🔷 ከዘካተል ፊጥር ብይኖች
- ዘካተል ፊጥር የዒድ ቀንና ማታው የሚበቃው ቀለብ ባለው ሰው ላይ ዋጂብ ነው ።
- እንዲሁም አንድ ሰው ቀለባቸው በሱ ላይ ዋጂብ የሆነበት ሰዎች ዘካቸው በሱ ላይ ዋጂብ ነው ።
- የህፃናቶች ዘካተል ፊጥር በወልያቸው ላይ ነው ።
- በፅንስ ላይ ላለ ህፃን ማውጣት ይወደዳል ።
- ዋጂብ የሚሆንበት ጊዜ የረመዳን ወር የመጨረሻ ቀን ፀሀይ ስትጠልቅ ነው ።
- የዒድ ቀን ከሶላት በፊት ማውጣት ይወደዳል ።
- ከዒድ በፊት አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ማውጣት ይቻላል ።
- ከዒድ ሶላት በኀላ ያወጣ ሰው በላጩ አምልጦታል ።
- የዒድ ቀን ፀሀይ እስክትጠልቅ ማቆየት ክልክል ነው ።
- ለኻዲሞች በፍቃዳቸው ማወጣት ይቻላል ።
- ዘካተል ፊጥር የተቀበለ ሰው መሸጥ ይችላል ።
- ዘካተል ፊጥር በእህል እንጂ በገንዘብ ማውጣት አይፈቀድም ።
እነዚህ ከዘካተል ፊጥር ህግጋቶች ጥቂቶቹ ናቸው ።
ይህ ትልቅ ዒባዳ ስለሆነ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ።
እንደ ልማድ አድርገን ሳይሆን ጌታችንን የምናመልክበት የዒባዳ አይነት መሆኑን አውቀን በተገቢው ቦታ ልናውለው ይገባል ።
ሱቅ ሄደን ዱቄት ገዝተን ተሸክመን ለድሆች ማድረሱ እራሱ ዒባዳ ነው ። በመኪና ማድረሱም ያው ነው ።
እኛ አጅር በዝቶብን ከሆነ ሌሎች እንዲያደርሱልን ማድረግ እንችላለን ።
ዘካተል ፊጥር አደረሳለሁ ብሎ ተቀብሎ ቁጭ ማድረግ አይቻልም ።
አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስራ የምንሰራ አላህ ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka