Comedybutton dan repost
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአርቲስት
ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።‼️
ፕሬዚደንቱ በሀዘን መግለጫቸው "በፊንፊኔ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀግናው ወንድማችን ፣ ደማችን ፣ የትግል የለውጥ ምልክት የሆነው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በመሳሪያ መመታቱን ሰማን፡፡ መረጃውን እንደሰማን ጉዳዩን ለማጣራት እና የወንድማችንን ህይወት ለማትረፍ በአቅራቢው ካሉ አካላት ጋር በመሆን ትልቅ ርብርብ ተደርጎ ነበር"ማለታቸውንና ኦቢኤን አማርኛ ዘግቧል፡፡
"በሀጫሉ ህልፈተ ህይወት እንደ አንድ አብሮ አደግ፣እንደ ትግል ጓድ እና እንደ አንድ ጀግና
የተሰማኝ ሀዘን ከፍተኛ ነው፡፡ ሀጫሉ አርቲስት ብቻ አይደለም አመራርም ነው፤ ለእኔ ደግሞ ወንድሜ አማካሪዬ ነው፤ ይህን ጀግና ነው ያጣነው፡፡
የዚህ ጀግና ግድያ እንደተራ ነገር የሚታለፍ አይደለም፤ ግድያውም ተራ አይደለም። ታስቦበት የተፈፀመ ግድያ ነው፤ በዚህ ምንም ጥርጥር የለኝም" ብለዋል አቶ ሽመልስ።
በዚህ ድርጊት የተጠረጠሩት የተወሰኑ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምርመራ መጀመሩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። "የፀጥታ አካላትም በሁሉም አቅጣጫ ተሰማርተዋል። ለውጡን የማይፈልጉ አካላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመጠን በላይ ሲዝቱ ቆይተዋል፤ ለውጡንም ለማደናቀፍ ብዙ ሙከራዎች አድርገዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ድርጊቶችን ለመቀልበስ የኦሮሚያ ፖሊስ እና የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል።
ዛሬ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦችን ለማጫረስ እንዲሁም የሀገርን ህልውና ለመናድ አቅደው ይህን ድርጊት ስለመፈፀማቸው ጥርጥር የለኝም" ነው ያሉት አቶ ሽመልስ።
ፕሬዘዳንቱ አክለውም "ድርጊቱን የኦሮሞ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በሰከነ ሁኔታ በመገንዘብ ተጠርጣሪዎቹንም አብረን በመቆም ጀግናው ታጋይ ሀጫሉ የተሰዋለት የለውጥ ትግልም ወደ ኋላ እንደማይቀለበስ ይልቁንም ለውጡ እንዲሳካ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመረጋጋት እና በመናበብ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እንድንሻገር ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በላኩት መግለጫ፡፡ ሁሉም የመንግስት መዋቅር በሀገሪቱ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመታደግ በአንድነት መቆም እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ ይህን ወንጀል የፈፀሙ አካላት በቀጣይ ሊያደርጉ ያቀዱትን ስለማናውቅ ሁሉንም ነገር በተረጋጋ ሁኔታ ማየት እና ማጤን አለብንም ብለዋል አቶ ሽመልስ፡፡
በመጨረሻም ለቤተሰቡ፣ ለዘመድ አዝማዱ እና ለኦሮሞ ህዝብ ሁሉ ፕሬዘዳንቱ መፅናናትን ተመኝተው" ታጋይ ቢወድቅም ትግሉ ይቀጥላል" ብለዋል::
#Esat_tv1