ጥላቻን ተጠየፉ!
፨፨፨/////////፨፨፨
ሰው በሰውነቱ የሚጠላ ፍጡር አይደለም። ሰውነት በአምላክ መልክ በአምላክ መንፈስ ተፈጥሯልና ከቡር ነው። እንዲሁ የተዳፈነ ጥላቻ መጫወቻ እንዳያደርጋችሁ ተጠንቀቁ። ሰውነት አይጠላም፣ ሰውነት አይንቋሸሽም፣ ሰውነትን አይጠየፉትም። ለሁሉም ሰው ቀን የሚወጣለት ጊዜ አለ። ያለውን እየወደዳችሁ የሌለውን ለመጥላት አትንደርደሩ። ጥላቻ ወጥመድ እንደሆነ አስተውሉ። አንዴ ልባችሁ በጥላቻ ከታወረ፣ አንዴ ውስጣችሁ ሰውን መጠየፍ ከጀመረ ያ ሰው ምንም በጎ ምግባር ቢፈፅም፣ ያ ሰው ምንም የሚጠቅማችሁ ሆኖ ቢገኝ እንኳን ጥቅሙንና መልካም ስራውን መመልከት አትችሉም። ጥላቻ የእርኩስ መንፈስ ዋንኛ መሳሪያ ነው። ጥላቻን አንግባችሁ በሰላም መኖር አይደለም ጤነኛ ንግግር እንኳን መናገር አትችሉም። ሁሌም ቢሆን ሰው ጥፋት አለበት፣ ይስታል፣ ይወድቃል፣ ከእርሱ የማይጠበቅን ተግባር ይፈፅማል። ቢሆንም ግን ጥላቻ ከክፉ ተግባሩ ሊመልሰው ወይም ሊያስተምረው አይችልም።
አዎ! ጥላቻን ተጠየፉ! በወጥመዱ አትውደቁ፤ ሀሳባችሁን ሁሉ መና አታስቀሩት። ጥላቻ ባለበት ሁሉ በቀልን የመሰለ ክፉ ተግባር መኖሩ አይቀርም። በገዛ ፍቃዳችሁ ነፍሳችሁን አታስጨንቋት፣ በቂም በበቀል፣ በጥላቻ በንቀት አታርክሷት። ነፍስ ነፃ ካልወጣች ህይወትም እንዲሁ ነፃ ልትሆን አትችልም። አቅም አላችሁ ነገር ግን አቅማችሁን ጥላቻ ለተባለ ክፉ መንፈስ መሳሪያ አታድርጉት። ሰው ይበድላችሁ፣ ሰው ይጉዳችሁ፣ ሰው ያሰቃያቸሁ እናንተ ግን በፍፁም ሰውየውን ለመጉት እያሰባችሁ በጥላቻችሁ ዳግም ራሳችሁን አታስጨንቁ፣ ለጉዳዩ ቦታ እየሰጣችሁ ይበልጥ መጠቀሚያው አትሁኑ። ጊዜ ፈራጅ ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ያያል ሁሉንም ያውቃል። የደረሰባችሁን በደል፣ ጉዳታችሁን፣ ህመማችሁን፣ ስቃያችሁን ሁሉ ያያል ያውቃልም፣ በጊዜውም ምላሽ ይሰጠል። ሁሉን ለርሱ ትታችሁ ውስጣችሁን ማጥራት ተለማመዱ፣ የሆነባችሁን መቁጠር አቁሙና ልባችሁን በፍቅር ሙሉት። ለመገፋት መገፋትን አትመልሱ፣ ለመጠላት ጥላቻን አትመልሱ። ለራሳችሁ ደህንነት ብላችሁ ከፍ ብላችሁ ተገኙ፣ ለገዛ ጥቅማችሁ ሁሉን በፍቅር ለመያዝ ካልሆነም እርግፍ አድርጋችሁ ለመተው ሞክሩ።
አዎ! ጀግናዬ..! የሆነው ሆኖ አንተ ግን ዛሬም የሆነውን እያብሰለሰልክ ልብህን የምታስጨንቅ፣ ጥላቻንም የምታንፀባርቅ ከሆነ ከሆነብህ በላይ የጎዳህ አንተ ራስህ እንደሆንክ አስተውል። ጥላቻ ጥላቻን አሸንፎ አያውቅም፣ ቂምና በቀልም ጥፋትን ሽሮ አያውቅም። የመጣብህን መከራ፣ የደረሰብህን በደል በዝምታ ቻለው፣ ተቀበለው። ፈጣሪ የሚሰጥልህን ምላሽ በትዕግስት ጠብቅ። በራስህ ሸንጎ ለመፍረድ አትሞክር። አንዳች ያለምክንያት የሚሆን ነገር ያለ እንዳይመስልህ፣ አንዳች በከንቱ የሚከወን ተግባር ያለ እንዳይመስልህ። ሁሉ በምክንያት ይሆናልናል በሆነ ባልሆነው ለመበቀል አትሯሯጥ። ስሜትህን ግዛ፣ ጥላቻ እንዲነግስብህ፣ ምቀኝነትም እንዲጫወትብህ አትፍቀድ። ዛሬ ባይሆንም እያንዳንዱ በሰው ላይ የምታደርገው ነገር ተመልሶ እንደሚከፍልህ አስታውስ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪