ጉዳያችን...(የሙስሊም ወጣቶች ሀላፊነት)


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ታዳጊ ቻናል ነው። እዚ ድረስ ከመጡ አይቀር ጆይን ይበሉ እንዲሁም ለሚወዱት ያጋሩ ባረከላሁ ፊኩም።
ረሱል (ﷺ)“ወደ መልካም ያመለከተ የሰራው ሰው አይነት አጅር (ምንዳን) ያገኛል።”

👉ለማንኛውም አስተያየት ➢ t.me/gudayachin_bot@salihul ላይ ያናግሩን

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




ከረጀብ ወር ጋር የሚያያዙ ደካማ ሐዲሦች
~
ከረጀብ ጋር ብዙ መሰረተ ቢስ ቅጥፈቶችና ደካማ ሐዲሦች አሉ። ለምሳሌ ያክል፦
[1ኛ]፡-
رجب شهر الله وشعبان شهري ورمضان شهر أمتي
“ረጀብ የአላህ ወር ነው። ሸዕባን የኔ ወር ነው። ረመዷን ደግሞ የህዝቦቼ ወር ነው።” አልባኒይ ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [አዶዒፋህ፡ 4400]

[2ኛ]፡- ረጀብ ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
اللهم بارك لنا في رجب وشعبان، وبلغنا رمضان
“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንም አድርሰን።” ነወዊይ በ“አዝካር”፣ ዘሀቢይ በ“ሚዛን”፣ ኢብኑ ሐጀር በ"ተብዪኑል ዐጀብ" ደካማ እንደሆነ ብይን የሰጡ ሲሆን አልባኒይም “ደካማ ነው” ብለዋል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 4395]

[3ኛ]፡-
فضل شهر رجب على الشهور كفضل القرآن على سائر الكلام
“የረጀብ ወር በሌሎች ወራት ላይ ያለው ብልጫ ቁርኣን በሌሎች ንግግሮች ላይ እንዳለው ብልጫ ነው።” ኢብኑ ሐጀር፣ ሙላ ዐሊይ አልቃሪ፣ አልዐጅሉኒይ፣ አልገዚይ እና አዘርቃኒይ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት ነው" (መውዱዕ) ብለዋል።

[4ኛ]፡-
خمس ليال لا ترد فيهن الدعوة أول ليلة من رجب، وليلة النصف من شعبان، وليلة الجمعة، وليلة الفطر، وليلة النحر
“አምስት ሌሊቶች በነሱ ውስጥ የተደረገ ዱዓእ አይመለስም። የመጀመሪያው የረጀብ ሌሊት፣ የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት፣ የጁሙዐ ሌሊት፣ የዒደል ፊጥር ሌሊት እና የዒደል አድሓ ሌሊት ናቸው።” አልባኒይ “መሰረተ ቢስ” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 1452] [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 2852]

[5ኛ]፡-
رجب شهر عظيم يضاعف الله فيه الحسنات، فمن صام يوما من رجب، فكأنما صام سنة، ومن صام منه سبعة أيام، غلقت عنه سبعة أبواب جهنم، ومن صام منه ثمانية أيام، فتحت له ثمانية أبواب الجنة، ومن صام منه عشرة أيام، لم يسأل الله شيئا إلا أعطاه إياه، …
“ረጀብ አላህ መልካም ምንዳዎችን የሚያነባብርበት ታላቅ ወር ነው። ከረጀብ አንድ ወር የፆመ ሰው አመት እንደፆመ ነው። ከሱ ሰባት ቀናትን የፆመ ሰባቱ የጀሀነም በሮች ይዘጉለታል። ከሱ ስምንት ቀናትን የፆመ ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል። ከሱ አስር ቀናትን የፆመ አላህን የሆነ ነገር አይጠይቅም፣ እሱኑ የሰጠው ቢሆን እንጂ፣ …” አልባኒይ “መሰረተ ቢስ” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 5413]

[6ኛ]፡-
إن في الجنة نهرا يقال له رجب ماؤه أشد بياضا من اللبن وأحلى من العسل من صام يوما من رجب سقاه الله من ذلك النهر
“በጀነት ውስጥ ረጀብ የሚባል ወንዝ አለ። ውሃው ከወተት የነጣ፣ ከማር የጣፈጠ ነው። ከረጀብ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ ከዚያ ወንዝ ያጠጣዋል።” አልባኒይ “መሰረተ ቢስ” ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 1902]

[7ኛ]፡-
صوم أول يوم من رجب كفارة ثلاث سنين، والثاني كفارة سنتين، والثالث كفارة سنة، ثم كل يوم شهرا
“የረጀብን የመጀመሪያ ቀን መፆም የሶስት አመት ወንጀል ያብሳል። ሁለተኛው የሁለት አመት ያብሳል። ሶስተኛው ደግሞ የአመት ያብሳል። ከዚያም እያንዳንዱ ቀን የወር ነው።” አልባኒይ ደካማ ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 3500፣ 5649]

[8ኛ]፡-
لا تغفلوا عن أول جمعة من رجب فإنها ليلة تسميها الملائكة الرغائب
“ከረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐ አትዘናጉ። እርሷ መላእክት ‘አረጋኢብ’ ብለው የሚጠሯት ሌሊት ነች።”
‘ሶላተ ረጋኢብን’ በተመለከተ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡- “እርሷን የፈጠረን ሰው አላህ ይርገመው! እርሷ አስቀያሚ ቢድዐ ነች!” [ሸርሑ ሙስሊም] በተጨማሪም እሷንና የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ሶላትን አስመልክተው “… ቢድዐና አስቀያሚ ፈጠራዎች ናቸው። በ‘ቁቱል ቁሉብ’፣ ‘ኢሕያእ ዑለሚዲን’ ኪታብ ውስጥ ስለተጠቀሱ ማንም እንዳይሸወድ። እነሱን በሚጠቁመው ሐዲሥም እንዲሁ (እንዳይሸወድ)። ምክንያቱም ሁሉም ውድቅ ነውና” ብለዋል። [አልመጅሙዕ፡ 3/548]

[9ኛ]፡-
أن رسول الله -ﷺ- لم يصم بعد رمضان إلا رجبًا وشعبان
“የአላህ መልእክተኛ ከረመዷን በኋላ ረጀብንና ሸዕባንን እንጂ አልፆሙም።” ኢብኑ ሐጀር በጣም ደካማ ነው ብለውታል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 12]

[10ኛ]፡-
من صلى المغرب في أول ليلة من رجب ثم صلى بعدها عشرين ركعة يقرأ في كل ركعة بفاتحة الكتاب، وقل هو الله أحد مرة، ويسلم فيهن عشر تسليمات، أتدرون ما ثوابه؟ قال: حفظه الله في نفسه وأهله وماله وولده، وأجير من عذاب القبر، وجاز الصراط كالبرق بغير حساب ولا عذاب
“በረጀብ የመጀመሪያ ሌሊት መግሪብን ሰግዶ ከዚያም በእያዳንዷ ረከዐ ፋቲሐንና ቁል ሁላሁ አሐድን አንድ ጊዜ እየቀራ፣ በአስር ተስሊማት እያሰላመተ ሃያ ረከዐ የሰገደ ሰው ምንዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አላህ በነፍሱም፣ በቤተሰቡም፣ በገንዘቡም፣ በልጁም ይጠብቀዋል። ከቀብር ቅጣትም ይጠበቃል። ሲራጥንም ያለ ሂሳብና ያለ ቅጣት እንደ ብልጭታ ያቋርጧል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/123] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 20]

[11ኛ]፡-
من صام من رجب وصلى فيه أربع ركعات ... لم يمت حتى يرى مقعده من الجنة أو يُرى له
“ከረጀብ ፁሞ፣ በሱ ውስጥ አራት ረከዓዎችን የሰገደ ሰው … በጀነት ውስጥ መቀመጫውን ሳያይ ወይም ሳይታይለት አይሞትም።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/124] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 21]

[12ኛ]፡-
إن شهر رجب شهر عظيم، من صام منه يومًا كتب الله له صوم ألف سنة ...
“የረጀብ ወር ታላቅ ወር ነው። ከሱ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺ አመት ፆም ይመዘግብለታል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/206-207] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 26]

ከረጀብ ጋር የሚያያዙት ዘገባዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም። እነዚህን ለምሳሌ ያክል ይዘን ሌሎቹንም ጭምር በሚመዝን የዓሊሞች ንግግር  ልቋጭ:—
1/ አልሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር - ረሒመሁላህ - “የረጀብን ወር ልዩ ብልጫም፣ መፆሙን ወይም ከፊሉን በተለየ እንዲፆም፣ ወይም ከሱ ውስጥ የተገደበን ሌሊት በሶላት ማሳለፍን፣… የሚጠቁም ለማስረጃነት የሚበጅ ትክክለኛ ሐዲሥ አልተላለፈም" ብለዋል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 6 እና 8]
2/ አልሓፊዝ አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ በክር አዲመሽቂይ (691 ሂ.) ደግሞ “እያንዳንዱ የረጀብን ፆም እና ከፊል ሌሊቶቹን መስገድን የሚጠቁም ሐዲሥ ውሸት፣ ቅጥፈት ነው” ብለዋል። [አልመናሩል ሙኒፍ፡ 1/96]

ልብ በሉ! በዚህ ወር ውስጥ ፆምና ሶላት አይኑር ለማለት አይደለም። ወሩን ከሌሎቹ ወራት በተለየ መልኩ መያዝ አይገባም ነው አጠቃላይ ጭብጡ።
= Ibnu Munewor




ስልጤ ሰፈር የሚገኘው ዓሊ መስጅድ በአዲስ መልክ እየተገነባ ነው። በ5 ወራት ውስጥ ብቻ ግራውንዱን ከታች በምትመለከቱት መልኩ አጠናቀውት በአላህ ፈቃድ ነገ እሁድ ይመረቃል። መስጅዱ በ1000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈና በአላህ ፈቃድ ባለ 3 ፎቅ ይሆናል። ግራውንዱን ሥራ አስጀምረው ቀሪዎቹን ፎቆች ከአላህ ቀጥሎ በእናንተ ርብርብ ለማስጨረስ አቅደዋል። እስካሁን ከመስጅዱ ኮሚቴዎች ጀምሮ የአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ በአቅሙ ልክ ተረባርቧል። አላህ ይቀበላቸው!
ጠንካራ የመስጅድ ኮሚቴ ሲኖር መጀመሪያ ከራሱ የአቅሙን አዋጥቶ ለሌላውም ሞራል ይሆናል። አንዳንድ ቦታ ደግሞ እንኳን ሊያዋጡ የተዋጣንም በሰበብ አስባብ የሚውጡ አሉ። የዚህ መስጅድ ጀማዓዎች ይህንን በ5 ወራት ውስጥ ሲያጠናቅቁ፤ ከ800 በላይ የመስጅዱ ታዳጊ ቂርኣት የሚቀሩ ተማሪዎቻቸው ደርሳቸውን ሳያቋርጡና የመስገጃ አገልግሎት ሳይቋረጥ ጎን በጎን አስቀጥለውታል። ነገ ሁላችሁንም በአክብሮት ጋብዘዋችኋል።

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
ተክቢርርርርርርርርርርርርርርር


📖 ቢፈድሊሏህ 1️⃣k ተከታይ አፍርተናል💙
ቻናሉን ሼር በማድረግ ፣ በማስተዋወቅ ያገዛችሁን ወንድም እህቶች ከልብ እናመሰግናለን
ጀዛኩሙሏህ😊

ይህንንም በማስመልከት ነገ ኢንሻአሏህ ሽልማት ያላቸው ጥያቄዎች ይኖሩናልና ተዘጋጁ

አሁን ካቆምንበት እንቀጥል ...

🧎📖 በቁርአን ውስጥ የሰዎች ሰጅዳ ያለባቸው ታሪኮች የሁለቱ ብቻ ናቸው!

በዩሱፍ ታሪክ ወንድሞቹ ፣ አባቱና እናቱ ለዩሱፍ ሱጁድ ሲያደርጉ ስናገኝ ፤ በሙሳ ታሪክ ደግሞ የፊርአውን ደጋሚወች ተዐምሩን ሲያዩ ሱጁድ መውረዳቸውን እናገኛለን ♡

وَخَرُّواْ لَهُۥ سُجَّدًاۖ
فَأُلۡقِىَ ٱلسَّحَرَةُ سُجَّدًا

ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት & ሰጋጆች ሆነው ወደቁ ...

ይቀጥላል !
ቻናላችን 👉 t.me/tedeburr


فِي هَذَا اليَومِ الفَضِيلِ ،
وَفِي هَذِهِ السَّاعَةِ الطَّيِّبَةِ
مِنَ أَيَّامِ المُبَارَكَةِ
اللَّهُمَّ يَا قَاضِيَ الحَاجَاتُ ،
يَا كَاشِفَ الكُرُبَاتِ ،
يَا مُجِيبَ الدَّعَوَاتِ
يَا غَفِرَ الزَّلَّاتِ
، عَافِنَا وَاعْفُ عَنَّا ،
وَفَرِّجْ هُمُومَنَا ،
وَاشْرَحْ صُدُورَنَا ،
وَأَصْلِحْ أَحْوَالَنَا ،
وَحَقِّقْ آمَالَنَا ،
وَاشْفِ مَرْضَانَا ،
وَارْحَمْ مَوْتَانَا ،
وَأَسْعِدْ قُلُوبَنَا
وَاجْعَلْنَا مِنَ المَقْبُولِينَ عِندَكَ ،
اللَّهُمَّ آمِينَ وَسَائِرَ الأَحِبَّةِ
وَالصَّحْبِ أَجْمَعِينَ ..
‏*اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَىٰ نَبِيِّنَا مُحَمَّد ..*

‏*💫فِي آخِرِ سَاعَةٍ مِنَ الجُمُعَة لَا تَنسَ الأَحْـيَـاءَ مِنْ أَحْبَـابِـكَ وَالأَمْـوَات 💫*

t.me/gudayachin_new


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
t.me/gudayachin_new


✍ውሻችን የገደለብን ሰው ግደ* ሉት!!

በአንዲት ገጠራማ መንደር ውስጥ የሚኖር አርብቶ አደር አባወራ ነበር። ይህ አባወራ የሚያረባቸው ከብቶች እና ልጆቹ አብረውት በዚችኑ መንደር ተሰብስበው ይኖራሉ። ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ ጥጋበኛ ይመጣና ለአርብቶ አደሩ ከብቶቹን ሲጠብቅለት የነበረው ውሻ ይገልበታል።
ይህንን ዐይተው የደነገጡ ልጆች በፍጥነት ወደ አባታቸው ሄደው የተከሰተው ይነግሩታል። አባታቸው………
"ሂዱና ውሻችን የገደለብን ሰው ግደ* ሉት።" አላቸው።

ልጆቹ እርስ በእርስ እየተያዩ ተነስተው ወጡ። ከአባታቸው ጋ ከወጡ በኋላ ግራ ተጋብተው መነጋገር ጀመሩ። "አባታችን ግን ምን ሆኖ ነው? እርጅና ነው ወይስ እብደት? እንዴት: ሰው ለውሻ ይገደላል?" ተባብለው ነገሩን በቸልታ አለፉት።

ቀናቶች ካለፉ በኋላ የመንደሩ ወሮ_በላዎች ተሰብስበው ከዚሁ ቤት ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው ይሮጣሉ። ክስተቱን የተመለከቱ ልጆች ወደ አባታቸው ቀርበው ይነግሩታል። አባታቸው ፍፁም በተረጋጋ ስሜት………
"ሂዱና ውሻችን የገደለብንን ግደ* ሉት" አላቸው።

ልጆቹ ይበልጥ ተናደዱ አዘኑም። አባታቸው ምንም የማያውቅ እርጅና ላይ መድረሱ ወይም አእምሮው ትክክል እንዳልሆነ ጠረጠሩ። "እኛ ስለ ከብቶች መሰረቅ እናወራዋለን እሱ ውሻ የገደለውን እንድንገድል ይነግረናል: ምን ዐይነት መዘባረቅ ነው?" ብለው ትተውት ሄዱ።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ከሚኖሩበት መንደር ራቅ ካለ ሰፈር የሚኖሩ ጎሳዎች ይመጡና የቤቱ ታላቋ እና ተወዳጇ ሴት ልጅ ጠልፈው ይወስዷታል። ልጆቹ ለአባታቸው ከመንገር ቅሮት አልነበራቸውምና አሁንም መጥተው መርዶው ይነግሩታል። እሱጋ ግን የተቀየረ ስሜትም ይሁን ንግግር አልነበረም………
"ሂዱና ውሻችን የገደለብን ግደ* ሉት" አላቸው።

ልጆቹ ከአባታቸው ጋ መግባባት ባለመቻላቸው እየተበሳጩ፤ በአባታቸው ሁኔታም እያዘኑ ግራ በመጋባት ላይ ሳሉ: ታላቁ ወንድማቸው "እንግዲያውስ ዛሬ የአባቴን ትዕዛዝ ልፈፅም ነው። የውሻችን ገዳይ እገድልና የሚፈጠረውን አብረን እናያለን" ብሎ ሰይፉን ስሎ ይሄዳል።

የውሻቸው ገዳይ ጋ ሲደርስ "አንተ ነህ የእኛን ውሻ የገደልከው?" ብሎ ካረጋገጠ በኋላ በቅፅበት ጭንቅላቱን ከአንገቱ ላይ በጠሰው።

ይህ ወሬ እንደጉድ ሀገሩ ላይ ተናፈሰ። ሁሉም ቦታ "የእንትና ልጆች ውሻችን ገድለሃል በሚል እከሌን ገድለ* ውታል" እየተባለ ይወራል።

ይህንን ዜና የሰሙ ዘራፊዎች "እነዚህ ሰዎች የውሻቸው ገዳይ የሚገድሉ ከሆኑ: እኛን ምን ሊያደርጉን ነው? በሚል ሰግተው ልክ መሸትሸት ሲል ጠብቀው የወሰዷቸው ከብቶች በአጠቃላይ አምጥተው ግቢ ላይ ለቀቋቸው።

ሴት ልጃቸው ጠልፈው የሄዱትም "የውሻቸው ገዳይ የሚገሉ ከሆኑ: ልጃቸው እና ክብራቸው ለደፈረማ ምንም ምህረት አይኖራቸውም" በሚል የጎሳቸው መሪ ለነበረው ንጉስ ለልጁ ሊድሯት ሽማግሌ መራርጠው ወደ አርብቶ አደሩ ቤት ላኩ።

ምን መሰለህ ወዳጄ…………
አንዳንድ መብቶችህ ሲረገጡ በዝምታ የምታልፍበት ሂደት በጣም ከበዛ ማንነትህ እና ህልውናህ የሚረግጥብህ ሌላ ቡድን ይመጣብሃል። በመብትህ ላይ የሚረማመዱ ጨቋኞቹ የሚቀያየሩብህ ግን እነሱ ጀግኖች ስለሆኑ ሳይሆን: አንተ ለመብትህ የማትጨነቅ ዝምተኛ በመሆንህ ነው።

ዛሬ ላይ………
በክልል አዋጅም ይሁን በተቋም ስርዓት ሊጣስ አይችልም የሚባለው የሀገሪቷ ህገ_መንግስት በመጣስ "ሙስሊም ሴቶች ሂጃብ መልበስ የለባቸውም" ብሎ የሚደነፋው የመንደር ዘገምተኛ ስርዓት ማስያዝ ካልቻልክ:
ነገ "ሙስሊም ወንዶች ፂማቸውን ማርዘም አይችሉም" ብሎ ያስልጭህና;
ከነገ ወድያ ደግሞ "ልጅህን አሕመድ ሙሐመድ ብለህ መሰየም አትችልም" የሚል አዋጅ ያፀድቅልሃል።

ይህ የሚሆነው ግን………
በእሱ ጀግንነት ሳይሆን: በአንተ ዝምታ ነው!!

Copy


ጠልሓ ቢን ዐውፍ ቸር ነበር። እጅግ በጣም ቸር። አንድ ቀን ባለቤቱ እንዲህ አለችው
“ከወንድሞችህ የበለጠ የመጨረሻ እርኩስ የሆኑ ሰዎችን አላየሁም።”
“ለምን እንደዚህ አልሽ”  አላት
“ገንዘብ ሲኖርህ  ይጣበቁብሃል፣ ምንም ከሌለህ ግን ጭራሽ አይጠጉህም።” አለችው
“ወላሂ… ይህ የመልካም ስብዕናቸው ውጤት ነው። ለነርሱ መስጠት በምንችልበት ጊዜ ወደኛ ይመጣሉ…  ሀቃቸውን መወጣት በማንችልበት ጊዜ ደግሞ ለራሳችን ይተውናል።” አላት።

ልብህ ንፁህ ይሁን።  ነገሮችን ሁሉ በመልካም መልካቸው ለማስተናገድ ሞክር። አዕምሮህ ሰላም እንዲሆንም ከፈለግህ  ሁሉንም ነገር አትፈልፍል። ሁሉንም ምክንያት ልወቅ አትበል።  ሰላም ትሆናለህ።

©️
t.me/gudayachin_new


ባል:- ባለቤቴን ሱብሂ ስቀሰቅሳት አትሰማም፤
መተኛት ሆነ ሥራዋ እንደው ምን ላድርግ ያ ሸይኽ?

ሸይኽ:- በሌላ ሴት ስም ጠርተህ ቀስቅሳት፤
የማን ስም ነው ብላ ብድግ ትላለች 😂

t.me/gudayachin_new


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
t.me/gudayachin_new


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መልካም ቀን

@gudayachin_new


.
#እህቴ  እነዛ የሚሸፋፈኑ እህቶችሽ አንቺ የተረዳሽውን ስልጣኔ ሳይገነዘቡና ኋላ ቀር ሆነው ሳይሆን ትክክለኛ ዋጋቸውን ስለተረዱና ምን ያህል ውድ እንደሆኑ ስለተገነዘቡ ነው::

t.me/gudayachin_new


#ተደቡር

💥የነብዩሏህ ዩሱፍና ሙሳ አስገራሚ መመሳሰሎችን ተደቡር ማድረጋችን ቀጥሏል ...

✨ «ጃሂሊን» የሚለውን ቃል ሁለቱም ነብያት ሲጠቀሙት እናገኛለን ።

ሙሳ “አዑዙ ቢሏሂ አን አኩነ ‘ሚነል ጃሂሊን’ ” ሲል ዩሱፍ ደግሞ "አስቡ ኢለይሂነ ወአኩን ‘ሚነል ጃሂሊን’ " አለ ..

• قَالَ أَعُوذُ بِٱللَّهِ أَنۡ أَكُونَ 《مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ
• وَإِلَّا تَصۡرِفۡ عَنِّى كَيۡدَهُنَّ أَصۡبُ إِلَيۡهِنَّ وَأَكُن 《مِّنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ


12 ቁጥር ..

የያዕቁብ ልጆች አስራ ሁለት መሆናቸውን ታውቃላችሁ .. የሚገርመው ታዲያ ሱረቱ ዩሱፍም በቁርአን “12ኛ ሱራ” ነች! ። በሙሳ ታሪክ ደግሞ 12 የበኒ ኢስራዒል ጎሳዎች ነበሩ .. ድንጋዩንም በበትሩ ሲመታው 12 ምንጭ ነበር የፈጠረው ...

وَقَطَّعۡنَٰهُمُ 《ٱثۡنَتَىۡ عَشۡرَةَ》 أَسۡبَاطًا أُمَمًاۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ إِذِ ٱسۡتَسۡقَىٰهُ قَوۡمُهُۥٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡحَجَرَۖ فَٱنۢبَجَسَتۡ مِنۡهُ 《ٱثۡنَتَا عَشۡرَةَ》 عَيۡنًاۖ

✨“ማጠጣት” የሚለውን ቃል በሁለቱም ታሪክ እናገኘዋለን ...

ሙሳ ወደ መድየን ሄዶ የተመለከተውን ክስተት ሲነግረን «ኡመተን ሚነናሲ ‘የስቁን’/ መንጋዎቻቸውን ‘የሚያጠጡ’ ሆነው አገኛቸው» ሲለን በዩሱፍ ታሪክ ደግሞ እስር ቤት በነበረበት ጊዜ ለአንዱ እስረኛ የህልም ፍችውን ሲነግረው « ‘ፈየስቂ’ ረበሁ ኸምራ/ ንጉሱን ጠጅ ‘ያጠጣል’» ሲለው እናገኛለን ። እዛም ማጠጣት ፤ እዚህም ማጠጣት .. ሱብሃነሏህ

•  وَجَدَ عَلَيۡهِ أُمَّةً مِّنَ ٱلنَّاسِ 《يَسۡقُونَ
•  《فَيَسۡقِى》 رَبَّهُۥ خَمۡرًاۖ
ይቀጥላል ..!

ቻናላችን 👉 t.me/tedeburr


قال حافظ المغرب الإمام ابن عبد البر رحمه الله
[ من أعجب برأيه ضلَّ،

በአመለካከቱ የተደነቀ ሰው ይጠማል

ومن استغنى بعقله زلَّ،

በአቅሉ የተብቃቃ ከሐቁ ይንሸራተታል

ومن تكبر على الناس ذلَّ،

በሰዎች ላይ የኮራ ይዋረዳል

ومن خالط الأنذال حقِّر،

በዲናቸው ላይ የወደቁ ዝቅተኛ ወራዳ የሆኑትን የተቀላቀለ ክብረቢስ ይሆናል

ومن جالس العلماء وقِّر

ከትላላቅ ሰዎች (ዑለማ) ጋር የተቀማመጠ ይከበራል ]

[جامع بيان العلم وفضله ١٤٣/١]


ሰአቱል ኢጃባ ነው ሰዐቱ ዱዐ አድርጉ

መልካም ማምሻ

@gudayachin_new


የጁመዓ ሱና

ለማስታወስ ያክል

@gudayachin_new


"..አለመልበስን የፈቀደች ሀገር መልበስን ልትከለክል አይገባም"

በፌዴራል መጅሊስ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ኡስታዛ ፋጡማ

- ሀሩን ሚዲያ፣ ታህሳስ 17/2017

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዲፈናቀሉ መደረጋቸውን ተከትሎ የፌዴራል መጅሊስ ምን እየሰራ ነው ስንል ጠይቀናል።

በጉዳይ ዙሪያ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሴቶች እና ወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ኡስታዛ ፋጡማ በሰጡት ምላሽ የፌዴራል መጅሊስ ችግሩን ለመፍታት ከትግራይ ክልል መጅሊስ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በቅርቡ ችግሩ እልባት አግኝቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ያሉት ኡስታዛ ፊጡማ መጅሊስ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከሰቱ መሰለል ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ሂጃብ የሴት ልጅ የእምነቷ የማንነቷና የክብሯ መገለጫ ነው ያሉት ኡስታዛ ፋጡማ አለመልበስ የተፈቀደባት ሀገር ላይ መልበስ ሊከለከል አይገባም ብለዋል።

በአክሱም ከተማ ሂጃብ ካላወለቃችሁ አትማሩም የተባሉ ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን መፍትሔ አለማግኝታቸውን ገልፀው አስቸኳይ እልባት እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።

© ሀሩን ሚዲያ


Alhamdulillah


መልካም ምሽት

@gudayachin_new


ስታገኝም፣ ስታጣም… በሁሉም ሁኔታ አላህን ፈሪ እና አመስጋኝ ባሪያ ሁን። ከፍም ዝቅም የሚያደርገው አላህ ነው።

መልካም ምሽት

@gudayachin_new


የተደበቀ ደስታ አለ። ግን ለመውጣት የኔን ኢስቲጝፋር ይጠብቃል። ኃጥያት ብዙ መልካም ነገሮችን ይደብቃል ግን በዋናነት  የመኖርን ደስታ ሲሸፍንብን ይኖራል። በኢስቲጝፋር እንግለጠው። ምህረትን እንጠይቅ!

«መኖራችን ካልቀረ የላቀ ኑሮ እንምረጥ»


መልካም ቀን

@gudayachin_new

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.