ሀሰተኛው @frombooks1234.pdf
ወደ ረድ ሠርዌ ስመለስ ወፍጮ ቤቱ ላይ እንዳተኮረ ነበር። አውሎ ንፋስ ያግለበለበው የመሰለ የዶቄት ብናኝ ይቦናል። ለፀጉራቸው ብቻ የሚጨነቁ ሴቶች ሻሻቸውን ቆልለው ቡላ ፊታቸውን አስቀድመው ይወጣሉ። ሻኛ የመሰለች የእህል ቋጠሮ ጀርባቸው ላይ አብጣ ትታያለች። ለአንድ ቤተሠብ የአንድ ቀን ፍጆታ ሳይሆን አይቀርም። የመከራ ጊዜው ያለፈ ቢመስልም በየሰው ልብ ውስጥ የተወው ቅሪት ዘልአለማዊ ሥጋት ሰንቅሮ ትቷል። ሰው ሥጉ ፍጡር መሆኑን የሚገልፀው እንዲህ ያለ ቀን ነው። የመከራ ጊዜ ፍላጎት አዘቅት ነው። ቁስ ብንከምር ብንቁልል ዓይናችን አይጠግብም። አንዳንድ ሴቶች እነሱ የማይችሉትን አስፈጭተው በሚችለው አሸክመው እየተገላመጡ ይቀድማሉ። ምናልባት አይን ውስጥ እንዳይገቡ ይሆናል። ከሸክሙ በጥቂት ምዕራፍ ይርቃሉ። እነዚህ ሴቶች ያልተረዱት ቢኖር ያሸከሙት ሰው ከዘረፋ ውጭ ምንም ተስፋ ከሌላቸው ወገን መሆኑን ነው። ነገሩ ዳግም ካገረሸና የከተማው አቅርቦት ድንጋይ ብቻ ከሆነ ድንጋዩን ጨብጠው እህሉ የገባበትን ቤት የሚከቡ ድሆች ይመጣሉ። አግበስባሾች ያግበሰበሱት መጥፊያቸው ይሆናል ።
አለማየሁ ገላጋይ ፤ ሀሰተኛው
📚📖 @gbw_dan
📖 @gbw_dan📚📖 @gbw_dan
አለማየሁ ገላጋይ ፤ ሀሰተኛው
📚📖 @gbw_dan
📖 @gbw_dan📚📖 @gbw_dan