Super christian tube ሱፐር ክርስቲያን ቱብ


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ። 1ጴጥ. 4÷7
ይህ ሱፐር ክርስቲያን ቱብ ነው!
# አላማችን
👉 በተግባሩና በህይወቱ የሚመሰገን በመንፈስ የጋለ ንቁ ክርስቲያን መፍጠር ነው።
በተጨማሪ በዩቱብ https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የአዲስ ኪዳን መካከለኛ
@superchristiantube7
@superchristiantube7
@superchristiantube7

#የአዲስ_ኪዳን_መካከለኛ
የአዲስ ኪዳን መካከለኛ እንደ እርሱ ሌላ የሌለ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ጌታ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው:: እርሱ ለእግዚአብሔርም ለሰውም ወገናዊነቱ እኩል ሹመቱም ዘላለማዊ የሆነ ነው::
#የአዲስ_ኪዳን_መካከለኛ_ወደሚሆን_ወደ_ኢየሱስ_ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል። ዕብ. 12÷24

#አሁን_ግን_በሚሻል_ተሰፋ_ቃል_በተመሠረተ_በሚሻል_ኪዳንም_ደግሞ_መካከለኛ_እንደሚሆን_በዚያ_ልክ_እጅግ_የሚሻል_አገልግሎት_አግኝቶአል። ዕብ. 8÷6

ሰውና ሰው ቢጣላ በመካከል የሚገቡት አስታራቂዎች ከአንድ በላይ ቢሆኑ ምንም አይደለም። ነገር ግን ጠቡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሲሆን ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በመካከል የሚገባና የሚያስታርቅ ሌላ መካከለኛ (አማላጅ) የለም። እግዚአብሔር አንድ ባይሆን ኖሮ ከምርጫው ብዛት የተነሳ የሰው ልጆች ግራ ሊጋቡ ይችሉ እንደነበረ፤ እንደዚሁ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ባይሆን ወደ እግዚአብሔር የመቅረቢያው መንገድ ዝብርቅርቁ ይወጣ ነበር።

ከኢየሱስ ሌላ አማላጆች ሰጥቶናል በሚሉት መካከል አማላጆቹ በመብዛታቸው ስለ የመካከለኛነት አገልግሎት የተቃወሰና ግራ የሚያጋባ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት አለ። የዚህን እውነት ለመረዳት ከአማላጆች አንዷ ክርስቶስ ሰምራ አደረገች የሚሉት ገድል መመልከት በቂ ነው። ክርስቶስ ሰምራ ሰውን ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ምልጃ አድርጋለች።

ገድለ ክርስቶስ ሰምራ
#ጌታም_ወዳጄ_ክርስቶስ_ሰምራ_ሆይ_እስኪ_የልብሽን_ሀሳብ_ወይም_ፍላጎትሽን_ንገሪኝ_አላት። #አቤቱ_ፈጣሪዬ_ፈቃድህስ_ቢሆን_የአዳም_ልጆች_ከስቃይ_ከኩነኔ_ይድኑ_ዘንድ_ዲያብሎስን_ይቅር_ትለው_ወይም_ትምረው_ዘንድ_እለምንሃለሁ። #የኃጥእን_መመለሱን_እንጂ_ጥፋቱን_አትወድምና_አለችው... >>

ሰይጣንንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ መሞከር መጽሐፍን ካለማወቅና ስለ እግዚአብሔር ሆነ ስለ ሰይጣን ማንነት በትክክል ካለመረዳት የሚመጣ ችግር ነው። ገ.ክ.ሠ. ዘግንቦት 36-39

ሌላው አማላጅ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ሁሉ ጌታ እንዲምርለት ማልዶ በጅምላ እንዳስማረ በገድሉ ውስጥ ተተርኮለታል።

ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#አባታችንም_ጌታችንን_አቤቱ_የኢትዮጵያን_ሕዝብ_አንድ_ሳታስቀር_በሙሉ_ማራቸው_አለው። #ጌታችንም_አባታችንን_እነሆ_የኢትዮጵያን_ህዝብ_በሙሉ_ዓስራት_እንዲሆኑ_ሰጥቸሃለሁ_እንድወደድህ_ላንተ_ይሁኑህ_መታሰቢያህን_ያድርጉ_በጸሎትህ_ይታመኑ_ደስ_ብሎአቸው_ለዘላለም_ይኑሩ አለው። ገ.ገ.መ.ቅ.ክፍል 7 ምዕ. 27፥26-28

እንደዚህ ገድል አገላለጽ ደህንነት በጅምላ ለኢትዮጵያዊ ሁሉ ተሠጥቶአል። በዚህ ገድል መሠረት ለመዳን የሚያስፈልገው በክርስቶስ ማመን ሳይሆን ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻና በገብረ መንፈስ ቅዱስ አማላጅነት መታመን ነው። በኢትዮጵያ በክርስቶስ የሚያምኑ፣ ሌላ የተለያዩ ኃይማኖት ያሏቸው፥ ደግሞም ለጣዖት የሚሰግዱ ብዙ ወገኖች አሉ። ስለዚህ ስለገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲል እግዚአብሔር ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ በጅምላ ይመራል ብሎ ማስተማር ከፍተኛ ስህተት ነው።

እነዚህን ገድል፣ ታምር የተባሉትን መጽሐፎች ለሚያነብ ሰው የአማላጆቹን ቀጥር ያህል ብዙ አሳፋሪና ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀሳቦች እንዳሉ ግልጽ ነው።
የአንዱን የኢየሱስ ክርስቶስን አማላጅነት ብቻ መቀበል ማለት ይህን ሁሉ አሮጌ ተረት መተው ማለት ነው። ስለዚህ ነው ሰዎች ክርስቶስን ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም ማለት የሚቀላቸው።

በጥላው ዘመን የነበሩትን የመካከለኛነት አገልግሎቶች ሁሉ አጠቃሎ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ እንዲሆን የተመረቀውና የተሾመው አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለዚህ እርሱ፦
ሀ) ሙሴ አስቀድሞ እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል ያለው ነቢይ ነው። (ዘዳ. 18፥15-17፣ የሐዋ. 3፥20-27፣ ሉቃ. 13፥33)

ለ) እንደመልከ ጸዴቅ የዘላለም ካህን ነው። (ዕብ. 5፥6፣ ዕብ. 3፥5፣ ዕብ. 3፥1 ዕብ. 7፥26፣ ዕብ. 4፥10)

ሐ) የዘላለም ንጉስ ነው። (ሚክ. 5፥2፣ መዝ. 2፥6፣ ኢሳ. 9፥6-7፣ ራዕ. 20፥4-6)

የሰብአዊ መጠሪያ ስሙ የሆነው #ኢየሱስ የሚለው ቃልና መለኮታዊ ስሙ #ክርስቶስ የሚለው ቃል ሁለቱም መካከለኛነቱን የሚያንጸባርቁ ናቸው።

መለኮታዊነቱን የሚገልጸው #ክርስቶስ የሚለው ቃል የመጣው #ክርስቶ ከሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን የቃሉ መሠረታዊ አመጣጥ ግን በብሉይ #መሲህ ከሚለው ከዕብራይስጥ ቃል ነው። #መሲህ ( #ክርስቶስ) ማለት #የተቀባ ማለት ነው። በብሉይ የሚቀቡት #ነቢያት፣ #ካህናትና #ነገሥታት እንደነበሩ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ሦስቱንም ማዕከላዊ አገልግሎት አጠቃሎ ለማሟላት #የተቀባ (የተመረቀ) በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ብቸኛው መካከለኛ ነው። #ኢየሱስ ማለት #መድኃኒት ማለት ነው። ኃጢያተኛን ከኃጢአት ዕዳና ፍርድ ነፃ የሚያደርገውና የሚያድነው ከእርሱ በቀር ሌላ ማንም የለም። (ሐዋ. 4፥12)
@superchristiantube7
@superchristiantube7
@superchristiantube7

ቢያንስ ቢያንስ ይህን መልእክት ለ2 ሰዎች #ሼር በማድረግ ወንጌልን ከእኛ ጋር አብረው ይሥሩ።
#SHARE




ምንም እንኳ ባያውቁቱም እነዚህ ሰዎች አማኞች ነበሩ እኔ ያደረግሁት ቢኖር አንድ እርምጃ ወደፊት ሄደው የድኅንነትን ልምምድ እንዲያገኙ ማድረግ ነበር።
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7

ክፍል 16
አንድ ጊዜ በመንገድ ላይ አንዲት ሩስያዊት የጦር መኮንን አገኘሁ። አስቀድሜ ይቅርታ በመጠየቅ ቀረብ አልኳትና ''በመንገድ ላይ የማያውቋትን ሴት ማነጋገር ጨዋነት እንዳልሆነ አውቃለሁ'' ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያን መሪ ስለሆንኩ ዓላማዬ ቅን መሆኑን ልገልጽልሽ እወዳለሁ #እስቲ_ስለ_ክርስቶስ_ጥቂት_ላነጋግርሽ አልኳት።
እርሷም #ለመሆኑ_አንተ_ራስህ_ክርስቶስን_ትወደዋለህ? አለችኝ። #አዎን_በሙሉ_ልቤ_ክርስቶስን_እወደዋለሁ በማለት መለስኩላት እየደጋገመች ሳመችኝ አንድ የቤተክርስቲያን መሪ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ በመንገድ ላይ መታየቱ ስላሳፈረኝ እኔም መልሼ ሳምኳት ይህን ያደረግሁት ዘመዳሞች እንደሆንን ለማስመስል ነበር። #እኔም_እንዳንተ_ክርስቶስን_እወዳለሁ አለችኝ። ወደቤት ይዤአት ሄደሁ። ስለ ክርስቶስ የምታውቀው በጣም በጥቂቱ ነው ክርስቶስ አዳኝ መሆኑን፣ የዘላለም ህይወት የሚገኘው በእርሱ በማመን እንደሆነ አታውቅም ግን ትወደዋለች። ሁኔታዋ ሥነ ልቦናዊ ጉጉትን አሳደረብኝና #ስለክርስቶስ_እንደሚገባ_ሳታውቂ_እንዴት_ልትወጂው_ቻልሽ? በማለት ጠየቅኋት።
እርሷም #በልጅነቴ_በስዕል_ማንበብ_ተምሬአለሁ። ለምሣሌ በ-በግ ቡ-ቡና ቢ-ቢለዋ በማለት። ሁለተኛ ደረጃ ከደረስኩ በኋላም ኮሚኒስት እናት አገሬን ማገልገል ስላለብኝ ቅዱስ ተግባር ተነገረኝ። ኮሚኒስታዊ ሞራልንም አስተማሩኝ ይሁን እንጂ #ቅዱስ_ተግባር ወይም #ሞራል ምን እንደሚመስሉ ግን እርግጠኛ አልነበርኩም። እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ገለጻ የሚሰጠኝ ነገር ፈለግሁ። አባቶቻችን በህይወት ለሚገጥሙን #ውብ #ድንቅና #እውነታ ላላቸው ነገሮች ስዕላዊ ገለጻ እንደነበራቸው አውቃለሁ። አያቴ አነዚህን ነገሮች ሁሉ ይወክላል በምትለው ስዕል ፊት ሁል ጊዜ በእክብሮት ስትንበረከክ እመለከታት ነበር። ያ ስዕል የክርስቶስ ስዕል እንደሆነ ነግራኛለች። ታዲያ ከጊዜ ብዛት ያን ስዕል ወደድሁት ስዕሉ ፈጠራ ብቻ ሳይሆን እውነት ሆነልኝ #ክርስቶስ የሚለው ስም ራሱ ይህ ነው ብዬ ልገልፀው የማልችለውን ደስታ ይሰጠኛል አለችኝ።
የምትናገረውን እየሰማሁ እያለ #ሐዋርያው_ጳውሎስ ለፊሊጵስዩስ ሰዎች በፃፈው መልእክት "ጉልበት ሁሉ ለክርስቶስ ክብር ይንበረከካል። አንደበትም ሁሉ ክቡር ስሙን ያመስግናል" በማለት የፃፈው ትዝ አለኝ። ምናልባትም የክርስቶስ ተቃዋሚ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ለተወሰነ ጊዜ ያደበዝዘው ይሆናል #የክርስቶስ_ስም_ግን_ወደ_እውነተኛ_ብርሃን_የሚመራበት_ሀይል_ነው።
#ክፍል_17_ይቀጥላል....

የዩቱብ ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ➽super christian tube በማለት ወይም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ምንጭ #ለክርስቶስ_ተሰቃየው_የሚለው_መጽሐፍ_ነው። ገዝታችሁ እንድታነቡትና ራሳችሁን እንድትፈትሹበት አበረታታችኋለው።
@superchristiantube7
@superchristiantube7
@superchristiantube7


#Share


ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ወይስ ተመላጅ?
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_አማላጅ_ነው_ወይስ_ተመላጅ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ከመስጠታችን በፊት #ማለደ የሚለውን ቃል ትርጉም እንመልከት።

ትርጉም

#ማለደ ለሚለው ቃል የሚከተሉት ሁለት ትርጉሞች ሊሰጡት ይችላል።
1⃣ #ማለደ ማለት አንድ ሰው ጉዞ ለመጀመር ወይም በሥራ መስክ ለመሰማራት ጎህ ሳይቀድ (በማለዳ) መነሳቱን ያመለክታል። (ምሳሌ #በማለዳ_ተነስቶ_ገሰገሠ፤ #ማልዶ_ተነሳ. . . . .ወዘተ)
2⃣ #ማለደ ስንል አንድ ሰው በደንብ የሚያውቀውን ሰው ስለሌላ ሦስተኛ ሰው ጉዳይ ለመነው፤ ይቅር እንዲለው፤ ዕዳው እንዲሰረዝለት ለመነለት (ማለደለት) ማለት ነው።

በተራ ቀጥር ሁለት ትርጉም መሰረት የአማላጅነት ሥራ ሦስት ሰዎችን ያካትታል። እነርሱም ሀ) #አማላጁ ለ) #ተማላጁ ሐ) #የሚማለድለት_ሰው ናቸው።

አማላጅ ተማላጁን በመለመን ዕዳን ያስምራል፤ በደልን ያሰርዛል፤ ይቅር ያስብላል። #አማላጅ ወይም #ተማላጅ የሚለውን ጥያቄ የምንመልሰው ከዚህ ትርጉም አኳያ ነው።

የተባለው የእግሊዘኛ መዝገበ ቃላትም #ማለደ Intercede የሚለውን ቃል #ከመካከል_መግባት go_between ሲል ይፈታዋል።

#መማለድ ሁለት ሰዎችን ወይም ወገኖችን ለማስማማትና ለማስታረቅ በሁለቱ መካከል የመግባት ተግባር ነው። ይህ በሁለት ሰዎች መካከል የመግባት ሥራ በእንግሊዘኛ to mediate (ማስማማት) ይባላል። የሚያስማማው ሰው ደግሞ Intercessor (አስማሚ ወይም አስታራቂ) ይባላል። አስታራቂ አማስታረቅ በሁሉት ሰዎች መካከል የሚገባ ሰው mediator ነው።

የመካከለኛነት አገልግሎት
መማለድና ምልጃ በክርስቶስ የመካከለኛነት ሥራ ውስጥ የሚካተት ሀሳብ ነው። ጊዜያዊና ሊመጣ ላለው ጥላ በነበረው ሥርዓት (ብሉይ ኪዳን) የመካከለኛነት አገልግሎት እንዲሰጡ ሦስት ዓይነት ሰዎች ይቀቡ ነበር። እነርሱም፦
1) #ነቢያት (1ኛ ነገ. 19፥15-16)
2) #ካህናት (ዘፀ. 28 እና 29)
3) #ነገሥታት (1ኛ ሳሙ. 10፥1) ናቸው።

በጥላው ዘመን የነበረው የእነዚህ ሁሉ የመካከለኛነት አገልግሎት ዘላለማዊነት አልነበረውም። ምክንያቱም በሚሞቱበት ጊዜ ማዕከላዊ አገልግሎታቸው ያበቃ ነበር እንጂ ወደ ሰማይ ፈጽሞም አልተላለፈም። የሚተላለፍ ቢሆን ኖሮ ከሰማይ ሆነው ማዕከላዊ አገልግሎት መስጠት ስለሚችሉ በሌሎች መተካት አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን የእነርሱ አገልግሎት ወደ ሰማይ መተላለፍ ስላልቻለ በምትካቸው ሌሎችን መሾምና መተካት ግዴታ ነበር። በጥላው ዘመን ማዕከላዊ አገልግሎት የሰጡት ሰዎች ቁጥር ብዙ የሆነበት ምክንያት ለዚህ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ነገር ሲጽፍ፤ #እነርሱም_እንዳይኖሩ_ሞት_ስለከለከላቸው_ካህናት_የሆኑት_ብዙ_ናቸው። ይላል። ዕብ. 7፥23

የአዲስ ኪዳን መካከለኛ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ግን ሹመቱ እንደ አሮን የክህነት ሥርዓት ሳይሆን እንደ መልከ ጸዴቅ የክህነት ሥርዓት በመሆኑና በሞት ባለመሸነፉ የዘላለም ካህን ነው። ስለሆነም የእርሱ የመካከለኛነት አገልግሎቱ ወደ ሰማይ ለመተላለፍ ችሏል።

ዕብ. 7፥24-25


ከላይ በተመለከትነው ጥቅስ መሰረት የክርስቶስ የመካከለኝነት አገልግሎት እንደ ጥላው ዘመን አገልጋዮች አይለዋውጥም። በምድር በነበረበት ጊዜ ሆነ አሁን በሰማይ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ሳለ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ዘላለማዊ ካህን የለም።

#ሐዋርያው_ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ 1ኛ ቆሮ. 8፥5-7

አህዛብ ሰፈር ቁጥር የሌላቸው አማልክቶች አሏቸው። የአማልክቶቻቸው ቁጥር የሚያንስ ከሆነም አማልክቶቹን የሚፈጥሩ እነርሱ በመሆናቸው የፈለጋቸውን ያህል መጨመር ይችላሉ። ነገር ግን ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው የክርስቲያም አምላክ አንድ ብቻ ነው። በአብና በሰው መካከል ያለው መካከለኛም አንድ ብቻ ነው። #አንድ_ፀሐይ_ብቻ_በሰማይ_ላይ_እንዳለች_እሷም_ለዓለም_ሁሉ! _ስለምትበቃ_እግዚአብሔር_ሌላ_ጸሐይ_መፍጠር_እንዳላስፈለገው_ሁሉ፤ ለሰዎችም መካከለኛ ሲሰጥ ከመረቀው ከአንዱ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ መካከለኛ ለሰዎች መስጠት አላስፈለገውም፤ አልሰጠምም።
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7

ይህን መልእክት ቢያንስ ለአንድ ሰው #ሼር አድርጉት።
#Share


#አንቺን_አላገባም
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7

ሰባኪው ለአቅመ አዳም የደረሱ ወጣቶችን ሁሉ ሰብስበው በቤተ ክርስቲያናቸው እንዲህ እያሉ የጋብቻ ትምህርት ማስተማር ጀመሩ > እስቲ ይህን ምሳሌ ልንገራችሁ:-

#አንድ_ወጣት_የአንዲትን_ልጅ_ዓይኗን_ወደደና_ለትዳር_ጠየቃት። #እርሷም_እሺ_ብለው_አብረው_ቀጠሉ። #አንድ_ቀን_ሽርሽር_ቦታ_ሄደው_ዋና_እየዋኙ_ሳለ_ወኃ_ውስጥ_የተደበቀ_ብረት_ዓይኗን_ይመታውና_አንድ_ዓይኗ_የፈስሳል። #በዚህ_ጊዜ_አንድ_ቀን ብሎ ይጠራታል። #እርሷም_መጥታ_የሚነግራት_ስለምን_እንደሆነ_ለማወቅ_ጓጉታ_ትጠይቀው_ጀመር። ስለሰርጋችን ነው? ስለ ቬሎ ነው? ስለምንጋባባት ቀን ነው? የምትነግረኝ ምንድን ነው? እርሱም > አላት።

(ምሳሌ. 17÷17)።

አዎ ጓዶቼ÷ ፍቅራችን በእውነት ፍቅር እንጂ በሚፈርሰውና በሚጠፋው አካል ብቻ እንመሠርት። የምናገባው #ዓይኗን #ፀጉሯን ወይም #አፍንጫዋን አይደለም የእግዚአብሔር አምሳል የሆነውን ክቡር የሰው ልጅን እንጂ። በእውነት እንዋደድ ለዚህም አምላክ ይርዳን። #አሜን!

ምንጭ የሰባኪው ምሳሌ ከሚለው መጽሀፍ ነው።
ገዝታቹ እንድታነቡት አበረታታችኋለው
🎚https://t.me/superchristiantube7🎚
🎚https://t.me/superchristiantube7🎚


#እግዚአብሔር_የሰማይና_የምድር_ፈጣሪ_ባይሆንም_የትንሿ_አውራ_ጣት_ፈጣሪ_ብቻ_በመሆኑ_እንኳ_ሊመሰገን_ይገባዋል። #ክፍል_15_ይቀጥላል...
@superchristiantube7
@superchristiantube7

ክፍል 1⃣5⃣
የኤሌክትሪክ አምፖልን ስልክንና የባቡር ሀዲድን ሌሎችንም ስለሰሩ #ኤዲሰንን #ቤልንና #ስታቬንስንን እናደንቃቸዋለን ታዲያ ይህን አውራ ጣት የሠራው ፈጣሪ መደነቅ ይበዛበታል? ኤዲሰን አውራ ጣት ባይኖረው ኖሮ ምናልባትም ምንም ነገር ላይሠራ ይችል ይሆናል አውራ ጣትን ስለፈጠረ ብቻ እግዚአብሔር ሊመሰገን ይገባዋል።
ብዙ ጊዜ ሚስቶች ከእነርሱ የሚሻል አስተሳሰብ ሲያቀርቡላቸው እንደሚናደዱት ሁሉ ይህም ባል ሚስቱ ባቀረበችለት ሀሳብ በጣም ተናደደ " #እንዲህ_ያለ_የማይረባ_ነገር_አትናገሪ_እግዚአብሔር_እንደሌለ_ተነግሮሻልና_ይህንኑ_ተቀበይ_በሰማይ_ምንም_አምላክ_ባይኖርም_እኔ_ግን_በዚህ_በሌለው_የአውራ_ጣት_ፈጣሪ_አምናለሁ" አለችው።
ስለዚህም በአውራ ጣት ፈጣሪ ማመን ጀመረች የኋላ ኋላ ግን እርሷ እና ባለቤትዋ እግዚአብሔር የአውራ ጣት ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን የሰማይና የምድር የከዋክብት የአበቦች የሰዎችና በጠቅላላው የነገሮች ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ማመን ጀመሩ።
#ሐዋርያው_ጳውሎስ ለወንጌል አገለግሉቱ ወደ አቴንስ በሄደበት ወቅት "የማይታወቅ አምላክን" ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር ተገናኝቶ ነበር።
እኔም ለእነዚህ ሰዎች እግዝአብሔር #የፍቅር #የጥበብ #የእውቀትና #የሀይል መንፈስ በመሆኑ በሰማይ ሊወሰን እንደማይችልና ባያውቁትም እንኮ በእርሱ ማመናቸው ትክክል እንደሆነ ነገርኳቸው። ይህም አምላክ ፍቅር ስለሆነ በእነርሱ ምትክ እንዲሞት አንድ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም እንደላከው አስረዳኋቸው።
ምንም እንኳ ባያውቁትም እነዚህ ሰዎች አማኞች ነበሩ እኔ ያደረግሁት ቢኖር አንድ እርምጃ ወደፊት ሄደው የደኅንነትን ልምምድ እንዲያገኙ ማድረግ ነበር።

የዩቱብ ቻናላችንን #subscribe ያድርጉት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

#ምንጭ ለክርስቶስ ተሰቃየው የሚለው መጽሀፍ ነው።

#ክፍል_16_ይቀጥላል....
#SHARE


በሩስያውያን ወታደሮች መካከል ወንጌልን እንድንሰብክ ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉልኝ እነዚህ ወገኖች ነበሩ። #ክፍል_14_ይቀጥላል
https://t.me/superchristiantube7✝
https://t.me/superchristiantube7✝

#ክፍል 1⃣4⃣
ምንም እንኳ ማንኛውም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ በነዚህ ክርስቲያኖች ህይወት በግልጽ ቢታይም ደስተኞች ግን አልነበሩም። ደስታን የተለማመዱት ጌታን በተቀበሉት ወቅት ነበር። ግን የደስታ ህይወት ወዲያውኑ ተቋረጠ። አንድ ጊዜ አንድ የባፕቲስት አባል የሆነ ክርስቲያንን #ምንም_ደስተኛነት_የማላይብህ_ለምንድን_ነው? ስል ጠየቅሁት #ክርስቲያን_መሆኔን_ደብቄ_በምኖርበት_ሁኔታ_እንዴት_ደስተኛ_ልሆን_እችላለሁ? የሚል መልስ ነበር የሰጠኝ። እያንዳንዱ አማኝ ከድኅንነቱ (ከድነቱ) ያገኘው ይህ ነው የማይባል ደስታ በጥልቅ ልቦናው ውስጥ አለው። ካለው ሁኔታ የተነሳ ግን ይህን ደስታ በውጫዊ መልኩ ሊገልጸው አይችልም።
በነፃው አገር ያሉ ክርስቲያኖች አንድን ሰው ወደ ክርስቶስ ሲያመጡ ወደ ምዕመናን ኅብረትና አንድነት ነው የሚያመጡት። እኛ በኮሚኒስት አገሮች ያለን ክርስቲያኖች ግን አንድን ሰው ወደ ክርስቶስ ስናመጣው እስራት እንደሚጠብቀው በማውቅ ነው። ምናልባትም ልጆቹ ያለ እናትና አባት ይቀሩ ይሆናል። አንድን ሰው ወደ ክርስቶስ ማምጣቱ የራሱ ደስታ ቢኖረውም ለዚህ የምንከፍለው ዋጋ አለ።
ከአዲስ ክርስቲያን ማህበረ-ሰብ ጋር ነው የተዋወቅነው በኅቡዕ ወንጌልን ከሚያስፋፉ ክርስቲያን ማህበረ-ሰብ ጋር።
እዚህ ላይ አንዳንድ አስደናቂ ሁኔታዎች ማንሳት ይቻላል። #ክርስቲያን_ሳይሆኑ_ክርስቲያን_የሆኑ_የሚመስላቸው_እንዳሉ_ሁሉ #ከሃዲ_የሆኑ_ቢመስላቸውም_ከሃዲ_ያልሆኑ_ብዙ_ሰዎች_ገጥመውናል።
አንድ ቀን ከሩስያውያን ባልና ሚስት ጋር እየተጫወትሁ ነበር። የተለያዩ ምስሎችን በድንጋይ የመቅረጽ ሙያ ያላቸው ናቸው። ስለ እግዚአብሔር ልነግራቸው ስጀምር "እኛ ቤዝቦንሽኪ (አምላክ የለሾች) ነን ስለዚህም በእግዚአብሔር ህልውና አናምንም ይሁን እንጂ አንድ ጊዜ ይገጠመንን አስደናቂ ነገር ልንነግርህ እንወዳለን" አሉኝ።
የስታሊንን ሐውልት በመሥራት ላይ በነበርንበት ወቅት ባለቤቴ "#ለመሆኑ_ስለ_አውራ_ጣት_አስበህ_ታውቃለህ? #ሌሎች_ጣቶቻችን_ከአውራ_ጣት_ጋር_በአንድነት_ባይሠሩ_ኖሮ_ምንም_ነገር_ለማንሳት_ባልቻልንም_ነበር፣ #ታዲያ_ይህን_አውራ_ጣት_የሠራው_ማን_ነው? #እኔም_ሆንኩ_አንተ_ማርክሲዝምን_ተምረናል_ሰማይና_ምድርም_ያለአንዳች_አስገኚ_ሀይል_እንደተፈጠሩ_ነው_የተማርነው። #እግዚአብሔር_የሰማይና_የምድር_ፈጣሪ_ባይሆንም_የትንሾ_ጣት_ፍጣሪ_ብቻ_በመሆኑ_እንኳ_ሊመሰገን_የገባዋል።

ምንጭ--- #ለክርስቶስ_ተሰቃየው_የሚለው_መጽሀፍ_ነው።

በተጨማሪ የዩቱብ ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ⏭ super christian tube በማለት ወይም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#ክፍል_15_ይቀጥላል...
#share


#አማላጅ
@superchristiantube7
@superchristiantube7

በአፍሪካ አማላጆች በጣም አስፈላጊዎች ናቸው። ብዙ ልምምዶች በአማላጅ አገልግሎት ዙሪያ ተመሥርተዋል። #አማላጅ_ሁሉት_ሰዎችን_ወይም_ቡድኖችን_ወደ_መስማማት_የሚያመጣ_አካል_ነው። ብዙ የእፍሪካ ጋብቻዎችና አንዳንድ የሥራ ግንኙነቶችም ሳይቀሩ በአማላጅ አማካኝነት የሚፈጸሙ ናቸው። ብዙ ባህላዊ ሀይማኖቶች እግዚአብሔር እንደ አያት ቅድማያት መንፈስ በመሳሰሉ አማላጆች አማካኝነት ብቻ እንጂ በቀጥታ ሊመለክ (ሊቀርቡት) እንደማይቻል ያምናሉ።

በእግዚአብሔር ፊት የሰውን ልጅ፣ በሰው ልጅ ፊት ደግሞ እግዚአብሔርን ሊወክል የሚችለው ማን ነው? የአናሳ መናፍስትን አማላጅነት ሳይጠቀሙ በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ይቻላል? ክርስቲያናዊ ያልሆኑትን ሃይማኖቶች የሚከተሉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የአያት ቅድማያት #መናፍስት #አማልክት #ነቢያት ወይም ሌሎች አዋቂዎች በሰው ልጆችና በእግዚአብሔር መካከል የአማላጅነትን ተግባር እንደሚፈጽሙ ያምናሉ። አንዳንድ ክርስቲያኖችም ሳይቀሩ የሞቱት ክርስቲያኖች ወይም የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል ሊያማልዱ እንደሚችሉ ያምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ይላል (1 ጢሞ. 2÷5)። ይህ ዓረፍተ ነገር በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል እግዚአብሔር የሚቀበለው አንድ ስልጣን ያለው አማላጅ እናዳለ ያመለክታል። እርሱም #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነው። (ዕብ. 9÷15)። ሌሎችን አማላጆች የሚፈልጉ ሰዎች በአጋንታዊ መናፍስት ሊጠበቁ ይችላሉ።

ይህም ክርስቲያኖች ለአማኝ ወዳጆቻቸው ሊጸልዩ አይችሉም ማለት አይደለም። ሊጸልዩ ይችላሉ መጸለይም አለባቸው። ይሁንና የሰውን ልጅ በእግዚአብሔር ፊት የመወከል ሥልጣን ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እግዚአብሔርንም ለሰው ልጅ የመወከል ስልጣን ያለው ክርስቶስ ብቻ ነው። በመስቀል ላይ ሞቶ ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀው እርሱ ብቻ ነው (ቆላ. 1÷19-20)። በተጨማሪም ከክርስቶስ ጋር በሚኖረን የግል ግንኙነት ላይ ካልተመሠረተ ለእግዚአብሔር መጸለዩ ዋጋ የለውም። በኢየሱስ ስም የመጸለይ ትርጉም ይኼ ነው (ዮሐ. 16:24-27)። ጸሎታችን በእግዚአብሔር አብ እንዲደመጥ ሊያደርግ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው። ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ በመናፍስት የማማለዱ አሳብ በጠቅላላው የአጋንት ማታለያ ነው (1 ጢሞ. 4:1)። ይህ ማታለያ አንዳንድ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ግላዊ ግንኙነት እንዳያደርጉ አቅቧል።

📱ይህን መልእክት ለጓደኞቻችሁ #ሼር እንድታደርጉ ለክርስቶስ ባላችሁ ፍቅር እለምናችኋለው📲
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሰፋ ባለ መልኩ ከተለያዩ መጽሐፍት አሰባስቤ በአማላጅነት ዙርያ ላይ የምጽፍላችሁ ቁም ነገር ይኖረኛል። ብሩካን ናችሁ!!!


የፈረንጅ ላም
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7

የቃል ጥናት ጥቅስ:- (ሉቃ. 6÷38)

መጋቢው፣ ለሚለው ትምህርታቸው መጋቢው ይህን ምሳሌ ተጠቀሙ።
አንድ ልጅ የፈረንጅ ላም በ5 ሺህ ብር ለመግዛት አስቦ 50 ሳንቲም በአባቱ ኪስ ማስቀመጥ ጀመረ። የሚያገኘውን ሳንቲም ሁሉ እያስቀመጠ በስድስት ወር ውስጥ አምስት ብር ደረሰ። ታዲያ በዚህ ሁሉ በነጋ በጠባው ልጁ አባቱን #የፈረንጅ_ላም_ለመግዛት_ብሬ_አልሞላም_ወይ? እያለ ይጨቀጭቃል። ዓመት ሲሆነው ብሩ እንኳን አምስት ሺህ ብር ሊሞላ ይቅርና አሥር ብር እንኳን አልሞላለትም። ይህ ትንሽ ልጅ ግን የፈረንጅ ላም የመግዛት ጉጉቱ ስለጨመረ በነጋ በጠባው አባቱን #አልሞላም_ወይ? እያለ መነዝነዙን ቀጠለ። በዚህ ጊዜ አባቱ የልጁ ንዝነዛ ስለበዛበት ከዚህ ሁሉ እኔ ብገዛለት ይሻላል ብሎ 5 ሺህ ብሩን አውጥቶ ገዛለት።
አዎ የእኛ አይሞላምና ከእግዚአብሔር ጋር እናጠራቅም። ያን ጊዜ እግዚአብሔር የልባችንን መሻት ይሞላል። የተትረፈረፈውንና የተጨቆነውን መስፈርያ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም እናየዋለን። ቤታችንም አገራችንም ተባርካ ለሌላውም ዓለም የምንተርፍ ሰዎች እንሆናለን።

(ምሳሌ. 19÷17)
ግጥምጥም:-
አንዱ ምክንያት ለካ ለዚህ ድህነቴ
አለመስጠት ኖሯል ወይኔ ስስቴ።

በተጨማሪ የዩቱብ ቻናላችንን ይጎብኙት👉Super_christian_tube
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


https://vm.tiktok.com/ZMdbJuGcg/
#Shorts #voiceeffects
user4704482265027 (@bekayie7) has created a short video on TikTok with music original sound. | #Shorts #voiceeffects


🤣🤣ቀልድ😂😂 3⃣
#እግዚአብሔርን_ስለመጠበቅ

👊🤛ቦክሰኛ አፍንጫውን ይሰብራል!🤜👊

የቃል ጥናት ጥቅስ ኤር. 29÷11

ውድ የ#super_christian_tube ቤተሰቦች ይህን ትምህርት አዘል የሆነ ቀልድ አንብባችሁ ስትጨርሱ ለጓደኞቻችሁ ሼር ማድረጋችሁን እንዳትረሱ!!
https://t.me/superchristiantube7
https://t.me/superchristiantube7

♈️ሰባኪው ለሚለው ስብከታቸው ቀጣዩን ምሳሌ ተጠቀሙ:-

😂አንዲት ቤት የምትሠራ ሰራተኛ ነበረች። ከእምነቷ የተነሣ ብዙ መንከራተትና ሥራ ማጣት ቢደርስባትም በእምነቷ የጸናች ነበረች። እና ጌታም ለሥራ አንድ ጌታን ከማይወዱ አክራሪ ሰዎች ቤት ውስጥ ከተታት፣ የምትፀልይበትንም ስላጣች ቤተሰቡ መተኛታቸው ካረጋገጠች በኋላ ኩሽና አመድ ላይ ተንበርክካ ትፀልይ ነበር። በዚህ ጊዜ እመቤቷ ከመኝታ ቤታቸው ይሄዱና ጸጉሯን ይዘው ብለው ሄዱ። #ደነገጠች አለች። አሁንም መጥተው አደናቀፉዋት። የመጨረሻም ማስጠንቀቂያ ሰጧት። እርሷም ብላ ስትወስን የጌታ መንፈስ ምስጢር ገለጠላት። #ጉዳዩ_ከድምፅ_አይደለም_አንቺ_ስትንበረከኪ_በሴትየዋ_ውስጥ_ያለው_ሰይጣን_ያውቃልና_ስትሰሚ_ገስጪ_አላት። በደስታ ዘለለች። እንዲህም አለች እንዳለችውም በቀጣዩ ቀን ማታ አመዱ ላይ ተንበርክካ ስፍራ ወደማይወስነው ጌታ ስትጸልይ እሜቴ እንደለመዱት በሩን ከፍተው መጥተው ጸጉሯን ሊይዙ ሲሉ #በኢየሱስ_ስም ስትል እሜቴ ወደቁ። ጸልያላቸው አጋንቱ ለቋቸው ወደ አእምሮአቸው ሲመለሱ ያዩት ነገር የተገላቢጦሽ ሆነባቸው በ60 ብር የቀጠሯት ሠራተኛቸው በክብር ቆማ እሳቸው ሽቶ በጠገበው ቢጃማቸው አመድ ላይ ተንከባለው ባዩ ጊዜ #ልጄ_ምን_ሆኜ_ነው? አሉ። እስሷም #ምን_ያልሆኑት_አለ ብላ ሊገድላቸው ከነበረው አጋንንት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደፈወሳቸውና እርሱን ማመን እንዳለባቸው መናገር ስትጀምር እጇን ይዘው #ነይ_ይህንን_ያዳነኝን_ጌታ_ወንጌል_አመድ_ላይ_አትነግረኚም_ወደ_ሳሎን_ቤት_እንሂድ ብለዋት ሄዱ ያመዱ ዘመን አበቃ።
💯አዎ እግዚአብሔር የሚጎበኝበት ጊዜ አለው እና ባስቀመጠን ቦታ ሳናጉረመርም የፊታችንን ክብር እያየን እናገልግለው 👊ቦክሰኛ አፍንጫውን ይስበራል። በፊት ያለውን ክብሩን እያለመ የዛሬ ውበቱን ያጣል። በአሸናፊነት ክብሩን ይጎናጸፋል። ክርስትናም እንዲሁ እንደሆነ እንድናስተውል ጌታ ይርዳን።

ግጥምጥም:-
#ባስቀመጠን_ቦታ_ብንቆም_ይሻላል÷
#የጊዜው_መከራ_እንደ_ጥላ_ያልፋል።

ምንጭ የሰባኪው ምሳሌ የሚለው መጽሐፍ ነው።

አዳዲስና ቆየት ያሉ አምልኮዎችንና የህፃናት ፕሮግራሞችን ለማግኘት የዩቱብ ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆




🎶ምሳልዬ🎼
አዲስ የክርስቲያኖች መዝሙር
ተለ🀄️🀄️
@superchristiantube7
@superchristiantube7

ለጕደኞቻቹ መዝሙሩን #ሼር አድርጉት

የክርስትናዬ ብርታት መመዘኛ
የቃል የኑሮዬ ውበት መወሰኛ
የረጅም ጉዞዬ ህያው መንገደኛ
ፍጽም ምሳልዬ የምግባሬ ዳኛ

ጌታ ኢየሱስ ምሳልዬ
ጌታ ኢየሱስ ምሳልዬ
ምሳልዬ ነህ
ጌታ ኢየሱስ ምሳልዬ ነህ

ተከትዬ ልጓዝ የግርህን ፍለጋ
ስምህን ታጥቄ ሰልፍህን ልዋጋ
በሞትም ልምሰልህ ለሌሎች ተርፌ
የትንሣኤህን ሀይል ልወቀው አልፌ

ጌታ ኢየሱስ ምሳልዬ.....

የእምነቴ ተቀዳሚ ኗሪ
የእርምጃዬ መሪ
የፍጻምዬ ልኬ ግቤ
ቀማሪ

ጌታ ኢየሱስ ምሳልዬ፡ ምሳሌዬ ነህ....

✅✅✅✅✅መንፈስን የሚያድስ 🎶መዝሙር🎶 ስለሆነ አውርዳችሁ እንድትሰሙት እናበረታታችኋለን✅✅✅✅✅
ሊንኩን በመንካት የዩቱብ ቻናላችንን ይጎብኙት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1


📀 ፍቅርን ከቃል በላይ 📀

ዘማሪ መቻል ወጂ

@superchristiantube7
@superchristiantube7

📱share ማድረጋችሁ አትዘንጉት📲

የዩቱብ ቻናላችንም ቤተሰብ ይሁኑ!!!
🌟https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1🌟


🎚 መንፈስ_ብቻ_አይደለህም🎚
ዶክተር ማሙሻ ፋንታ dr. Mamusha fanta

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1


🎚https://t.me/superchristiantube7🎚
🎚https://t.me/superchristiantube7🎚

ዋና ዋና የእግዚአብሔር መገለጫ ባህርያት

1⃣⚪️ እግዚአብሔር መንፈስ ነው የዮሐንስ ወንጌል 4÷24
2⃣🟢 እግዚአብሔር በራሱ ያለ ነው የዮሐንስ ወንጌል 5÷26
3⃣🟡 እግዚአብሔር ዘላለማዊና የማይለወጥ ነው ትንቢተ ሚልክያስ 3÷6

9ኙ (ዘጠኙ) የእግዚአብሔር መገለጫ ባህርያት
⓵👉 ፍጹም ሀይል ያለው ወይም Elishaday ነው።
⓶👉 በአንድ ጊዜ በሁሉ ቦታ መገኘቱ ነው።
⓷👉 ያልተገደበ እውቀት ባለቤት መሆኑ ነው። መዝሙረ ዳዊት 139÷1-3
⓸👉 ቅዱስ ነው።
⓹👉 ጻድቅ ነው።
⓺👉 እውነት ነው።
➆👉 ፍቅር ነው።
⓼👉 የኪዳን አምላክ ነው።
➈👉 የሰማይ የምድር ፈጣሪ ነው።

🔸እግዚአብሔር በስሞቹ ውስጥ ይገለጣል🔹
የመጀመርያው ሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች:-
➊ ኤሎሂም-🌎እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው ማለት ነው።🌏
❷ ያህዌ ጀሆቫ (ጌታ አምላክ)
#ያህዌ_ራሱን_የገለጠ _ራሱ_የሚኖር_ነው።
#ያህዌ_የኪዳን_አምላክ_ነው።
➌ አዶናይ -ሎዓላዊ ጌታ ማለት ነው።

በኤል የሚጠሩ ስሞቹ

➽ኤልሻዳይ
➤#እግዚአብሔር_ሁሉን_ቻይ_ማለት_ነው።
➤#የእናት_ጡት_ያለው_ተሸካሚ_አባት_ማለት_ነው።
➤#ለመኖር_አስፈላጊ_የሆኑትን_ምግብ_የሚያቀርብ_ማለት_ነው።
➤#በቂ_ከበቂ_በላይ_የሆነ_ማለት_ነው።

➽ኤል ኤሊዖን
➤#ልዑል_እግዚአብሔር_ማለት_ነው።

➽ኤል ኦላም
➤#ዘላለማዊ_ጸንቶ_የሚኖር_ማለት_ነው።

ያህዌ በሚል ስም የሚጠሩ ስሞቹ:-
ያህዌ የቃል ኪዳን ስሙ ነው

➽ያህዌ ኤሎሄም
➤ጌታ አምላክ ማለት ነው።
➤#ፈጣሪ፣ #አለቃ፣ #ገዢ እንደማለት ነው።

➽አዶናይ ያህዌ
➽ያህዌ ሰባኦት
➤ሁሉ በሁሉ የሆነ ጌታ ማለት ነው።
➤የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ማለት ነው።

7ቱ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ስሞቹ:-

1⃣ ያህዌ ጃራ➤እግዚአብሔር ያቀርባል (ያዘጋጃል) ማለት ነው።
2⃣ ያህዌ ነሲ➤ ጌታ አርማዬ (መታወቂያዬ) ማለት ነው።
3⃣ ያህዌ ሻሎም➤ እግዚአብሔር ሰላም ነው ማለት ነው።
4⃣ ያህዌ ሮሂ➤ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው እንደማለት ነው።
5⃣ ያህዌ ጽድቀኑ➤ እግዚአብሔር ጸቃችን ነው ማለት ነው።
6⃣ ያህዌ ሻማ➤ እግዚአብሔር እዚያ አለ ማለት ነው።
7⃣ ያህዌ ራፋ➤ እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው እንደማለት ነው

የዩቱብ ቻናላችንን የቀላቀሉት super christian tube በማለት ወይም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


እምነትና ሥራ #ክፍል_1
🎚https://t.me/superchristiantube7🎚
🎚https://t.me/superchristiantube7🎚

✍ ሰው የጽድቅን መንገድ የሚጀምረው በእምነት ነው። የጽድቅን መንገድ የሚጀምረው ብቻ ሳይሆን የጽድቅን መንገድ የሚጨርሰውም በእምነት ነው።
✍ አንድ ሰው በእምነት አማካይነት ሲጸድቅ የጸደቀበት አምነት አጽድቆ ብቻ የሚያስቀምጥ ሳይሆን በቀጣይነት በህይወቱ የሚገልጣቸው ሥራዎችም አሉ: በመሠረታዊ ደረጃ በክርስትና ሕይወት ውስጥ ለዘመናት እያጨቃጨቁ የኖሩ ሀሳቦች ቢኖሩም መዳን በሥራ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች አሉ: ሲቀጥል ደግሞ መዳን በእምነት ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎችም አሉ። እምነት + ምንም = ድነት ብለው የሚሉ ማለት ነው። እነዚህ ሁሉት ሀሳቦች በአመታት መካከል ሲያጨቃጭቁ የኖሩ ሀሳቦች ናቸው።
✍ እንደ ክርስቲያን በሥራ ባንድንም ለሥራ ግን ድነናል፧ ሠርተን አይደለም የዳንነው ግን ስንድን ልንሠራ ነው የዳንነው። አምኛለው የሚል ሰው አምኖ ብቻ የሚቀመጥ ሳይሆን በእምነቱ አማካይነት የተቀበለው መንፈስ ቅዱስ ወደሚያፈራቸው የእምነት ፍሬዎች ማደግ አለበት።
✍ እምነት የዘላለምን ህይወት ነው ለሰው የሚሰጠው። ህይወት ደግሞ ሕይወትነቱ የሚታወቀው በእድገትና በማፍራት ነው፧ የማያድግና የማያፈራ ነገር የሞተ ብቻ ነው። አታድግም፣ አታፈራም ማለት በህይወት የለህም ማለት ነው ምክንያቱም የተቀበልከው ህይወት ያድጋል ያፈራል።
✍🥇 ለመዳን እምነት + ምንም = ድነት ብለው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፧ ከዚህ የተነሣ የዳንኩት ያለሥራ ነው ስለዚህም የምኖረውም ያለሥራ ነው ብለው ይናገራሉ። በሌላ ጥግ ደግሞ ሐዋርያው ያዕቆብ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው ብሎ ይፅፋል።
✍ እምነት ሲነሣ ሊረሳ የማይችል ነገር ቢኖር ሥራ ነው። እምነትና ስራ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው። እምነትና ሥራ አንበስና ዘውድ ናቸው። ዘውድ በሌለበት አንበስ እንደማይዘረዘር ሁሉ ሥራ በሌለበት እምነትም አይዘረዘርም።
✍ #ሐጢአተኛ_የሚድነው_በእምነት_ነው ። #ሰው_እግዚአብሔርን_ደስ_ማሰኘት_የሚችለው_በእምነት_ነው። #በእምነት_ያልሆነ_ነገር_ሐጢአት_ነው። #አማኝ_በህይውት_ሊኖር_የሚችለው_በእምነት_ነው። እነዚህ ነገሮች መሠረታዊ ነገሮች ቢሆኑም
✍✳️ አምነት ማለት ያለምንም ማረጋገጫ አንድን ነገር ማመን ማለት አይደለም ነገር ግን የሚያስከትለው ምንም ይሆን መታዘዝ ማለት ነው።

#ምንጭ____ከአገልጋይ_ዮናታን_ስብከት

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ 🤌👉super_christian_tube
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍


#ክፍል_13
ጴጥሮስና ጳውሎስ እነማን ነበሩ? አልኳቸው የመለሰልኝ ግን አልነበረም...እኔም ✔️@superchristiantube7✔️
✔️@superchristiantube7✔️
እኔም ጴጥሮስና ጳውሎስ እነማን እንደነበሩ በመናገር ላይ እያለሁ ከሽማግሌዎቹ ወታደሮች አንዱ አቋረጠኝና #ፊቱንም_አንተ_የመጣኸው_ሰዓት_ለመግዛት_ሳይሆን_ስለ_ሀይማኖት_ለመስበክ_ነው: #እስቲ_እርፍ_በልና_ንገረን_ግን_ልብ_አድርግ_እዚህ_አከባቢ_ያሉት_ሁሉም_ደኅና_ሰዎች_ናቸው_ከማን_መጠንቀቅ_እንዳለብን_ስለምናውቅ_እጄን_ጉልበትህ_ላይ_ሳደርግ_ስለ_ሰዓት_ተናገር_እጄን_ከጉልበትህ_ሳነሣ_ግን_ካቆምክበት_ስብከትህን_ቀጥል_አለኝ። ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እኔም ስለ ጳውሎስና ሰለ ጴጥሮስ እነርሱም ሲያገለግሉት ስለ ነበረው ክርስቶስ ነገርኳቸው የማይተማመኑበት ሰው ወደ አጠገባችን ሲመጣ ያ ወታደር እጁን ጉልበቴ ላይ ያደርጋል: እኔም ስብከቴን አቋርጥና ሰለ ሰዓት አወራለሁ። ተጠርጣሪው ሲሄድ ደግሞ ካቆምኩበት ስፍራ ስለ ኢየሱስ አዳኝነት መስበኬን እቀጥላለሁ። በካምፑ ውስጥ በነበሩ ክርስቲያን ሩስያውያን አማካይነት በተደጋጋሚ እየሄድሁ ወንጌል ስለ ሰበኩሁላቸው ብዙዎች ጌታን ተቀበሉ ብዙ ቅዱሳት መጽሐፍትንም አሠራጨን።
ምንም እንኳ ብዙ የእምነት ወንድሞቻችናኗንና እህቶቻችን በተለያየ ሁኔታ ወንጌልን ሲሰብኩ በመገኘታቸው ቢደበደቡም አነርሱ ግን ስለ ጌታ ኢየሱስ አዳኝነት መመስከራቸውን ለማቆምም ሆነ ሌሎችን አሳልፈው ለመስጠት አልፈለጉም።
በዚህ እንቅስቃሴያችን በሩስያ ውስጥ እንደ እኛ ወንጌልን በኅቡዕ ያስፋፉ የነበሩ ክርስቲያኖችን አገኘን ስለ ስራ ልምዳቸውም ያካፈሉን ሀሳብ በጣም ነበር የጠቀመን። እነዚህ ክርስቲያኖች ለብዙ አመታት ኮሚኒስታዊ የክህደት ትምህርት ሲስፋፋበት በነበረ አገር የኖሩ ናቸው። አንዳንዶቹም በኮሚኒስት ዩኒቨርስቲዎች የተማሩ ነበሩ። ይሁን እንጂ ዓሣ በጨው ባህር ውስጥ ቢኖርም ዓሳነቱ ተለውጦ ጨው እንደማይሆን ሁሉ እነዚህ ወገኖች በኮሚኒስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሩ ቢሆኑም እምነታቸውን አልካዱም። በክርስቶስ ኃይል ነፍሳቸውን በቅድስና ጠብቀዋል።
እነዚህ ሩስያውያን ክርስቲያኖች #በባርኔጣችን_ላይ_ያለው_መዶሻና_ኮከብ_የክርስቶስ_ተቃዋሚ_ዓርማ_እንደሆነ_እናውቃለን_ሆኖም_ምንም_ማድረግ_አንችልም በማለት ሲናገሩ በታላቅ ሀዘን ነው። በሩስያውያን ወታደሮች መካከል ወንጌልን እንድንሰብክ ክፍተኛ ድጋፍ ያደረጉልኝ እነዚህ ወገኖች ነበሩ።

#ምንጭ_______ለክርስቶስ_ተሰቃየው የሚለው መጽሐፍ ነው

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉Super_Christian_Tube
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕
#ክፍል_14_የቀጥላል. . .


ስለነቢዩ ሙሃመድ መታወቅ ያለባቸው 6 ነገሮች:-
@superchristiantube7
@superchristiantube7
1👉 ገና እድሜያቸው ከሁለት አመት በታች እያሉም ሰይጣን ነበረባቸው።
ሳሂም ሙስሊም 1: 311 አንብቡ✔️

2 👉 ወደ ሰይጣኖች መንደር ተጋብዘው ይሄዱ አብረዋቸውም ያድሩ ነበር። ስሞታቸውንም ሰምተው ትእዛዝ ያወጡ ነበር። ወንድማማችነት በመካከላቸው ተፈጥሯል፣ የእርሳቸው ቁራኛ ሰይጣን ይህንን አድርግ ያንን ተው ይላቸው ነበር። ሳሂህ ሙስሊም 39:6757✔️ አንብብ

3👉 አላህ እንዴት አሳቡን በእርሱ ላይ እንዴት እንደቀየረ ባይታወቅም ነብዩ ሙሃመድን ለሰይጣን መልእክተኛ አድርጎ ላካቸው። አላህ ሰይጣንን በረገመው ሰዓት ምን እንደተነጋገሩ መዘንጋት የለብንም።
ሱረቱል አል-ሂጅር 15: 35-39
ሱረቱል ዩሱፍ 12: 104☑️✔️

4👉 ሰይጣን እንዳለባቸው ከሰይጣን ተጽዕኖ ነጻ መሆን ለአነርሱ ከባድ መሆኑን ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ይነግሯቸዋል።
How to protect youself from jinn & shaytan page 34
ሳሂም ሙስሊም 39: 6757✔️✔️☑️

5👉 ቁራኛ የተደረገባቸውን ሰይጣንን በበላይነት መርግጥ ይቅርና ወደ ክፋ እንዳይወሰውሳቸው ማስለም እጅግ ከባድ መሆኑን፣ ገነት መግባትም ለአንድ ሙስሊም ጭንቅ መሆኑን፣ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከቁራኛቸው እንደ ማይላቀቁ፣ ይህ ሁሉ ከአላህ ውሳኔ የተደነገገባቸው መሆኑን ሰብከዋቸዋል። ሱረቱል አል-ዝህሩፍ 43:36-38፣ ሱረቱል ሓ ሚም አል-ሰጅዳህ 41:25☑️✔️✔️

6👉 በአገልግሎት ዘመናቸውም ሰይጣን ነበረባቸው። ስለነበረባቸው ነው ሰይጣን አለባችሁ እኔም አለብኝ እያሉ የተናገሩት። ለአንድ አመት ሙሉ ከሚስታቸው ጋር ሳይሆን ከማይታይ አካል ጋር ወሲብ ይፈጽሞ የነበረው መቼም ሳይሆን በአገልግሎታቸው ዘመን ነው። ነቢይነታቸው ከዚህ የድግምት ጥቃት አላዳናቸውም ነበር። ሳሂህ አል-ቡኻሪ 71: 660 ቅጽ 7
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕🖕


ክፍል ⓬
✝️
https://t.me/superchristiantube7✝️

የወንጌል ስብከት በወታደሮች ካምፕ ውስጥ

ለሩሲያውያን የምንሰጠው የወንጌል አገልግሎት በግለሰብ ምስክርነት ብቻ አልተወሰነም: መጠነኛ ስብሰባ በማድረግ ማስተማር ጀምረን ነበር።
ለሩሲያውያን የእጅ ሰዓት ብርቃቸው ስለነበር በየመንገዱ ከሚያገኙት አላፊ አግዳሚ ሁሉ ሰዓት የማስፈታት ልምድ ነበራቸው የሪሲያ ወታደሮችን ብዙ የተለያዩ ሰዓቶችን በሁለት እጃቸው አድርገው መመልከት የተለመደ ጉዳይ ነበር። አንዳንድ ሩሲያውያን ሴት ባለሥልጣኖች የጠረጴዛ ሰዓት እንደ ሀብል ሁሉ አንገታቸው ላይ አጥልቀው ይታያሉ። ከዚህ በፊት ሰዓት ስላልነበራቸው አጋብሰው አይረኩም። በካምፓቸው ውስጥ የተሰረቁ ወይም የተዘረፉ ሰዓቶች ይሸጡ ስለነበር ሰዓት የሚፈልጉ ሩማንያውያን ወደ ካምፕ በመሄድ አማርጠው ይገዛሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የተሠረቀባቸውን ወይም የጠፋባቸውን የራሳቸውን ሰዓት ገዝተው ይመለሳሉ። እኛም ሰዓት ለመግዛት በሚል ሽፋን ወደ ካምፕ እንሄድና አጋጣሚው ሲመቸን ወንጌል እንሰብካለን።
በበኩሌ ወደ ካምፑ የሄድሁት ጴጥሮስ ወጳውሎስ የሚባል የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በዓል በሚከበርበት ጊዜ ነበር ወደ ካምፑ የገባሁት ሰዓት ለመግዛት በሚል ሰበብ በመሆኑ አንዱን ከአንዱ በማማረጥ አንዱን በጣም ውድ ነው ሌላውን በጣም ትንሽ ነው ሌላውን ደግሞ በጣም ትልቅና ከርፋፋ ነው በማለት ሁኔታዎችን አመቻች ጀመር። ብዙ ሰዓት ሻጭ ወታደሮች ከበቡኝ እያንዳንዱ #ይሄኛው_ይሻልሃል_ይሄኛው_በጣም_ጥራት_ያለውና_ዋጋውም_መጠነኛ_ነው እያሉ ሰዓታቸውን ያቀርቡልኝ ነበር። እኔም ፊቱንም የሄድኩት ሰዓት ለመግዛት አልነበረምና #ለመሆኑ_ከእናንተ_መካከል_ጳውሎስ_ወይም_ጴጥሮስ_የሚባል_ይኖራል? በማለት ጠየቅኳቸው። በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች #አዎን ይሚል መልስ ሰጡኝ። ወድያውኑ ቀጠል አደረግሁና #ዛሬ_የሩሲያ_ኦርቶዶክስ_ቤተክርስቲያን_የጳጥሮስ_ወጳውሎስ_ቀን_የምታከብርበት_ዕለት_መሆኑን_ታውቃላችሁ? አልኳቸው ከሽማግሌዎች በቀር ወጣቶቹ እንደማያውቁ ነገሩኝ። ጴጥሮስና ጳውሎስ እነማን ነበሩ? አልኳቸው የመለሰልኝ ግን አልነበረም...እኔም

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉super christian tube ወይም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

#ክፍል_13_ይቀጥላል

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

220

obunachilar
Kanal statistikasi