ጎራችሁን ለዩ!
፨፨፨////፨፨፨
ኬትኞቹ ትሆኑ? ችሎታው ካላቻው፣ ስጦታው ከተሰጣቸው ነገር ግን የማሳደጉና የማሻሻሉ ረሃብ ከሌላቸው ወይስ ችሎታቸውን ለማወቅ፣ ስጦታቸውን ለመረዳት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እለት እለት ከሚፈልጉት፣ እለት እለት ራሳቸውን ለማሻሻል ከሚጥሩት፣ ስኬትና እድገትን ከተራቡት? ከቴኞቹ ናቸሁ? የትኞቹ ይወክሏችኋል? ተሰጥዖ ያለ ስራ ምንም እንደሆነ አስታውሱ። ተሰጥዖ ሲኖራችሁ ነገሮች ሊቀሏችሁ ይችላሉ፣ ከሌላው የተሻለ አፈፃፀም ሊኖራችሁ ይችላል በየጊዜው የማሻሻሉና የማሳደጉ ድፍረትና ተነሳሽነት ከሌላችሁ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰጥዖውን ሳያውቅ አንዱን የሚያስደስተውን ዘርፍ መርጦ ከሰራበት ሰው ያነሰ ህይወት ስትኖሩ ትገኛላችሁ። ምንም ውደዱ፣ ምንም ያስደስታችሁ፣ ምንም አይነት ስጦታ ይኑራችሁ ምንም ሳትሰሩ ከተኛችሁበት ግን ህይወታችሁ ወዴትም ሊቀየር አይችልም። አትዘናጉ፤ ባለተሰጥዖ መሆን የስኬት ዋስትና አይደለም፣ እውቀት የስኬት ዋስትና አይደለም። ዓለም ያልተማረ ሰው ችግር የለባትም፣ ምድር ተሰጥዖ የሌላቸው ሰዎች እጥረት የለባትም። ትልቁ እጥረት በተሰጥዖአቸው ላይ ጠንክረው የሚሰሩ፣ የተማሩትን የሚተገብሩ፣ ከልባቸው ለውጥና እድገትን የሚመኙ ሰዎች እጥረት ነው።
አዎ! ጎራችሁን ለዩ፤ ተሰጥዖ ኖሯችሁ ዛሬም ተኝታችሁ ከሆነ ተሰጥዖውን ከማያውቀው በምን ተሻላችሁ? ህይወት ለእናንተ ያዳላች ቢሆንም እናንተ ግን መደበኛውን ኑሮ ተላምዳችሁታል። ማሰብ፣ ማለም፣ ማቀድ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ማናችንም እናውቀዋለን። ሰርቶ ማሳየት፣ ተግብሮ በውጤት መገለጥ ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው። "እኔ ተሰጥዖ የለኝም፣ መክሊቴን አላውቀው" ማለት አሸናፊም ሆነ የተሻለ ምክንያት አቅራቢ አያደርግም። ሁሉም ሰው ወደ ህይወት ሜዳ ሲመጣ የሚለካው ባለው ተሰጥዖ ወይም በሚደረድረው ምክንያት ሳይሆን ሰርቶ በሚያሳየው ውጤት ብቻ ነው። እውነታው መረር ቢልም ሁሌም ጠንክሮ መስራት ተሰጥዖን በሚገባ ያሸንፈዋል። በተሰጥዖአችሁ የምትመኩ፣ መክሊቴ ይበቃኛል ብላችሁ ለተቀመጣችሁ መደበኛው የመካከለኝነት (mediocrity) ህይወት ተስማምቶኛል ካላላችሁ በቀር ከሳጥኑ ወጥታችሁ እንደማንኛውም ሰው የመታገል ግዴታው አለባችሁ። ምናልባትም የእናንተ ትግልና ድካም እንደ አብዛኛው ሰው ላይሆን ይችል ይሆናል እንጂ መታገላችሁ ግን የግድ ነው፣ መስራታችሁ የግድ ነው፣ ሌት ከቀን መጣራችሁ ግዴታ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ዓለም የጠንካራ ሰራተኞች ነች። የትም ቦታ ለሰነፍና ለሰበበኛ ቦታ የለም። አንገትህን ደፍተህ አቀርቅረህ ትሰራለህ ቀና ብለህ ደረትህን ነፍተህ በልበሙሉነት ትራመዳለህ። በምድር ላይ እንደ ስራ የሚያስከብር ምንም ነገር የለም። የናጠጥክ ሃብታም ብትሆን እንኳን ሃብትህን በውርስ ወይም በስጦታ ያገኘሀው እንደሆነ ሰረተህ እንዳመጣህ ሊያኮራህና ቦታ ሊያሰጥህ አይችልም። ምንም መመፃደት አያስፈልግም፤ እንዲሁ በባዶ ሜዳ ራስን ያለ ልክ አግዝፎ መመልከትም አያስፈልግም። መስራት ካለብህ ዝቅ ብለህ ስራ፣ የእውነት ህይወትህ እንዲቀየር ከፈለክ ትምክህትህን አርቀህ ጣለው። በዛሬው ውጤት አልባ ጥረትህ አትበሳጭ፣ ዛሬ በማትመለከተው ለውጥ አትናደድ። ዝም ብለህ ስራህን ስራ፣ ትኩረትህን ስራህ ላይ አድርግ፣ የመጨረሻውን አቅምህን ተጠቀም፣ እውቀትህን ሁሉ አንጠፍጥፈህ አውጣው፣ ስራህም በተሻለ አፈፃፀም ፈጣን ውጤት እንዲያመጣ አድርገው።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪