"ፍለጋ"
ማልጄ ወጥቼ
ከደጄ ባሻገር ካለው
ተራራ አናት ዘውትር
የምቆመው
ወሬ ሽቼ አይደለም
አንቺን አይ ብዬ ነው።
ከዱር ከገደሉ
ከጋራ ሸንተረር
ስባዝን 'ምውለው
ዙረት እኮ አይደለም
አንቺን እያሰስኩ ነው።
ከባህር ከውቅያኖስ
ከሃይቅ ከወንዙ
ስጠልቅ የምከርመው
ዋና አምሮኝ አይደለም
አንቺን ስፈልግ ነው።
የማትመጪ እንደሁ
ወይ የማላገኝሽ
ላኪብኝ እባክሽ
ትርፍ እድሜ የለኝም
ከፍለጋው ድካም
ለኔ አይብስብኝም
"አልመጣም!" ብትዪኝ
የምስራች እንጂ
መርዶ አይሆንብኝም!!
---------❤-------
@tigiwaaa
@tigiwaaa
ማልጄ ወጥቼ
ከደጄ ባሻገር ካለው
ተራራ አናት ዘውትር
የምቆመው
ወሬ ሽቼ አይደለም
አንቺን አይ ብዬ ነው።
ከዱር ከገደሉ
ከጋራ ሸንተረር
ስባዝን 'ምውለው
ዙረት እኮ አይደለም
አንቺን እያሰስኩ ነው።
ከባህር ከውቅያኖስ
ከሃይቅ ከወንዙ
ስጠልቅ የምከርመው
ዋና አምሮኝ አይደለም
አንቺን ስፈልግ ነው።
የማትመጪ እንደሁ
ወይ የማላገኝሽ
ላኪብኝ እባክሽ
ትርፍ እድሜ የለኝም
ከፍለጋው ድካም
ለኔ አይብስብኝም
"አልመጣም!" ብትዪኝ
የምስራች እንጂ
መርዶ አይሆንብኝም!!
---------❤-------
@tigiwaaa
@tigiwaaa