🧑‍🎤 የሀድራ ግጥሞች✍


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


ልትልኩልን የምትፈልጉ
በዚህ @Yehadragtmoch_bot ያድርሱን::

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መሕፉዝ ዓብዱ እና ሙዓዝ ሐቢብ || ያ ሙስጦፋ አል አናሚ || የመጅሊስ ላይ መንዙማ

@yehadra_gtmoch \\ የሀድራ ግጥሞች


Hik promo dan repost




Salah promotion dan repost
❤ አምስት ቤተሰብ ያለበት ቤት ውስጥ አራት ዳቦ ካለ...
እናት 'እኔኮ ዳቦ አልወድም ትላለች'
❤❤❤

💛እናቴ ወላሂ እወድሻለዉ💛

እስኪ እናቱን የሚወድ💛


😍😍😍😍😍
ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ;

❤የመዲናውን ; ባየነው አይኑን
በኑር አረንጓዴ ; የተኳለውን

❤የውነት ከሆነ እኔ ; አንቱን መውደዴ
ሀበሻ ምድር ላይ ; አትፈርስም ጀሰዴ

❤አልሀምዱ ሊላሂ ; ልንዘክራችን
ያየኑር ጡሩራ ; የጀነት ቁልፉን
የድል ሁላ ቤቱን ; የጥሜት ሰይፉን
ካፋፍ ላይ አወጣው ; ሰው አህባቦቹን
ያለ እርሱ ወገን ; ሌላ የለኝ እኔ


❤ጌታየዋ ሸውቁ ; ሩሄን ቢያቃጥላት
ወንጀሌ ተሀድራው ; ደሞ ቢነጥላት
ዪቺን አበጀሁኝ ; እንድንሞጥላት
ከዚያ ባንቱ ሀድራ ; አላህ ቢቀጥላት
አንቱን ካዬች ወዲያ ; ብትሞትም እንዳሻት

❤ወርውሮ የመታኝ ; በሙሀባው ሎሎ
ልቤን የረገጠው ; ሌላ አካሌን ዘሎ
ሀያራ ሱካራ ; ያረገኝ አግሎ
ማንም አረታኝም ; እሱን አስመስሎ
ዉቡን ሁላ አዝሎ ; ወደቁለት እኔ

❤ሷሂቡል ኢህሳኒ ; ሀቢቡ ረህማኒ
ነሩ እሚንቧለቀው ; ፊኩሊ ዘማኒ
የፊቱን ብልጭታ ; ቢያሳየን መናኔ
ይሄ ነው ሀጃዬ ; መስከረምም ሰኔ
ቅረቡኝ ወደ ኔ ; እንዳልወድቅ ከኋላ

❤የሷሊሆች ቀለብ ; የደጎች መደድ
በስሙ ይነሳል ; ሙላውም ሀሲድ j
ባንቱ ነው ሚጠራው ; የኔም ጉዳጉድ
ላንቱ ስወዘወዝ ; ሌላው ቢለኝ እብድ
ቀስዴ ነው በለህድ ; አንቱን ማግኜት እኔ

❤ነቢ ለኔ ብለው ; የዋሉት ውለታ
መች ተከፍሎ ያልቃል ; እስከ ቂያማ ለታ
እኔ ልራብሎ ; እኔ ልንገላታ
እኔው ድንጋይ ልሰር ; ሆኜ ባንቱ ቦታ
እኔው ላልቅስሎ ; ብዬ ዋኔ ዋኔ

ኩራቴዋ ነቢ
ደስታዬ ደስታዬ

❤የትልቅ ሰው እቃ ; የተቀበለ ሰው
ምንድን ማረፊያ አለው ; አፈር እስኪያለብሰው
ተማር ይጣፍጣል ; መድሁን ለቀመሰው
ሙሂቦ ቢጠጣው ; የማይጨረሰው
ጫማዎን ልላሰው ; ይከፈል ሀዘኔ

ወረቴዋ ነቢ
ወዳጄ ወዳጄ

❤ልፈልግ ዘመድ ; መርጬ ወንድ ወንድ
በሀድራ እሚጣድ ; በፍቅሮ እሚርድ
በነቢ ሙሀባ ; እምባ የሚያወርድ
በፍቅሮ ይለካል ; ሴትም ሆነ ወንድ
የሌለው መውደድ ; ስሙን አላቅ እኔ

❤ደርቦ የኖረው ; የሀቁን ልባስ
ኸልቆ ያደመቀው ; ጌታችን ቅዱስ
በርሱ የሚነፍሰው ; የተውሂድ ንፋስ
ሹመተ ገናና ; የጦይባው አሩስ
በሙሀባው ልብስ ; አልብሱኝ ያዘይኔ

ወለላው ነብዬ

❤ሙሂቡ በሸውቁ ; በሀሳብ ገስግሶ
ሌላውን እረስቶ ; ወስጡ ተረስርሶ
የዱንያ ጉልላት ; ከልቡ ላይ ፈርሶ
ያንቱ ሙሀባ ሟች ; እንባው አልቆ ፈሶ
ይታያል ታድሶ ; በስሙህ ብያኔ

ደስታዬዋ ነቢ;
ወረቴዋ ነቢ;

❤ዳኢም ሚጋረፈው ; የሁብሁ ወላፈን
በኛም ላይ ዘነቡ ; ምነው በሸወቀን
ወዳጆቹ ጋራ ; የፊቱ ወጋገን
ጮራው ያልተለዬው ; በሌሊትም በቀን
ያኔ እኛም ተመርጠን ; ባሳመሩን ዘይኔ

❤እርግጥ ነው ባንቱ ; ላይ አለ የኑር ነገር
ለሙሂቦች እንጂ ; ለኔ ማይነገር
በርሱ ተቋድሰው ነው ; ያገኙት መከበር
በዱንያ ላይ ሁኖ ; የኔ መደናበር
በወንጀል ወታደር ; በዛ መታደኔ

ረውዷው ነብዬ

❤በመኳያው ኩሎ ; አህሉ ቢያደርገኝ
ፊት እንዳጠጣቸው ; ለኔም ቢግተኝ
በውዱ ባህር ላይ ; ጠምቆ ቢያስዋኜኝ
ይሄ ነው ሀጃዬ ; ሌላም አልመኝ
ጠረኑ ይድረሰኝ ; ኸፈላዬ ይንደድ

❤ከደጁ ላይ ቁሟል ; የውዱህ እንግዳ
ባትችልም መዴ ; ባይጠናላት ክንዷ
ነው ከወዳጆቹ ; ከአባቶቿ ለምዳ
ፈይዱን የገበዩት ; በጧት በማለዳ
ካገኙት ሰዐዳ ; መቅመስ በመውደዴ

❤ቀሀዋ አይል ጫካ ; ባንቱ ተመንጥሮ
እንደሌላው ሳይሆን ; ዳኢም በንጉርጉሮ
እንዳንቱ ማን አለ ; የሚያሳምር ኑሮ
ነጃ አውጡኝ ሰይዲ ; ከጥሜት ማሰሮ
የሀሲድ ቋጠሮ ; ይበጣጠስ ከኔ

❤ሰይዲ አደራሁን ; ጣሉብኝ ጥላሁን
ቢሆን መሀያሁን ; አለዛ ጦይፍሁን
ውዴታሁ እሚባል ; አጣብቀው ሁዳሁን
ደህና መስያለሁ ; ታምሚያለሁ አሁን
ና በሉኝ ፊትሁን ; እንቅልፉን ይፍጅ አይኔ

❤ለጂሀድ ሲነሱ ; ሁኜ ከጎንሁ
ካንቱ ጋር ባበርኩኝ ; እንደ አስሀባሁ
እንደ አቡዱ ጃና ; ሁኜ ከፊትሁ
ጥቃት መመለሻ ; ሁኜ እንደ ጋሻሁ
ይፍሰስሎት ደሜ ; እንደ አባይ ይውረድ

❤ለመውሊዱ ድንኳን ; ልሁንለት ማገር
ኸልቁ ተመችቶት ; አንቱን እንዲዘክር
የጎጆዬ አጠና ; ተሰብሮ ይማገር
ልብሴም መሬት ይውደቅ ;ይነጠፍ ለመውሊድ
አህባቡ በሶፋ ; እንዲሎት አህመዴ

❤ለመውሊዱ አጪጄ ; እህሉን ኡጓሮ
በጀርባዬ አስሬ ; ውሀ በማሰሮ
ለአህባቦቹ ሂድሚያ ; እግሬ ቁሞ አድሮ
ከቀልቤ ላይ ይርገፍ ; ደሜ ተመንጥሮ
ሩሄ ጅስሜ አምሮ ; በአይኔ ልዮት ዘይኔ

❤አሰላም አለይኩም ; አህመድ ብልሀቴ
በዱንያ ዙረት ላይ ; የዘለው ጉልበቴ
መውሊድ ያድሰዋል ; ሙላወን ጉድለቴ
አመቱን ስጠብቅ ; በዛ መጎዳቴ
ይሙላ ፍላጎቴ ; ልበል ጉድ ጉድ

❤የቀረበ ጊዜ ; ረቢዒል አወል
ሙሀባን ያዘለ ; ንፋስ ይነፍሳል
ሙዕሚን ቀልበ ; ጥሩ ያኔ ይደሳል
ደግሞ ሸይጧን ጭፍራው ; ደስታው ይነሳል
ብሎ ያለቅሳል ; ዋ ጉዴ ዋ ጉዴ

ወለላው ነብዬ;

❤ሩሄ ዝቅ ብሎ ; ወድቆ እንደ መሬት
አስሬ ተሺጬ ; እኔ ለባርነት
በማወጣው ዋጋ ; መውሊዱ ይውጣበት
ተምኪንን እሻለሁ ; ለሩሄ ሽልማት
ጀማልሁን ማየት ; ይሁን እጣ የኔ

❤መውሊዱን ከምንቅ ; አፈሩ ይብላኝ
ጉድጓድ ትግባ ነፍሴ ; ምቾት ይራቀኝ
መቆም እስኪያቅተኝ ; ጉልበቴ ይክዳኝ
ከአንቱ ሌላ ደስታ ; እኔ ምን አለኝ
ዘይኔ ና በሉኝ ; ተቋደስ ከማድ

❤የመውሊዶን ጠላት ; ልምታው እንደ ድቢ
እኔ እንድወዛወዝ ; እርሱን አንገብግቤ
ቢሰራ ነው እንጂ ; ቀልቡ እንደ ሹርቤ
በወንጀል ቢጠለፍ ; ሩሁ እንደጋቢ
የኸይራቱን ግቢ ; የመጣው ሊያነድ

❤ቢወርድ ለኢሳ ; ከሰማዩ ማድ
ጌታን ለማመስገን ; አደረጉት ኢድ
ምግብም ከተገባው ; ይሄን ያህል ሀምድ
እንዴት ይዘነጋል ; ያንቱ መወለድ
እናከብረዋለን ; እስክንገባ ለህድ

❤ሶላትና ሰላም ; በሞላው ቁጥር
ከሰማይ ምድር ; ባረከው ስፍር
ከሳር ቅጠል በልጠው ; ካሸዋ ክምር
በኸልቁ ሁላ እድሜ ; ቆጥሮ ዘር ማንዘር
አውርደው ቃዲር ; ረህመቱን በዘይኔ

😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ

😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😘ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ
😍ሙሀመድ ነብዬ:
ሶለሏህ ዐላ

#Al burda jeme'a

👏👏👏👏👏👏👏👏
@yehadra_gtmoch
👏👏👏👏👏👏👏👏






አላሁ ያአላህ
👏👏ያአላህ ያአላህ
አላሁ ያአላህ
👏ያአላህ ያአላህ(2x)

በሰርግ ላይ ሰርግ
በሊካ ላይ ሊካ 2x)
አላህ ይወፍቀን
የዘዋጅ በረካ (2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
የዛሬው ሙሽራ
በስሟ አትጥራት(2x)
ስሟን ቀየር አርገህ
ሀቢብቲ በላት(2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
በነብዩ ሱና
ሰርጋቸው ሲከበር(2x)
ምንኛ ደስ ይላል
እንበል አላሁ አክበር(2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
አርሂቡ በያቸው
መቷል ያንቺው ጀግና(2x)
የፍቅራቹ ሚዛን
በሀላላል ሱና(2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ኢንሻአላህ በይው
በኢማን ቁሚና(2x)
እንምጣ መዲና
አንቱ ያነቢና(2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ማሻአላህ በሏቸው
እልል በሉላቸው(2x)
የኢማኑን ግማሽ
ጀሊሉ ሰጣቸው(2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
የሚያምር አህላቅ
እንዲማሩልን(2x)
ቁርአን እናስተምር
ሀዲስ ይያዙልን(2x)
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

@yehadra_gtmoch
@yehadra_gtmoch


ሰለላ ወሰሌ ማላ ዘይኔ አሚና
ሰለላ ወሰሌ ማላ ሸምሰል መዲና


ሀምደን ሊረቢል አለሚን
ጠበቀ ቀለሜ እንደገና

በፊት መንዙማ ቀጥሎ
ልከምል ብሎ በደህና

እንዲሰጠኝ ነፃነቴ
በህፃናቴ እንድዘፍና

ሰላት ሰላምን በነቢ
አውርድ ያረቢ መውላና

ወአለል አሊ ወል አስሀብ
ወአለል አህባብ ከል ሙድና

ዘይኔ መንበዑል በረካ
ሄጄ ላሳካ ልመና

በዛሬ ቅዳሜ እንዲሆን
ፍቃዱን አዘናልና

በዛሬ ቅዳሜ ፍታኝ
አስደስተኝ ልፈታና

እንደው በነፃ ፍቱኝ
አሰናብቱኝ በደህና

ልግለፅ ፊቴ በደስታ
በእልልታ በምስጋና

ሰለላአለይ ወሰለም
እንደነሱ የለንቀብና

በደህና ተቀበሉኝ
ልቀቁኝ ልበል ቀና

ዛሬ ያለማመናታት
መፈታት ሸልሙኝና

ልፈንጥዝ ካህባቦቼ ጋር
በሊቃ ባዝካር በደህና

ከሙሉ ነፃነቴ ጋር
ቀን ሆነ አዳር ልዝከራ

ደስታዬ ለወገኖቼ
ላህባቦቼ ላልብስና

ይኑሩ እንደለበሱ
ወደነሱ ልድረስና

በቃላ በኮለን ዞሬ
ሀገሬን ላሰልፍና

ልግባ በሬሳ ከተማ
እነ ከተማ እነ ዳና

ፈለሁመቹ ያልኳቸው
ደስታቸው ገይረ መምኑና

ይኸው ዘለኩ ብንጠራራ
ሄደ ተጠራ ጎዳና

ሰለላአለይ ወሰለም
እንደነሱ የለንቀብና

በደህና ተቀበሉኝ
አውጡኝ በዪ ፈተና

የምትል ስለስራት
ልንገርለት እንደጠና

አሁን ባለፉት ዘመናት
በብዙ ፍርሀት ኖርኩና

ወጥቼ በገዛ አገሬ
በዘሬም ተለየሁና

ሰምተው ነበር በመቅናቴ
ያውም በሳዳቴ ዝና

ሁላቸው ተደናበሩ
ግርግሩ አበዙና

አድመው በሸር ፈለጉኝ
ሊገድሉኝም አሰቡና

ከተንኮላቸው ሰወረኝ
ጠብቆኝ አኖረኝና

ካሰጋኝ ሁሉ ጠበቀኝ
አዘለቀኝ ጠበቀና

ተቀበሉኝ በመፈታት
ነፃነት ሸልሙኝና

አርግዤ ዘይኔ ሙስጠፋ
ስለፋ ተሸከምኩና

ብዙ ሺ አመት ሰይዲ
በሆዴ አሳደኩና

በምጡ ብቻ ያለ እረፍት
ሦስት አመት ተጨነኩና

ባለፉት ሦስት ወራት
ለእስራት ተሞከርኩና

መብራት እያለ ጠፍቶብኝ
ጥሎብኝ የምጥ ፈተና

ካሚነተል ወብ ብሶብኝ
መውለድ ደርሶብኝ ሸምሰና

ሚያስወልደኝ አጥቼ
አህባቦቼን አጣውና

ብቸኝነቴን ለብሼ
አልቅሼ መላለስኩና

እንባዬን ጠራረኩና
አመጡና አመኩና

እልል በሉልኝ ወለደኩኝ
በጄ አዘለኩት ሳብኩና

ተቀበሉዋቸው በደህና
ሁላቹ እልል በሉና

ዘይኔ አሚና ወለድኩኝ
ተደሰትኩኝ ወለድኩና

ዘይኔ መንበዑል በረካ
በመካ ተወለዱና

አድገው በሀረመል አሚን
በዘምዘም ሀኪም በሚና

ሆኑ ሰይደል ሙርሰሊን
ባዕዳ 40ኢን ቢሰና

አሚን ኢንደል ሀቅ ተልኮ
ሰጠው ባርኮ የስልምና

አለን ግልፅ ነው ታሪኩ
በመውሊድ ቀኑ ኢትነይና

ረቢኢል አወል ወር
ኢትነ አሸር ነበርና

መሪ ናቸው ለከውን ሁሉ
ያስደስታሉ ለዜና

ለሰርጌ ትብላ ወት አሉ
ያስደስታሉ ሀዚና

አላቸው ብዙ መሊሀት
አስተያየትም ህሊና

ተቀበሉዋቸው በደህና
ወዳቹ ተከተሉና

ገለታ ይድረሰው ለጌታ
ውለታ አይረሳምና

ዘይኔ አሚና ሙሀመድ
ሁሌም ሲወለድ አለና

ግቡና ዘይኔ ግቡና
ልካድሞት የኔ ኖትና

ሰላት ሰላምን በነቢ
አኑር ያ ረቢ መውላና
@yehadra_gtmoch


            ♣ሰለላ አላ ሰለላ አላ♣
          ♣ሙሃመድ ሳሂበል ኢስራ♣  
@yehadra_gtmoch
@yehadra_gtmoch
 🎵አልሃምዱሊላ ሃምደንከሲራ
        አገራን ነቢን ልንጠራ                                     
🎵ሰላት ሰላምታ ይውረድ ከጌታው
        ባይነታው በኸይረልወራ
🎵ሂጃቡን አንሳ ያቅሜን ላውሳ
        ይወሳ ያአበዛህራ
🎵ደጉ ነብይ ሣሂበልወህይ
        ኡምይ አይጽፍ አይቀራ
🎵አለው ኻሊቁ ወማየንጢቁ
        ማወቁ ነው በኛ ቁድራ
🎵ነብይነቱ 40አመቱ
        ጀመረ በጀበል ሂራ
🎵ዳእዋውን ይፋ ይዞ ሙስጠፋ
        ሊስፋፋ በኡመልቁራ
🎵ኺላፍ ካነሳው የገዛ ጎሳው
        ደርሶበት ብዙ መከራ
🎵ነበር አጎቱ ደሞ ዘውጀቱ
       ብርታቱ የቀኝ የግራ
🎵አጎቱ አርፎ ሃዘንን ታቅፎ
        አለፉ ኸዲጃም ኩብራ
🎵ጀሊል ሊያፅናና ቡራቅ ጫነና 
        ላከና ከጅብሪ ጋራ
🎵ባክስቱ ቤት አዝኖ ባለበት
         መጣለት ትልቁ ቡሽራ
🎵ለረጀብ ወር 3 ቀን ሲቀር
         ነበረ ለይሉ እንደደራ
🎵ጉድ ነው ቡራቁ ደስታና ሳቁ
         ያ አህለል ዘውቁ ሲያወራ
🎵አለው ገስግስ ቤተል መቅዲስ
         ድረስ አምቢያንም ምራ
🎵እንዲመራቸው ሊያሰግዳቸው
         ቀሰቀሳቸው በቁድራ
🎵ጉድ ነው ቡራቁ ደስታና ሳቁ
         ያ አህለል ዘውቁ ሲያወራ
🎵አሉት ሰከረ ይዞት በረረ
         ፊትም ነበረ ሃያራ
🎵ሰግደው ሲያበቁ ሲተዋወቁ
         ሲጠያየቁ ዚያራ
🎵ደግሞ ሲወጡ ቀርቦ መጠጡ
         ሊመርጡ ወተት ወ ኸምራ
🎵መርጠው ወተት አርገው ጥጥት
         ትንሽ ብቻ ሲቀራ
🎵በየ መንገዱ እየወረዱ
         ሲሰግዱ ቦታው ተወራ
🎵የኛ ነብይ ወደ ሰማይ
         ሚእራጅ ላይ ያዙ በረራ
🎵ቀልቡን አጠቡ እንዲያው ላደቡ
         ፊትም ነው ልቡ የጠራ
🎵ሞላ ሰማዩ በአርሂብ ባዩ
         እያዩ አያተል ኩብራ
🎵ከጅብሪል ጋር ደርሰው ሙክታር
         ከሰማይ በር ሃዚራ
🎵ዘብ ነው መለኩ ያለው ሲያንኳኩ
         ማነህ ከማንስጋራ
🎵ጅብሪል ነኝ እኔ ያለው ከጎኔ
         ዘይኔ ነው ሰይደል ወራ
🎵ታየ ከልቡ ሆነ ባደቡ
         አገባቡ የዚያራ
🎵አቤት ድምቀቱ ሰፍ መስራቱ
         ጉጉቱ ሊያየው ያጭፍራ
🎵በየሰማይ አለ ነብይ
          አርሂብ ባይ አበልበሸራ
🎵የህያና ኢሳ ሃሩን ወሙሳ
          ኢድሪስም እንደየተራ
🎵ዩሱፍም አሉ ደግሞ ኸሊሉ
          ነው ሁሉን አልፎ አኺራ
🎵እስከሙንተሃው ሲድረተል አብረው
          ዘልቀው ከጅብሪልጋራ
🎵አለ ጅብሪል ከዚክልል
          ማለፍ አልችል ስንዝራ
ከዛረፍረፍ ይዞት እልፍ
          ጀሊል ደጃፍ ሃዚራ
🎵ነብዬን እጣው ከሁሉ አብልጣው
          የወጣው በአርሸል ኩብራ
🎵በሩህ በጂስሙ ነው መታደሙ
          ከተአለሙ ሲወራ
🎵ካእበልቀውሰይኒ ቀርበው ሃሉል
          አወድን አያትን ቅራ
🎵አተህያቱ ብለው ማለቱ
          ሆነ ቃላቱ ሲወራ
🎵ያወጣው አርሹን ሰጠ ምላሹን
          ጭራሹን በሱኮ አምራ
🎵አለወአላ ባርያህ በሙላ
           ከመውላ መልስ ጭመራ
🎵ከጀሊሉጋ ቀርቦ ሲያወጋ
           3ኛ የለዛ ስፍራ
🎵ከጀሊልሰሚ ለኛተርጓሚ
           ተስማሚ ሆነ ሲያወራ
🎵5ቱን ሰላት 50ሊያሰላት
           አመጣት ዋጂቧን ስራ
🎵ኸሊል ሲመክሩ አሉን ዘክሩ
           የቀልብ ጀነት ላይ ያፍራ
🎵ምክሩ ሰላቱ ነው ለኡመቱ
           የሰማሁሉ ሊሰራ
🎵ከባዱን ወሬ አልችል ሰትሬ
           ነው ማሳጠሬ ቢገራ
🎵የጀሊል ወህዩ ያዩት ነብዩ
           ነው ልዩ ሃያተል ኩብራ
🎵ጫፍም ሳልደርስ ልበል መለስ
           ብዬ ሱብሃነመል አስራ
🎵ብዙ አጃኢብ አይተው ሃቢብ
            በአደብ መጡ ምድራ
🎵ወቅቱ ሲሰላ እጅጉን ቀላ
            ቃሉም በለየን ተቀራ
🎵ከዛ ሙክታሩ ሆነው በምድሩ
            ሲያወሩ የለይሉን ሃድራ
🎵ያኔ ቁረይሹ ከፍሮ ጭራሹ
            ላይዋሹ ሌላ ምስከራ
🎵ያሉት ነው ሃቅ አሉ ሲዲቅ
            አርገን ኻሊቅከሱጋራ
🎵አልቻለ አቅሜ ማኸታተሜ
            ባይችል ቀለሜ ዝርዘራ
🎵ትዛዙን ሰሪ ሌላንም ጥሪ
            ያርገን ባህሪ ሚያፈራ
🎵ሙሉኢማን ስጠን ኢኽሳን
            ሂክማንም ኸይረን ከሲራ
🎵ቀልቤን አፅዳው ከሚጎዳው
            ሁዳው በልቤ ያብራ
🎵ይሞላልቤ ቢሁቢነቢ
            ወፍቀኝ ረቢ ዚያራ
🎵አድርገን ሃብታም ዱያም አኺራም    ቢኹስኒልኺታም አደራ
🎵ተቀበሉኝ ነቢ ታዩኝ
             ሁኑኝ ዱኒያም አኺራ
🎵ሰልዋቱላህ ሰላሙል መውላ
            ይሞላ በኸይረልወራ
🎵ከዛም ቀጥለን ሣህበን ወ አህለን
            እኛንም በለን አብሽራ
🎼ሰለላ አላ ሰለላ አላ ሙሃመድ ሳሂበል ኢስራ🎼
         🎧ሙሃመድ ሳሂበል ኢስራ🎧
         🎧ሙሃመድ ሳሂበል ኢስራ🎧
         🎧ሙሃመድ ሳሂበል ኢስራ🎧
 ቻናላችን አዲስ ኘሮግራም አውጥቷል
ሰኞ ሙሉ መንዙማዎች አዳዲስ እንዲሁም የቆዩ (ድቤ)
ማክሰኞ ሙሉ መንዙማዎች አዳዲስ እንዲሁም የቆዩ (እንጉርጉሮ ነሺዳ)
እሮብ የ መንዙማ ግጥሞች
ሀሙስ የ ሀድራ መንዙማዎች
አርብ አስተያየታቹን የምንቀበል ይሆናል
ቅዳሜ መንዙማ challenge
ለ አስተያየት @Yehadragtmoch_bot
@Yehadragtmoch_bot

👉 @yehadra_gtmoch
🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝


🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

📿 በነቢዩ (صلى الله عليه وسلم) ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

🚿 ሸዋር መውሰድ

👚 ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

😁 ስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

🌹 ሽቶ መቀባት

🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

🚶🏿‍♂ ወደ መስጅድ በግር መሄድ

📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

🤲🏾 ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ

🥀🥀 #ጁመዓ mubarek 🥀🥀

👇join
@Yehadra_gtmoch
@yehadra_gtmoch






👏 #አልፉ_ሶላት ግጥም 🙏👎

ገለታ ይድረሰው ሩሁን ላነገሰው #ነቢይ

ከተውሂድ ጀረት ላይ ለኛ እንዳፈሰሰው #ነቢይ
ከውኑን ለርሶ ላንቱ በልፍኙ ደገሰው #ነቢይ
ኧሀ አልፎ አዝልቆ ለኛው አወረሰው #ነቢይ
በራህመቱ መርጊያ ከውናቱ የረጋው #ነቢይ
በነቢ ስፍራ ነው የራህመት መፍለቂያው #ነቢይ
ለርሶ የሾማቸው ሰጥቷቸው ከአደጋው #ነቢይ
በስሙ ሸክረው ተገኙ ከሊቃው #ነቢይ
አሃ ጨለማውን ራስ ሽበት እስኪያነጋው #ነቢይ
ጉልበታቸው አልቆ መሬት እስኪያድኸው #ነቢይ
ፈርጣማው ክንዳቸው ከአለት የጠናው #ነቢይ
የእርጅና ጉጠት እስኪያሸበሽበው #ነቢይ
አሃ የኡምራቸውን ጠጅ ለህዱ እስኪጠጣው #ነቢይ
በሁቡህ አልቅሰው እንባቸውን ጨርሰው #ነቢይ
እናቱን እንዳጣ ህፃን ተፈቅፍቀው #ነቢይ
ሀዘን ፊታቸውን ዳምኖ እስኪያጠቁረው #ነቢይ
በትካዜ መርከብ እንዳለ ተጭነው #ነቢይ
ቀናት በነሱ ላይ ያልፋሉ ተቆጥረው #ነቢይ
አሃ ደግሞ ሲያሰደሳቸው ደርሶ ጀማሉሁ ያሰይዲ ያረሱለሏህ



#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

ሆሆሆ በውበቱ ድርማ ላይ ውስጡን ታንጦ
ሁሉንም በለጠው መጨረሻ መጥቶ
ሽርክን ገለባብጦ በተውሂድ አንጦ
አለሙን አበራው በኑር እየቀባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

መፈጋፈግንጂ ማን ሊችለው ነእጁን
ሲፈዎትን በማስፈር የርሶን ዛት ሲፈቱን
ማን በነገረልኝ ሆዴ መባባቱን
እጅ ማሰጠቱን የሙስጦፋ ሀይባ ያሰይድ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

👏👏👏🙏👏👏👏👏👏👏👏👏

ገና ፊትም ሆነው በናትዎ ማፀን
ጫልዩ ጌታችሁ መድሁን ለማጠንጠን
ስንቱን ሞት አነቁት ሶለዋት በማጠን
ለኛውም ይሰጠን የነሱ መሀባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

የርሶ ስም አይደል ወይ ሲዲቅን ያላቀው
ኡመሩል ፋሩቅን በከሽፍ ያደመቀው
ኡስማንን የሀያእ ዝናን ያስታጠቀው
አልይን ያሳደገው ሂዳያ እያጠባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

የቡሰይሪን ፈሊጅ ሲሩን ያፈለሰው
የቡራኢን ሀዘን ጠራርጎ ያጠፋው
የዘቡሯ ልጇን ልሳን ያቀመሰው
አንዩን ዳንዩን መቃም ያደረሰው
አብደርይን በኢልም ጀህልን ያስገረፈው
ሸይኽ አሊ ጎንደርን ሞት ያስቀሰቀሰው
ስንቱን አነገሰው ከኸልዋ እያስገባ ያሰይዲ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

በልቼ እየጠጣሁ ይርብ ይጠማኛል
መድሀኒት ወስጀም አጥብቆ ያመኛል
መከዳ ታቅፌ እንቅልፍ ይርቀኛል
መነመነ ጅስሜ ናፍቆት እየሰባ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

ጀሊሉ የርሶን ስም በክብር ሲያኖጋው
በተጠራ ቁጥር ባንድነት ያስጠራው
እርሱ ነው አማላጅ እርሱ ነው ባላልጋው
ከውኑን ያረጋጋው መስመር እያስገባ


#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

አልፉ ሶላት የፍቅርሁን ንጋት
የኔ ጌታ በላዩ ላይ ዘልቆ
አልፉ ሶላት የሰራ አካሉቱን
የኔ ጌታ ያልቃል እንባ ፈልቆ
አልፉ ሶላት ከውስጡ እየገባ
የኔ ጌታ ትንፋሹን ሰንጥቆ
አልፉ ሶላት ያስወተውተዋል
የኔ ጌታ ያን ጨረቃ ናፍቆ
የኔ ነቢ ይወርቃል ተንጋሎ
ወለላየ አረፋውን ደፍቆ
ጌታየዋ ነፍሱን ያሰረተዋል
የኔ ጌታ ልቡ ተሰንጥቆ
አልፉ ሶላት ይዞ እያናፈለው
አልፉ ሶላት ውስጡን አሟሙቆ
አልፉ ሶላቱ ጀንበር ከመድና
የኔ ጌታ እየታየው ዘልቆ ያሰይድ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

አልፉ ሶላት አንቺ የኸይር ንፋስ
የኔ ጌታ ገልጠሽ የልቤን
አልፉ ሶላት ብለሽ ንገሪልኝ
ወለላየ ለዛ መኮነን
አሃ ዛሬስ አዳረሰው
አልፉ ሶላት የሰራ አካሉን
የኔ ጌታ ጉበቱ ነደደ
አልፉ ሶላት አፈላው ደሙን
የኔ ጌታ ስጋውን ጨርሶ
አልፉ ሶላት አወራው ጅስሙን
የኔ ጌታ አበደ ጨርሶ
የኔ ነቢ ወሰደው ልቡን
አልፉ ሶላት አካላቱ አለቀ
የኔ ጌታ ተፍቆ እንደ አንጀት
የኔ ጌታ ስጋውን አፍግቶ
የኔ ጌታ ይሄዳል ባጥንት
አልፉ ሶላት ጉበቱ ሁሉ ሳስቶ
የኔ ነቢ እንደ ወረቀት
የኔ ጌታ ሲቆም ደህን መሳይ
አልፉ ሶላት ልብስ ሸፍኖት
የኔ ጌታ ነውጂ እስከቀኑ
አልፉ ሶላት አልተረፈም ከሞት
ወለላየ አድርጉልኝ እዝነት
አልፉ ሶላት የብርሃን እልፍኝ
የኔ ጌታ አኳሀሗኔን ሁላ
የኔ ጌታ እንድትነግሪልኝ
አልፉ ሶላት አካላቴ አለቀ
አልፉ ሶላት ጉልበቴም ከዳኝ
የኔ ጌታ አጥንቴም አለቀ
የኔ ጌታ ደሜ አቃጠለኝ
አልፉ ሶላት ቀኑም ተራዘመ
ጌታየዋ እኔንም ከዳኝ ሰይዲ ያረሱለሏህ

#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ
#አልፉ_ሶላት_ወሰላም_አላ #ነቢይ

👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌

ሌሎችንም የነሽዳና መንዙማ ግጥሞች ለማገኘት👇👇
@Yehadra_gtmoch


ያረቢ ሶሊ ወሰሊም አላ
ያ ረቢ ሶሊ ወሰሊም አላ
ሙስጠፋ ሸራቢ ሶፋ
❤💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ማልዶ ቢያነሳኝ እንቅልፍ ነሳኝ
ናፍቆቱ አከሳኝ እንዴት ልፋፋ
💚💚❤❤
አሁን ምን ነበር ተከፍቶልኝ በር
ያን የኑር ጀምበር ባየሁት ኢፋ
💚❤💚❤
አደራ ዘይኔ አልጣው ካይኔ
ያላንቱኮኔ የለኝም ሶፋ
💚💚❤❤
ስጋዬ ደሜ ተቃጥሎ አዝሜ
ጠንቶ ህመሜ ይታያል ኢፋ
💚❤💚❤
ሌት ቀን መባከን እንደው መብከንከን
ታድያ እንዴት ልስከን ሳላይ ያን ስርፋ
💚❤💚❤
እንድሆን ብርቱ እርዱኝ በወቅቱ
ክብረቴን ባንቱ አርጉት የሰፋ
💚❤💚❤
ደካማው አቅሜ ስጋዬ ደሜ
ጠንቶ ህመሜ ይላል ሙስጠፋ
💚❤💚💚
ሌት ቀን ይሰክራል ጉድ ይፎክራል
አንቱን ይጣራል በሁሉም ስርፋ
❤💚❤💚
ተነስቶ ማልዶ በሸውቁ ነዶ
ይጣራል አብዶ ልጅሁ በኢፋ
❤💚❤💚
ጉድ ነው ተው ጉድ በል የፈይዱ ማዕበል
በከውኑ ዘምበል ብሏል በኢፋ
❤❤💚💚
ፈይዱ ሊፈጋ ዳምኖ ተንጋጋ
መጠጫው ዋጋ ሀድራ ነው ሶፋ
💚❤💚❤
ይከፈት ባቡ ያጥግብ ዝናቡ
ይደሳ አህባቡ ይመንዳ ኢፋ
❤❤💚💚
ይዋላል ልቡ ይጎርፋል እምቡ
ነብዬ ግቡ እሳቱ ይጥፋ
❤❤💚💚
ዋለልኩ አልቻልኩም በጣም ሰከርኩም
ሰላም አለይኩም በሉኝ ሙስጠፋ
❤💚❤💚
አበደ ልጅሁ ጋቱት ከሀውድሁ
በሰፊው እጅሁ አርገሁ የሰፋ
❤❤💚💚
ከዱንያ ጣጣ ና በሉኝ ውጣ
እንድቀናጣ በሀድራሁ ኢፋ
❤❤❤❤
ኑሩን ቢያፈጋው ከውኑን አነጋው
ከፍ ያለው አልጋው የኔ ጎንታፋ
💚❤💚❤
ጅብሪል ለለበ እየጋለበ
ሀቁ ገለበ ባጢል ተደፋ
💚💚💚❤
ከውድሁ ጠጣው ናፍቆት ተቀጣሁ
ስጠራሁ መጣው በሉኝ ሙስጠፋ
💚💚❤❤
አድርገው ወረት የሰፋ ክብረት
ያድናል ክፍረትመላ ሲጠፋ
💚💚❤❤💚
በኩሌው አይኑ ስንቱ መነኑ
በየ ዘመኑ አህባብመች ጠፋ
❤❤💚💚
የሱማ ሸውቅ መድፍ ነው ትጥቅ
በህር ነው ገርቅ በጣም የሰፋ
❤💚💚❤
ወዳጄ ዘይኔ ዝለቁ ባይኔ
ገልጧል ሊሳኔ የልቤን ተስፋ
💚💚❤❤
ፈጠረው ጀሊል ከ እብራሂም ኸሊል
ዚሉን ሙዘሊል አርጎ የሰፋ
❤💚❤💚❤
ሸራቤ ጠጄ ሶላቴ ሀጄ
ሱለም ሚዕራጄ ሀድራዬም ሶፋ
❤❤💚💚
ልበለው ውዴ የዳኢም እዴ
ጋሻዬ ክንዴ የኔ ሙስጠፋ
❤💚❤💚
ሶብዩ መንገድ ጀመረ መሄድ
አብሸር ተራመድ በሉት ሙስጦፋ
❤💚❤💚
ለመሄድ ርቆት እንዳይቀር ጨንቆት
ውዴዋ አትራቁት ና በሉት ግፋ
❤❤💚💚
የኑሩ ገላ የአለም ጥላ
ያረገው መውላ የሁሉም ተስፋ
❤❤💚💚
ካንቱ ፈይድ ጋት ሲጎርፍ ልጋት
ሳይገለኝ ውጋት ደም እያስተፋ
💚💚❤💚
ከፈይዱ መጠጥ ተግቼው ልፍጠጥ
ልገረም ልስመጥ በህሩ እንደሰፋ
💚❤❤💚
አለበት ሂጄ ሲል ጠርቶኝ ልጄ
ይዤ እጆን በጄ እዛው ልደፋ
❤️💚❤️💚
ቀለቤ ኩቴ ሸራብ ሚለቴ
ናልኝ ናፍቆቴ ጭንቀቴ ይጥፋ
❤💚❤💚
ሩሄ ነህ ጅስሜ ለስጋ ደሜ
ያላንተ ህመሜ በምን ሊጠፋ
💚💚❤️❤️
ናፈቀኝ ኩሌሁ ልይሁ ና ብለሁ
ጉንጭሁን ስሜሁ ናፍቆቴ ይጥፋ
💚❤❤💚
ለሚንሀት ለኔ ቁሙልን ዘይኔ
እንደ ጀይላኔ ማዳችን ይስፋ
❤❤💚💚
የጀነቱ ለም ራህመተል አለም
አምሳያው የለም ክብረቱ ሰፋ
❤💚❤💚
ያ ረሱሉሏህ የኔ ዘንፋላ
ሁኑኝ ከለላ አለም ሲጠፋ
💚💚❤❤
ሀድራው ነደደ ኩሌው ተጣደ
አህባብ አበደ ቢታየው ኢፋ
💚❤💚💚
💚💚❤❤
ጩኬ ካንቱ ቤት ብያለው አቤት
ይኸው 40 ቤት ቀለሜ ገፋ

@Yehadra_gtmoch


መልካም ኸሚስ በዱዓችሁ አትርሱን

" እገጥምሎታለው "

በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

አድምጡት

@Yehadra_gtmoch


አህመድ ነቢ ሙሀመድ
ያ ሸፊየል ቂያማ
ኑሩ ሰላም አለይካ


ጀመርን በከሪሙ
መድህና ኒዛሙ
እንዲኖረዉ በረካ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጀምረናል በስሙ
እንዲጣፍጥ ኺታሙ
በማሊከል ሙሉካ
፡፡፡፡፡
ይገባሀል ምስጋና
ስላረከን ረበና
ለ አሽረፈል ኸልቂካ
፡፡፡፡፡
ሰላምታችን ዪድረስ
ለአለሙ ንጉስ
አሰላሙ አለዪካ

፡፡፡፡
ዋሪዳሆ መጣና
አሳጥቶኛል ጤና
ሳዎድሶ አልረካ
፡፡፡፡፡
ከሆነ ፍቃዳቹ
ልምጣና ከደጃቹ
ክፈቱልኝ ሳንኳኳ
፡፡፡፡፡
አታርቀኝ ያረቢ
ከውድህ ሀቢቢ
ሩሄ ሄደች ተማርካ
፡፡፡፡፡
ስጠሮት ያጀማሉ
እንግዲህ አቤት በሉ
ልቤ ቶሎ እዲረካ
፡፡፡፡፡፡፡
ምሩኝ ባውራ መንገዱ
ሰክሬ በመደዱ
እንዳልጉዋዝ በጫካ
፡፡፡፡፡
ደረሰና ሰአቱ
ታጠቁ ወዪዛዝርቱ
ሊጡም ቶሎ ተቦካ
፡፡፡፡
ለመዉሊዶ ረሱሉ
በሬዉና ግመሉ
አሉ ለርሶ ፊዳካ
፡፡፡፡፡
ገብተን ገብተን ከመዉሊዳቹ
ዘክረን በስማቹ
ሀጀት ሁሉ ሊሳካ
፡፡፡፡፡፡
ደስታችን ነዉ ዉልደቱ
ይከበራል እለቱ
የጦሀ ሙባሪካ
፡፡፡፡፡
ከገቡማ መደድ
ሙሀባና ንዳድ
ይብሳል ሲነካካ
፡፡፡፡
ጉድ ነዉ ባልደረባው
ውሎ አዳሩን ቢያየው
አለ ሩሂ ፊዳካ
፡፡፡፡፡
እሱ ነዉ ማረፊያዬ
አዳሬም መዋያዬ
መጠለያዬ ዋርካ
፡፡፡፡
የአዘል ነዉ ንጉስ
ሲሄድ ሲገሰግስ
ሚታጀብ በመላዪካ
፡፡፡፡
ሙሀመድ ያሚናቱ
በአዘል ነዉ ውበቱ
ኩሉ ጂስሙ በረካ
፡፡፡፡፡
ባትወጣ ኳ ፀሀይ
ግንባሩ ነዉ ፀደይ
በልጦ ብርሀን ሚተካ
፡፡፡፡፡፡
ደጋግ ደግነቱን
ወሰን የሌለውን
በምን አቅሜ ልለካ
፡፡፡፡፡፡
አቤት የመብቃቃቱ
አያልቅበት ብዛቱ
ተለግሶ በረካ
፡፡፡፡፡
በስማቸዉ ታሰረ
በአዘል ነዉ ኸበር
የ አደም ኒካ
፡፡፡፡
የተፃፈው እውነት
የሌለው ነዉ ግነት
እንዳይመስልህ ትረካ
፡፡፡፡፡፡
ከቶ ከቶ አይደለም ልብ ወለድ
የውነት ናቸዉ ሙመድ
አቻም የሌዉ ሚተካ
፡፡፡፡
እናቱ በመናሙዋ
ሆኖ አየች አጠገብዋ
ኮከብና ጨረቃ
፡፡፡፡፡
ጉድ ነበረ ኮከቡ
ማማርና መዋቡ
እንደፀዳል የፈካ
፡፡፡፡
ደግሞም ቲኒሽ ቆይቶ
በኢሻራዋ መጥቶ
አባሸራት መላይካ
፡፡፡፡
በሆድሽ ያለዉ ጨቅላ
ነዉ ሰይደል ሙርሰላ
ስጋት አንቺን አይንካ
፡፡፡፡፡
የጌታዉ ነዉ ተወዳጅ
የኡመቱ አማላጅ
ሁሉም በሱ ሚመካ
፡፡፡፡፡፡
አንተ አዩህነቢዩ
የአንቢያቶች ልዩ
አሉት ሰላም አለይካ
፡፡፡፡
መጡ ወደ አሚናት
መርየምም አሲየት
መዉለጃዋ ሲጠጋ
፡፡፡፡፡፡
ምጥም የለው በቶሎ
ተወለደ ተኩሎ
ሰኞ ለት ሊነጋጋ
፡፡፡፡፡
በመውሊዱ ሙስጠፋ
ኢልቢስ ብቻ ተከፋ
ሌቱን ሲጮህ አነጋ
፡፡፡፡፡
የነብያት ድምድሙ
ደረጃና መቃሙ
አደድ የለው ቢለካ
፡፡፡፡፡፡
የኛን የአለም ኑሩ
እያለች እሹሩሩ
አጠባችው በረካ
፡፡፡፡፡፡
አጂብ የዚች ሀበሻ
አድጎ በሱዋ ትከሻ
በፍቅሩ መማረኳ
፡፡፡፡፡
የሙሀባዉ ቁዋጠሮ
ያኔ በሱዋ ጀምሮ
መጣልን ሲተካካ
፡፡፡፡፡፡፡
አላሁ ያ ሰመዱ
አታዉጣን ከመንገዱ
ከሼሆቻቺን ዲካ
፡፡፡፡፡፡፡፡
ከማርሚጣፍጠው
ሁለግዜ ማወሳው
እኖራለው ሳቦካ



፡፡፡፡፡፡
ለምጠ ካቱሚ ደቼ
አሮት ማልት በቢቼ
ሙሀባሙ አትሜካ
፡፡፡፡፡፡፡
ኢንሻአላህ መጣለዉ
ሀገሩሁን አያለው
መዲናም ቢሆን መካ
፡፡፡፡፡፡፡
የነቢዬ ወዳጂ
በፆም ሰላት ሰጋጂ
አድርገኝ ሸሪካ
፡፡፡፡፡፡፡፡
የኻቲማን ነገር
አደራህን ሰታር
ስሽኝም በኦሳካ
፡፡፡፡፡፡
ሰለዋት እንደጉድ
አዉርደዉ ያሰመድ
ቁጥር የሌለው ዲካ
፡፡፡፡
በውዶቹም ጠቅላላ
ሰላምህን ያመዉላ
ለግሰን በረካ
፡፡፡፡፡፡
አህመድ ነቢ ምለው
ሁልልጊዜ ማዉሳው
ከጀሊሉ ተልካ
፡፡፡፡፡፡
አህመድ ነቢ ሙሀመድ
መውደዱ ነዉ ፈርድ
ወሰላሙ አለይካ
፡፡፡፡፡፡፡፡
እስክትመጣ ህልፈት ከስጦታም ስጥት
አልተውም ሰለዋት የለገሰን ሙሚት
ኑሩ ሰላም አለይካ የረቢዑ በረካ
፡፡፡፡፡፡፡፡

@Yehadra_gtmoch


አሚን መንዙማ ክሊፕ || ሙሐመድይ መልቲሚዲያ || Amin men sum
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
@Yehadra_gtmoch
@Yehadra_gtmoch


      ⚫አሰላምዐለይክ አሰላምዐለይክ⚫
      ⚪አሰላምዐለይክ አሰላምዐለይክ⚪
     ⚫ያ ሸምሰል ሀረም አሰላምዐለይ⚫


🎧በጥላዉ አርገን በአርዱል በይዳ
          ጌታዬ ከሱ አታርገን ባዳ

🎧ሙሂቡሁ ሁላ እምባዉ ይፈሳል
          በለቅሶ ብቻ ዛቱ ይከሳል

🎧እኔስ እኔንጃ ቀልቤ ፈርታለች
          እርሶን እስክታይ በጣም ጉዋጉታለች
 
🎧በዉዴታህ ሰይፍ ኸልቁን ጨረስከዉ
          ኡመቴ እያልክ ሆዱን አባስከዉ

🎧እርሶን ማወደስ ከሆነ ቢድዐ
          መኖር አልሻም ለ 1 እንኩዋ ሰዐት

🎧ቀብር ሳልገባ ጨልሞብኛል
          ሲመሽ ሲነጋ አንቱን ይለኛል

🎧የዱንያ ፍቅር አሽጎት ቀልቤ
          ያለ ሰለዋት አጣዉ ዶክተሬን

🎧ያሽር የለ ወይ ራሱን ለሳተ
         ያለብሱ የለ ወይ ለተራቆተ

🎧ሲደለቅ ሲያረግድ ዛቱ ቢከሳ
         ከርሶዎ ሀድራ ያገኛል ካሳ

🎧ለጭንቅ ሀዘኔ ሆኑ ማስረሻ
         ለቂያማ ለት ሆኑኝ መሸሻ

🎧ስሞት ሲነሳ ሆድ ይብሰኛል
         መብላት መጠጣት ሁሉ ያስጠላኛል

🎧ኦፕራሲዮን አድርጉት ቀልቤን
          ታዝኑኛለሁ ስታዩት ጉዴን

JOIN👇👇👇👇
@yehadra_gtmoch
@yehadra_gtmoch


ፉአድ አል ቡርዳ


ስላህ አላ ሙሀመድ
ወሰሊም አለይሂ
👏👏👏👏👏👏

#join belu
👇👇👇👇👇
@yehadra_gtmoch

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

615

obunachilar
Kanal statistikasi