ኡሉል ዐዝም
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
46፥35 *"ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ"*፡፡ فَاصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُولُو الْعَزْمِ مِنَ الرُّسُلِ
አምላካችን አሏህ ወደ መጀመሪያው ነቢይ ወደ አደም ወሕይን አውርዷል፥ ግን አደም አሏህ አትብላ ያለውን በመርሳት ቆራጥነትን አልተገኘበትም፦
20፥115 *"ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ ረሳም፡፡ ለእርሱም ቆራጥነትን አላገኘንለትም"*፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ فَنَسِيَ وَلَمْ نَجِدْ لَهُ عَزْمًا
"ዐዝም" عَزْم ማለት "ቆራጥነት" ማለት ነው። ዩኑሥ ከአሏህ መልእክተኞች መካከል አንዱ ነው፥ በትእግስት ቆራጥነት ስላልታየበት፦ "እንደ ዓሣው ባለቤትም አትኹን" የሚል መመሪያ አለ፦
37፥139 *"ዩኑሥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው"*፡፡ وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
68፥48 *"ለጌታህም ፍርድ ታገሥ! እንደ ዓሣው ባለቤትም አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ ጌታውን በተጣራ ጊዜ"*፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ
"ኡሉል ዐዝም" أُولُو الْعَزْمِ ማለት "የቆራጥነት ባለቤት" ማለት ሲሆን ከአሏህ መልእክተኞች መካከል "የቆራጥነት ባለቤት" የተባሉት መልእክተኞች የትእግስት ምሳሌ ስለሚሆኑ፦ "ከመልእክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ" የሚል መመሪያ አለ፦

"ረሡል" رَسُول ማለት "መልእክተኛ" ማለት ሲሆን "ሩሡል" رُّسُل ማለት ደግሞ "መልእክተኞች" ማለት ነው፥ "ሩሡል" ከሚለው ቃል በፊት "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በራሱ "ኡሉል ዐዝም" የተባሉት ሁሉም መልእክተኞች ሳይሆኑ በከፊል መሆናቸውን ጉልኅ ማሳያ ነው። እነዚህም "ኡሉል ዐዝም" የሚባሉት መልእክተኞች ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሣ፣ ዒሣ እና ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ናቸው፥ አሏህ ከእነዚህ የቆራጥነት ባለቤት መልእክተኞች ጋር የከበደን ቃል ኪዳን አድርጓል፦
33፥7 *"ከነቢዮችም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሣም ከመርየም ልጅ ዒሳም በያዝን ጊዜ አስታወስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን"*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا
42፥13 *"ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፣ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን፣ ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን ደነገግን"*፡፡ شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ
“ፈድል” فَضْل የሚለው ቃል “ፈዶለ” فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስጦታ” “ችሮታ” “ጸጋ”Bounty” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በደረጃ በማብለጥ የተለያየ ፈድል ሰቷቸዋል፦
2፥253 *"እነዚህን መልእክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፥ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ"*፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۘ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ ۖ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ
እዚህ አንቀጽ ላይ "አበለጥን" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "ፈደልና" فَضَّلْنَا ሲሆን ፈድል በመስጠት ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በደረጃ ማብለጡን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ነገር ግን የተሰጣቸው ፀጋ የራሳቸው ስላልሆነ እኛ አንዱን መልእክተኛ ከሌላው መልእክተኛ ሳንለይ በሁሉም መልእክተኞች መልእክት እናምናለን፦
4፥152 *"እነዚያም በአላህ እና በመልክተኞቹ ያመኑ፣ ከእነርሱም በአንድም መካከል ያለዩ እነዚያ ምንዳዎቻቸውን በእርግጥ ይሰጣቸዋል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ وَلَمْ يُفَرِّقُوا بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ أُولَـٰئِكَ سَوْفَ يُؤْتِيهِمْ أُجُورَهُمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 54
አቡ ሠዒድ 4ንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በነቢያት መካከል አታማርጡ"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " لاَ تُخَيِّرُوا بَيْنَ الأَنْبِيَاءِ ".
አምላካችን አሏህ ከመልእክተኞች የቆራጥነት ባለቤቶች ከሆኑት ጋር መልካም ጎረቤት ያርገን! አሚን።
https://t.me/Reslan1