*ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ*
*ክፍል 2*
√ *_የዘካተል ፊጥር መጠን_*
ኢብኑ ዑመር ሀዲስ ላይ እንዲህ የሚል መልዕክት ተላልፎል:- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› በእያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያ፣ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡››(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ሷዕ የመስፈሪያ አይነት ሲሆን በድሮ ጊዜ የነበረ የእህል መስፈሪያ ነው። በዘመናዊ መለኪያ አንድ ‹‹ሷዕ›› 2.04-2.5 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ 1ሷዕ = 4 የሁለት ዕጅ እፍኞች ነው።
√ *_ዘካተል ፊጥር በማን ላይ ግዴታ ይሆናል?_*
ዘካተል ፊጥር ግዴታ የሚሆነው ሁለት መስፈርቶችን ባሟላ ሰው ላይ ብቻ ነው። እነርሱም:- 1ኛ\ ሙስሊም በሆነ 2ኛ\ ዘካተል ፊጥር ማውጣት ግዴታ በሚሆንበት ቀን እና ሌሊት፤ ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ የሚበቃ መብል ኖሮት የተረፈው እና ተጨማሪ ነገር ያለው ነው፡፡
√ *_ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው መቼ ነው?_*
ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ሲሆን፤ ማውጣቱ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት የሚጀምረው ከረመዳን የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ ነው፡፡ ነገር ግን ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች ያደርጉት እንነበረው ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ይፈቅዳል፡፡
ክፍል 3 ይቀጥላል…
✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*
👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!
t.me/tahaahmed9