እግዚአብሔርን አመስግኑ dan repost
*ፈጣሪህን እግዚአብሔርን አስብ*
መክ 12:1-7
✝️ *ታላቁ የእግዚአብሔር ሰው ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ እንዲህ ብሎ መከረን፣*
ማስተዋሉን ያድለን
መክብብ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ *የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤*
² *ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፤*
³ *ቤት ጠባቆች በሚንቀጠቀጡበት፥ ኃያላን ሰዎችም በሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች ሆነዋልና ፈጭታዎች ሥራ በሚፈቱበት፥ በመስኮትም ሆነው የሚመለከቱ በሚጨልሙበት፥ በአደባባይም ደጆቹ በሚዘጉበት ቀን፤*
⁴ *የወፍጮ ድምፅ ሲላሽ፥ ከወፍ ድምፅ የተነሣ ሰው ሲነሣ፥ ዜማም የሚጮኹ ሴቶች ልጆች ሁሉ ዝግ ሲሉ፤*
⁵ *ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፤ ሰው ወደ ዘላለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤*
⁶ *የብር ድሪ ሳይበጠስ፥ የወርቅም ኵስኵስት ሳይሰበር፥ ማድጋውም በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፥ መንኰራኵሩም በጕድጓድ ላይ ሳይሰበር፥*
⁷ *አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።*
✝️ *እናም አፈር የተባለ ሥጋችን ወድ አፈርነት ሳይመለስ፣ ነፍሳችን ደግሞ ወደ አስገኚው ወደ እግዚአብሔር በሞት ሳይመለስ እባካችሁን እግዚአብሔርን እናስብ።የሰንበት ጌታ እርሱን እስበን በየሰንበቱ ከቤተሰቦቻችን ሁሉ ጋር ቤተ እግዚአብሔር ሄደን እንድናስበው ይፍቀድልን።*
✝️ *ብሩህ ሰንበት* ✝️