ተገማች አትሁኑ!
፨፨፨///////፨፨፨
ሀሳባችሁ መሪነት እንጂ ተመሪነት ካልሆነ ተገማች አትሁኑ፤ ፍላጎታችሁ ስኬት እንጂ ውድቀት ካልሆነ ተገማች አትሁኑ፤ እቅዳችሁ ትልቅ እንጂ ትንሽ ካልሆነ ወርዳችሁ አትገኙ። ሰዎች ተገማች ሰውን በቀላሉ ያውቁታል፣ በሚያውቁት ልክም ከእርሱ ይጠነቀቃሉ ወይም በቀላሉ ጠብቀው ያጠቁታል ብሎም ይጠቀሙበታል። ብዙ ሰው ስለእናንተ ብዙ ነገር የሚያውቅ ከሆነ፣ መግቢያ መውጫችሁ ለሰው ሁሉ ግልፅ ከሆነ፣ ሁሌም እዩኝ እዩኝ የምትሉ ከሆነ፣ እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችሁን ለሰው የምታሳውቁ ከሆነ ያለምንም ጥርጥር ይሔ ባህሪያችሁ ብቻ አንድ ቀን ከከፍታችሁ አምዘግዝጎ ይጥላችኋል። ተደብቆ መኖርን የመሰለ ነፃነት የለም። ድብቅነታችሁ ግን እንደ እድገታችሁ መጠን ይወሰናል። ጠንክራችሁ ከሰራችሁ፣ አቅማችሁን ካጎለበታችሁ፣ ስማችሁን በጥሩ ነገር ካስጠራችሁ፣ አካባቢያችሁን የእኔ በምትሏቸው ሰዎች ካጠራችሁ በእርግጥም በጥቂቱ ብትገመቱም ለጥቃት ግን ተጋላጭ አትሆኑም። እናንተ ራሳችሁን ካልጠበቃችሁ ማንም ሰራዊት አቁሞ፣ ዞሪያችሁን ከቦ አይጠብቃችሁም። ማን ማንን ሲንቅ አይታችኋል? በእርግጥም ከልክ በላይ መተዋወቅ ያናንቃል፣ ድንበር አልባ መቀራረብ ያስጠቃል።
አዎ! ተገማች አትሁኑ! ማንም ሰው ተነስቶ ስለእናንተ ማውራት የሚል፣ ለማንም ሰው ክፍት የሆነ የህይወት ዘይቤ ያላችሁ አይነት ቀሊል ሰው አትሁኑ። ድል አድራጊነት ዋናው መሰረቱ ያልታየ ስራ ነው። ልታይ ልታይ ሲሉ የነበሩ ስንቶች ከእይታ ጠፍተዋል? "ያለእኔ አዋቂ የለም፣ እኔ ነኝ ጎበዝ፣ እኔ ነኝ ጠንካራው" ሲሉ ከነበሩት ስንቶች እኔነታቸው ማንነታቸውን አሳጥቷቸዋል? ስብዕናቸውን አናግቶታል? ሰዎች ስለእናንተ ያውቁ ዘንድ የግድ እናንተ መናገር ያለባችሁ ደረጃ ላይ ካላችሁ ገና ናችሁና ከማውራታችሁ በላይ ስራችሁ ላይ ብቻ አተኩሩ። ገና ፈታኙን የለውጥ ጉዞ ከመጀመራችሁ ተደነቃቅፋችሁ እንዳትወድቁ እያንዳንዱን እርምጃችሁን እየመጠናችሁ ተራመዱ። ታላቅነት ዋጋ አለው። ትልቁ ዋጋውም ዝምታ ነው፣ ፀጥታ ነው፣ ተደብቆ፣ ከብዙዎች ተሸሽጎ፣ ውስጥ ውስጡን ራስን ማብቃት ነው። የሆነ ጊዜ ቀን እንደሚወጣላችሁ፣ አንድ ቀን የተመኛችሁትን ስኬት በእጃችሁ እንደምትጨብጡ ካመናችሁ ለአላፊ አግዳሚው ገመናችሁን ማጋለጥ አቁሙ፣ እዚም እዛም የማይረባ ስፍራ መገኘት አቁሙ፣ ከነዚህ ከነዛም ጋር መዘባነን አቁሙ። ህይወታችሁን አሁኑኑ መስመር አስይዙ። በወዳጅ ሰበብ በጠላት ተከባችሁ ስላለመሆኑ እርግጠኛ ሁኑ።
አዎ! ጀግናዬ..! ዙሪያህን በአደገኛ አጥር በማጠርህ ሰው ስለሚሰጥህ ስም ሳይሆን አንተ ስለምታገኘው ነፃነት አስብ፤ ሰው ስለሚያደርስብህ ጫና ሳይሆን አንተ ስለምታገኘው ብርታትና ጥንካሬ አስብ። ያንን ጊዜ አስታውስ። ማንም ከጎንህ ሳይኖር በፈጣሪህ እገዛና ባንተ ብርታት ብቻ የሰዎችን የምቀኝነት መረብ የምትበጥስበትን ጊዜ፣ የታሰበልህን ክፉ ሀሳብ ተሻግረህ የምትሔድበትን ጊዜ። በጣም የተባረከና ልቡ በጥሩ መንፈስ የተሞላ ወዳጅ ካልሆነ በቀር በዚህ ዘመን ጥሩ የሚያስብልህ ሰው አታገኝም። ሁሉም ተጠላልፎ ለመውደቅ የማያደርገው ጥረት የለም። አንዱ ሌላኛው እንዲያልፍለት አይፈልግም፤ የአንዱ ውድቀት ለሌላው ስኬት ይመስል ሁሉም እርስበእርስ መሰናክል ለመሆን ይጠባበቃል። "ጠላቴን እኔ ጠብቀዋለሁ፣ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ" የተባለው በምክንያት ነው። ከወዳጅ መሳይ ጠላት ትድን ዘንድ በዋናነት ፀልይ በመቀጠል ግን በቀላሉ የምትገመት፣ የምትታወቅ ሰው አትሁን። ማንም ሰው የሚዳፈረው የሚያውቀውን ሰው እንደሆነ አስታውስ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪