ተውሒድ እና ሽርክ
ክፍል አስራ ስድስት
እስቲ ልብ ብለን እንመልከት ነብዩ ﷺ
✅ ለተውሒድ ሲሉ አገር ለቀው ተሰደው ፣
✅ ሴት ልጆቻቸው ትዳራቸው ተፈቶ ፣
✅ ጥርሳቸው ተሰብሮ ፣
✅ እግራቸው ደምቶ ፣
✅ ማንም ላይ ያልደረሰ ፈተና ደርሶባቸው ፣
✅ ለአላህ በማመስገን ሰላት ላይ
ከመቆማቸው ብዛት የተነሳ እግራቸው
ተሰነጣጥቆ ፣
✅ ስንት መከራዎችን ታግሰው ፣
✅ ስንት መልካሞችን ሰርተው ፣
✅ በሰሃቦች አንደበት “(ከአላህ) የተላክበትን መልክት አድርሰሃል ፣ አደራህን ተወጥተሀል ፣ኡማውን መክረሃል ” ተብሎላቸው፣ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር አላህ “ብታጋራ ስራህ ሁሉ ውድቅ ይሆናል ” አላቸው።ታድያ የአላህ ባርያዎች ሆይ !እኛስ ምን ይዋጠን ? ለምንድ ነው ለተውሒድ ትምህርት ተገቢው ትኩረት የማይሰጠው ? ለምን ይሆን ስራን ሁሉ አመድ የሚያስገባውን ሽርክ ከምንም በላይ የማንጠነቀቀው ?
አለማዊ ስሌት።
በሂሳብ ትምህርት እንደሚታወቀው ማባዛት ሚባል ነገር አለ ማንኛውም ቁጥር በዜሮ ከተባዛ እራሱን ዜሮን ነው የሚሰጠው። ለምሳሌ፦
1×0= 0
100×0= 0
100,000×0= 0
1,000,000×0= 0
1,000,000,000×0= 0
የሽርክም መጨረሻው ይህ ነው። ሰውየው እምነቱ ሳይስተካከል ቢለፋ ቢለፋ መጨረሻው ላይ ይኸው ለፍቶ መሆን ነው።ሰውየው ሽርክ ሳይቀላቀልበት ተሰርቶ የተቀመጠ መልካም ስንትና ስንት ምንዳ ያለው ስራ ቢኖረውም ትልቁ ሽርክ ሲቀላቀልበት እንዲሁ ዜሮ ያስቀረዋል። ሽርክ ስራችንን አመድ እንዳያደርግብን ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ ግድ ይላል። በእምነት መካድ ምን እንደሚያስከትል አላህ እንዲህ ይለናል ፦
وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡[አል-ማኢዳህ:5]
አላህ ሆይ !ወደ ወዱ የተውሒድ መንገድ ምራን ፣ ከእርኩሱ ሺርክም እኛንም ዝርያዎቻችንንም ጠብቀን። በተውሒድ መንገድ ላይ ግደለን።
✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
(ተውሒድ እና ሽርክ ገፅ 32-34)
“ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide