Õfflçlàl❤lu💕


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


Jøiñ mã chãnñêl😍
Shøw mã pîç😘vídêø ñéw
Sõñg ñ
Mà❤

Fríeñd pîç 👬👭👫💑
jøín😘 jöiñ😍jòìñ😇jòïñ
@lulucuti

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


❤️"የደሀ ልጅ ፍቅር"❤️

ክፍል 2
በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,
ክረምት አልቆ መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋ አዲስ አመት
ተጀመረ የማትሪክም ውጤት መጣ .በሚገርም ሁኔታ በከፍተኛ
ደረጃ ነበር ያለፍኩት .ደስ የሚል ዜና እናቴ ይሄንን ስትስማ
የሚሰማትን ደስታ ሳስብ በጣም ተደሰትኩ .,ሜላትም አልፋለች
በከፈተኛ ውጤት ባይሆንም ጥሩ ሰርታለች ሁለታችንም ተደሰትን
ኦ አምላኬ ነገን አንተ ታውቃለህ አልኩ በልቤ!!
ሜላቴ እናቴጋ መሄድ አለብኝ አልኳት አብረን እንሂድ አለችኝ እሽ
ብያት እናቴ ጋ ሄድን እናቴ ገና ከውጪ ስታየኝ ፊቴ በደስታ
መሞላቱን ስታይ እልልታዋን አቀለጠችው ተንበርክካ ጌታ ሆይ
አንተ ታውቃለህ አለች!!የደስታ እንባ በጉንጮቻ ላይ ኮለል ብለው
ወረዱ እኔም ተንበርክኬ እናቴን አቀፍኳት በደስታ ተላቀስን ,"እናቴ
ገና አኮራሻለው"አልኳት በጆሮዋ የደስታ እንባ እየተናነቀኝ,.
ሜላት ፍዝዝ ብላ የሚሆነውን ሁሉ ታያለች እሷም ግን በቁሟ
እንባዋ ይወርድ ነበር ,እኔና እናቴ ተቃቅፈን ተነሳን እናቴ በቃ
ቤተክርስትያን ተሳልሜ ልምጣ ገብርኤል ስለቴን ሰምቷል ብላ
ነጠላዋን አንጠልጥላ ከቤት ተመስገን ተመስገን!!እያለች ሄደች
,ናቲ ,"አይገርምህም እኔም እንዳንተ ጅግና ነው የምሆነው"ብሎ
መጥቶ ተጠመጠመብኝ .,ጎበዝ እንደዚህ አስብ እሽ ብዬው
መጣሁ እዚሁ ሁን ብዬው ሜላትን ልሽኝ ወጣሁ,.
ሜላት የሆነ ነገር ውስጧን እየከነከነው ነው ግን ምን እንደሆን
አላውቅም.ወደ ኪሷ ገብታ 20 ብር አውጥታ እንካ አለችኝ ምን
ላድርገው አልኳት ካፌ ገብተን ትንሽ እናውራ አለችኝ እሽ
አልኳትና ብሩን ወደ ኪሴ ከተትኩት.,
ካፌ ገብተን ሻይ አዘዝን ታውቃለህ ፍቅሬ የናንተ ቤተሰብ በጣም
ያስቀናል አለችኝ መሬት መሬት እያየች .እኔ አሁን እቤት ስገባ
ማለፍና መውደቄን እንኳን አልጠየቅም እንኳን ይሄን ያክል ፍቅር
ላይ ይቅርና አሰቀንታችሁኛል አለችኝ እንዳቀረቀረች,.እኛ ቤት
ንፁህ ፍቅር እንዳለ አውቃለው የሷን ስትነግረኝ ግን ግራ
ገባኝ.,ብቻ በፍረሀት ለምን?አልኳት .እ!አለች,.እኛ ቤት ማንም
ስለምይንም አይጨነቅም ትማራለህ ካልተሳካልህ የፈረደበት
የአባቴ ካንፖኒ አለ እዛ ትገባለህ በቃ ይሄ ነው አለችኝ በንዴት,.
አሁን ደግሜ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ዝም አልኩ
ለማንኛውም እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት የሰጠችኝን ብር ከኪሴ
አውጥቼ ከፍዬ ከካፌው ወጣ እሷን ታክሲ አስይዜ ቻው ተባብለን
ተለያየን,.
ወደ ቤት እየተመለስኩ ብዙ ነገሮችን አሰብኩ ለምን ቤተስብ
ፍቅር የለውም ,ለነገሩ ገንዘብ ስላላቸው ባይማሩስ ሜላትም
ዝም ብላ ነው የምትደክመው ምናለ እኔ የነሱ ቤተሰብ በሆንኩ.,!
አይ ተመስገን እንኳንም አልሆንኩ የእናቴ ፍቅር ከገንዘብ በላይ
ነው ::እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ .,እቤት ስደርስ እናቴ ብና አቀራርባ
ሻማ ገዝታ ጠበቀችኝ ደስ አለኝ ,"እናቴ እወድሻለው"ብዬ
ግንባሯን ስሜ ተቀመጥኩኝ.,
እናቴ ደስ ስላላት ደስ ብሎኛል,በቃ እናቴ ከዛም ከዛም ብላ
ያጠራቀመቻትን ብር ሰብስባ ዬኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ ሜላት
ዬኒፎርሙን ቀድማ አሰፍታ አመጣችልኝ በጣም ሰነገጥኩ እኔ
ከዚህ በላይ እንድትረጂኝ አልፈልግም አልኳት,ሜላት ግን በቃ
እሽ ብላ ዬኒፎርሙን ሰጥታኝ ከቤት ቻው ብላ ሄደች.እናቴ
ደነገጠች እኔም ተከትዬ ሳልሸኛት ፈዝዤ ቀረሁ..........
✍✍✍ይቀጥላል✍✍✍.....

ከወደዱት ሼር እና ላይክ👍 ያድርጉ
:*:*:*:*:*🌺:*:*🌹:*:🌺*:*:*:*:*:*:
••●◉Join us share @Yfiker_Sawe
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
...📩 @Hena_251




❤️"የደሀ ልጅ ፍቅር"❤️

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,::
ክፍል 1
ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግሁት ስም የለውም ማለቴ አዲስ
አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ ነው አባቴን
አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም እንድ ወንድም አለኝ
ናቲ ይባላል,ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ
ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት
አልፈልግም ትላለች ,
እናቴ ያገኝችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ
ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ መልስ
ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ
ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ
መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ
ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር
ትፈልጋለች ,
በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት
አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች
የ 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም
አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም
የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ
ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው ከትምህርት ቤት እምደተመለስክ
የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ
ግዴታዬ ስለሆነ,.
በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት
አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ
ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም
አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ
ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ,
እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን
የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን
ሀብታሞች,የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ
አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን
ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር ክንፍ ብለናል,
የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት በደረጃና
በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን
አላማና ፍላጎት ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን
ማትሪክ ተፈተንን,ሁለት ወር ክረምትን ሜላት ከቤት ብዙም
መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን
ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን
ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን
ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች
ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም
ብቻ ተመስገን ነው .
ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዬ ልብስም እቃም ታመጣለች
የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት
ግን አልፈልግም እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር ዝም
የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት
መጣ,.......
✍✍✍ይቀጥላል✍✍✍.....

ከወደዱት ሼር እና ላይክ👍 ያድርጉ
:*:*:*:*:*🌺:*:*🌹:*:🌺*:*:*:*:*:*:
••●◉Join us share @Yfiker_Sawe
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
... 📩 @Hena_251


Selam wdoche wddrun edemtayut aguwagi new wddru eskiyalk 1 des yamil tarik engemralen tarikun tewedutalachu bye tesfa adergalew





😘😘😘😘😘😘






Wddrun edu bamare huneta tegemruwal lehulum fkregamoch melkam edl demo ayleyachu







😘😘😘😘😘😘😘😘



























20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

288

obunachilar
Kanal statistikasi