በማህበራዊ ህይወትህ በተግባቦት ለመኖር ሊረዱህ የሚችሉ አንዳንድ ማህበራዊ ህጎች፡-
1. አንድን ሰው ያለማቋረጥ ከሁለት ጊዜ በላይ አትጥራ!
2. የተበደርከውን እቃ ወይም ገንዘብ፥ የተበደርከው ሰው ሳያስታውስህ ወይም ሳይጠይቅህ መልስለት። የአንተን የታማኝነት ባህሪ ያሳያልና።
3. የሆነ ሰው ምሳ ወይም እራት ሲጋብዝህ ውድ የሆነውን አትዘዝ።
4. ‘እስካሁን አላገባህም?’ ወይም ‘ልጆች የሉህም?’ ወይም ‘ለምን ቤት አልገዛህም?’ ወይም ‛ለምን መኪና አትገዛም?’ የሚሉ የማይጠየቁ ጥያቄዎችን አትጠይቅ።
5. ከጓደኛህ ጋር በታክሲ ስትሄድ፥ እሱ ዛሬ ከከፈለልህ በሌላ ቀን አንተ ክፈል።
6. የሀሳብና የእይታ ልዩነቶች አክብር። ለአንተ 6 የሆነውን በሌላው ዘንድ 9 ሊሆን ይችላል።
7. ከማንም ጋር ስታወራ የሰው ሀሳብ አታቋርጥ። እስኪጨርስ ጠብቀው።
8. ማንም በምን ነገር ከረዳህ "አመሰግናለሁ" ማለትን ይልመድብህ።
9. ማንንም ስታመሰግን በአደባባይ አመስግን። ትችትህ ደግሞ በግል ይሁን።
10. የሆነ ሰው ስልኩ ሰጥቶህ፥ ከስልኩ ላይ ፎቶ ሲያሳይህ፤ ካሳየህ ፎቶ ሌላ ለማየት አትሞክር።
11. አንድ የምታውቀው ሰው፥ የሀኪም ቤት ቀጠሮ እንዳለው ቢነግርህ፤ ለምን እንደሆነ አትጠይቅ! "መልካሙን ያሰማህ" በለው እንጂ!
12. አንድ ሰው ከአንተ ጋር እያወራ፣ ስልክህ ላይ ማፍጠጥ ነውር ነው።
13. እስካልተጠየቅክ ድረስ በጭራሽ ምክር አትስጥ።
14. ከብዙ ጊዜ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ስትገናኝ፣ ስለእድሜውን እና ደመወዙን አትይጠይቀው። እርሱ ራሱ ለማውራት ጀምሮት፤ ፈቃደኛ እስከሚሆን
15. በቀጥታ በማያሳትፍህ፣ በማያገባህ ነገር አትግባ።
16. በመንገድ ላይ ከማንም ጋር እየተናገርክ መነፀር አድርገህ እንደሆነ አውርደው። የአክብሮት ምልክት ነው። የዓይን ለዓይን ግንኙነት እንደ ንግግርህ አስፈላጊ ነውና!
17. በድሆች መካከል ስለ ሀብትህ ፈጽሞ አትናገር። እንዲሁም በመካኖች መካከል ስለ ልጆችህ ፈፅሞ አታውራ።
18. እንዲህ አይነቱ፦ ጥሩ መልእክት ካነበብክ በኋላ "ስለመልእክቱ አመሰግናለሁ" ማለትን አትርሳ።
https://t.me/ewuketmad