ድፍረትና ቆራጥነት!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ምኞትን ወደ እውነት፣ ህልምንም ወደ ስኬት መቀየር የሚችሉ ወሳኝ መሳሪያዎች ድፍረትና ቆራጥነት ይባላሉ። ብዙ አስቡ፣ በትልቁ አስቡ፣ አውጡ አውርዱ፣ ፍተሉ ጎንጉኑ፣ አውሩ አብራሩ የማድረጉ ድፍረትና የማስቀጠሉ ቆራጥነት ከሌላችሁ ግን ጥረታችሁ ሁሉ መና ነው። ዝምተኛ ሁኑ ተጫዋች፣ ጠንካራ ሁኑ ልፍስፍስ፣ አዋቂ ሁኑ አላዋቂ ድፍረትና ቆራጥነት ከሌላችሁ ግን አሁንም ያላችሁ ነገር በሙሉ ዋጋ ቢስ ነው። አዋቂው እውቀቱን ሰው ፊት ቆሞ ያካፍል ዘንድ ድፍረትና ቆራጥነት ያስፈልገዋል። ህልመኛው ህልሙን ይኖር ዘንድ ብሎም ያሳካው ዘንድ ፍረሃቱን አርቆ ጥሎ ድፍረትን መላበስ፣ ከጅማሬውም ቦሃላ ከዳር ለማድረስ ወደኋላ የማይመልሰው ፅኑ ቆራጥነት ያስፈልገዋል። ደፋሮችና ቆራጦች ሽንፈትን አያውቁም። ድፍረታው ለውድቀት ቢያጋልጣቸው ዳግም የመነሳት ብርታቱ አላቸው፣ በቆራጥነታቸው ሌላ የሚያጡት ነገር ቢኖር ለእርሱ ሃላፊነት ይወስዳሉ። አደጋን አይፈሩም ይባሱን ተጋፍጠውት ያልፋሉ፣ ወሬ አያሰናክላቸውም ይልቅ እልህ ውስጥ ያስገባቸዋል።
አዎ! ድፍረትና ቆራጥነትን ተላበሱ። በራሳችቹ ተማመኑ፣ ከልባችሁ ወስኑ፣ መለወጥ ያለበትን የህይወታችሁን ክፍል ቆርጣችሁ ለውጡት። የፈለጋችሁትን የትኛውንም በጎ ነገር ከማድረግ ማንም የማያስቆማችሁ ቆራጥ ሰው ሁኑ። ከፊቱ አደጋ ቢጋረጥበት፣ ሰዎች ቢተናኮሉት፣ ያለውን ነገር ሁሉ ቢያጣ፣ በህይወቱ ያልጠበቀው ነገር ቢከሰት፣ ብዙ ተቃውሞ ቢደርስበት፣ ፍረሃትና የበታችነት ደጋግመው ቢፈትኑት እንኳን ካመነመት ፍንክች የማይል፣ ጀግኖ የሚያስጀግን፣ ደፋር ሆኖ የሚያደፋፍር፣ ቆሮጦ የሚያስቆርጥ ሰው ሁኑ። ብዙ ሰው የፍረሃቱ ባሪያ ሆኗል፣ መሬት ላይ ሆኖ ከመሬት ላለመውደቅ እየተጠነቀቀ ዘመኑን ይፈጃል፣ የሚፈልጋትን ዓለም መቼም ፈጥሮ ሊኖርባት እንደማይችል እያሰበ በተገደበች ዓለም ውስጥ በጭንቀት ይመላለሳል። ትናንትም ዛሬም ነገም ውጤት አምጪው በድፍረት የተጀመረውና በቆራጥነት ውጤት የሚያመጣው ስራና ስራ ብቻ ነው። ማንም አያስቆመኝም ብላችሁ መስራት የጀመራችሁ ቀን የሚያስቆማችሁን ሳይሆን የሚቆምላችሁን ወዳጅ ታገኛላችሁ።
አዎ! ጀግናዬ..! የመጣው ይምጣ፣ ያጣሀውን እጣ ህይወትህ እስካለ ድረስ ዘመንህን በሙሉ ጥግ ላይ በጭንቀት እየኖርክ አታሳልፈው። ከኮርነሩ ውጣ፣ ከማይመችህ አጣብቂኝ ተላቀቅ፣ ራስህን ወደፊት ግፋው፣ ከአካላዊውና ከአዕምሮው እስራት መንጭቀህ አስወጣው። የዛሬው ህይወትህ እንደማይመጥንህ ካመንክ እምነትህን በተግባር ለመግለጥ አትፍራ። አቅም እያለህ እንደ አቅመቢስ፣ ተስፋ እያለህ እንደ ተስፋቢስ አትኑር። ወደኋላ ማፈግፈግን ተማር ነገር ግን በፍፁም በዛው እንዳትቀር። ከራስህ በላይ ለሰውም የሚተርፍ ወኔና ብርታቱ እንዳለህ አስታውስ። በፍረሃትህ ውስጥ ህይወት የለም፣ በጭንቀትህ ውስጥ ህይወት የለም። እየፈሩ መኖር ምንም ስለማይጠይቅ ብዙ ሰው እየኖረበት ነው። በድፍረትና በቆራጥነት የሚፈልጉትን እያደረጉ መኖር ግን ከክፍያው በፊት የሚያስከፍለው ዋጋ አለና ብዙዎች አይመርጡትም። ዛሬ መክፈል ያለብህን ዋጋ ክፈል ቦሃላም ልክ ቆንጆዋ ወፍ ነፃነትህን በልበሙሉነት አጣጥም።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪