ጦቢያ ግጥምን በጃዝ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ጦቢያ ግጥምን በጃዝ is monthly poetry and jazz event happening were on first Wednesday of the month at Ras Hotel at 5:30 But as of the COVID-19 we are moved to Sky light hotel starting from 12:00 ቤተሰቡ ብቻ ሀሳብ ፣ አስተያየት ፣መረጃ የሚለዋወጥበት ቻናል።
Group-> @tobiyamisraktere

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


"ምኑ ነው ስህተቴ''
ደገመችው !!
(ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ)
===========
ተሳሳትሽ አትበለኝ የቱ ነው ስህተቴ፤
ጥበብ ነው ማርከሻ የብዕር ጥይቴ።
አዎ መንጋማ አለ ከጥንት መሰረቱ፤
እየሱስን አስረው በርባንን ሲያስፈቱ።
ዛሬም በኔ ዘመን
የመንጋ ፍርድ ነው ሀገሬን የፈታት፤
አዋቂ ዝም ብሎ መንጋ እየፈተታት።
በድንጋይ በርሚል ውስጥ ሽ ድንጋይ ቢቀቀል፤
ሽ ዘመን ተጥዶ እልፍ አመት አይበስል።
አገር ተረክቦ በሰፈረ የኮራ፤
የመንጋ ፍርድ አይደል ያበቃን ለተራ።
የቱ ጋ ነው የሳትኩ አርመኝ መምህሩ፤
ምላስክን አጥፈኽው ሞክር በብዕሩ።
ዘመን የሰጠው ቅል ድንጋይ ቢሰብር ጣሪያ፤
ማዕዘን ተደርጎ አይሆን ለቤት መስሪያ።
ሰውነት ነው ልኩ የሰው ሚዛን ፍርዱ፣
አዋቂ እንዲበይን መንጋዎች ይውረዱ።
አሁንም እላለው
በመንጋ ተፈጭቶ በመንጋ ተጋግሮ፤
እልፍ ጾም አዳሪ ወና ነው ጉረሮ።
ቤት መምታት ቤት መድፋት ስንኝ መቋጠሩ
ጥበቡ ቢያቅተው፤
ቤት እያፈረሰ ህዝብ እያስደደ
አገሩን አመሰው።
እኔ ይሄንን ሰው፣
ሌላ ምን ልበለው፣
መንጋነትም ሲያንሰው።
በባዶነት ሙሌት በዘር እብሪት ታስሮ፣
ከጥበብ ጓዳ ውስጥ ከሰውነት አጥሮ።
አበውን ሲያሰደድ ሲያርድ ሲያጎሳቁል፣
አንተም መንጋ ካልሆንክ መቼም ሰው ነው አትል።
እና ምኑ ላይ ነው ብዕሬ የሳተች፣
ብሔር የነቀፈች ህዝብን ያዋረደች።
ንገረኝ በሞቴ የመንጋው ጠበቃ
አንተም ሰው ሁንና መንጋነትህ ይብቃ"
ባለፈ አመት ክረምት ፣ ዛሬ አይታረስም
ጀግኖች አይጠሩም ፣ በፈሪዎች ስም፡፡


​​
ይፋዊ ገፆቻችን
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya


የተወደዳችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች ረቡዕ ግንቦት 11 በግራንድ ኤልያና ከ12.00 ሰዓት ጀምሮ "ዓባይ" የተሰኘ ደማቅ ምሽታችንን ለመካፈል ትኬት የሚገኝባቸው ቦታዎች እነሆ።

​​
ይፋዊ ገፆቻችን
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya


ከወደዱት


የሞት ጥቁር ወተት ~ [ የግጥም መድበል ]

ተስፋኹን ከበደ ( ፍራሽ አዳሽ )

"ሰው አምላክ ቢኾንስ? በሐሳብ መቅደሱ
ፈጣሪስ ሠው ቢኾን? ሥጋን በመልበሱ
ድንቅ ነው! ረቂቅ ፤ ካ'ምላክ መወዳደር
ከምድር ላይ ቆሞ ፣ ሰማይ ላይ መንደርደር::
ከጥቁር ሰማይ ሥር . . .
በቃል ኀይለ-ብእር ፣ ብርሃንን መልበስ
በሕያው ነፍስ ላይ . . .
የሞት ጥቁር ወተት ፣ ለዘላለም መቅምስ::"

ተስፋኹን ከበደ
( ፍራሽ አዳሽ )
2013 ዓ.ም



ይፋዊ ገፆቻችን
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya


​​ቁልቁል እያሰቡ ምንድነው ከፍታ
መብት እየነጠቁ ምንድነው ግዴታ
እስከ መቼ ተረት ግድ የለም ይነጋል
ምርኩዝ እየቀሙ መንገድ ምን ያደርጋል...?

መልካም ምሽት

ይፋዊ ገፆቻችን
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya










ጦቢያ ግጥምን በጃዝ ® dan repost
የተወደዳችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች ረቡዕ ግንቦት 11 በግራንድ ኤልያና ከ12.00 ሰዓት ጀምሮ "ዓባይ" የተሰኘ ደማቅ ምሽታችንን በክብር ጋብዘንዎታል ።


ጦቢያ ግጥምን በጃዝ ከአርትስ ቲቪ ጋር በመተባበር

ግጥም ለመላክ @TobiyaPoeticJazzAdmin_bot

ይፋዊ ገፆቻችን
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya


ጦቢያ
ለ ዓባይ

ረቡዕ ግንቦት 11

በግራንድ ኤልያና ሆቴል


መልካም
የአርበኞች መታሠቢያ በአል
ክብር ሁሉ ለእነርሱ
በደም እና በአጥንታቸው ላፀኑን
ሀገራችንን ለጠበቁ


አፍጥረናል!!!!

#Ethiopia | አገራችን ደሴ፣ ግሸን ነው ደብራችን፣
በረመዳን ሰሞን፣
እናፍጥር ብለውን፣ጠርተውን ሼሃችን፣
የመፍቀሬ ልጆች፣
አረብ ገንዳ በታች፣
አብረን አፍጥረናል፣ከነ መስቀላችን።

ይኸው ነው።

(ግጥም ጃኖ መንግስቱ)

***
ትናንት አመሻሹ ላይ በደሴ ተካሂዶ በነበረው ታላቅ የአፍጥር ፕሮግራም ላይ የአባም አብሮነት አልተለየም ነበር ።

ይህች ናት ኢትዮጵያ ❤️


ውድ❤ የጦቢያ ቤተሰቦች ለምታከብሩ ሁሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ !
የበዓሉን ልዩ ዝግጅት የመጀመሪያ ክፍል እነሆ ጋበዝናችሁ!

ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!

#ትንሳኤ
#ጦቢያግጥምንበጃዝ
#TobiyaPoeticJazz
#artstvworld
#SkyLightHotel

https://youtu.be/eM2Go9_HsU0


...... #ትንሳኤ .......

መድኔ....ስለኔ አከላቱ ደምቷል፣
የበደሌ ሸማ በሞቱ ተገፏል፣
እነሆ ...ተነስቶ ለዘላላም ነግቷል ።
፨፨፨
ሀጢያተኛው እኔ... ከነ ግሳንግሴ
የጥፋቴ ጋሪ ፥ ከብዶ ለፈረሱ
ሳያወላክፈኝ..... ፊዳ ሆኖ እርሱ
በእድፋም ገላ ፥ ክንዱን መንተራሴ
ሞቴን ቢሞትልኝ ፥ነፃ ወጣች ነብሴ።

#ክበር _ተመስገን!!

✍ አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abrham_teklu


@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya


#ትንሳኤ_በጦቢያ
እሁድ በ8፡00በ አርትስ ቲቪ ይጠብቁን።




pökä arts ™ dan repost
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሠሮ ለሰይጣን - አግአዞ ለአዳም፤
ሰላም - እምይእዜሰ፤
ኮነ - ፍስሐ ወሰላም
ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ፤
ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤
ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍጹም ሰላምና ደስታ ሆነ✝️❤️

በምክንያት ጠብቆ በሠላም ያደረሰን በክቡር ደሙ በቅዱስ ስጋው የዋጀን ቤዛም የሆነን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድሀኒአለም እየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ2013 በአለ ትንሳኤ በጤና አደረሰሽ/ህ መልካም በአል ከመላው ቤተሠብሽ/ህ ጋር ይሁን !

ፀባዖት ሶልአኪያ


እንደ ፆመ ሠው ለመፈሠክ ምንሯሯጠው ስ ነገር !

እንደው የፈጣሪ ይቅር ባይነት እንጂ የኛ የሁለት ወር ፆም ፀሎት አድኖን ነው ?
ምህረቱ የማያልቅ ሁኖ እንጂ እኛ ዝንት አለም ብንፆም ይቅር የምንባል ሠዎች ነን ግን ?
ከኣመት አመት የሀጢያት ስራችን አበል እንደሚከፈለው ፖለቲከኛ እየገነነ እንደምንኖረው ኑሮ እየናረ እንደ ዱር ቃጠሎ ጢሥ ሠማይ እየነካ እዚህ ደርሠናል ፤ የሚያልቁት ቢያልቁም የሚሠደዱት ቢሸሹም የሚረግፉት ቢረግፉም እኛ ደሞ ዛሬ ላይ ቆመን አለነው ። ለዛውም አማርጠን እየበላን እየጠጣን ለዛውም በልብስ ላይ ልብስ በጌጥ ላይ ጌጥ እየደራረብን ካዝናችንን የሞላው ገንዘብ አላዘጋ ቢለን ወጥተን በመዳራት በዳንኪራ በቅሚያ ገንዘባችንን በትነን ለስንቱ ሞት ምክንያት ሁነን ዛሬም አለን።

ከንግዱ አለም ከድሀው ሠርቀን ለሀብታም አጎብድደን ራሱኑ አጭበርብረን ርካሽ እቃ በውድ ሽጠን ያገኘነው ገንዘብ እውነት በርክቶልን ስራ ሠራንበት? ተለወጥንበትስ ? መልሱን ልባችንና ኪሳችን ይወቀው .
ስራ ለመቀጠር ተወዳድረን ለህክምና ትምህርት የኢንጂነሪንግ ምሩቅ በዘመድ ያስገባን የገባን እንዴት ነው ስራውና የተማርነው የትምህርት ዘርፍ ክላሽ አላረገም ?

ቤተ እምነት ብለን ወጥተን ቤተሠብ አስጨንቀን ገንዘብ ተቀብለን ሳይሆን (ፈልጠን ፣ነጥቀን) ቀኑን ስንዘል ርኩስ ነገር ስናደርግ በፈጣሪያችን ስም እየማልን አምልኮት ላይ ነው የቆየነው ስንል ያልተቀፀፍን ስንቶች አለን !

የቤት አከራይና ተከራይ ፣ በየመስሪያ ቤቱ በየተቋማቱ በአገልግሎት መስጫው በየትምህርት ቤቱ ሁሉ በቋንቋ ካልገጠመ ዘሩ ብሔሩ እያልን እየሠነጣጠቅን ስራ የማናስቀጥር ቤት የማናከራይ ሠብኣዊ እርዳታ እንኳን የማንሰጥ እኛ ርጉማን ስንሞት ምን ይውጠን ይሆን ?

ክልል ተብለን ሀገር ጎሳ ተሠጥቶን በመልክ በቀለም ተነጥለን ከአንድነት ምህተብ የተፈታን የኛን ቃል ያላወራ የራሱን መነሾ ያልመሠለ በመሀላችን ሲገኝ እንደመጤ የሠማይ ፍጥረት UFO ተቆጥረው በቀስትና በጎራዴ በቆጥራ በገጀራ በጥይት አሩር የቆላናቸው በራቸውን እየዘጋን ቤታቸውን በላያቸው ላይ ያነደድን ያቃጠልን እኛ ከዘላለም እሳትስ እንድን ይሆን ?

ቤተ እምነት እያወደምን እያቃጠልን የእምነት አባቶች እናቶች ወንድምና እህቶችን ህ ፃናቶችን በግፍ በአሠቃቂ ሁኔታ የምንገድል እኛ አንድ ቤት ሳይበቃን አንድ ሙሉ ከተማ የምናወድም እኛ ንፁሀንን ከሠላም ጉዟቸው ነጥለን በዱር በሜዳ እንደከብት የምናርድ የዳቢሎስ እኩያ ወንድሞች ማንነትን መሠረት እያደረገ አብሮን የኖረ ወንድማችንን ዘቅዝቀን እንደ ከብት ስጋ የምንሠቅል በሲኦሉ እሳት ለመንደድ እያማሟቅን ነውን ?

ከምንም በላይ ሀገር የተባለችው ክብርት መኖሪያ ዳር ድንበሯን መሀል ሀገሯን ታሪኳን የሚያዛባ ቅርሷን የሚሸጥ ባንዳ ተላላኪ ተራ ቅጥረኛ ወገኑን እንደይሁዳ ለማይረባ ዲናር የሚሸጥ አስመሳይ ምስጥ ሴረኛ ሁላ
ያሣደገውን የሚከዳ ያጠባውን ጡት የሚነክስ ልቡ በነውር የታፈነ የሠላም አየር መተንፈስን የተፀየፈ እርሱ አሟሟቱስ ያምርለት ይሆን ????


የኛ የሀጥያት ስራ ሠይጣን እንኳን ሊያደርገው የማይደፍረው ስለመሄኑ ጥርጥር የለኝም ።
እና ለዚህ ስራችን ዝንት አለም ፆም ፀሎት ስግደት ምፅዋት ብንታዘዝ ይከፋናል ? ክብር ለፈጠረን ይሁንና አለን የሚሉት በቀን 4 ግዜና ከዛ በላይ አማርጠው ቢበሉ
አልነሳንም የምንል በቀን 3 ግዜ ብንበላ
አጣሁ የሚለው በሁለት ቀን ወይ በሳምንት ጥቂት ፍርፋሪ ቀምሶ እንደሚያድር አስበን እናውቃለን ?
እናውቅ ይሆናል ግን ማካፈልን መለገስን ግን ፈፅመን አናውቅበትም !

ከማመስገን ማማረር ስለሚቀናን
ከፀሎት ከንቱ ውዳሴ ስለሚሻለን
ከመልካም ስራ ይልቅ ያልተነካ ሀጢያት ፍለጋ ስለምንባዝን
በየት በኩል ሠው ስለመሆን እናስብ እንጨነቅ ? ? ?
ልቦና ሠጥቶን ልባችን ከተደፈነ ፤
ወገብ ሠጥቶን ዝቅ ማለትን ከናቅን
እግርን ሠጥቶን ወደ ጥፋት መንገድ ብቻ ከሮጥን
እንዴት ሁኖ ነው ሰው የሚባለውን ፍጥረት የምሆነው ?

እንፀልይ እንፁም ፈጣሪን እንለምን
እንደዘንድሮው ሳይሆን እንደቀድሞው እንደአባቶቻችን ዘመን እንሁን
ፍቅር ይስጠን ሠላም ይስጠን የሚመጣውን ግዜ ያቅልልልን
እንባ የመገፋት የስቃይ እርጎ ነው !

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይጠብቅ
አሜን !

ፀባዖት ሶልአኪያ
ሚያዝያ 2013
ግላዊ ሂስ

@misrakterefetobiya
@tobiyamisrakterefe
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead


#ኦ_ማስያስ
--------------
እኔ ለበደልኩት ትህዛዝህን ሽሬ
ሕያው ነኝ ባንተ ሞት ቀሎልኝ ቀንበሬ!
ፍቅር አንተ በእውነት ፍቅር አንተ ውእቱ
ለኔ ነው ሚገባ መስቀልና ሞቱ
ሕማሜን ታመካል ጤናዬን ልትመልስ
ምከፍልህ የለኝም ይህን የሚመልስ!
ዝም ብዬ ላንባ መስቀልህን ሳየው
ንጹህ ሆነ ሳለህ የሞትከው ለኔ ነው!
የፊትህ ወዝ ጠፍቶ ደም ተሞልቶ ሳየው
በማያልቀው ፍቅርህ እመራመራለው
ይሄን ሁሉ ፍቅር ምህረትህን አይቼ
ዛሬም ማልመለስ ንስሐ ገብቼ
ይሄን ደንዳና ልብ የትዕቢት መንፈሴን
አውልቅልኝና አንጻልኝ እራሴን
አንተን ብቻ እያሰብኩ መስቀልህን ይዤ
መኖር ነው ምናፍቅ በሕማምህ ተክዤ
እንደ ቁጹረ ገጽ እንደ ዮሐንስ ያለ
አምላኩን ዘወትር በልቡ የሰቀለ
እንኳን ክፉ ሊመኝ እንኳን ሰው ሊያማ
መስቀሉ የገባው ቀን ለዕንባ ነው ሚሻማ!
ተው ሰው ፊትህን መልስ
ተው ሰው መስቀል ፍራ
ዳግመኛ አትስቀለው
ጌታን ባንተ ስራ!

****+++***

ዲ.ን ማቴዎስ መኩርያ
2013 ዓ.ም ዕለተ አርብ ስቅለት

@tobiyamisrakterefe
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

945

obunachilar
Kanal statistikasi