#እባቡ እና እኔ
ትላንት ማታ ወደ 3ሰአት አካባቢ በክፍሌ ውስጥ ፊልም እያየው እያለ የጎረቤታችንን ኡኡኡኡ ድረሱልኝ እባብ እባብ 🐍🐍.... የሚል ጩኸት ሰማው፥ ወዲያው ትልቅ እንጨት አንስቼ እየሮጥኩ ቦታው ላይ ስደርስ😳😳ማጋነን አይሁንብኝ እና እስከ ዛሬ ካየዋቸው ሁሉ በጣም ትልቅ የሆነ እባብ፥የድሮ አብሮ አደጌ የአሁኗ crush-a የጎረቤታችን ልጅ ላይ አፍጥጦ አንገቱን ቀስሮ ቆሟል፤
እኔ በደረስኩ በትንሽ ሰከንድ ውስጥ ጩኸቱን የሰሙ ከ6 ያላነሱ ጎረቤቶቻችን እያንዳንዳቸው ጣውላ እና ፍልጥ ይዘው ደረሱ፤ ታድያ እኔ ሆዬ ይሄን ሁሉ ሰው ስመለከት ዛሬ ደፋር፣ ጀግና እና ትክክለኛ ወንድ መሆኔን ለሷ የማሳይበት ቀን ነው፥ ይህን እባብ መግደል ያለብኝ እኔ ነኝ ብዬ ወሰንኩ(በውስጤ)
ከዚያም ወደ እባቡ በመጠጋት በያዝኩት ዱላ ሶፋውን መታ መታ አድርጌ እባቡ ፊቱን ወደኔ እንዲያዞር አደረኩት እና ለ Crush-a ከነበረችበት ቦታ ቀስ ብላ ወደ ውጪ እንድትወጣ ነገርኩዋት፤ የሚገርመው ደግሞ ይሄ ሁሉ ሰው መቶ እንኳን እባቡ ንቅንቅ አላለም አንገቱን ወደ እኔ አዙሮ ከማፍጠጥ ውጪ🙄🙄 አሁን እኔ እና እባቡ ፊት ለፊት ተፋጠጥን፥ አንተ መጥፎ እባብ ዛሬ የመጨረሻ ቀንህ ነው በእጄ ትሞታለህ እያልኩ እየፎከርኩ፥ ለጎረቤቶቼ ከ1 እስከ 3 እቆጥራለሁ 3 ስል ሁለችንም አንዴ እባቡን እንመታዋለን ብዬ ነገርኳቸው እና በቀስታ መቁጠር ጀመርኩ 1.....2.. ብዬ 3 ልል ስል ቡም መብራት ጠፋ😳😳💔💔 ሰዎች መብራት ጠፋ ነው ያልኩት ደንግጡ እንጂ (እናንተ እንዴት ሆናቹህ ካላቹኝ)
የደነገጥነው ድንጋጤ የገባንበት በር እንኳን በየት በኩል እንደነበር አስረሳን 💗😳 Guys የሰው ልጅ ያን ያህል ደንግጦ ራሱን እንደማይስት ያወኩት በዚሁ በራሴው research ነው፤ ከዛ እራሴን እባቡ ካለበት ቦታ ለማራቅ ስል የድንጋጤ ፍሪጁ ላይ እንደወጣው እራሱ ዘግይቶ ነው የገባኝ😁😁 ሌሎቹም እንደዛው.....
ከትንሽ ሰከንድ በኋላ በጣም ለስላሳ የሆነ ነገር እግሬን ሲነካኝ ተሰማኝ😳🙄 እባቡ ነው ብዬ immediately በያዝኩት ፍልጥ ስለው ወዲያው ወይኔ ወይኔ ጭንቅላቴን አህህህህህ ኡኡኡ እያለ አንዱ መጮህ ጀመረ😂 እኔም በሀይል ስሰነዝር ሰውነቴን መቆጣጠር ተስኖኝ ስለነበር ከፍሪጁ ጋር ተከነበልኩ በምኔ እንዳረፍኩ ሁላ አላውቅም ብቻ ቶሎ ብዬ ብድግ ለማለት የምደገፈው ነገር ለመፈለግ እጄን ስዘረጋ የሆነን ሰው 🦶እግር ነካው፥ እሱም እንደኔው እባብ መስዬው ነው መሰል መጠኑን በማላውቀው በትልቅ ጣውላ ሰረበኝ🏸 ኧረ ምን ሰረበኝ ብቻ ይሄ cricket 🏏የሚሉት የህንዶች ጨዋታ አለ አይደል እሱን ነው የተጫወተብኝ ብቻ ምኔን እንደመታኝ ባላውቅም ሽንቱን በጣም ወጥሮት እንደሸና ሰው ኡፍፍፍፍፍ ነው ያስባለኝ...
ኡፍፍፍ ማለቴን ሳልጨርስ መብራት መጣ💡 Guys እኔ ካልገደልኩ ስል የነበርኩት ልጅ እንዴት ከቤቱ ውስጥ እየሮጥኩ እንደወጣሁ አጠይቁኝ 🏃♂🏃♂🏃♂
መልዕክት፦ ድፍረት ጨለማ ውስጥ የለም & መብራት ሀይል ደግሞ እምታጠፋበትን ሰአት ምረጡ please
✍️✍️Ted
@poethaymi