ማንንም አይጠብቅም!
፨፨፨፨////////////፨፨፨፨
የሆነ ጊዜ ይረፍዳል፤ ሁሉም ያበቃል፣ የጀንበሯ ብረሃን እየጠለቀ ይመጣል፣ ሰውነት ይዝላል፣ አቅም ያንሳል። ልክ እንደ ዛሬው መሮጥ መጫወት ከባድ ይሆናል። ጊዜ ማንንም ቆሞ አይጠብቅም። እኛ ብንቆም ባንቆም፣ እኛ ብንሰራ ባንሰራ፣ እኛ ብንሞክር ባንሞክር የጊዜው ሂደት አይቆምም። ሰከንዱ፣ ደቂቃው፣ ሰዓቱ፣ ቀናቱ፣ ሳምንታቱ፣ ወራቱ፣ አመታቱ እያንዳንዳቸው በተለመደው ፍጥነታቸው እየቆጠሩ ነው። ዛሬ ለቆመ ነገ የመርፈዱ ነገር ሳይታለም የተፈታ ነው፣ ዛሬ ለሰነፍ ነገ የቁጪቱ ቀን መሆኑ ግልፅ ነው። ቀናት ይቀያየራሉ እናንተም አብራችሁ ካልተቀየራችሁ ግን ቆማችሁ እንደቀራችሁ እወቁ። ጊዜውን መቅደም ባትችሉ እንኳን ከጊዜው ጋር ለመራመድ ሞክሩ፤ ቁጭ ብላችሁ ከምታማርሩ የቻላችሁትን ሁሉ አድርጉ። ካላችሁ ሌላ እንዲመጣላችሁ አትጠብቁ፣ ዛሬ በእጃችሁ ያለ ሁሉ ነገር ስጦታችሁ ነው። ጊዜን የመሰለ ትልቅ ስጦታ ደግሞ የላችሁም። ጊዜያችሁን ተጠቀሙ፣ በስጦታችሁ አትርፉ፣ ከገፀበረከታችሁ ተቋደሱ። ጊዜ ላዘኑለት ያዝናል፣ ለጨከኑበትም በብዙ እጥፍ ይጨክናል።
አዎ! ማንንም አይጠብቅም! እርሱ ፍተሃዊ ዳኛ ነው። ለጥቂቶች አዳልቶ የሚዘገይ፣ በጥቂቶችም ጨክኖ የሚፈጥን አይደለም። ጊዜ ሳያዳላ ይፈርዳል። በአግባቡ የተጠቀመውን ይሸልማል፣ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ ያሳለፈውንም በሚገባ ይቀጣል። በጊዜ አለንጋ ከመገረፍ ራሳችሁን ጠብቁ። ሳቁ፣ ተጫወቱ፣ አሹፉ፣ ቀልዱ ነገር ግን በፍፁም በውድ ጊዜያችሁ አታሹፉ፣ በፍፁም ትልቁን ስጦታችሁን አታዋርዱት። ራሳቸውን የገዙ፣ ስሜታቸውን የተቆጣጠሩ፣ ስራቸውን በአግባቡ የሰሩ፣ ሁሌም ከዛሬያቸው የሚያተርፉ ሰዎች ጊዜ ጌታ ያደርጋቸዋል፣ ክብር ላይ ክብርን ፀጋ ላይም ፀጋን ይጨምርላቸዋል። በምትኩ በህይወታቸው ያረፈዱትን፣ ጊዜያቸውን በስንፍና የጨረሱትን፣ ሲበዛ ግዴለሽና ደንታቢስ ይሆኑትን፣ አቅማቸውን በዋዛፈዛዛ ያባከኑትን የስራቸውን ይከፍላቸዋል፣ ባይፈልጉትም በግድ ይቀጣቸዋል፣ እንደተጫወቱበት በተራው ይጫወትባቸዋል፣ አንገት ያስደፋቸዋል፣ አሸማቆ ወደ ኋላ ያስቀራቸዋል።
አዎ! ጀግናዬ..! የጊዜ ተጠቂ አትሁን፣ አይንህ እያየ ጀንበር አታዘቅዝቅብህ፣ በየትኛውም መንገድ እንዲረፍድብህ አትፍቀድ። አትቁም ተንቀሳቀስ፣ አትፍዘዝ ነቃ በል፣ አየር አትምረጥ ባለው አይር ብረር፣ አትስነፍ እንደ አቅምህ ዞር ዞር በል። እንደሚባለው ቀላል ላይሆን ይችላል ነገር ግን ማድረጉ የግድ ነው። ህይወት ትቀል ዘንድ ከባባድ ውሳኔዎች መወሰናቸው ብሎም በተግባር መገለጣቸው የግድ ነው። ውድድርህ ሊሰበር ከሚችለው ሰው ጋር አይደለም፣ ውድድርህ ለአፍታ ብትዘገይ በብዙ ርቀት ጥሎህ ከሚሄደው ጊዜ ጋር ነው። አትዘናጋ። ነገ ላይ ሆኖ ለዛሬ ማልቀስ የሚቀይረው ነገር እንደማይኖር እወቅ። ሁሌም ቢሆን ዓለም የአሸናፊዎች ነች። ጊዜህን ተጠቅመህ አሸንፍ፣ በሰዓቱ ከፍ ብለህ ታይ፣ እንደ ወቅቱ ተንቀሳቀስ። መጣል ያለብህን ሸክም ጣል፣ አየሩን ተቆጣጠረው፣ በቻልከው ከፍታ ለመብረር ሞክር። አንገት ደፎቶ ማላዘን ምንም ቀይሮ አያውቅም። የተሻለ ህይወት ለመኖር ጨከን በል፣ ስጦታህን በአግባቡ ተጠቀም፣ በፍፁም ውድ ህይወትህ ሲባክን ቆመህ አትመልከት።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪