የግድቡን ሙሌት ለማዘግየት የምንስማማ ከሆነ ታሪካዊ ስትራቴጂካዊ ስህተት ነው የሚሆነው። ይቺን ጊዜ ካለፈ የግብጾች levarage እየጨመረ ስልሚሄድ እነሱ በሚፈልጉት ፍጥነት እና ይዘት ብቻ የሙሌት ሂደቱን እንድናካሂድ ልንገደድ እንቻላለን። በተጨማሪም ስምምነት መድረስን እንደቅድመ ሁኔታ የምንቀበል ከሆነ መሌት መጀመሩንና አጠቃላይ ግድቡን ለግብጽ እምቢተኝነት እስረኛ (hostage) እንዲሆን መፍቀድ ነው።