ለምን አሉታዊነትን?
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ሰውነት ሚዛን እያለው፣ መልካም ማሰብና ማድረግ እየቻለ፣ ለሰዎች ጥሩ መፈፀም እየቻለ ግና በአሉታዊነት ገመድ ታስሮ እራሱን ጥሎ ሌሎችን ለማሰናክልና ለመጣል ይደክማል። አሉታዊነት ቢጎዳ ቀዳሚው ተጎጂ አንተ ነህ፣ አዎንታዊነት ቢጠቅም ቀዳማዊው ተጠቃሚ አንተ ነህ። ለማንም ለምንም ብለህ ሳይሆን አሉታዊና እንቅፋት ከመሆን ይልቅ ዝም የማለት ምርጫም አለህ። ያንተ ውድቀት ሳያንስ ሌላውንም ወደ ውድቅት ለመሳብ አትድከም። መደጋገፍን፣ መረዳዳትን፣ መበረታታትን የመሰለ መልካም ምግባር እያለ ስድብን፣ ነቀፋን፣ ክፋትን መምረጥ የምትወድቅበትን ጉድጓድ ቢያርቀው እንጂ በህይወትህ አንዳች የሚጨምርልህ ነገር አይኖርም። አንድ ሰው በገዛ ፍቃዱ ፈልጎና መርጦ ያደረገውን ነገር ግዴታ የመውደድና የማድነቅ ግዴታ የለብህም፤ እንዲሁ ባንተ የእሳቤ ደረጃና አቅጣጫ እንዲፈፀም መጠበቅ አይኖርብህም። አንተ ባትችል የሚችሉት ችለው፣ አድርገው ቢገኙ የምታጣው ነገር ምን ይሆን?
አዎ! ጀግናዬ..! ለምን አሉታዊነትን? ለምን ክፋትን? ለምን ስድብን? ለምን ነቀፋን? ለምን ሰዎችን በሚያደናቅፍ መንገድ መታወቅን ፈለክ? መጥፎ፣ ጎጂና አጥፊ ስሜት ሆኖ ሳለ ስለምን ከዝምታና ከአዎንታዊነት፣ ደግ ከማሰብ እርሱን መረጥክ? የሚገነባህ አዎንታዊነት ሆኖ ሳለ ስለምን በሚያፈርስህ አሉታዊነት ትመላለሳለህ? የሚጠቅምህ መልካም ማሰብ ሆኖ ሳለ ስለምን ክፋትን መረጥክ? ሰላም ያለው፣ ፍቅር የሚነግሰው፣ መትረፍረፍ የሚመጣው በጥላቻ ውስጥ አይደለም፤ በሰው ውድቀት ውስጥ አይደለም፤ በአሉታዊነትና የሌሎችን ስሜት በመንካት አይደለም። የሰላም ምንጭ አዎንታዊነት ነው፤ ደስታ መገኛው መልካምነት ነው፤ የሃሴት ማደሪያ ቅንነት ነው፤ የመትረፍረፍ መሰረቱ ደግነት ነው።
አዎ! የሚጥረውን ስላበረታታህ፣ ለደከመው ብርታት ስለሆንክ፣ ተስፋ ላጣ ተስፋን ስለሰጠህ፣ በህይወት መንገዱ ድጋፍ ለሚፈልግ ድጋፍ ስለሆንክ የምታገኘው እንጂ መቼም የምታጣው ነገር አይኖርም። በህይወትህ የሚገለጠው በሰዎች ላይ የምታንፀበርቀውና የምታደርገው ነገር ነው። የሌሎችን ድካም መረዳት ከቻልክ ሁሌም ከጎንህ የሚቆም ሰው አታጣም፤ የድጋፍ እጅህን የማትሰስት ከሆነ ሁሌም የምትደገፈውን ከጎንህ ታገኛለህ። የማይወክልህን አሉታዊነት፣ የማይገልፅህን ክፍታ እንድታንፀበርቅ የሚያደርግህን ኢጎ (ego) ከእራስህ ላይ አስወግድ፤ ማንንም ከማይጠቅም ጭፍን ጥላቻና ምቀኝነት ውጣ። መልካም አስብ፣ መልካም አድርግ፣ በመልካም መንገድ ተመላለስ፣ የሚሰራን ደግፍ፣ የሚለፋን ከልብህ አበረታታ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪