ኢቅራ የቂራት ማእከል


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan



Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri














#ኢኽዋኖች #እናንተን??
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
#አሏህ #ይፋረደን
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
ውዱ ሀይማኖቴን ከምሸጥ ለጥቅም፡
ሱናውን ደምስሸ ባጢል ከምለቅም፡
ውሸት እየቀመምኩ ሁሌ ከምደክም፡
በሽተኛ ሆኜ ጤነኛን ከማክም፡
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
የእምነት ገዋን ለብሶ በድን ከመነገድ፡
የሱና ሰዎችን ሌት ቀን ከማሣደድ፡
ከጠላት ጋር ቆሞ ወዳጅ ከመሀሰድ፡
ከኢኽዋኖች ሴራ ይጠብቀን ሶመድ፡
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ከአይሁዶች ይልቅ የበደል ፅዋቸው፡
ባንተ ላይ ይብሳል የግፍ ብትራቸው፡
በሱናው አንበሳ በእምነት ወንድማቸው፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;//;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ከአይሁድ ይብሣል የኢኽዋን ክፋቱ፡
አርቆ ላሰበ ገና ከጂምሩ ከአመሰራረቱ፡
የመጨረሻው ጎል ሞገስና ግርማው፡
እስልምና አይደለም ስልጣን ነው አላማው፡
——————————————————
#ኢኽዋን___‼?
````````
አስመሣይ ቀጣፊ በእምነቱ ቀላጅ፡
ባጢል ለማስፋፋት ቤንዚንና ነዳጅ፡
የሀቅ ሰዎችን አስገዳይ አሣዳጅ፡
እነርሱን የሚወድ#40#አርባ ፊት ያዘጋጅ፡
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
ረሀቡ ጠንቶ መከራው ቢበዛ፡
ችግር በርትቶብኝ ብጓዝ በቃሬዛ፡
የሰውነት ክብሬ ቢረግፍ እንደ ጤዛ፡
እምታለሁ እንጂ አልገባም ወደዛ፡
-----------------------------------------
#ወይ #ደግሞ………
`````
ምንም ሀብታም ብሆን ገንዘቤ ቢበዛ፡
ሞልቶ ተትረፍርፎኝ ምድርን ቢያወረዛ፡
እውቅናየ በዝቶ አለም ላይ ቢያዘግም፡
እንኳን ኢኽዋን መሆን፤
ኢኽዋን የሆነን ሰው ማየት አልፈልግም፡
የስልጣን ሱሰኛ፡
መናጢ ሸረኛ፡
አስመሣይ ዘረኛ፡
ቀጣፊ ምቀኛ፡
ተቀየርን እያሉ ሁሌም ለረከሱ፡
ከፍ ባሉ ቁጥር ኪሎ የሚቀንሱ፡
አዳድስ ጥመትን ሁል ጊዜ እሚቀምሱ፡
እውነትን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ፡
ከኢኽዋኖች በደል ጌታችን ጠብቆ ይፋረደን እርሱ፡
≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤≤
እውነተኛው አምላክ ሀቅን ካስወደደን፡
ወደ ኋላ አንቀርም በናንተ ተሣደን፡
ምክንያቱም ደግሞ፤
በተአምር ፈፅሞ፤
ተሣስተን እንጂ በእስልምናችን አናውቅም ቀልደን፡
አንቀርም እንደዚህ፤
በደላችሁ በዝቶ እምባችንም ፈሶ ማየት ከጋረደን፡
ነዐም፤
እናንተ ጋር ፍትሀዊው አምላክ አሏህ ይፋረደን፡
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
#በኑረዲን አል–አረቢ
````````````````````````````````````
ኢኽዋኖች ሆይ ወሏህ ለአሏህ ስል በጣም እጠላችኋለሁ።
==========================
መቸም አይሣካላችሁም፡
ምክንያቱም ሀቅ አልያዛችሁም፡
~~~~~~~~~~~~~~~
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
~~~~~~~~~~~~~~


*አል-ኡሉሂያህ* (الألوهية) "አምላክነቱ" "ተመላኪነቱ"
-----------------------------------------------

አልሐምዱሊላህ ወስ-ሶላቱ ወሥ-ሠላሙ ዐላ ረሡሊላህ፡፡

ይህ አል-ኡሉሂያህ የአሏህ አምላክነቱ ብቸኛ የአምልኮ ባለቤትነቱን የሚገለፅበት ነው፡፡ ከሱ በቀር በሐቅ የሚመለክ የለም፡፡ ከገድለት ነገር ሁሉ የጠራ አምላክ ነው፡፡ ከፍጡራኑ መካከል አንዱንም ምንም ነገር አምልኮ የሚሠጠው የለውም፡፡

አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
20:14 - «እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡

" إنني أنا الله لا إله إلا أنا فاعبدني وأقم الصلاة لذكري "

• እሱ ብቸው የአምልኮ ባለቤት ነው፡፡ ይህንን ሼይኽ አሥ-ሠዕዲ ረሂመሁሏህ በተፍሢራቸው ላይ እንዲህ ይገልፁታል፡፡

لأنه الكامل في أسمائه, وصفاته, المنفرد بأفعاله, الذي لا شريك له, ولا مثيل, ولا كفو ولا سمي.
" ምክንያቱም እሡ አሏህ በሥሞቹ ፣ በባሕርያቱ ምሉዕ ነው ፣ በተግባራቱ የተነጠለ (ብቸኛ ነው) ፣ ያም ምንም ተጋሪ ፣ ምሳሌ ፣ አቻ ፣ የሚመሣሠለው የሌለው ነው፡፡ " ይላሉ፡፡

*አምልከኝ* (فَاعْبُدْنِي) ሲል አሏህ በሁሉም አይነት ዒባዳዎች ለኔ ብቻ አድርገህ አምልከኝ እያለ ነው፡
" 📚 ተፍሢር አሥ-ሠዕዲ

አሏህ እንዲህ ይላል ፦

2:163 - "አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡"
" وإلهكم إله واحد لا إله إلا هو الرحمن الرحيم "
40:65 - እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለእርሱ ያጠራችሁ ስትኾኑ «ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይኹን» የምትሉ ኾናችሁ ተገዙት፡፡

" هو الحي لا إله إلا هو فادعوه مخلصين له الدين الحمد لله رب العالمين "


ለመላው የባዕድ አምልኮ ባለቤት አድርሱልኝ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ግሩም_ደማቅ ታሪክ
#ከሰለፎቻችን_አንደበት!!
=========================
✍ኢብኑ ቁዳማ አል_መቅደሲ ረሒመሁሏህ ኪታቡ ተዋቢን በተሰኘው ኪታባቸው ላይ አብዱል ዋሂድ ቢን ዘይድ ከተባለ ሰው እንዳስተላለፉት ክስተቱን እንደ ሚከተለው ጠቅሰውታል_______

ከዕለታት አንድ ቀን በጀልባ እየተጓዝን ሳለን ጀልባችን ንፋስ አናወጣትና ከሆነች ደሴት ላይ አረፍን በማለት ትዝታቸውን ያስቃኙናል_____።
እዛ ቦታ ላይ ግን አንድ ታቦት የሚያመልክ ሰው ነበር። ወደሱም ተቀጣጨንና አናገርነው።

እኛ =)>
አንተ ሰው ሆይ ምንድን ነው የምታመልከው❓አልነው

#እሱ=)>
ወደ ታቦቱ አሳየን
#እኛ=)>
ይህ እኮ የሚመለክ አምላክ አይደለም‼ አልነው

#እሱም=)>
እናንተስ ምንድን ነው የምታመልኩት❓አለን

#እኛ=)>
አላህ አልነው
#እሱ=)>
አላህ ምንድን ነው❓አለን

#እኛ=)>
ያ አርሹ ከሰማይ በላይ የሆነው፣ በምድር ላይ ተቆጣጣሪ የሆነው፣ በህያውና በሙታን ላይ የእሱ ውሳኔ ብቻ ሚፈፀመው ነዋ አልነው
#እሱ=)>
ስለ እሱ እንዴት አወቃችሁ❓ አለን
#እኛ=)>
ይህ ትልቅ አሸናፊና የተከበረ የሆነው ጌታ ወደ እኛ መልዕክተኛ ላከልንና በእሱ አማካኝነት ነገረን አወቅነው አልነው‼
#እሱ=)>
እሺ መልዕክተኛው ምን አደረገ❓አለን
#እኛ=)>
መልዕክቱን አደረሰ ከዝያም አላህ ወሰደው‼ አልነው
#እሱ=)>
እናንተ ዘንድ ምልክት ትቷልን❓ አለን
#እኛ=)>
አዎን‼ አልነው
#እሱ=)>
ምንድን ነው የተወው❓
#እኛ=)>
ከዛ ከሀያሉ ንጉስ የተሰጠው መፅሀፍ (ቁርኣን)‼ አልነው
#እሱ=)>
እስኪ የንጉሱ መፅሀፍ አሳዩኝ። ከዚህ ንጉስ የሆነው መፅሀፍ እጅግ ያማረ መሆን አለበት‼
#እኛ=)>
የያዝነው ቁርኣን ነበር ሰጠነው
#እሱ=)>
ይህማ ማንበብ አልችልበትም። አለን
`
#ከዝያም_ከቁርኣን_የሆነች ሱራ (ምዕራፍ) መርጠን ማንበብ ጀመርን እኛ እንቀራለታለን እሱ ያለቅሳል በዚህ መልኩ ሱራውን ጨርሰን ቀራንለት።
#እሱ=}>
ቁርኣኑ ካዳመጠን በኋላ እንዲህ ዐይነቱ ጌታማ ሊታመፅ አይገባውም። አለና እስልምናን ተቀበለ‼‼
#ከዝያም_የተወሰኑ_የቁርኣን_አንቀፆችና የእስልምና ድንጋጌዎች አስተምረነው ከእኛው ጋ ይዘነው ሄድን።
_የተወሰነ ከተጓዝን በኋላ ሲጨላልምብን ማደሪያችን አመቻችተን አረፍን። የተወሰነ እንዳረፍን ተነሳና
#እሱ=}>
እናንተ ሰወች ሆይ ይህ አምላካችሁ ለሊቱ ሲጨልምበት ይተኛልን❓ ሲል ጠየቀን
#እኛ=}>
አይ እሱማ ብርቱና ህያው ነውና አይተኛም‼ አልነው
#እሱ=}>
እናንተማ ክፉ የሆናችሁ ባሪያዎች ናችሁ❗ጌታችሁ አይተኛም እናንተ ትተኛላችሁ እንዴ❓❓
አለንና ትቶን ዒባዳውን መፈፀም ጀመረ።

,,,,,,,,,,,,, ከጉዞ ጨርሰን ወደ ሀገራችን ስንደርስ ወደ ባልደረቦቼ ሄጄ,,,,,,,,ይህ ሰውዬ ወደ እስልምና ከገባ ገና ቅርብ ጊዜው ነው ለሀገሩም እንግዳ ነው;;,,,,,,,,,,,
,,,,,,,,,,, ስለዚህ የሆነ ነገር ያስፈልገዋል ብያቸው የተወሰነ ነገር ሰበሰብንለትና ልንሰጠው ሄድን።
የሰበሰብንለት ሳንቲም ስንሰጠው,,,,,,።

=}> ይህ ምንድን ነው❓አለን

እኛ=}> ለሀገሩ እንግዳ እንደ መሆንህ የሚያስፈልጉህ ነገሮች እንድታደርግበት ነው። አልነው
#እሱ_በአግራሞት =}>
لا إله إلا الله
=}>ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለምዛሬ ላይ በሀገራችን የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች የተመረተው የት እንደሆነ እንኳ የማይታወቅ ከእንጨትና ከብረታ ብረት ተጠርቦ የተሰራ ታቦት የተለያየ ስም እየሰጡ ሲያመልኩና ሲያጎበድዱለት ሳይ ይህንን ማራኪ ታሪክ ትዝ ይለኛል።

=]>ከውስጤም ቀረብ በልና ይህንን ታሪክ ተርክላቸው የሚል ስሜት ያቃጭልብኛል።
ግና የአብዘሃኞቻቸው ሀሳብና የአስተሳሰብ ውጤታቸውን ስለ ማውቅ ሌላ ነገር እንዳይፈጠር ዝም እላለሁኝ።
#እናንተንም_አሏህ_ይምራችሁ
#እኛንም_በሀቅ_ላይ_ያፅናን
#የተወሰደ________!!
ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ ወበረካቱህ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi


ወንድማዊ ምክር ለሙስሊሟ እህቴ!

በጥሩ ንያ አንብቡት በአላህ ፍቃድ አንድ ቀን ይጠቅማችሁ ይሆናል!

✍ጌታችን አላህ ለትልቅ አለማ እኛን ፈጥሮናል።በምን አይነት መንገድ እሱን(አላህን)መገዛት(ማምለክ)እንዳለብንም ነብይ ልኮ፣መፅሐፍት አውርዶ ነግሮናል። ባወረደውም ቁርኣን እንዲህ ብሎናል "ጂንንም ሆነ ሰውን እኔን እንዲገዙ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም"‼️

ወደ 👉ወነው አርስቴ ስገባ ሴቶችዬ ከወንዶች ጋር (በተለይም ከካፊር ወንዶች ጋር መቀራረብን የምናበዘ እህቶች ረሳችንን ለምን አይነት ከባድ አደጋ አሳልፈን እንደምንሰጥ እንወቅ!


በየ ሶሻል ሚድያውና በየሰፈራችን የምንሰማው ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ታሪክ ማስተዋል ለቻለ ትልቅ ትምህርት አለው። ለምሳሌ ያክል ከዚህ በታች ባለው ቻናል የተወሰኑትን አስቀምጣለሁ ።

እህቴ ሆይ! ራስሽን ጠብቂ ! ከሁሉም ወንድ ካልተጀናጀንኩ፣ከሁሉም ወንድ ካላወራሁ፣ከሁሉም ወንድ ካልተለፋሁ አትበይ በአላህ እህቴ ክብርሽን ጠብቂ!

ሶሃባው ኡመር ያለውን አልሰማሽምንዴ?!! "በጣም አስጠሊተሟ ሴት ማለት በወንዶች ላይ በጣም ደፋር የሆነቿ ናት"ስለዚህ እህቴ ሀያሽን ጠብቂ! ጌታችን አላህ አንቺንኮ አልቆሻል።

ጌታችን አላህ አልቆሽ ሲያበቃ እሱን ለማምለክ ፈጥሮሽ ሲያበቃ አንቺ ግን ይህንን ችላ ብለሽ ከካፊሩም፣ከሙስሊሙም ፣ከቦዘኔውም ከሁሉም እየተጨማለቅሽ ከሆነ የምትኖሪው በትልቁ ቀይ መስመር ላይ ነሽ እህቴ ሆይ!ተመለሺ ግዴለም ተመለሺ መመለሱ ይጠቅምሻል እንጂ አይጎዳሽም!!

ብዙዎች ፍቅር ምን እንደሆነና ለከባድ አደጋ እንደሚጥል ሳይረዱ እንደ ቀልድ ከካፊሩ ጋር ልቅ በሆነ ቅርርባቸው የተነሳ በፍቅር ዮድቃሉ። ያው እንደሚባለውም ፍቅር አይነስውር ነው አይደል? ግን ፍቅር ያለ ምንም ቅርርብ አይዝምና እህቴ "ፍቅር ነው ጉድ ያደረገኝ"ከማለተሽ በፊት ጠንቀቅ በይ!

እናስተውል!

"ሙስሊም የሆነች ሴት ካፊር ወንድን ማግባት አይፈቀድላትም ካደረገችውም እሷ የምትኖረው ያለ ኒካሕ ነው"

ደሞ ከተጋቡ በኋለ መክፈርም አለ፣

ወላሂ! ተወዳዳሪ የሌላት ቂል ማለት ለዚህች ጠፊ ዱንያ ብላ ዘውታሪ የምትሆንበትን አገር አፍርሳ ለወንድ ብላ የምትከፍር ሴት ናት!ከዚህች ሴት የሚወዳደር ቂል ቢኖር በተለያየ ዱንኒያዊ ጥቅም እስልምናን የሚሸጥ ለጠፊዋ ዱንያ የሚከፍር ናው።

እናም በብዛት እህቶችን ለዚህ እጅግ ከባድ አደገ ለመውደቅ ሰበብ የሚሆንባቸው


👉የመጀመራውና ትልቁ ልቅ የሆነ ከወንዶች ጋር መቀራረብ
👉መጥፎ የሆኑ ዘመናዊ የፍቅር ፊልሞች
👉ዲናቸውን በሚገባ አለመረዳትና ግዜያቸውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ካለ መረዳት
👉መጥፎ የሆኑ ስለ ፍቅር የሚዘፍኑ ዘፋኞችን ዘፈን ማዳመጥ
👉በቀልድ የተጀመራ ጅንጀና የመሳሰሉት ተደማምሮ ወደ መጥፎ ነገር ውስጥ ይከታል


ስለዚህ ሙስሊሟ እህቴ ፀፀት ውስጥ ከመውደቅሽ በፊት ፀፀት ውስጥ ከሚጥልሽ ነገር ታቀቢ እላለሁ።

👌ሳጠቃልል

መሞታችን አይቀርምና ይህን ሞት የሚባለውን ነገር በሚገባ እንረዳው።ጓደኞቻችን፣ቤተሰቦቻችን፣


ዘመዶቻችን የወሰደው ሞት ለኛም ቀጠሮ ይዞ እየጠበቀን ነው።ለምንድነው ሞትን እሩሩሩሩሩሩሩሩቅ አድርገን የምንመለከተው?!!
//
እስኪ እናንተም በሰፈራችሁ የገጠማችሁን ታሪክ በወንድም ይሁን በሴት ለወንድ ብላ የከፈረች ፣ለሴት ብሎ የከፈረ ካለ በኮሜንት ወይም በቻናሉ በቦት (በአስተየት መስጫ)ላኩልኝ ባረከላሁ ፊኩም።ሼር አድርጉ

ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

✍ወንድማችሁ Abdurhim Sane አቡ ኡካሻ ነኝ ከአዳማ

https://telegram.me/gfyygy


አይ ሙመይአዎች ትገርማላችሁ
➪➪➪➪➪➪➩➩➩➩➩➩➩

ስለ ሙመይአዎች በሰፊው
➘➷➴ በዚህ ጥንቅር ይከታተሉ
➘➷➴➘➷➴➘➷➴➘➷➴➘➷
https://t.me/AbuImranAselefy/1829

➩➪➩➪➩➪➩➩➪➩➪➩➪
ሰው ወደ ቢድዓ ሲጓዝ ትናንት ባጢል
ያለውን ዛሬ እንደ ሀላል ይቆጥረዋል።


በዚህ ደረጃ መቅለጥ ገርሞ ይገርማል።

ጋዜጠኛው Murad Tadesse የዳዕዋ ፕሮግራም እንዳለ ካስተዋወቀ ቡኋላ እንዲህ አለ

➷➴➘➷➴➘
==================
===================>
ከታች በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ኡስታዝ ሰልሰቢል ዙመካን ኮርሱን ጀምሯል።
መስጅዱ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሞልቶ ጸጥ ረጭ ብሏል።

==================
===================>

ከዛም ተገርሜ ወደ ጠቆሞው ፎቶ ስሄድ ከሰልሰቢል ጀምሮ አምስት ሰዎችን በማንሳት ከመስጂዱ ዳር እስከ ዳር ጭቅ ብሎ ሞልቷል ሲል ይናገራል።

ከውሸቱ ሰዎችን ፎቶ በማንሳት ለሚዲያ ፍጆታ ማዋሉ ገርሞ ይገርማል። እነዚህ የሚፎክርላቸው ኡስታዞች ትናንት ፎቶን ሲያወግዙ ነበር። ዛሬ ሲንሸራተቱ እነሱኑ ፎቶ እያነሳ ይለቃል። ገራሚ ናችሁ።

ስለ ሙመይአዎች ወደፊት በሰፊው እንዳስሳለን #ኢንሻአላህ


ከኑረዲን ግጥም ተጠቀሙ
➷➴➘➷➴➘➷➴➘➷➴
#ሙመይዕ_ይህች_ነች!!
================
ከመሀል ላይ ቆመሽ መንሀጁን አትረብሽ፡
ኢኽዋን ነኝ በይና ሀቅ
አውጭ ይመርብሽ
እኛም ቁርጡን አውቀን ረድ እንስጥብሽ፡

ቆላ ሲሏት ደጋ ቦሌ ሲሏት ሳሪስ፡
ይህች ነች ሙመይዕ
በመንሐጇ እስፕሪስ፡
=====================>
የኢኽዋኖች አሽከር የጀይላን ደጋፊ፡
አስመሳይ ሙልጭልጭ ሀቅ አደናቃፊ፡
የሱና ሰው ጠላት ተውሒድ የሚያሟሟ፡
ከኢኽዋን ሳትወጣ ከበፊቱ ስሟ፡
በተምይዕ መጥታለች በአድሱ ትርጉሟ
=====================>
ገፀ ባህሪዋ ነው ማድከም ሰለፍያን፡
ከጎኗ አስከትላ ምድረ ኢኽዋንያን፡
በማታውቀው ገብታ ዶክተር ነኝ ትላለች፡
ከጥመት መንጋ ጋር ሱናን ታሟሟለች
ወሏሒ እንወቃት ሙመይዕ ይህች ነች፡
~~~~~~~~~~~>
#በኑረዲን_አል_አረቢ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi


ሙመይአዎች ኡስታዝ ባህሩ እንዳለው ለኢኽዋኖች ግንባታ ብለው ብሎኬት የሚያቀብሉ ሰራተኞች ናቸው።
የሚያሳዝነው ደግሞ ከግንባታው ከኢኽዋን እኩል እንኳን አለመጠቀማቸው ነው።

ሙመይአዎች ኢኽዋን ከሚያጠፋው በላይ እያጠፉ ዳዕዋ ሰለፍያን እየጎዱ የሚገኙ ናቸው።


የተቋሞቻቸው መስፋፋት የሱና እንቅስቃሴ ያለበት አካባቢ ጋር መዛመዱ ከአደገኝነታቸው ማሳያዎች የሚጠቀስ ነው።

ልክ በሙስሊሞች ስር ተወሽቀው ከካፊር በላይ እስልምናን እንደሚጎዱ ጠማማ ቡድኖች ሁሉ በሰለፍያም ስር ተውሽቀው ከማማ ቡድኖች በላይ ሰለፍያን የሚጎዱት ሙመይአዎች ናቸው።

አላህ ከተንኮላቸው ይጠብቀን!!!

https://t.me/AbuImranAselefy/2295

https://t.me/AbuImranAselefy/2295


#ጀግና_ይሁን_ልብህ!!
~~~~~~~~~~~~
ከስህተትህ ታረም ከወንጀልህ ፍራ፡
ከጥመት ተጠበቅ መልካም ነገር ስራ፡
ቀጥ በል ተስተካክለህ ተግባርህ ይቀደም፡
ሽርክና ቢዲዐ ፊት ለፊትህ ይውደም፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;://;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ፍፁም አይምረርህ ጭቆናና ግፉ፡
ከሀቅ አታሸግሽግ ፀፀትህ ነው ትርፉ፡
በመረጃ በርታ በርጋታ ተቀመጥ፡
በደል ቢፈጂህም እንደ ሣት ረመጥ፡
ይሻልሀልና ኋላ ከመርመጥመጥ፡
========\\\==========
ሀቅ ላይ ስትሆን አይቀርም ፈተና፡
ገለባና ምርቱን ሊለይ ነውና፡
በቂርዐት በርታ በእውቀት ተዘጋጂ፡
ለጠላትም ቢሆን ሁን እውነትን ፈራጂ፡
≈≈≈≈≈≈≈≈≈\\≈≈≈≈≈≈≈≈
ባንድራውን ይዘህ ወደፊት ተራመድ፡
ገደል አታስተውል ፈፅሞ አትሽመድመድ፡
በዕምነትህ ኩራ በል ወደፊት ገስግስ፡
የሽርክ የቢዲዐ የጥመት ግሣንግስ፡
ተጠንቀቅ አደራ ለሰው አታግበስብስ፡
በንፁህ ልብህ ላይ ንፁህ ተውሒድ አንግስ፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሰለፍያ ይሁን ውብ ትምህርት ቤትህ፡
ቁርዐት ሀዲስ ይሁን ምንጊዜም ትርክትህ፡
የነብያት ታሪክ ፤
የሰሀቦች ገድል ይህ ይሁን ቀለብህ፡
ፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ጀግና ይሁን ልብህ፡
።።።።።።።።።//።።።።፡።።።።።።።።።።።።
#በኑረዲን አል–አረቢ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
=======================


《ሰዎች ዘጠና ዘጠኝ ጥንካሬህን ትተው በአንዷ ድክመትህ ይንቁሃል።》
ኢማሙ አሸዕቢይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
💎"በአላህ እምላለሁ! ሰዎች ዘጠና ዘጠኝ መልካም ነገሮች ቢኖሩኝ እነርሱን በመተው አንዷን ስሕተት ብቻ ይቆጥሯታል።"
📚【ሲየሩ አዕላሙ ኑበላእ (4/308)】
https://t.me/joinchat/AAAAAEUsWDvj8ctkp9pQmA


ታላቁ ዓሊም ሸኽ ዑሰይሚን ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላሉ :-
" የሰለፍያ ሚንሀጅ ማለት የነብዩና - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - የሶሀባዎቹን መንሀጅ መከተል ማለት ነው ምክንያቱም እነሱ ከኛ በፊት ያለፉ ቀደምት ( ሰለፎች ) ስለሆኑ እነሱን መከተል ሰለፍያ ይባላል "
አል ባቡል መፍቱሁ ( 1322 )


➻ስለ ዲናችን ጠንቅቀን እንወቅ!!
በምንችለው ሁሉ እንተግብር!!
、、、、、
የተለያየ አጀንዳ በተነሳ ቁጥር መደናበር፣ መወዛገብና መጨቃጨቅ በዋነኝነት የእውቀት እጥረት ችግር ነው። ታዲያ ችግሩ ይህ ሆኖ ሳለ ለችግሩ ትክክለኛውን መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በዱኒያዊ ጉዳዮች ተጠምደው ይህን ትልቁን ድርሻ ሲዘነጉት ይስተዋላል።

አብዛኛው ሰው በየ አቅጣጫው ጭንቀቱ ውጣ ውረዱ ለዱኒያዊ ጥቅም ነው። ዱኒያዊ ጥቅምም ቢሆን እንዴት ማግኘት እንዳለበት ሸሪዓዊ እውቀት ያስፈልገዋል። አላህ እውቀትን እንዲጨምርለት ከመለመን ይልቅ፣ ስለ ዲኑ ግንዛቤ እንዲሰጠው ከመለመን ይልቅ ዱኒያን እንዲጨምርለት በመለመን ለዱኒያ መጨነቅ የብዙዎች መለያ ነው። ለዱኒያ ሳይጨናነቁ አላህ ዱኒያውንም እንዲያስተካክል ዱዓ ማድረጉ የሚወገዝ ባይሆንም ዲን እንደ ትርፍ ነገር ተቆጥሯል።

የእውቀትን ትሩፋትና ወሳኝነት የሚገልፁ ብዙ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎች አሉ። አላህ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እውቀትን ጨምርልኝ በል ሲል ይናገራል:-

فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۗ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰ إِلَيْكَ وَحْيُهُ ۖ وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا

«እውነተኛው ንጉስ አላህም (ከሓዲዎች ከሚሉት) ላቀ!፡፡ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈፀሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፡፡ “ጌታዬ ሆይ! እውቀትንም ጨምርልኝ” በል፡፡» ጧሀ 114

ይህ አንቀፅ የእውቀትን ትልቀነት ያስገነዝበናል። ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እውቀትን እንጂ ሌላ ነገር "ጨምርልኝ በል" ብሎ አላዘዛቸውም።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር:-

اللَّهُمَّ انْفَعْنِي بِمَا عَلَّمْتَنِي، وَعَلِّمْنِي مَا يَنْفَعُنِي، وَزِدْنِي عِلْمًا

“አላህ ሆይ! ባሳወቅከኝ ነገር ጥቀመኝ፣ የሚጠቅመኝን ነገርም አሳውቀኝ፣ እውቀትንም ጨምርልኝ” ትርሚዚይ 3599 ላይ ኢብኑ ማጀህ 251 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ በሶሂህ ኢብኑ ማጀህ ሶሂህ ብለውታል።

የተለያዩ የሺርክና የክህደት ቡድኖች እስልምናን ለማጥቃት በአንድነት ተነስተው ይንቀሳቀሳሉ፣ የቢድዐ/የጥመት አንጃዎች ሁላቸውም ባሉበት መንገድ አንድ ባይሆኑ እንኳን የሱናውን ሰው በመታገል ግን በተዘዋዋሪም ሆነ በግልፅ አንድ ናቸው። ታዲያ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ ከሁሉ ነገር በላይ እውቀት መታጠቅ ግዴታ ነው። ሁሉም በያለበት በሚችለው አቅም ሁሉ ለእውቀት ከምን ጊዜውም በላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጥና ራሱንም ሆነ ቤተሰቡን በእውቀት ሊያደራጅ ይገባል።

እውቀት ሲባል ያወቁትን ማሳወቅንም ይመለከታል። አንዳንድ ሰዎች ተምረው አውቀውት በጊዜው ገብተዋቸው ያለፉት ኪታብ መልሶ ሲጠፋቸው ይስተዋላል፣ ይህ ትልቅ ጥፋት ነው። ለዚህ መፍትሄው መሻይኾች እንደሚሉት ያወቁትን በማስተማር መበርታት ነው ይላሉ። ያወቁትን ማሳወቅ በራሱ እውቀት እንዲጨምር ከሚረዱ ነገሮች አንዱ ነው።

እውቀት ያለውና የሌለው ፈፅሞ እንደማይገናኝ ይታወቃል!፣ አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ አለ:-

قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ

«እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?፣ በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡» አዝ-ዙመር 9

አዋቂና መሃይም ፈፅሞ እኩኩል አይሆኑም!። በሚያሳዝን ሁኔታ አንድ ሰው ይህን ተጨባጭ እያወቀ ሲታመም ለሰውነቱ በትክክል እውቀት ያለውን የጤና ባለ ሞያ ሲፈልግ ለአኼራ ለዱኒያው የህይወቱ ዋስትና ለሆነው ዲን ጊዜ ግን ያለ እውቀት ራሱ ሲያቦካ ይስተዋላል። ይህ ደግሞ ከባድ ዋጋ የሚያስከፍለው ጉዳይ ነውና ትክክለኛ እውቀት ያላቸው ሰዎች ዘንድ እውቀት ሊቀስም ይገባል!፣ እውቀት በሌለን ነገር ደግሞ ዝምታ ይስፋን!።

እውቀት የሚገኝበት መንገድ ከምን ጊዜውም በላይ ሰፊ ነው፣ ዒልም የሚሰጥባቸውን ቦታዎች ጎራ ብሎ መቃኘትና መደበኛ ሆኖ በደረጃ የሚመጥንን ቂርኣት መከታተል ነው!። ይህ ከከበደ የተለያዩ መሻይኾች በድምፅ አቅርተው ያለፏቸው በየ ደረጃው የተለያዩ ትምህርቶች አሉ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጎልቶ ጊዜ ከማቃጠል የመሻይኾችን ት/ቶች አውርዶ በስርኣት መማር ይቻላል።

እውቀት ደረጃው የላቀ ነው!፣ ለዚያም ነው ትግስት የሚፈልገው። አላህ እውቀት ኖሯቸው በእውቀታቸውም ተግባሪ የሆኑ ሰዎችን ከሌሎች የላቀ ደረጃ እንዳላቸው ሲገልፅ እንዲህ ብሏል:-

يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ

«አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡» አል ሙጃደለህ 11

አላህ በአማኞች ውስጥ ያሉ አዋቂዎችን በሰበሰቡት እውቀትና ተግባር ምክንያት ደረጃቸውን ከፍ ያደርጋል ማለቱ ነው።

በሌላ አንቀፅም አዋቂዎች ፈሪሀ አላህ እንደሆኑም ሲገልፅ እንዲህ ብሏል:-

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ

«አላህን ከባሮቹ ውስጥ (ተገቢውን መፍራት) የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡» ፋጢር 28

ከፍጡሮቼ የሀያልነቴን፣ የአሸናፊነቴንና የስልጣኔን ደረጃ የሚያውቅ ነው የሚፈራኝ ማለቱ ነው። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አሉ:- “እውቀት ማለት ሀዲስን በብዛት መሸምደድ አይደለም፣ ነገር ግን እውቀት ማለት አላህን በመፍራት ብዛት ነው!።”
ሀሰኑል በስሪ (ረሂመሁላህ) “አዋቂ ማለት አላህን በምስጢር የፈራ ነው!” ይላሉ።

እውቀት አላህን ከመፍራትና ከተግባር ጋር ካልሆነ ከአይሁድ ያመሳስላል። ያለ እውቀት በመሃይምነት አላህን ማምለክም ከክርስቲያኖች ያመሳስላል። በመሆኑም እንወቅ! ባወቅነው ለመተግበር የአቅማችን እንጣር!። ከመሃይመነት ጭለማ በመውጣት የተለያዩ የጥመት ቡድኖችን ለይተን አውቀን እንጠንቀቅ እናስጠንቅቅ!።
◦◦🖋ኢብን ሽፋ: ጁማዱል ኡላ 21/1442 ዓ. ሂ
Join ➴➘➘➷
◦➧ http://t.me/Menhaje_Aselefiy


ለሱና ሰወች ስብስብ አድርሱልኝ!!
!!
#የሱና___ስብስብ!!
=============
ሱናን ለማስፋፋት ሌት ቀን የሚለፉ;
ጥመትን አዋርደው ሀቅ የሚደግፉ;
የሽርክን ጨለማ በደዕዋ እሚገፉ፡
ቢዲዐን በሱና ሁሌ እሚናደፉ፡
በዕውነት የቆሙ ፍቅራቸው የሚስብ፡
አሉ ጀግና ህዝቦች የሱና ስብስብ፡
===========//=========
ሱና ሱና እሚሉ ዘወትር ማለዳ፡
ከልቦናቸው ውስጥ ሁቡ እየፈነዳ፡
ተውሒዲን መገንባት ነውና እቅዳቸው፡
እወዳቸዋለሁ ለኔ ጀግኖች ናቸው፡
አብቦ እንዲያፈራ የብርሀን ጮራ፡
ሱናውን እያገዝን ለተውሒድ እንስራ፡
ምንም ለሀቅ ሰው ቢበዛም ጥላቱ፡
ጨለማው ቢያስፈራ ቢያስጨንቅ ፅልመቱ፡
በፅናት እንቁም አይቀርም መንጋቱ፡
=======================
አህባሽና ኢኽዋን ሱፍያን ጨምሮ፡
መንጋው ሙመይዑ ኩፋሩም ተባብሮ፡
እውነትን ለማጥፋት ሁሌ ቢሯሯጡም፡
እውነት ያው አውነት ነው ምንም አላመጡም፡
ጠማሞቹ ሁሉ ሆ ብለው ሲመጡ፡
በቢዲዐ ስሜት ሱናውን ሊውጡ፡
ተራራን በቡጢ ንደው ሊቀመጡ፡
እጃቸው ተሰብሮ ቀሩ እንደዘቀጡ፡
=====================
#ታዲያ_ጀግኖቼ_ሆይ!!
ሲለፋ ሲዋደቅ ጠላት ለጥመቱ፡
በአሏህ እገዛ ሴራው ቢሆን ከንቱ፡
ለምን ነው ሱንዬች የማንነቃቃው፡
ለምን ነው በኛ ላይ ሴራ እማያበቃው፡
በሉ እንግድህ ሀያ ቆርጠን እንነሳ፡
ሁላችን እንንቃ እንሁን አንበሳ፡
በገጠር ከተማ በዝተን እንራባ፡
አድማሳችን ይስፋ መድረሳው ይገንባ፡
ሁሌ እየተበደልን አናፈስም እምባ፡
=====================
ቀደምቶች ለዒስላም ህይወት ገብረዋል፡
ለተውሒድ ለሱና ሲለፉም ኖረዋል፡
ታድያ እኛ ለተውሒድ ምን አደረግንለት፡
ከጀነት በር ድረስ ለሆነው ሰንሰለት፡
ስለዚህ ባለን ተረዳድተን ሱናን እናስፋፋ፡
ተውሒድ ሱና መንሀጂ ይነገር በይፋ፡
ገንዘብ ያለው ይርዳ የሌለው ባሳቡ፡
ከሱና ስብስብ ፍጠኑና ግቡ፡
ሱናን እንደግፍ ብለናል አርሒቡ፡
====================
እንታገል በዕውነት በርቱ ወገኖቼ፡
መንሀጂ ወዳድ ጀግኖች እህት ወኖድሞቼ፡
በኩፋር መረገጥ፤
በጥመት መገፋት ጭቆና እስከመቼ!!?
#ሰለዚህ____!!"
በገጠር ከተማ ይገንባ መድረሳ፡
ከሰለፍዮች ላይ ችግሩ ይነሳ፡
ጭቆና እንድጠፋ ሀያ እንተባበር፡
ከጥመት ርቀን እንቁም ከሀቅ በር
በሉ ሀያ እንንቃ በአፅንዖት እናስብ፡
እውነትን እንርዳ ኸይርን እንከስብ፡
በአንድነት እንቁም የሱና ስብስብ፡
======================
#በኑረዲን_አል_አረቢ
======================
http://t.me/nuredinal_arebi/9276
http://t.me/nuredinal_arebi/9276
http://t.me/nuredinal_arebi/9276
==========================


መልካም ሴት እና መልካም ያልሆነች(ክፉ) ሴትን የተመለከተ አጭር የንፅፅር ገለፃ!
المرأة الصالحة والمرأة السيئة
قــال عمر بن الخطاب رضي الله عنه :-
ዑመር ኢብኑልኸጣብ አላህ ስራቸውን ይቀበላቸውና…
والله ما أفاد امرؤٌ فائدة بعد إيمان بالله عزوجل خيراً من امرأة حسنة الخُلُق ، ودود ولود
《በአላህ እምላለው አንድ ወንድ ልጅ በአላህ ከማመን ቡሀላ መልካም ስነምግባር ያላት፣ ባሏን የምትወድ(ባሏን አፍቃሪ)ና ልጅ የምትወልድ(ወላድ) ሴት ልጅን ከማግባት የሚልቅ ውጤታማነት(መታደል) አይገኝለትም።》ብለዋል
والله ما أفاد امرؤٌ فائدة بعد كفر بالله عزوجل شراً من امرأةً سيئة الخلق ، حديدة اللسان
《በአላህ እምላለው አንድ ወንድ ልጅ በአላህ ከመካድ(ከኩፍር) ቡሀላ መጥፎ ስነምግባር ያላትና ምላሳም(ተሳዳቢና ያለ አግባብ በመናገር የምታምን ምላሰ ሰይፍ) ሴት ከማግባት የከፋ አስቸጋሪና ፈታኝ አደጋ አይገጥመውም።》ብለዋል
والله إن منهن لغُلّاً ما يفدى منه!
《ወላሂ ከሴቶች መሀከል አንዳች ፈኢዳ የማይገኝባት ምድረበዳና የእድገት መሰናክል ብሎም ወጥመድ የሆነች ሴት ስትኖር ።》
وإن منهن لغنما ما يحذى منه.
《ወላሂ ከሴቶች መሀከል ሁሌ ግልገሎችን ከመወለድና ወተትን ከመስጠት እንማያቋርጡ የርቢ የቤት እንስሳት እጅግ ፍሬያማና ውጤታማ ሴቶች አሉ።》ብለዋል
المصدر :
[ الجعديات (1077) -
مصنف ابن أبي شيبة (17427) ]
ምንጭ
አልጃዕዲያት(1077)
ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ(17427)
الشرح :
አጠር ያለ ማብሪያሪያ
جعل عمر رضي الله عنه أمر المرأة الصالحة والسيئة بعد الإيمان والكفر لأمور منها :
ዑመር ኢብኑልኸጣብ አላህ ስራውን ይቀበለውና…
《መልካም ሴት ከኢማን በመቀጠል ትልቋ የወንድ ልጅ ፀጋ፣ መልካም ያልሆነች ሴት ደግሞ ከክህደት(ከኩፍር) በመቀጠል አስከፊዋ የወንድ ልጅ አደጋ አድርጎ የገለፀበት ምክንያቶች……
❶ ـ أن في صلاحها وفسادها صلاح الرجل وفساده وإعانته على الخير أو الشر .
1ኛ:የሴት ልጅ መልካምነት በወንድ ልጅ(በባሏ) መልካም መሆን ላይ እጅግ ትልቅ አስተዋፆዕ ስለሚኖረውና የሴትልጅ እኩይ መሆን ደግሞ በወንድ ልጅ(በባሏ) እኩይ(የብልሹ መገለጪያ ባህሪያት ባለቤት) በመሆን ላይ እጅግ ትልቅ ተፅዕኖ ስላለው ነው።》
ومنها أن لذلك تأثير على الرجل والأسرة والمجمتع وبصلاح هذا وفساده تصلح الدول أو تفسد.
2ኛ《የሴት ልጅ መልካምነት ለባሏ፣ለቤተሰቧ፣ላለችበት ህብረተሰብና ላለችበት ሀገር ማማርና ጥሩ ለመሆን እጅግ ትልቅ ግብአት ስለሆነችና የሴት ልጅ እኩይ መሆን ከራሷና ከቤተሰቧ አልፎ ለሀገር አሰከፊ አደጋ ስለሆነ ነው።》
ومنها أن الرجل إذا ارتاح في بيته ومع أهله أنتج وعمل وطلب ودرس وتجاوز همومه ومشاكلة بقليل من الراحلة.
3ኛ《ወንዶች መልካም ሚስት አግብተው የቤት ውስጥ ሂይወታቸው ካማረ ከቤት ውጪ ባለው ሂይወቱ ፍፁም ውጤታማ ስለሚሆን።》
وعكس ذلك إذا اجتمع عليه هم في بيته وهم في خارجه فقد يهلك إلا أن ينجيه الله عزوجل .
4ኛ《ወንዶች እኩይ(አደገኛ) ሴት አግብተው የቤት ውስጥ ሂይወታቸው ውጥንቅጡ ከወጣ ከቤት ውጭ ባላቸው ሂይወት ውጤት(ስኬት) አልባ ስለሚሆኑ።》ነው ተብሏል
...🖊 Abu Ebrahim
➧ "ተውሂድ ሺርክን ሲያጠፋ
ኢስቲግፋር ደግሞ ወንጀሎችን ያብሳል።
(فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنْبِكَ)
" እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ
ስለ ስህተትህም ምህረትን ለምን
ሙሐመድ 19


*የዱንያ ነገር!!*
~~~~~~~~~~~
ዐልይ ኢብኑል ሀይሠም እንዲህ ይላሉ:–
"አምሳያ ያላየሁለት የዘመን መገለባበጥ፣ የጊዜ መለዋወጥ አይቻለሁ።
★ የአልፈድል ኢብኑ ረቢዕ ንብረት በአንድ ሺህ ግመል ተጭኖ አይቻለሁ። ሌላ ጊዜ ግን ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተደብቄ አይቻለሁ። በውስጧ መድሃኒቶቹ ተጨምረው።

★ አልሐሰን ኢብኑ ሰህልን ደግሞ ጠቅላላ ንብረቱ አንዲት ዘንቢል ውስጥ ሆና ተመልክቻለሁ። ከዚያ ግን ንብረቱ በአንድ ሺ ግመል ላይ ተጭኖ አይቸዋለሁ።"

||

ዱንያ እንዲህ ነች። መርጋት የማታውቅ ወላዋይ!!
♣ ሃያላን ይዋረዳሉ። ደካሞች ይነግሳሉ።
♣ ሀብታሞች ጎዳና ላይ ይወድቃሉ። ምንዱባን በሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይንፈላሰሳሉ።
♣ ሳር ቅጠሉን የተፀየፈው ጨፍጫፊ አረመኔ አለም ጠባው ከአይጥ ጎሬ ሲያደፍጥ ታየዋለህ። የትላንቱ ተሳዳጅ ተራውን ሲያሳድድ ትመለከታለህ።

® ይሄው ነች ዱንያ!! ብልጭ ብላ ድርግም፣ ቦግ ብላ እልም የምትል። ሁሌ ሳቅ የለም! ሁሌ ድል የለም።
|
♣ በድር ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ፣ ጥጋብ ያስከራቸው ቁረይሾች፣ 70 መኳንንቶቻቸው ትላንት ሲያሳድዷቸው በነበሩ ሶሐቦች ሰይፍ ተበልተው፣ ሌላ 70 ደግሞ በምርኮ አስረክበው የሐዘን ማቅ ለብሰዋል። መካ በዋይታ ተንጣለች።
|
♣ ኡሑድ ሌላ ቀን ነው። ሌላ ተራ!! አጋሪዎች የፈነደቁበት፣ እነ ሐምዛን፣ እነ ሙስዐብን ጨምሮ ከ70 በላይ ታላላቅ ጀግኖች ወድቀው ሌላ 70 የቆሰሉበት፣ አሳዝኝ ክስተት እውን የሆነበት ቀን። ሶሐቦች አካላቸው በስለት፣ ልባቸው በሐዘን ቢቆስል ጊዜ አላህ እንዲህ ሲል አሳሰባቸው: –

(إِنْ يَمْسَسْكُمْ قَرْحٌ فَقَدْ مَسَّ الْقَوْمَ قَرْحٌ مِثْلُهُ ۚ وَتِلْكَ الْأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيْنَ النَّاسَ)

"ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ እናም እነዚህን ቀናት በሰዎች መካከል (በመልካምና በሌላ) እናቀያይራቸዋለን፡፡" [ኣሉ ዒምራን: 140]

|||

ዱንያ አመሏ ነው። ዛሬም እንዲሁ ናት።
ግን ማነው የሚማረው? ግን ማነው የሚመረምረው? ግን ማነው የዱንያን ከንቱነት ተገንዝቦ ለዘላለም ቤቱ ከልብ የሚጨነቀው?
እስከ መቼ ነው የምናንቀላፋው?
እስከ መቼ ነው የምንዘናጋው?
እስከ መቼ ነው በከንቱ የምንባዝነው?
ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን!!
ኢላሂ ልብ ስጠን!!

ibnu munewor


የጥቅም ትስስር እስከ ምን ድረስ?
———————
የጥቅም ትስስር ብዙ ሰዎችን እያወራቸው በተጨባጭ በዐይናችን እየተመለከትን ነው። የጥቅማጥቅም ትስስር ሰዎችን ሀቁን እያወቁት ዝም እንዲሉ እያደረጋቸው ነው። ሀቁን እያወቁትም ለባጢል እንዲሞግቱ እያደረጋቸው ነው።

የሚሞግቱት ግን ትላን ሲያስተምሩት የነበረውን ሀቅ ነው!፣ ዛሬ ላይ ደርሰው ያለ ማስረጃ እውነት ነው ብለው እውቅና የሚሰጡት ትላን በማስረጃ ሲያወግዙት የነበረውን ባጢል ነው። ይህ ደግሞ በዲን ላይ መቀያየር ነው!።

ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” አል-ኢባነቱል ኩብራ 571

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! የጥቅማጥቅም ትስስር ከሀቅ መንገድ ዘወር እንዳያደርጋችሁ ተጠንቀቁ!! ዛሬ ላይ ኡስታዝ ነው ስለ ሚንሃጅ ጠንቅቆ ያስተምራል ይባልለት የነበረን አካል ጥቅማጥቅም ምን ያህል እያወረው እንደሆነ እየተመለከትን ነው። በሀቅ ላይ ታገሱ! ፅኑ! ይህቺ የቅርቢቷ አለም እንዲህ እንዲህ እያለች የተሰጠችን አጭር ጊዜ አልቃ ወደ ቀጣዩና ዘላለማዊ አለም እየተሸጋገርን ነውና ለዘላለማዊ አለም የሚሆነን ስንቅ ይዘን እንጓዝ!!

የጥቅም ትስስር ትላንት የሚያውቁትና የሚያስተምሩት የነበረን ሀቅ እንደ አዲስ ሊደብቁት የሚታገሉ ኡስታዞችን እየተመለከትን ነው። ስለ ትላንቱ አቋማቸው ሲጠየቁ ማስረጃ ማቅረብ ስላቀታቸውና የትላንቱን እውነት መደበቅ ስላልቻሉ "አልበሰልንም ነበር" የምትል አስቂኝም አሳዛኝና አሳፋሪ መልስ መስጠቱን ከተያያዙት ቆየት ብሏል።

መብሰል አለመብሰል ከመች ጀምሮ ነው ማስረጃ መሆን የጀመረው? ሀቅ እስኪበስሉ ነው እንዴ የሚያዘው? ምንድነው ያበሰላቸው? በእድሜ ከነሱ በላይ የሆኑና በሳል የሆኑ ሰዎች እዚያው ሀቅ ላይ ፀንተው ነው ያሉት!፣ ወይስ ጥቅማጥቅምና ጎጠኝነት ነው ያበሰላቸው?

እንዲህ ያሉ ሰዎች ተማሪዎቻቸውንም ለማሳት እየታገሉ ይገኛሉ፣ ይሁን እንጂ ከማንም በፊት ትላንት ሀቅ ያስተማሯቸው ያራሳቸው ተማሪዎች "ዛሬ አቋም መቀየሩና መላላቱ ለምን አስፈለገ? ትላንት የተማርነውስ?" እያሉ በማፋጠጥ ሌላ ፈተና ሆነውባቸዋል!። ግራ ሲገባቸውም "አልበሰልንም ነበር" የሚል መልስ ከመደጋገም የዘለለ ማስረጃም ሆነ ሌላ መልስ ሊያገኙ አልቻሉም።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለራሳቸው ጠመው የሚያጠሙ መሪዎችን ፈርተውልናልና እንጠንቀቅ!፣ ኡስታዜ ስለሆነ ሸይኼ ስለሆነ ብለህ ወገንተኝነት አይያዝህ! ከሀቅ መንገድ ዘወር ካለ ሳታቅማማ ተጠንቀቀው!!።

መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ከምፈራው ነገር በጣም በህዝቦቼ ላይ የምፈራላቸው ነገር አጥማሚ መሪዎችን ነው።” ኢብን ሂባን የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂሁል ጃሚዕ 1551 ላይ ሶሂህ ብለውታል።

ዘንግተውት እንጂ ከዱኒያ ጥቅማጥቅምና ብልጭልጭ አኺራ እንደሚሻል አምላካችን አላህ እንዲህ በማለት ተናግሯል:-

بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا۞ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ

«ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትሆን፡፡» አል አዕላ 16-17

እውነትን እንጂ የማይናገሩት፣ የተናገሩት ሁሉ የሚከሰተው ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰዎች ለዱኒያዊ ጥቅማጥቅም ብለው ዲናቸውን የሚሸጡበት ጊዜ እንደሚመጣ ተናግረዋል፣ አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል:-
“በመልካም ስራ ተሽቀዳደሙ፣ (ከፊታችሁ) የጨለመ ሌሊት ቁራጭ አይነት ፈተና አለ፣ አንድ ሰው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሃዲ ሆኖ ያመሻል፣ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሃዲ ሆኖ ያነጋል፣ ዲኑን በዱኒያ ጥቅማ ጥቅም ይሸጣል።” ሙስሊም 198 ዘግበውታል

ከነቢያት በኋላ የነቢያት ወራሽ የሆኑ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች ዲኑ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከነቢያት በኋላ ሰበብ የሆኑት የተለያየ ችግር ሳይደርስባቸው አይደለም፣ ነፍሲያቸውን ለዱኒያ ጥቅማጥቅም ብለው ዲናቸውን ከመሸጥ ተስፋ አስቆርጠዋት ነው።
ታላቁ የየመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“አፈር እንኳ ቢሆን ልንበላ ዝግጁ ነን፣ (ለጥቅማጥቅም ብለን) ዲናችን እና ሀገራችን አናታልልም፣ አንቀያየርም! መቀያየር ከአህሉሱንናዎች ባህሪ አይደለም!”
[አልባዒስ ዐላ ሸርህ አል-ሀዋዲስ 57]

↪️ ልብ በሉ! የጥቅማጥቅም ትስስር ሲባል አይነቱ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት አያስፈልግም፣ ከፊሉ በደሞዝ፣ በንግድ ትስስር፣ ከሌላ ቦታ የተሻለ ደሞዝ በማግኘትና… ወዘተ በጥቅማጥቅም በመተሳሰር የሚያውቁትን ሀቅ ማምታት አለ።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ጁማዱል አወል 24/1442 ዓ. ሂ

#Join ⤵️

https://telegram.me/IbnShifa


اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
ይህ ደዕዋ የተደረገዉ በደሴ ሸዋበር መስጂድ በትናንትናዉ ዕለት እሁድ ዙህር ላይ ኢኽዋኖች በሰሩት ሴራ ተቋርጦ ከአሱር ቡሃላ ነዉ።
ከአሱር ቡሃላ ይህ ደዕዋ ሲደረግ ኢኽዋን አቅፎ የያዛቸዉ የተደመራቸዉ ሱፍይና አህባሽ ሲነሱ በኢኽዋኑዩ ሸይኽ ያቁት ምክኒያት አሻፈረኝ በማለቱ ተቋርጧል።
ከሱፍይ ከተክፊር ተቀይጦ የተመሰረተዉ የኢኽዋን ቡድን በትናንተናዉ ዕለት ደሴ ላይ በሆዱ ያረገዘዉ ሱፍይ ሲነካበት እንዳማጠና ሊያጨነግፍም እንደደረሰ በገሃድ አሳይቷል።

በመቀጠልም

ሸይኽ ያቁት ተብዬዉ ለሱፍይ ያለዉን ወገንተኝነት በሆዱ የገነባዉን ዶሪህ ግልፅ ስላደረገልን በጣም እናመሰግናለን።

ይድረስ ለደሴ ወጣቶች👇

በደሴና አካባቢዋ ያላቹህ ወጣቶች ሆይ! ኢኽዋን እስከነ አጋሮቹ ሱፍይና አህባሽ ጋር በመደመር ወጣቱን የሱፍያ ሙሪድ ለማድረግ ሱናን እንዳይገዘብ የሱፍያን የአህባሽን ጥመት እንዳያዉቅ በዲኑ ላይ እዉቀት ሳይሆን ሙቀት ብቻ እንዲኖረዉ በማድረግ ኢኽዋን ለሚፈልገዉ አላማ ማሳኪያ ማገዶ እያደረጋቹህ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል።

ወጣቱ ሆይ ንቃ!

ደሴ ላይ በኢኽዋን በሱፍይም በአህባሽ በሃዳዲይ ጥመት በመወረር የሱና ወጣቶች ወኔ ታፍኗል።

ከንግዲህ ይብቃ ተነስ አንገትህን ቀና አድርግ የጥመትን ቡድን ከአፈር በታች ለማድረግ ታጠቅ።

ፈራጃችን ቁርአንና ሓዲስ ብቻ ነዉ።

የሺርክና የቢድዓ ቅርጫት የዉሸትና የቅጥፈት መጠራቀሚያ የሆነዉ ኢኽዋን በቁርአንና በሓዲስ ፈንጅ እናፈነዳዋለን።

https://t.me/abu_reyyis_arreyyis/1943

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

74

obunachilar
Kanal statistikasi