የሰራህበት ያፈራል!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ከጥረትህ ጀርባ የሚፈካ ብረሃን፣ የሚያፈራ ተክል፣ የሚያብብ አበባ አለ። አርፈህ ብትቀመጥ በቀጣይ የሚገጥምህን ህይወት መገመት አይከብድህም፤ ጠንክረህ ብትሰራ የት መድረስ እንደምትችል ብዙ አይሰወርብህም። እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የሚያስከትለው ውጤት አለው። ጠንክሮ መስራት፣ በቸልተኝነት መስራት፣ ምንም አለመስራትም እንደየደረጃው የእራሱ ውጤት አለው። ይብዛም ይነስም ያለምንም ትርፍ የሚባክን ጉልበትም ሆነ ገንዘብ አይኖርም። ተቀምጠህና ተነስተህ ተመሳሳይ ስፍራ ላይ አትደርስም፤ አቅደህና ያለእቅድ እየተጓዝክ ለተመሳሳይ መዳረሻ አትበቃም። ምንም ብትዘራ እንደ እንክብካቤህና በሚያገኘው ግብዓት ልክ የተዘራው ፍሬውን ይተካል። ዓለም የምትመራው ሰጥቶ በመቀበል መርህ ነው። ህይወትም ምልልሷ በዓለም ነውና ከዚህ መርህ ውጪ መሆን አትችልም።
አዎ! ጀግናዬ..! የሰራህበት ያፈራል፤ የደከምክበት ይከፍልሃል፤ የተፋለምክለት ለድል ያበቃሃል። ከልብ መስራትና እንደነገሩ መስራት፣ በስሜት መኖርና በሃሳብ ብቻ መመላለስ ልዩነታቸው እጅግ ግዙፍ ነው። ከማንነትህ የተዋሃደ ስራ በምንም መስፈርት ቢመዘን ሊወድቅም ሆነ ዋጋ ሊያጣ አይችልም። አንተነትህ በእራሱ ሀይልና ብርታት ይሆነዋል፤ ጉልበትና ገንዘብ ይሆነዋል። ማቆምህ ሳይሆን አንድ ቀን መዝለልህ ሙሉ ስሜትህን ይቀያይረዋል፤ ከልብህ መነሳቱና ከማንነትህ ጋር መቆራኘቱ ፍሬውን ጣፋጭ፣ ውጤቱንም አርኪ ያደርገዋል። በማሰብ፣ በማውጣት በማውረድ፣ በማመዛዘን ስታውቅውና በስሜት በልብህ ስትረዳው ምንም ነገር ልዩነት መፍጠሩ አይቀርም። የተሰጠህ ስጦታ ለፍሬ እንዲበቃ መትጋት ከምንም በላይ ቀላልና ብዙ ጥረትን የማይጠይቅ ነው።
አዎ! የሚሰበሩ ህግጋቶች የመኖራቸውን ያክል በቆራጥነት ልንመራባቸውና ወደፊታችንን ልናስተካክልባቸው የምንችላቸው ወሳኝ ህግጋቶች አሉ። የዘራሀውን ታጭዳለህ፤ በስራህ ልክ ይከፈልሃል፤ ከፈለከው በላይ የሆንከውን ትስባለህ። ታታሪነት ፈልገህ አልማጭ፣ አላጋጭ ሰራተኛ ብትሆን ስለፈለከው የሚመጣ ታታሪነት ሳይሆን ስለሆንከው የሚዋሃድህን አልማጭነት ታተርፋለህ። ህይወት ትመራሃለች ወይስ ህይወትህን ትመራታለህ? በስሜት ትኖራታለህ ወይስ በስሌት ትገፋታለህ፣ ችግሯን ብቻ ትዘረዝራለህ፣ ክፍተቷን ብቻ ትመለከታለህ? ፈልገህ ታመሰግንባታለህ ወይስ በምርጫህ ታማርርባታለህ? ብትወድቅ በውሳኔህ የታገዘው ምርጫህ ይጥልሃል፤ ዳግም ብትነሳም በብርቱ ውሳኔ የታገዘው ምርጫህ ያነሳሃል። ታታሪነትን ለመምረጥ፣ ጠንካራ ለመሆን፣ ወደፊት ለመራመድ፣ በተስፋ ለመሞላት፣ በጥረትህ ለማመን፣ በአምላክህ ሃይል ለመተማመመን ከምንም ጊዜ በላይ የፈጠንክ ሁን። በመረጥከው ልክ የሚመጣውን ከልብህ ተቀበል፤ ወሳኙን ተግባር እንደ ወሳኝነቱ፣ አስፈላጊውንም እንደ አስፈላጊነቱ ከውነው። ህይወት በመረጥከውና በሆንከው ነገር ልክ በአስደሳች ውጤት እንድትከፍልህ አድርግ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikreaimro 😊 💪