❌ ሰልፍ ❌
📁 ይህ ሸይኽ ዓብዱረህማን ብን ሰዕድ ብን ዓልይ አሽሸስሪ “አልሙዟሀራት ፊ ሚዛኒ አሽሸሪዓቲ አልኢስላምየቲ” በሚል ርዕስ ካዘጋጁት መጽሐፍ ከገጽ 84-108 የተወሰደ አጭር ትምህርት ነው፡፡ አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት ሰላማዊ ሰልፍን በቁርኣን እና በሐዲስ የሚገመግም ሲሆን በዚህ መጽሐፍ የሰላማዊ ሰልፍ ቋንቋዊና ሸሪዓዊ ትርጉም፤ በመሪዎች ላይ ማፈንገጥ ያለው ሸሪዓዊ ብይን፤ ሰላማዊ ሰልፍ እያስከተለ ያለው አደጋ፤ ሰላማዊ ሰልፍ መቸ ተጀመረ?፤ ማን ጀመረው?፤ የሰላማዊ ሰልፍ ብዥታዎችና መልሶቻቸው እና የመሳሰሉ ርዕሶች የተዳሰሱበት በመሆኑ በተለያዩ ቋንቋዎች ቢተረጎም ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ከፍተኛ ፋይዳ ያስገኛል ብየ አስባለሁ፡፡
ይህችን አጠር ያለች ጽሁፍ ለመክተብ ያነሳሳኝ በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ብሎም በአለም የስንት ሙስሊም ወንድሞቻችንን ህይወት ያስቀጠፈ፤ ከአገር ያሰደደ፤ ያስገረፈ፤ ክብራቸው እንዲጣስና አካለ ስንኩላን እንዲሆኑ ያስደረገ ፤ ያለአግባብ የሙስሊሞች ገንዘብ እንዲወድም እንዲዘረፍ እና በአጠቃላይ የሙስሊሞችን አገር የበታተነ ስለሆነው “ሰላማዊ ሰልፍ” በኢስላም ይፈቀዳል? ወይስ አይፈቀድም? በሚል በየመንደሩና በየጓዳው ማስረጃን መሰረት ያላደረገ ክርክርና ብዥታዎችን ከአንዳንድ ወጣቶች በማስተወሌ ነው፤ በመሆኑም ምንም እንኳ የሚያጠግብ ባይሆንም የወጣቱን ግለት በተወሰነ መልኩ ያበርዳል፤ የተንሻፈፈውን አመለካከት ያቃናል፤ ያለእውቀት በዚህ አውዳሚ እንቅስቃሴ ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እነዚህን 18 ብዥታዎች እና መልሶቻቸው ሲያስተውሉ በአላህ ፈቃድ ከነበራቸው ጠንካራ አቋም ይመለሳሉ ብየ ስላሰብኩ ነው፡፡
አላህ ሁላችንንም ወደሐቁ መስመር ይምራን!
📝 ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዘሁሏህ
https://t.me/AbuImranAselefy/5069