kamil dan repost
በፌስቡክ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ገፆት የቴክኖሎጂ መረጃ የሚያቀርቡ ከአስር በላይ የፈጠራ ባለሙያዎች Ethiopia Tech Insider የሚል የፌስቡክ ገፅ በመክፈት የጋራ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማቅረብ ስብስብ ፈጥረዋል። ገፁን ላይክ በማድረግ ይከታተሉ። https://m.facebook.com/EthiopiaTechInside


#
✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧✧

ህይወቴን ቢሞላት ኮተተ ባዘቶ
ህልሜ አይባክንም ታያለህ ተሳክቶ

ግን ታስታውሳለህን መጠሪያውን የኔ
ስትል እንዳልነበር የኔ ግራ ጎኔ
የኔ ሄዋን ውቧ ሞናሊዛ
ይህ የኔ ስም ነበር አሁን ሆነ ጤዛ

ጠዋት አይሀለሁ አሁን ግን የለህም
ከእንቅልፌ ስነቃ ከጎኔ አላጣህም
እንደ ጠዋት ፀሐይ እንደምታሳሳው
ሳልጠግብህ ትሄዳለህ እንደው ለምንድን ነው

የኔ ውብ አበባ ትለኝ አልነበረ
ማነው ይሄን ታሪክ አሁን የቀየረ?
እባክህ የኔ ንብ አሁን ፈጥነህ ናልኝ
በክንፎችህ በረህ ና እና እኔን ቅሰመኝ

ያለምንም ድጋፍ ሁለታችን ብቻ
አስፈላጊ ነበርን ፩ ሲያረገን ጋብቻ
ማሩን ከሌሎቹ አንንፈግባቸው
ተረዳኝ እባክህ ፍቅር እኮ እንዲህ ነው
ፍቅሬን ተቀበለኝ ካልሆነ ፀፀት ነው።


@efremsyum


ፊደል እስኪጠፋኝ…
እጄን ያሰርክበት
በዚ አንድ ታሪክ …
ሌላ ያንተ እውነት
ያንተ እውነት ፍቅር
የኔ ፊደል ድርድር
ደብዘዝ ያለ ብርሀን…
ይታየኛል ምነው
የማትታይ ፀሀይ …
ጋርዶ ያ ዳመናው
ፊትህን ፍራቻ …
ልቦናዬ ፈርሶ
በፃፍካቸው ቃላት…
ስብእናህ ነግሶ
ተውጫለሁ እኔስ …
በሀዘን በትካዜ
ከፊቴ ናትና …
በደል ሁል ጊዜ
ብቻ ማረኝ ውዴ
በፊትህ ክፋትን አድርጌያለሁ እኔ
ምንም ፋይዳ አይኖረኝ …
እስካለሁ በህይወት ዘመኔ
የተሰባበረው አጥንቴ እንዲጠገን
ይቅርታህ ያሻኛል አንድ ላይ እንሁን

ይቅርታ አድርግልኝ 😔🙏🏽🙏🏽🙏🏽


© ያንተው Çiñtã
ለ D hope 😊🙏🏽


#በአቢሲኒያ_ፈንታው

በከንፈርና ጉንጭ መካከል
ሳምኩህ!
ሁለት ጣዕም አጣጣምኹኝ፤
የከንፈርህን ዳር ነካሁ፣የጉንጭህን ስጋ ገመጥኹኝ
በፍራቻ ጣዕም መጠጥኹ፣
ሳታውቅብኝ በጣም ቋመጥኹኝ፤
ስስምህ፦
ከንፈርህ እንዳይቀርብኝ፣ በከንፈሬ ትንሽ ጨልፌ
ከጉንጭህ ትንሽ ፈቀቅታ፣ስውር ጣዕምህን ሞልጭፌ
የልቤን የትርታ ድምጽ ፣የሰውነቴን መንቀጥቀጥ፣
የውስጤን ፍላጎት ጫፍ፣የስሜቴንም መናወጥ፤
ዋጥ!
ጥጥት!
በሴትነት አበባዬ፣ በመሽኮርመም የውበት ልብስ፣
የውስጤን ራቁት ሸፈንኹ ፣ተው ልቤ እያልኩኝ ታገስ፤
ይሄው፦
ከመንገድ ዳር ላለመጣል፣ልቤን ብሄድ አንጠልጥዬ ፣
ለዓመታት እየጎተትሁ፣ ተገኘሁኝ ደክሞኝ ዝዬ።
ይሄው ያኔ...
በከንፈርህና በጉንጭህ መካከል፣ የተደወለው ደውል፣
ዛሬም እያነቃኝ፣አቅቶኛል መተኛት በውል።

.
(ስንቅ ገጽ 92)

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#ክራር_እና_ቅር

ትግስት በሌላት በጨከነች ሌሊት
ወዳጅ ለወዳጁ ደብዳቤ ፃፈላት
ከመፃፉ በፊት ...
ከጥቁር ሰማይ ላይ ሦስት ኮከቦች አየ
ለጥቂት ቅፅበታት ከከዋክብቱ ላይ ሀሳቡን አቆየ
አንደኛዋ ኮከብ እጅግ የደመቀ ብርሃን ትረጫለች
ሁለተኛዋ ግን ደመቅ ትላለች ካንዷ ትሻላለች
ሦስተኛዋ ደሞ እርሱን ትመስላለች
በሁለቱ መካከል ፈዛ ትታያለች
እርሱን ለምትመስለው ብዕሩን አነሳ
ሁለቱን ከዋክብት ልቦናው ረሳ
አሁንም ዳግመኛ ከመፃፉ በፊት
ከአንድ አመት ቀድሞ በርሷ የተፃፈ ደብዳቤዋን አየው
የደብዳቤው ሀሳብ የደም ዕንባ አስነባው
እንባው ማፍቀሯ ነው መፈቀሩም እንባው
የሀሳቧም ሀሳብ ለሁለት ዘላለሞች አፈቅርሃለሁ ነው
በትንሹ ታምኖ ብዙ ያልወደደ
ስለተፈቀረም ትንሽ ካላበደ
በትንሽነቱም ያልተወላገደ
ፍቅርን እንዴት ያውቃል እንዴት ይረዳዋል
ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
የሆነ መስመር ላይ አስተውለው ብለሽ ከታች ያሰመርሽው
ፊደል እስኪጠፋው እጁን ያሰርሽበት
የፍቅር ቀለማት የማይጠፉ ቃላት
የእውነት መገነዣ ሌላ ያንቺ እውነት
ያንቺ እውነት ፍቅር የርሱ ፍቅር ፊደል
ካፈቀረስ በቀር ፍቅርን ማን ይገልፃል
ማንበብ ክፉ ነገር መፃፍ መገላገል
ይሄ አይደል መታደል
ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
አስተውለው ብለሽ የሆነ መስመር ላይ ከታች ያሰመርሽው
ይልቅ ያን አስታውሰሽ የክራሩን ድምፅ አሰሚኝ
የዜማ ድምፅ ከዚያ ይውጣ
እኔም ክሩን ሆኜ ባንቺ ጣት ልቀጣ
እኔና አንቺ እንዲያ ነን በሁለት አንድነት ዝንት አለም የታሰርን በቅኝት ቢወጣ ጣት እና ክር ነን
ወይም ድምፅ እና ክር
ፍቅርን ጣት አርገነው ባንድነት ምንዘምር
ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
በፃፍሽው መስመር ላይ መብረቅ ፍቅር አለ
የዝናብ ድምፅ የለም ደመና ግን አለ
ከደመናው በፊት የደብዳቤሽ ቃላት
አንተ ማለት ባህር እኔ ማለት ትነት
በፀሀይ ፈገግታ ጨውን የምንፈጥራት
አንተ ማለት ጸጸት እኔ ማለት መዳፍ
የቀደመ ዕንባህን ካይንህ ላይ የምገፍ
አንተ ማለት ጥማት እኔ ደሞ እርካታ
በበርሀ ንዳድ የምገኝ ጠብታ
ማንበቡን ቀጠለ
የመብረቅ ብልጭታ የዝናብ ድምፅ አለ
በጥቁር ደመና ቀድሞ የታዘለ
ደብዘዝ ያለ ብርሃን የማትታይ ፀሀይ
የተኳረፈ ፍቅር ያረገፈ አደይ
በሁለታችን አዝኖ የተከፋ ሰማይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
መዳፍሽ እርቋል
ጨውነቱም ጠፍቷል
ቃሎችሽ ሰክረዋል
በዚያ ታላቅ ዝናብ ምድር ስትቀጣ
በመብረቅ ብልጭታ ነፍሳችን ስትወጣ
እኮ በምን እግሬ ከደጃፍሽ ልምጣ
አንቺ እንደሆን ንግስት የመኳንንት ልጅ
ህንፃ ፍቅር ልብሽ ጉብዝናን የሚያስረጅ
እኮ በምን ሀይሌ ልርገጠው ያንቺን ደጅ
ማን በምን ጉልበቱ በየት ጀግንነቱ
ዝም ባለ ቅፅርሽ ያንቺ ጉርፊያ ነግሶ
ፊትሽን ፍራቻ ልቦናዬ ፈርሶ
በሳምንት ዘመንሽ ዐይኔ ደም አልቅሶ
እኮ በምን አቅሙ እንዴትስ ተደፍሮ ደጅሽ ይረገጣል
አይኑስ እንዴት ደፍሮ ዕንባውን ጠራርጎ ያንቺን ዐይን ያያል
ምን ነበር የፃፍሽው ወይስ እኔ ፃፍኩኝ
ከፍቅርሽ ላይ ወይን ደብልቄ ጠጣኹኝ
ፍቅር እና ወይን
የሁለት አንድነቱን የጣትና ክሩን
በስልት የተቃኘ ክር ድምፅነትን
ፍቅርን ጣት አርገነው በተነካን ቁጥር
በስሱ ከላይዋ እንደተመታች ክር
በራሳችን ቃና በራሳችን መዝሙር
ለዘላለም እድሜ ባንድ ተገመድን
ወይስ ምንም ሆንን
እውነት ምንም ሆንን
ዜማ ሰጭ ፍቅራችን ተበጠሰ ላላ
የኛ ቅኝታችን በኔነት ተበላ
ያለሙያው ገብቶ ያለመጠን ነክቶ
ያለስልቱስ ቃኝቶ
ክራር ፍቅራችንን ክሩን ማን በጠሰ
በምን አይነት ስልትስ ዜማችን ታደሰ
ከሐሳቡ ነቃ
በራሱ ክር ላይ የራስ ስልቱን ቃኘ
ለደብዳቤዋ መልስ ሊመልስ ተመኘ
ላንተ ያለችውን ላንቺ ብሎ

//ኤፍሬም ስዩም//

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#ቃሌ_ይሰማሻል ።

በተደፈነ ሀገር በጠፋ መብራቱ ፣
ሠዉ በሌለበት ሠዉነት መጥራቱ ፣
አንተ ብሎ ማዉራት እገሌ ማለቱ ፣
ሠዉ ሠዉን በልቶ አይኑ በማየቱ ።


ቃሌ ይሰማሻል።
የመርዶ ጋጋታ የይሁዳ ድግስ ፣
በተቀረበበት በልዩ ጊዜ ላይ ፣
እንደ ሚታረድ በግ ስታይ ፣
አዝኖ የቆመ ሠዉ የለም በዚያ ድግስ፣
ቃሌ ይሰማሻልድምፄ ሲገነደስ ፣
እንደ አረጀ ዛፍ ነፍሴ ሲበጣጠስ።

ቃሌ ይሰማሻል ።
አካሌ ሲታመስ ፣
ሳይጠጋ በሩ ቅ ስጋዬን ሲያፈራርስ፣

ቃሌ ይሰማሻል።
ህመሜ ስቃዬ ሁሉ ይገባሻል፣
በዐይነ ብረትሽ ቁጭ ብለሽ አይተ ሻል። ስቃዬን ባትቀምሽም ፣
ህመም ቁስሌን ባትነኪም።
በስሜት አዝነሻል
እንደ እናት አልቅሰሽ ይሆናል።

ቃሌ ይሰማሻል።
በመጨረሻም እንዲህ እልሻለሁ፣
ከቅፍሽ እያለሁ ያሸለኩኝ ዕለት ፣
በእንባ ጎርፍ በሀዘን ቁስለት።

አዉቃለሁ።
ማዘንሽን ፣
መከፋትሽን ፣
እናቴ ሆይ መቃብር ብወርድም።
መሬት ዉስጥ ብሆንም ።
አሁንም ደግሜ አስታዉስሻለሁ።
ዘላለም ስምሽን ሳነሳ እቆያለሁ።
እናቴ እ❤️ወ❤️ድ❤️ሻ❤️ለ❤️ሁ።

// ሠማኸኝ እሸቴ //

https://t.me/joinchat/AAAAAE7FY82buFwojFZtzg


ከተመቸኝ የጧት ድግስ እንዲመችሽ አሰብኩና -----


በላይ በቀለ ወያ

ከእለታት አንድ ቀን
በአካል ማላውቃት ልጅ ፣ በሥራዬ አድንቃኝ
ሰይጣን ነው ለሚሉ
መልአክ ነው እያለች ፣ ስትመሰክር ደንቃኝ
"ቀድሞ ማሞጋገስ ፣ ለሀሜት አይመችም
ስትጠዪኝ "ሰይጣን ነው" ፣ ትይ ይሆናል አንቺም።
ስለዚህ አትሟገች
"ደግ ነው" አትበዪ ፣ ክፉ ነው ለሚሉ
ሰው መሆን በቂ ነው!
ክፋት ደግነቴ ፣ ሰው መሆን ውስጥ አሉ
ጥሩም ሆነ መጥፎ
ስለኔ አታውሪ ፣ ይፍረድ ጊዜ ዳኛው
ሁሉም በጊዜው ላይ ፣ ልክ ነው መገኛው
አንዱ ሰይጣን ያለው ፣ መልአክነው ለአንደኛው።
በማለት ብነግራት ፣ ንግግሬ ሳባት
ከዛን ቀን ጀምሮ
ያወራኋት ቀን ሳቅ ፣ ዝም ያልኳት ቀን ማንባት
ሥራዋ አደረገች
ከእለታት አንድ ቀን ፣ አድራሻ ፈለገች
ስልክ ቁጥሬን ቸርኳት
ደውላ "ውዴ " አለች ፣"ርካሽ ነኝ "አልኳት
ቀልዴን አልነበረም ፣ ቀልደኛ መሠልኳት
ብዙ ብዙ አወራን ፣ አወጋች አወጋሁ
ላግኝህ ስትለኝ ፣
እሺም እምቢም ሳልል ፣ የስልኬን አፍ ዘጋሁ።
።።።
ከእለታት ሁለት ቀን
"አወይ አነጋገር ፣ ወይ የድምፁ ማማር
እሱን ካወራሁት ፣ ባልሠራ ባልማር
ከዓለም ምን ጎደለኝ?
ሁሉ ሙሉ ይሆናል ፣ አንድ እሱን ካደለኝ።"
የሚል ግጥም ፅፋ
ሁሉን አሳነሰች ፣ አንድ እኔን አግዝፋ።
የዛን ቀን ምን አልኳት?
አንዱን ለማወደስ ፣ አንዱን አታሳጪ
ለክፉም ለደጉም ፣ ደግ ሀሳብ አስቀምጪ
ሁሉ ሙሉ እንዲሆን ፣ መጉደልን ምረጪ!"
ይህን ስል ም አለች?
ምንም አላለችም ፣ የምትለው ጠፋት
ቃል አደናቀፋት
ትናጋዋ ከዳት ፣ አፏ ተሳሰረ
በስተመጨረሻ
ትንፋሽ በዋጠው ቃል ፣ በተሰባበረ
"ልዩ ሰው ነህ " አለች ፣ "አንድ አይነት ነኝ" አልኳት
ቀልዴን አልነበረም ፣ እሷን ግን አሳቅኳት።
።።።
ከእለታት ሶስት ቀን
ጥቂት ጊዜ ውስጥ ፣ ብዙ ባላወራት
ላግኝህ ስትለኝ ፣ የት ብዬ ባልቀጥራት
ወይ ንቀት ፣ ወይ ኩራት
ወይም ከንቱ ጉራ ፣ መሰላት ያለብኝ
ታዲያ እኔ ምን ግዴ?!
ካለመናገሬ ፣ ሹመት ቢቀርብኝ
ስንት የነገር እሳት ፣ እንደነደደብኝ
እሷ አታውቅም እንጂ ፣ ሆና በኔ ቦታ
በወረኞች እሳት
የተፈተነ ጌጥ ፣ ወርቄ ነው ዝምታ።
ብዬ ዝም ብላት ፣ እሷ እልህ ተጋባች
ወዳጆቼን ሁሉ ፣ አድፍጣ እያደባች
ጠላት ታረግ ጀመር ፣ የአዞ እንባ እያነባች።

https://t.me/joinchat/AAAAAE7FY82buFwojFZtzg


#ምንም_ህልም_አይደለም


ድንገት ጋደም ስል በደከመው ግኔ
ሲዞር ይታየኛል ታላቅ ነበር ባይኔ
ያ አጉል ዘር ከፋፋይ ጉረኛው ፈላስፋ
በወንድሞች መሐል መርዝ እንዳያስፋፋ
ታርሞ ተነቅሎ ከሀገር ሲጠፋ
ያገር ዕድገት ጠላት የዕድል አሳዳጅ
ጥቅምን ሁሉ ሊያንቅ እንዲያ ሲጎመጅ
በግራ በቀኙ እየዘረጋ እጅ
ሌላውን ሁሉ ገድሎ ለራሱ እሚያበጅ
የጥቅሙ ተካፋይ ሳይሆን አማላጅ
በወንጀል ፈርዶበት ፈራጅ
ሲማቅቅ ሲከርም ሲማቅቅ ሲባጅ
ሲባል የህብ ጠላት የሰይጣን ወዳጅ
በሌላ እንኳ ሳይሆን በስልጣን ሰበብ
የሣንቲሟን ግማሽ የቀማ ከህዝብ
እንደ ሰረቀ ሰው የመንግስት ገንዘብ
በሰንሰለት ታስሮ ታጅቦ በዘብ
ቅጣቱን ሊቀበል ፍርድ ቤት ሲቀርብ
የኢትዮጵያ ህዝብ ከልብ ተቀራርቦ
ባንድ ቃል ተናግሮ ባንድ ልብ አስቦ
የጠላቶቹን አፍ ዘግቶ እና ሸብቦ
አብሮ የዘራውን ባንድ አብሮ ሰብስቦ
ሳይኖር ራብተኛ ሁሉም እህል ጠግቦ
በኢትዮጵያ ወገብ እንደ መቀነት
የተጠመጠመው ለምለሙ መሬት
ከወባ ተላቆ ህዝቡ ሰፍሮእበት
ባለም ታይቶ ማያውቅ የሰሊጥ ብዛት
የጫኝ ያለህ የሚል ጉድ የጥጥ ጭነት
የጤፍ የበቆሎው የስንዴውም ምርት
ተትረፍርፎ ሲቀር ካመት እስካመት
እንደ ተነበዩት ቀድመው ሊቃውንት
አገራችን ሁና የዳቦ ቅርጫት
ለሩቅ ወዳጅና ለቅርብ ጎረቤት
እስከቻልን ድረስ ሁሉም ሰው ተምሮ
ማብራሪያ ተሰጦት በአዋቂዎች ተሞክሮ
ራሱም አስቦ ሁሉም ተመራምሮ
ሙግት ጭቅጭቅን ወዲያ ጥሎ አንቅሮ
እግዜር እንዳዘዘው አንዱ አንዱን አፍቅሮ
ራሱም እንዳየው በለመደው ኑሮ
ባንድ አብሮ እርሻን አርሶ ባንድ አብሮ መንጥሮ
ባንድ አብሮ አጨዳ አጭዶ ባንድ አብሮ ከምሮ
አንዱ ሲዳር አንዱ ዘፍኖ አንዱ ሲሞት ቀብሮ
ስኖር በደስታ ከብሮ ተከባብሮ
ሁሉም ወገናችን ምስጢሩ ገብቶት
ለመደሩ አሰራር ቅጥ መጠን ሰጥቶት
የጋራ መሬቴን ያባቱን ርስት
ደረቁን ለመንደር ሜዳውን ለከብት
ለምለሙን ለእህሉ ጓሮውን ላታክልት
ከፋፍሎ መድቦ ሰርቶ ባንድነት
የመንግስት እርዳታ በቀላል ደርሶለት
ታማሚው መድኃኒት ህፃኑ ትምህርት
ሳይወጣ ሳይወርድ ሲያገኝ በወቅት
ተምሮም ሲሰራ ሰርቶ ሲያገኝ ሀብት
ሲረሳ ግሙ ዕድል መሆን ስራ-ፈት
በዐራቱ ማእዘን በለምለሙ ሜዳ
የወዳደለ ከብት ብዙው ቀንዶ -ጎዳ
ግማሽ ለወተት ሌላው ለፍሪዳ
ከዚህ ላይ ፍየሏ ከዚያ በጓ ወልዳ
የታከመው መንጋ ጤናው ያልተጎዳ
ጠግቦ እየፈነጨ ወደቤት ሲንነዳ
የንዱስትሪውን የርሻው ውጤት አብሮ
በከባድ መኪና በባቡር ተሳፍሮ
በዓለም ሁሉ ሊናኝ ሲጫን በመርከብ
ብዙ ለውጥ ሊያመጣ ወይንም ገንዘብ
ታላላቁ ወንዞች ዓባይ አዋሽ ባሮ
ተከዜ ነው ዋቢ?ምኑስ ምን ተቈጥሮ!
ለሐበሾች ጥቅም ኃይሉ ተወስኖ
ግማሹ ለጉልበት ግማሹ ለመብራት ሌላውም ወስኖ
ይውልና ሁሉ በየመልኩ ሆኖ
ብርሃን ብቻ ሁኖ ገጠሩ ከተማው
በሁሉም ቀን ሲሆን ተገፎ ጨለማው
በጭራሽ ሲረሳ ኩራዙና ሻማው
ናፍጣ ችርቻሮ ሥራ መሆን ሲቀር
በከተማው ኪዎስክ እንዲሁም በመንደር
በዚያም በዚህም ሲያንጎራራ ፋብሪካ
መሬትን ሊያስወስድ ቆፋሪው መኪና ዘቅዝቆ ሲያሽካካ
ጎበዙ ሠሪ ሕዝብ ባገሩ በሥራው በኑሮው የረካ
"ወዮለት !ጠላት እርሷን ለሚነካ!
ታላቋ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!"እያለ ሲያወካ
ይኽ ብቻ አይደለም ከዚህ የሚበዛ ይህን የመሰለ
ዞትር እየመጣ ባኔ ላይ ተሳለ።
ይህ አጉል ሕልም ይሆን የምኞት ቅጅት
ዓለም እስከምታልፍ የማንደርስበት?
ወይስ የሚቻል ነው የፈጠጠ እውነት?
የሚያደክም ምክር የባዕዳን ትንቢት
ሳይኖረን ሳይገባን ሐኬት
አብረን በማስወገድ ያለብንን ችግር
ሁላችን ከሠራን ባንድ ልብ ላንድ አገር
ምኑም ህልም አይሆንም ከዚህ ሁሉ ነገር።
የምዕራብም ሰዎች ይኸንን ከሠሩ
የምሥራቅም ሰዎች ይኸንን ከሠሩ
በኛስ አገር ቢሆን ምንድን ነው ችግሩ
ሕዝቡ ተባባሪ ባለጸጋ ምድሩ ።

ምንጭ" ሬት እና ማር "የግጥም መፅሐፍ
✍🏽...ከአቤ ጉበኛ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#አበስ…ገበርኩ…እቴ

ከአንጀትሽ ላይወጣ ከሆድሽ ታምቆ
ልብሽን ልቤ አድባር አውጋር አውቆ
ነጋሪት ጎስመን ክተት አስነግረን
ጦር፣ሠይፍ፣ጎራዴ…ዝናር አስደርድረን
እዩን!! እዩን!! ብለን
ላንቆስል ተታኩሰን ላንጣጣል ታግለን
እንዲያ ተጫጩኸን ፎክረን አቅራርተን
ከፍቅር አውድማ ላይ ተገኘን ተጣብቃን
ኧዲያ…ባክሽ ይብቃን
ደከመን …ታከተን
ተኩሱ ይቁም…ይስከን
ቆርጦ ላይቆርጥልን ችለን ላንሠለች
አንቺን ብሎ ተኳሽ ደግሞ እኔን ብሎ ሟች🙆‍♀🤦🏽‍♀

//በአባይ ፍቅሩ//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@yinuca
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#ምላስ

የዘንድሮ ሴቶች መሳም ይወዳሉ
በቀን ሶስት ከንፈር አስተናገድን አሉ
ለሶስት ከንፈርማ እኔስ መች አንስና
ምላሳቸው እንጅ የሆነኝ ፈተና
የረጠበው ከንፈር አዳለጠኝና
ማለፍ የተሳነኝ እወዳድቅና
ጠልፎ ያስቀረኛል ምላሳቸውማ

//Amanuel Debesay//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@yinuca
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#ሙግት

ጊዜ ለሰው ህይወት
ዘበት አይታክተው
እኔም ምላሽ ባጣም
መጠየቄን አልተው ።
ኩታ ገጠም ናቸው አልፋና ኦሜጋ
እንዴት ቀን ይመሻል በቅጡ ሳይነጋ?
ማን ዘረፈው ጠጉሬን?
ማን አሰረው እግሬን ?
ጉልበቴን ምን በላው ?
አቅሜን ማን ወረሰው ?
ተወልዶ ሳይጨርስ እንዴት ያረጃል ሰው ? 🤦🏽‍♀

//በውቀቱ ስዩም//

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


#የፍለጋ_ህመም

እኒህ ገጣሚያን
እኒህ ደራሲያን
እኒህ ሰዓሊያን…
ሶስቱ አማልክቶች
ረዳት ፈጣሮች
ሦስቴ ይስታሉ
ሦስቴ ይክዳሉ…

ሃሳቡ ሳይመጣ እንፃፍ ይላሉ

ሃሳቡ እንዲመጣ ሃሳብ ያስባሉ

ሃሳቡ ሲመጣ ሃሳብ ይመርጣሉ
ትተው ይነሳሉ።
0

//ኤፍሬም ስዩም//
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟




አንቺ ውብ ጨረቃ ያለሽው በሰማይ
ሰምተሽኝ ከሆነ ብቻዬን ሳወራ
ለሰው አትናገሪ ሚስጥሬን አደራ
ውስጤ ሰውን ፈራ መስሎት ከዳተኛ
እባክሽን ጨረቃ አድርጊኝ ጓደኛ 😔🙏🏽

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

284

obunachilar
Kanal statistikasi