Betelhem Tachbel
በቀል
.
አንድ ቄሬናዊ~ስምኦን የሚባል ሰው፤
በርባን ከተባለ~ክፉ ወንበዴ ጋራ መጥፎ ቂም ነበረው
ከእለታት አንድ ቀን..
ይህ ክፉ ወንበዴ~ከወህኒ መውረዱን ስምኦን ድንገት ሰማ፤
ሊበቀለው ሻታ....
መስቀያውን እንጨት~እሱ እንደሚሰራው ከአይሁድ ተስማማ
(አይሁዳውያኑ...ወንጀልን የሰራ ተሰቅሎ ይገደል~ስለሚል ህጋቸው፤
ስምኦን ይህን አውቆ~እርጥብ ከባድ መስቀል ሰርቶ አስረከባቸው)
.
ምን ያደርጋል
.
ፍርድ ተሳሳተ~ወንበዴውም በርባን ከእስር ተፈታ፤
በምትኩ ታስሮ~የሚወደው መምህር ቆመ ሊንገላታ
ያንን ከባድ መስቀል..
አሸክመው ገፋት~ደጋግሞ ወደቀ አልቻለውምና፤
ስምኦን ልቡ አልቻለም~ጥፋቱን አሰቦ እንዴት ነብሱ ትፅና?
.
ኢየሱስ መምህሩ~በሰራው መስቀል ላይ ታርዶ ተሰቀለ፤
ለጠላት ያለው ዕፅ~ወዶ ያልጠገበውን ወዳጁን ገደለ!!
#ሼር
@Sheelff
በቀል
.
አንድ ቄሬናዊ~ስምኦን የሚባል ሰው፤
በርባን ከተባለ~ክፉ ወንበዴ ጋራ መጥፎ ቂም ነበረው
ከእለታት አንድ ቀን..
ይህ ክፉ ወንበዴ~ከወህኒ መውረዱን ስምኦን ድንገት ሰማ፤
ሊበቀለው ሻታ....
መስቀያውን እንጨት~እሱ እንደሚሰራው ከአይሁድ ተስማማ
(አይሁዳውያኑ...ወንጀልን የሰራ ተሰቅሎ ይገደል~ስለሚል ህጋቸው፤
ስምኦን ይህን አውቆ~እርጥብ ከባድ መስቀል ሰርቶ አስረከባቸው)
.
ምን ያደርጋል
.
ፍርድ ተሳሳተ~ወንበዴውም በርባን ከእስር ተፈታ፤
በምትኩ ታስሮ~የሚወደው መምህር ቆመ ሊንገላታ
ያንን ከባድ መስቀል..
አሸክመው ገፋት~ደጋግሞ ወደቀ አልቻለውምና፤
ስምኦን ልቡ አልቻለም~ጥፋቱን አሰቦ እንዴት ነብሱ ትፅና?
.
ኢየሱስ መምህሩ~በሰራው መስቀል ላይ ታርዶ ተሰቀለ፤
ለጠላት ያለው ዕፅ~ወዶ ያልጠገበውን ወዳጁን ገደለ!!
#ሼር
@Sheelff