Semir amicle


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


እንኳን እኔ ቀርቶ ያላየሁት ፊቱን
ያያቸው አልቀረም ሲጠበስ አንጀቱን
የወሊዬችን ቀልብ መተረው መሃባ
አንቱን አንቱን ሲሉ በነጋ በጠባ 
።።።።
የሶሃቦች ፍቅር ታጣለት ግጣሙ
ሙስጦፋን ነበረ ሚራቡም ሚጠሙ
ከቶ ሌላ አያዩም ሌላውን አይሰሙ
ከቤተሰብ ከሃብት ዘይኔን ያስቀደሙ

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


(የ ኢብሊስ ታሪክ ክፍል 1)
……

የታሪክ መቃኛ መነጥራችንን በርካታ ዘመናትን ወደ ኋላ መልሰን ከወደ ፍጥረተ ዓለም ጅማሮ የነበሩ ሑነቶችን ለመቃኘት ሀ ብለን ተነሳን።የዓለማቱ ጌታ ብቻውን ሆኖ ሳለ፣ፍጥረታትን ማስገኘት ሲሻ በ ኩንያ(ሁን በማለት)ትዕዛዝ የፍጥረታትን መጀመሪያ ኑር አድርጎ ከዚያም ሲልሲላውን በጠበቀ መልኩ የተለያዩ ፍጥረታትን አስገኘ።(ቀድሞ የተፈጠረው ውሃ ነው የሚል እሳቦት ያላቸው ዑለሞችም እንዳሉ እናስታውሳለን) ቢሆንም ከሃሳባችን ጋር ለመጓዝ ይኼ የ ቂያስ ልዩነትን መጥቀሱ ለሃሳብ ተቃርኖዎች ያለንን ክብር  ለመጠቆም እንጂ ሌላ አይደለም።እናም  ቅኝታችንን እንዲህ በረጋ እና በሰከነ የጉብኝት መንገድ  እንቀጥላለን።

ከቀዳማይ ግኝቶች ውስጥም ሰማይና ምድር ይገኙበታል።ሌሎች መውጁዳቶችንም እነ አርሽ፣ ኩርስይ፣ለውህ፣ቀለም፣ውሃ፣ጀነት፣ጀሐነም፣እንዲሁም ሌሎችን በርካታ ነገሮችን ረበል ዓለሚን ፈጥረ። ከዚያም ሰማይና ምድርን አሁን ባለበት ሑናቴ ካነባበረ በኋላ የምድር የመጀመሪያ ነዋሪያንን አስገኝቷል።እነሱም ከሰው ልጅ መፈጠር ብዙ ሺህ አመታትን ቀድመው በምድር የኖሩት ጂኒዎች ናቸው።

የሰው ልጅ ኹሉ አባት የሆነው አባታችን አደም(ዐሰ) ተፈጥሮ ሰዋዊ አካልን ይዞ ሩህ ተዘርቶበት ወደ ጀነት ከመግባቱ ከበርካታ ዓመታት በፊት፣ምድር ላይ የነበሩ ፍጥረታትን ስንዳስስ አንድን ታሪክ እናገኛለን።«የ ሱመያዕ ልጆች»ታሪክ። አባት ሱመያዕ ማለት የመጀመሪያው ጂኒ እና የጂኒዎችም ሁሉ አባት ሲሆን፣በምድር ላይ ተፈጥሮ መኖር ሲጀምር ከ አሏህ ጋር የተጋባው ቃል ኪዳን አብሮ ይወሳል።
የጂኒዎች አባት "ሱመያዕ" በወቅቱ ምድር ላይ የነዋሪነት ፍቃድ ሲሰጠው እጅግ በጣም ሷሊህ እና የአሏህ ህገ ደንብ በስርዓቱ የሚያከብር እና የሚተገብር ነበር።
………
(የጂኖች አፈጣጠር ጅማሮ)

አሏህ ምድርን በመልኳ ዘርግቶ ለረጅም ዓመታት ምንም ዓይነት ፍጥረታት ሳይኖሩባት በዝምታ እንድትቆይ ካደረገ በኋላ በመጨረሻም እሱን ሚያመልኩ ጂኒዎችን ማስገኘት ፈለገ።በቅድሚያም  "ሱመያዕ"የተባለው አባታቸውን ፈጠረው።
«የፈለግኸው ምኞትን ተመኝ!»በማለትም ጠየቀው።ሱመያዕ ምኞቱን አስከትሎ ነገረ።
«1,ጌታዬ ሆዬ እኔ እና ዝርያዬን ቁጥራችንን አብዛልን!
2,እድሜያችን ወደ እርጅና ሲሔድም እንዳዲስ ወጣት አድርገን።
3,እኛ ሌሎችን ሁል፣የምናይ ስንሆን ሌሎች ግን እኛን እንዳያዩ አድርገህ ሰውረን»።አሏህም ሶስቱንም ጥያቄዎች ከተቀበለው በኋላ፣«እኔን እንጂ ሌላን ላታመልክ፣የኔን ትዕዛዝ ልትተገብር።»ብሎ ቃል ኪዳን አስገባው።አባት ሱመያዕም የአሏህን ትዕዛዝ ተቀብሎ ቃለ መሃላውን ፈፅሞ ምድር ላይ አሏህን እየተገዛ መኖር ጀመረ።በየጊዜውም ዝርያዎቹ ቁጥራቸው እየጨመረ፣ግዛታቸው እያሰፉ፣አባት ሱመያዕም ምድሪቱን እያስተዳደረ፣በሰላምና በምቾት መኖራቸውን ቀጠሉ።
በመሰረታዊነት እዚህ ጋር የምናሰምርበት ነገር ቢኖር 1ኛ የሰው ልጅ ምድር ላይ ከመኖሩ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት የምድር ነዋሪያን ጂኒዎች እንደነበሩ ልብ ይሏል።እነዚህ ጂኒዎች የአሏህን የጌትነት ክብር ያወቁና፣አሏህን ብቻ ለመገዛት ቃልኪዳን የተጋቡ ሷሊህ ባሮች የነበሩ ሲሆን፣በሒደት ሁኔታቸው ወዴት እንዳመራ አብረን እንቃኛለን። ስለዚህ ውድ አንባቢያን! በተረጋጋ መንፈስ ሆናችሁ፣ታሪካቸውን አብረን እንቃኝ ዘንድ  ተከተሉኝ ስል ባክብሮት እጋብዛለሁ።
…………………

የአባት " ሱመያዕ" ዝሪያቹ እየበዙና እየተበራከቱ፣አሏህም በነሱ ላይ ያኖረውን ገፀ በረከት በማክበር እና እሱን ብቻ በማምለክ መኖር ቀጥለዋል።በወቅቱ የራሳቸው የሆነ ምድራዊ መጠቃቀሚያዎች የነበራቸው ሲሆን በተለያዩ አዝዕርቶችና ምግቦች በመጠቀም የተንበሻበሸ የበረከት ዘመናትን እንዳሳለፉ የታሪክ ድርሳናት ጥቁምታን ይሰጣሉ።በዚህም ሁኔታ ብዙ ሰላማዊ፣የተደድላ እና አሏህን የማምለክ ዓመታት ታለፉ።
…………
እነሆ በረከቶች መንበሻበሽ እና ተለምዶ ሲመጣ ግን ዘመን እየተጓዘ ሲሄድ እንዚያ ሷሊህ የነበሩ ጂኒዎች ቀስ በቀስ አሏህን ማመፅ፣ቃልኪዳናቸውን መጣስ እና ትዕዛዙን መቃረን ጀመሩ።ይሄ እርምጃቸውም ቀስ በቀስ እየባሰ ወደ ፍፁም አመፀኛነት አመራቸው።ከዚህም አልፎ የተጠላውን ደም የመፋሰስ ወንጀል ተዳፍረው እርስ በርሳቸው መገዳደል ጀመሩ።

አሁን በምድሪቱ ህገ አምላኮዎች ተረስተዋል።አሏህም የነሱን ሁናቴ ሲከታተል ቆይቶ፣በነሱ ላይ የነበረውን ተስፋ እና ትዕግስት ጨረሰ።ስለሆነም እኝህ አማፂያን ከምድረ ገፅ እንዲጠፉ አዘዘ።እርምጃወን ለመውሰድም የመላዒኮች ጁንድ፣ ከሚነሏህ የሆነ የሰላ ሰይፋቸውን ታጥቀው፣ወደ ምድር ዘልቁ።
ጂኒዎችን እንዳልነበሩ አድርገውን አወደሟቸው።ጥቂት ጂኒዎች ግን የመላዕክትን ጦር መቋቋም የማይቻል መሆኑን ሲገነዘቡ፣ ወደ ተለያዪ የባህር ዳርቻዎች፣ደሴቶች፣ጠረፍ ወዳሉ ገደላገደሎች እና ተራሮች እግሬ አውጪኚ ብለው ፈረጠጡ።(እሰይ😄)

የመላዒካው ብርጌድ የጦር አውድማውን በማጣራት ላይ ሳለ፣መሐል ሜዳ ላይ ድንገት አንድ የ 4 ዓመት ታዳጊ ጂኒንን ያገኛሉ።እሱም ተይዞ በቁጥጥር ስር ዋለ።ከዚያም የአሏህ ትዕዛዝ መጣና ይሄ ታዳጊ ጂኒ በመላዕክት ተይዞ ወደ ሰማይ ተወሰደ።ይህ የ 4ዓመቱ ጂኑ ኢብሊስ በመባል ይታወቃል።

ክፍል 2 ይቀጥላል…


ህይወትን ፍለጋ መንገድ ላይ ከመሆንህ ጋር   መኖርን ግን አትርሳ..


ወደ መስታወቱ ፊቴን በደንብ አስተጠጋሁ
በደንብ አርጊ እራሴን ተመለከትኩት
ነገር ግን ሁሌ የማየው ፊቴን አላየሁም እንግዳ ሰው አየሁ አዲስ ነገር አየው
ከመልኪ ,ከአይኖቺ ,
ከአፍንጫዬ,ከጁሮዎቺ ,.....

ያለፈን ነገር የጠለቀን , የሰጠመን ነገር  ያማረን... ነገር አየሁ::
ለመጅመሪያ ግዜ እኔን አየሁ በህይወቴ ለመጅመሪያ ግዜ እኔነቴን አስተዋልኩት

ከየት መጣ የማይባል ጥልቅ የሆነ ሰላም , ሀሴት, ደስታ, ፍቅር ..... ተሰማኝ

ሳኩ.....
እሱም ሳቀ


ተሳሳቅን.....


ሁለታችንም ቀልዱ ከብቱናል
እና በደንብ ተሳሳቅን

እስከዛሬ እራሴን የፈለኩበት  ባታ ሳስታውስ
ይበልጥ ሳኩ😂😂😂😂😂

Sem


እስኪ አብሽሪ እናብሽር እላለሁ ሁሌ ለራሴ እና አዚ የምትለኝ "ልብሽን ጠብቂ ቡቡሽ "እየቆየ እየቆየ ይገባኛል እየቆየ ልቤን ሲያመኝ ምናምን.... እና ልቤን መጠበቅ ሲያቅተኝስ እላለሁ ማለት እራስ ለራስ ሳይበቃ ይቀር የለ አለ አደል አንዳንዴ አለ ኣ.......💔


እኔ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስመረቅ ብርሃኑ ነጋ አሸባሪ ነበር🤣


ሁለት መስመር ግብህ

በመሰንበት አትመዝነው የህይወትን
                ጥዑም ለዛ
ለጭረቱ መጨነቅ ነው ሙሉ ስዕሉን
                  የሚገዛ

ከተፃፉት በላይ አሻራ ለመክተብ
ማጤን እኮ ያሻል የሰሩትን ማንበብ

በገፆች ብዛት አይለካም ገድል
ሁለት መስመር ግብህ ልትሆን ትችላለች
     ጥራዙን የምትጥል !!


ሁለት ነገሮች አሉ :: በህይወታችን እኛ  ማሳደድ የሌለብን እነሱም እውነተኛ ጓደኛ እና እውነተኛ ፍቅር ናቸው::

ሰዎች ግዜን ይሰጣሉ:: ከእነሱ ጋር መሆንን ከሚፈልጉቸው ሰዎች ጋር ሰዎች ይፃፃፋሉ ማውራት ከሚፈልጉቸው ጋር ሰዎች አብዝተው አይመቸኝም ሲሉህ እመናቸው እነሱም በግድ ግዜን እንዲሰጡህ ለማሳመን አትሞክር ቢፈልጉ ይሰጡሀል ::

ያማል አውቃለሁ :: ግን አንድን ሰው ላንተ ስሜት እንዴኖረው ማስገደድ አትችልም ::

አንድ ሰው እንዲያፈቅርህ ልትለምነው የተገባ አይደለም::አንድን ሰው ላንተ ይጨነጭ ዘንድ ልትለምነው የተገባ አይደለም ::አንድን ሰው ጥረት ያደርግ ዘንድ ልትለምነው የተገባ አይደለም::
አንድ ሰው ያወራህ ዘንድ ልትለምነው የተገባ አይደለም:: እንድን ሰው አንተን መጅመሪያ ያደርግ ዘንድ ልትለምነው የተገባም አይደለም ::እሱ ከፈለገ ያደርግሀል::

ሰዎችን ባንተ ህይወት ውስጥ ተቀዳሚ አታድርግ :: አንተ ለነሱ ምርጫ ብቻ ሆነህ ሳለ ::
Jay shetty


https://t.me/semirami


Personally ጥላ መያዝ አልወድም idk why but ሌላው ወንድ'ም ባይዝ እመርጣለሁ ግን "ወንድ ልጅ ጥላ ሲይዝ..." ምናምን እያላችሁ ምታሽቋልጡ ጥላ ቢስ ሴቶች ግን እረፉ ! 😅


ትልቅ ሰው !!!!!

ትንሽ ያሳደገው ፤ ትናንሹ ነግሶ፤
ያገር ሽማግሌ፤
የወንዙ ከራማ ፤ በትናንሾች ፈርሶ፤
የትንሾች ትንሽ፤
ያንንም ይህንንም፤
በክስና ዶሴ ፤ እያለቃለቀ፤
ይኸው በኔ መንደር፤
በትንሾች መንደር ፤ ትልቅ ሰው አለቀ።

        semir ami


ከምር የምንስቅበት ቀን አምጣልን!!!!" ብለን ዱኣ
ልናደርግ ነው!!!!!ጀምኣው ተከተል እንግዲህ!!!!"
ሸጋ ጁምኣ!!!!


የማትገዙትን እቃ ዋጋው ስንት ነው? ብላቹ አጠይቁ ለጠቅላላ እውቀትም ቢሆን አይጠቅማችሁም☹️


'
ሴት ልጅን በማይበድል ወንድ ላይ የአላህ ሰላምና እዝነት ይውረድ 🖤💚

Sem


ሰኞ

ቲክቶክ ብዙ አልጠቀምም። ዛሬ በድንገት ብገባ አንድ ፀጉሩ የተንጨባረረ ወጣት አንዲትን ህጻን ልጅ ይጠይቃታል ...

ጠያቂ - 'ላንቺ .. ከቀኖች ሁሉ  ምርጡ ቀን ማን ነዉ?'

ህፃኗ - 'ሰኞ'

ጠያቂ - 'እንዴት ሰኞን መረጥሽ'

ህፃኗ - 'ምክንያቱም .. ሰኞ ቀን ረሱላችን (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የተወለዱበት ቀን ስለሆነ ነዉ!'

◎ ሰኞን በጥቁር መስለዉ አሳዩን ምክንያቱም ለኛ ብርሃን የፈነጠቀበት ቀን ለነሱ ጨለማቸዉ ነዉና!

ቅኑን መንገድ ይምራቸዉ ለኛም ኻቲማችንን አላህ ያስዉብልን! መልካም ምሽት 🙏


ልጅ ሆኜ እያለሁ ...

~ሁሉም ሰው ኸይር የሚመኝልኝ ይመስለኝ ነበር።
~በአላህ የሚምል ሰው ሁሉ የሚዋሽ አይመስለኝም ነበር።
~ምድር ላይ መጥፎ የሚባል ሰው ያለ አይመስለኝም ነበር።
~ጓደኛ የሚከዳ አይመስለኝም ነበር።
~በዕድሜ ትልቅ የሆነ ሰው ሁሉንም ነገር የሚያውቅ ይመስለኝ ነበር።
~ምኞት ሁሉ በቀላሉ የሚሳካ ይመስለኝ ነበር።

እናንተስ ምን ይመስላችሁ ነበር ?


እሁድን

አንድ በዕድሜ ገፋ ያሉ አድማጭ ሸገር ሬዲዮ ደውለው “መንግሥት የሚሰማኝ ከሆነ ሐሳቤን በአጭር እንድገልጽ ይፈቀድልኝ!” አሉ፡፡

“እሺ ይቀጥሉ” አለ ጋዜጠኛዉ፡፡

ጉሮሯቸውን ከጠራረጉ በኋላ “እኔ እንኳ ብዙም የምለው የለኝም። በአጭሩ ሐሳቤን አጠቃልዬ ለመግለጽ ያህል ነው…::” አሉ እጅግ በበዛ ትህትና፡፡

“ይቀጥሉ አልኩ እኮ አባት…ይቀጥሉ” አለ ጋዜጠኛዉ፡፡

“….እሺ…እንግዲያውስ ከተፈቀደልኝ ልቀጥል… “ለአፍታ ትንፋሻቸውን ሰበሰቡና…
.
.
.
.
“ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ
ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ..."
😂

◎ በ'ርግጥ ሁላችንም ያለንበት ሁኔታ እንደዚህ ነዉ። ጩኸን ችግራችን ቢጠፋልን ምኞታችን ነበር 🤔

ሊንኩን ተጫኑና ኑ አብረን እንጩህ


. . .🌺🌸
ስለ ክብር ምን ያህል ታውቂያለሽ?
የሳቀልሽ ሁሉ የወደደሽ . . . ያከበረሽ አይምሰልሽ..... የዛሬን አትይ ብዙ መናቆች የሚመጡት ቀድሞ ከመከበር ነው. . .ወዳጅ ነን ባዮችሽን የምትይዥበትን መንገድ እወቂ ..ለሁሉም አንድ አይነት ቦታ አይሰጥም! አክብረሽውም የማይከበር ብዙ ሰው አለ. . . . . ስለ ነገ መከበርሽ ግን ዛሬን ታገይ. . .
 

🌺🌸


ወንድ ልጅ ሂወቱ መልካም አትሆንም በመልካም ሚስት ቢሆን እንጅ so ለባልሽ መልካም መሆን አለብሸ  አንተም  እንደዛ ለእሷ ክብር ሊኖርህ ይገባል ክብር ይሠጥህ ዘንድ

https://t.me/semirami


አንድ የማታሳማ እህት አለችኝ እግሬን ዘርግቼ እያማሁኝ ተመሳሰጠው እሺ ከዛስ እያሉ እየሰሙኝ በማህል አስተግፊሩላህ በሉ በቃቹ ዱአ አድርጉ ምንምን ስትል እንዴት ደሜ እንደሚፈላ 🤦‍♀️


'
ማለቂያ የሌሉት ችግሮች አለባቹ ?
አትጨነቁ አላህ ያልተገደበ መፍትሄ ነው ያሉት ።

Nice day


'
ምክር ስመክርህ ሙሉሰው እንደሆንኩ አድርገህ አታስበኝ..
ምክር መለገስ የዉዴታ እንጂ የመብለጥ ምልክት አይደለም!!

መልካም ምሽት 😘


ሰላም 🙌 ጥሪዬን አክብራችሁ የቴሌግራም ቤቴን ስለተቀላቀላችሁ ከልብ አመሰግናለሁ! 🥰🥰

ስለመጣችሁ ደስ ብሎኛል።

https://t.me/semirami
https://t.me/semirami

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 156

obunachilar
Kanal statistikasi