أبو فوزان عبدالسلام


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


አዋቂዎች አይደለንም ግን አህለል ቢድዓ አይሸውዱንም።
የቻናሉ ዋና አላማ፡-
1. ተውሒድን ከዳር እስከ ዳር ማስፋፋት
2. ቁርአንና ሐድስን በሰለፎች አረዳድ ማስተላለፍ
3. ከምንም በፊት ቅድሚያ ለተውሂድ
-በዚህ ቻናል በቻልኩት መጠን ሀቅን የበላይ ለማድረግ እና ባጢልን የበታች ለማድረግ የበኩሌን ለማድረስ እሞክራለው።
•ሀይማኖታችንን ምንወስደው
1 ከቁርኣን
2 ከሀድስ
3. በሰለፎች ግንዛቤ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Bahiru Teka dan repost
➡️ የተከበራችሁ ሰለፍይ እህትና ወንድሞች ባህር ዳር ላይ አነሳናቸው ስላሉዋቸው ነጥቦች እያናዳንዱን አንስቼ ለሞሞገት አንባቢያንን እንዳላሰለች ብዬ ነው የተውኩት ። በተለይ እስካሁን የት ነበራችሁ የሚለው ሹብሀ እንደ ተብሊጎች ሁሉም በአንድ ቃል የሚዘምሩት ስለሆነ አስፈላጊ ከሆነና አላህ ካለ ወደ ፊት እመለስበታለሁ ።


Bahiru Teka dan repost
አሁን ውይይቱ ምን ያህል አስፈላጊ ነው ወደሚለው ነጥብ እናምራ ፡፡ በኢብኑ መስዑዶች ላይ አሁን ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፣ ኢብኑ ሙነወር ፣ "ተብዲዕ እንደማናደርግ ከፊታችሁ አልተናገርንም ?" በማለት በጥያቄ መንገድ መልስ ሰጥቶበታል ፡፡ ባጭሩ የኢብኑ መስዑድ ሰዎች የቢዳዐ አራማጆች አለመሆናቸው እንደሚያምኑ እየተናገሩ ነው ፡፡
እኛም በግልፅ ማወቅ የፈለግነው ይህንኑ ነው ። የሰለፎችን መንሀጅ በተለያየ ጊዜ በመጣስ ትልቅ ስህተት ስለሰሩትና ከስህተታቸውም ስላልተመለሱት የኢብኑ መስኡድ አመራሮች እነኢብኑ ሙነወር ግልፅ በሆነ መንገድ አቋማቸውን እንዲነግሩን፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የውይይት ጥሪ በተለያዩ ወንድሞች ሲቀርብ አሻፈረኝ ብለው ባህር ዳር ሁለት ሆነው በመሄድ አመክኗዊ ( ሎጂካዊ) ነጥቦችን አንስተው ያገኙትን መልስ እንደ ድል ቆጥረው መመለሳቸውን ይሄውና ኢብኑ ሙነወር ነግሮናል፡፡
ሀቁ ይህ ከሆነ ፣ ውይይቱን ማካሄድ የሚያስገኘው ጥቅም ምንድ ነው ? የጥመት መንገድን ከመረጡ አካላት ጋር ውይይት ያካሄዱ ሰለፎች በጣም ውስንና የተወያዩትም አንዴ ብቻ ስለመሆኑ ከፍ ሲል ለማሳየት ተሞክሯል ፡፡ ታዲያ ከነዚህ ሰዎች ማለትም ከነኢብኑ ሙነወር ጋር መወያየት ያለብን ስንት ጊዜ ነው ? ከአሁን በኋላ ስንት ጊዜ እንድናካሂድ ነው ሶሻል ሚዲያውን እያጥለቀለቁት ያሉት ? እኛ ከሰለፎች አካሄድ በማፈንገጥ በውክልና ከእነሱ ጋር የምንከራከረው እስከ መቼ ነው ?
ሀቁን ማወቅ ለፈለገ ሀቁ ከጠራራ ፀሀይ የበለጠ ደምቆ ይታያል ። ሀቁን ላልፈለግ ቀኑ ከጨለማ የተለየ አይደለም ፡፡
ውይይት አይካሄድም እንጂ ቢካሄድ - ከዚህ በፊት ከነበሩን ውይይቶች በተግባር እንዳየነው - ለራስና ለጭፍን ተከታዮች የአሸናፊነት ስነልቦናን የሚያቀዳጁ ሶስት "የማሸነፊያ" ዘዴዎችን ታጥቀው ነው ወደ ውይይት ለመግባት እየተጣሩ ያሉት ፡፡
1 – በውይይቱ ላይ የመከራከሪያ ሀሳብም ሆነ ተቃውሞ የሚያቀርቡት የሰለፎችን መንሀጅ ተከትለው ሳይሆን በዚህ ምትክ አመክኒዮ (ሎጂክ) ነው የሚያቀርቡት ፡፡
ለምሳሌ፡- "እከሌ የተባለ አሊም እገሌ የተባለውን አሊም ሙብተዲዕ ብሎታል ፡፡ እንቶኔ የተባለው አሊም ግን የዘመናችን ምርጥ ሰለፍይ ብሎታል ፡፡ ይሄን ምን ትሉታላችሁ ?" በቃ - በሎጂክ ላይ ሎጂክ ፣ በሎጂክ ላይ ሎጂክ…
2 – የፈለገ የመረጃና የማስረጃ ክምር ከቁርአንና ከሀዲስ እንዲሁም ከሰለፎች ቢቀርብላቸው ፣ ሀቁን ባለመቀበል ሁሉንም "ድባቅ" የሚመቱበት ፣ "ላዩቅኒዑኒ" (አያጠግበኝም)  የሚል ካርድ አላቸው ፡፡ የፈለከውም መረጃ ብትደርድር ፣ የፈለከውን ማብራሪያ ብታዥጎደጉድ ፣  "ላዩቅኒዑኒ"ን የማሸነፊያ ስትራቴጂ አድርጎ የሚጠቀምን ሰው ምንጊዜም ልታሳምነው አትችልም ፡፡    
3 –  ሶስተኛው "የማሸነፊያ" ካርዳቸው ፣ "ላየልዘሙኒ" (አይዘኝም)  የሚል ነው ፡፡ ይሄ ውይይቱን ለማሳረግ ሲፈልጉ የሚመዙት ካርድ ነው ፡፡ "ላየልዘሙኒ" (አይዘኝም)  ከሰለፎችም ሆነ ፣ ከሰለፍዮች የፈለገ አስተማማኝ የሆነ ማስረጃም ሆነ ፈትዋ ቢገኝ ፣ ውይይቱን "በአሸደናፊነት" ለመውጣት የሚመዘዝ ካርድ ነው ፡፡  "ላየልዚሙኒ" (አይዘኝም) ብሎ ድርቅ ካለ ምን ማድረግ ትችላለህ ?
እነዚህ ሶስት ካርዶች በሙመይዐነት የተጠቁ ወይም ለሙመይዖች ጋሻ አጃግሬ የሆኑ ሰዎች አዘውትረው የሚጠቀሙባቸው  "የማሸነፊያ" ዘዴዎች ናቸው ፡፡
የሰለፎችን መንሀጅ አሽቀንጥሮ ጥሎ እነዚህን እንደ ስልት የሚጠቀም ሰው ፣ ማንኛውንም ውይይት "በአሸናፊነት" የሚወጣው እሱ ነው ፡፡ "በአደባባይ ካልሆነ አንወያይም ፤ ከዚህ በፊት ተነድፈናል ፤ ቅብጥርሴ" የተባለውስ ለዚህ ሳይሆን ይቀራል?  እነዚህን ካርዶች የሚጠቀሙ ሰዎች ምሳሌያቸው ፣ ከጉድጓዷ ደጅ ላይ ሆና ድመት እያያት እንደምትደነስ አይጥ ብጤ ነው ፡፡ ድመቷ ገና ማድባት ስትጀምር ፣ ወደ ጉድጓዷ ጥልቅ ነዋ !!!!!! ።
ለማንናውም ወንድሜ ኢብኑ ሙነወር ከዚህ በፊት " ውሸታም ፣ ቀጣፊ ፣ ተንኮለኛ ፣ ዐቂዳን ለድርድር ያቀረቡ ፣ ወላእና በራእ የዐቂዳ ጉዳይ እንዳልሆነ ሊግቱን ይዳዳቸዋል" ። ስትላቸው የነበሩትን የመርከዙ ሰዎች ዛሬ እኔ ከፈለግሁኝ ድንጋይን ዳቦ ብዬ ማሳመን እችላለሁ በሚል አይነት ስሜት እነሱን ወክለህ እኛን ለመሞገት ቆርጠህ የተነሳህ በመሆኑ ላሳውቅህ የምወደው ከዚህ በኋላ ኢብኑ መስዑዶችን ከምንፋለመው በላይ ተወካዮቹን የምንፋለም መሆናችንን ነው ። አሸናፊነት በተመለከተ ፈቅደናል አሸንፈናል በሉ ። ዋንጫውንም ተረካከቡ በውይይቱ ፋንታ ህዝብ እያያችሁ ከኢብኑ መስዑዶች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ተከታዮቻችሁን አስጩሁ ።
ባህር ዳር ላይ የተካሄደውን ውይይትና ጥሪውን አስመልክቶ ከመሻኢኾቻችን ማሳረጊያ እንጠብቃለን ።
https://t.me/bahruteka


Bahiru Teka dan repost
ለመጨረሻ ውይይት ጥሪ ምላሽ

ቀደም ሲል ወንድማችን ኢብኑ ሙነወር ለውይይት ጥሪ በማድረጉ ምክንያት ፣ የውይይቱን ጥሪ ለመቀበል ሁለት መስፈርቶችን ማስቀመጣችን ይታወሳል ፡፡
መስፈርቶቹም ፣ በኢብኑ መስዑዶች ላይ አሁን ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉና ፣ ክብርራቸውን የነኳቸውን መሻኢኾች ይቅርታ እንዲጠይቁ የሚጠይቁ ነበሩ ፡፡
የመጀመሪያውን መስፈርት በተመለከተ ፡-
ኢብኑ ሙነወር ይህን በተዘዋዋሪ መንገድ አቋማቸውን ግል አድርጓል ። ይኸውም : –
በመጀመሪያ ፁሑፉ ላይ ኢብኑ መስዑዶች የውይይቱ አካል ሆነው ሳለ እንደ መስፈርት መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን በመግለፅ ። በሌላ አባባል እነርሱ ሰለፍይ ናቸው ብለው እንደሚያምኑና ከኛ ጋርም ውይይቱ በዚህ ላይ እንደሚሆን በመግለፅ ።
በሁለተኛው ፁሑፉ ላይ ባህር ዳር ሄደው ከነ ሸይኽ ሐሰን ገላው ጋር ስለኢብኑ መስዑዶች ተወያይተው አሸንፎ እንደመጡ ለማሳየት ሞክሯል ። ይህም አሁንም በኢብኑ መስዑዶች ላይ ያላቸው አቋም ሰለፍዮች ናቸው የሚል መሆኑን ያጠናክራል ።
ሌላው ለዚሁ የውክልና ውይይት እኛን ኢልዛም ለማድረግ ከሰለፍ ዑለሞች እነ ኢብኑ ዐባስ ፣ ዑመር ኢብኑ ዐብዱል ዐዚዝ እንዲሁም ኢማሙ አሕመድና ከዘመናችን ዑለሞች ደግሞ ሸይኽ አልባኒ
ከኸዋሪጆች ፣ ከሙእተዚላዎች እና ኢኽዋኖች ጋር መወያየታቸውን በመጥቀስ ፣ "እናንተ ከነኢብኑ ዐባስ ከኢማሙ አሕመድና ከነአልባኒ ትበልጣላችሁ ወይ ..."? የሚል ጥያቄ አንስቷል ፡፡ ይህን ሀሳቡን የጀመረውም :–
" በያዘው አቋም መተማመን ያለው አካል እንዲህ አይነት ማሰናከያ አያቀርብም " በማለት ጭምር ነው ፡፡ እነዚህ ሁሉ ትርፍ ንግግሮች የተቃራኒ ወገንን ስሜት ለመንካት ታስበው የተሰነዘሩ ጉሸማዎች መሆናቸው ግልፅ ነው ::
እዚህ ላይ የወንድማችን ኢብኑ ሙነወር ሐሳብ እርስ በርሱ የተጋጨ ሆኖ እናገኘዋለን ። ከላይ እንዳየነው በውክልና ሊወያይላቸው የተዘጋጀላቸው የመርከዙ ሰዎች ሰለፍዮች ናቸው እንደሚል ነበር ። አሁን ደግሞ ከኸዋሪጅ ፣ ሙእተዚላና ኢኽዋን ጋር አመሳሰላቸው !!!! ። ከዚህ ጋር በተያያዘ መታወቅ ያለበት ነጥብ ማንኛውም ትክክኛ ሰለፍይ በማንኛውም የዲኑ ጉዳይ ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ነው የሚከተለውና የሚተገብረው ፡፡ በዲን ላይ የሚደረግ ውይይትም ከዚህ ውጭ አይስተናገድም ፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን ነጥቦች ማየት ግድ ይላል ።
1– ኢብኑ ሙነወር የጠቀሳቸው ሰለፎች ከአፈንጋጭ ቡድኖች ጋር ያለ መስፈርት ወይም ቅድመ ሁኔታ የተወያያዩት ፣ ያፈነገጡት ቡድኖች አቂዳም ሆነ መንሀጅ ፍንትው ብሎ የታወቀ ከሆኑ አካላት ጋር ነው ፡፡ መንሀጃቸውን ፣ አቂዳቸውንም ሆነ አቋማቸውን ይፋ አድርገው እያለና ለዐቂዳቸው እየሞገቱና ወደ እሱም እየተጣሩ ፤ "መንሀጃችሁ" ወይም "አቂዳችሁ" ወይም "አቋማችሁ ምንድነው? መጀመሪያ እሱን አሳውቁን" ብሎ መጠየቅ ተገቢም አይደለም - ምናልባትም ቂልነት ቢሆን እንጂ ፡፡
ለዚህም ነው ኢብኑ ሙነወር የጠቀሳቸው ሰለፎች ይህን ጉዳይ መስፈርት ያላደረጉት ፡፡
የነኢብኑ ሙነወር የውይይት ጥሪ ግን ከሙኻሊፎቹ ጋር ቀጥታ ሳይሆን እነሱ ሙኻሊፎች አይደሉም ሰለፍዮች ናቸው ለሚሉዋቸ አካላት የውክልና ውይይት ጥሪስለሆነ ነው ። በኢብኑ መስዑዶች ላይ አሁን ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉ የጠየቅናቸው ፡፡
የዚህ አይነት የውክልና ውይይት ከሰለፎች አልተገኘም ምናልባት ከዚህ በኋላ እነኢብኑ ሙነወር በቀደዱት ቦይ የሚፈስ ከተገኘ እንጂ ።
የኢብኑ መስኡድ ሰዎች ፣ በተለይም ደግሞ ከጥቂት ከአመታት ወዲህ በሀገራችን ላይ ከተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ ጀምሮ እጅግ ግልፅ በሆነ የመንሀጅና የዐቂዳ ሙኻለፋ ላይ ላይ ወድቀው ተመለሱ ሲባሉ አሻፈረኝ ብለው ለአቋማቸው ወላእና በራእ መስርተው ይገኛሉ ፡፡ በመሆኑም ነው እኛ ከኢብ መስዑዶች ጋር ያለን ልዩነት የሚንሃጅና የዐቂዳ ነው ያልነው ። እነርሱ ማለት አሁን ከነ ኢብኑ ሙነውር ጋር የልዩነታችን ዋና ምክንያት ስለሆኑ ፣ እነኢብኑ ሙነወር በኢብኑ መስኡድ ሰዎች ላይ ያላቸውን አቋም ግልፅ ማድረግ ይኖርባቸዋል እያልን የነበረው ፡፡ አሁን አሳውቀውናል አልሐምዱ ሊላህ ።
እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት ይህ ውይይት ከኢብኑ መስዑዶች ጋር ቢሆን ኖሮ ይህ መስፈርት የማይቀርብ እነደነበር ነው ።
2 – ሌላው ኢብኑ ሙነወር ከጠቀሳቸው የእነዚህ ሰለፎች ውይይት ፣ ሌላም ልንረዳው የሚገባ ትልቅ ነጥብ አለ ፡፡ እሱም በየዘመናቸው ከነበሩ አፈንጋጭ ቡድኖች ጋር ውይይት ያደረጉት አንዴ ብቻ ነው ፡፡ በመጀመሪያው ውይይታቸው አፈንጋጭ ቡድኑ ወደ ሀቁ ጎዳና ከተመለሰ እሰዬው ።
የተያያዘው የቢድአና የጥመት ጎዳና ልቡን ሰልቦት "አሻፈረኝ" ካለ ግን ፣ "መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ" ብለው ነው የሚተውት ፡፡ እናም ከአንድ አፈንጋጭ ቡድን ጋር ፣ በድጋሜ የተወያዩበት ሁኔታ የለም፡፡
አሏህ ሀቅን ለማየት ለወፈቀው ሰው ፣ ሀቅ ሁሌም ግልፅ ነው፡፡ የውሀ ወቀጣ አይነት ክርክር ፣ ውዝግብ ፣ ጭቅጭቅና ንትርክ አላስፈለጋቸውም ፡፡ ሀቁን እንዲያይ አሏህ ካልወፈቀው ደግሞ የፈለገ ጊዜ ያህል ውይይት ፣ ክርክር ቢካሄድ የሚገኝ ውጤት የለም - የልብ ድርቀትን ከመጨመር ውጭ ፡፡ ለዚህም ነው ሰለፎቹ የቢድዐና የጥመት መንገድን ከሚከተሉ ቡድኖች ጋር ከአንዴ በላይ ያልተወያዩት ፡፡ ይሄን ያደረጉት ግን በያዙት አቋም መተማመን አጥተውና ማሰናከያ ፈልገው አይደለም ፡፡
ለምን ይሆን ታዲያ እነ ኢብኑ ሙነወር የውክልናውን ውይይት ባህርዳር ሄደው አድርገው ከመጡ በኋላ በድጋሚ የፈለጉት ? ወይስ እነርሱ እዛ አሳክተነዋል ያሉት ድል !!!!! ለሁለተኛ ጊዜ ደግመውት ቲፎዞዎቻቸውን አስጩኸው ዋንጫውን ለኢብመስዑዶች በተመልካች ፊት ለማስረከብ ?
3  – ሌላው ልንረዳው የሚገባን ነጥብ - በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሰው እንደ ተጠበቀ ሆኖ - አብዛኛዎቹ ሰለፎች ከሙብተዲኦች ጋር ለውይይት አልተቀመጡም ፡፡ ከሙብተዲእ ጋር መወያያትን አጥብቀው ይጠሉ ነበር ፡፡ እንደውም ለውይይት መቀማመጥ ቀርቶ ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን ከሙብተዲዖች ጋር መቀመጥን አምርረው ይሸሹ ነበር ። ይህ ነው የሰለፎች መርህ ። የቢዳዐንና የጥመት መንገድ ልክ እንደ ተላላፊ በሽታ ይፈሩት ስለነበር ፡፡
አሁን ነገሮች ተገለባበጡና "አህለ ሱና ነን" የሚሉ አካላት ራሳቸው ፣ "ለሙኻሊፎች ( መሻኢኾች ሙብተዲዕ ላሏቸው) ጠበቃ ሆነን ካልተከራከርን" የሚሉበት ዘመን መጣና ይሄውና ውይይቱ በአደባባይና በህዝብ ፊት ካልተደረገ ፣ "ሞተን እንገኛለን" አይነት ጥሪ በየጊዜው እያቀረቡ ይገኛሉ ፡፡ ውይይቱን በጃሂሉም ፣ የዲን እውቀትን ገና በመማር ላይ በሚገኘውም ፣ የመንሀጅን ምንነት በተረዳውም ፣ ባልተረዳውም ፊት "ካልሆነ አንወያይም" ማለትስ ያውም የውክልና ውይይት ከየትኞቹ ሰለፎች የተገኘ አካሄድ ይሆን ?
ለማንኛውም የዲን ውይይት ፣ የምርጫ ቅስቀሳ ካለመሆኑም በላይ ፤ የቲፎዞ ጭብጨባም ፣ አጨብጫቢም አያስፈልገውም ፡፡


አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

👉ያ ጀማዓ እንዴት ናችሁ?

✍ ሰላማችሁ እንደ ሰማይ ኮከብ ብዝት ይበል።

⏱ በመቀጠል አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁና መልሱ ለራሳችሁ ልተወው ጥያቄውም ዲናችሁን ከማን ነው ምትይዙ?

👉 ምክንያቱም አሁን ባለንበት ዘመን ሁለት መሰሪ አስተሳሰቦችን አንግበው ወደ ሚፈልጉት ምዕራፍ ለመሸጋገር ሚውተረተሩ ሰዎች እየበዙ ነውና ጥንቃቄ ያሻል።

💊 እነዚህም ሁለት መሰሪ አስተሳሰቦችን ይዘው ሚንቀሳቀሱ ሰዎች እነ ማን ናቸው ? የሚለው ነጥብ ፈጥኖ አዕምሮዓችሁ ላይ የሚመጣው ጥያቄ ነውና መልሱን እንካችሁ፡-

1/ የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው ሚንቀሳቀሱ

2/ በዲን ስም ሚንቀሳቀሱ ናቸው።

1/ የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው ሚንቀሳቀሱ ሰዎች የያዙትን እርካሽ ፖለቲካቸው በቀጥታ ሚገዛቸው አካል እንደሌለ ሲያውቁ በተዘዋዋሪ መንገድ የህብረተሰቡ የልብ ትርታ የሆኑትን ችግሮች በማጥናት እነዚህን የህብረተሰቡ ችግሮች ደጋግመው በማስተጋባት ወደ ሚፈጉት ስልጣን ወንበር ይመጣሉ።
ነገር ግን ልክ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ጀምረው ያ ሁሉ የጮሁለትን የህዝብ ጥያቄ ወደ ጎን በመተው የራሳቸውን ጥቅም በማስጠበቅ ላይ ቢዚ ሲሆኑ ይስተዋላሉ።

2/ ልክ እንደዚሁ በዲን ስም ሚንቀሳቀሱ አካላትም የያዙትን የተበላሸ የሆነውን አቂዳ ይዘው በቀጥታ ወደ ህዝቡ ቢቀርቡ ህዝቡ ምን ሊላቸው እንደሚችል አስቀድመው ስለሚያውቁ ህዝቡን ለማታለል ሚመች የሆነን ቃኢዳ መስርተው ወደ ህዝብ ይቀርባሉ።

👉 ቃኢዳውም የሙስሊሞች አንድነት የሚል ነው። ነገር ግን እውነታው ሲታይ ትክክለኛ የሆነ የሙስሊሞች አንድነት ሳይሆን የውሸት አንድነትን የተፈለገበት በቀጥታ ቁርዓንና ሃዲስን የሚቃረን አንድነት ነው።

👉 ይህ አንድነት እስከ መቼ ነው ሚጠቀሙበት እንዳልከኝ እንደሆነ ልክ መጀመሪያ ላይ የሚፈልጉትን ነገር ለማሳካት አስበው እንደተስማሙት ሁሉ አሁንም አንድ ሚልጉት ነገር ሲቀርባቸው ያፈርሱታል።

👉 ይህ ነው እንግዲህ የሙስሊሞች አንድነት እያሉ የሚያዜሙትና ጭፍሮቻቹውም በጭፍን ተከትለው የሚያስተጋቡት።

✏️ ስለዚህ ያ ሸባብ ሆይ!!! ዲንህ ማለት ልክ በቁጥር አንድ ላይ እንደገለፅኩት እርካሽ ፖለቲካ ዱኒያ ላይ ብቻ የምትከስርበት ሳይሆን ዱኒያ አሄራህንም የምትከስርበት ነውና ከማንና ከምን ዲንህን መያዝ እንዳለብህ ጠንቅቀህ አውቀህ የሙጥኝ ልትል ይገባሃል።

📢 ይህ ሳይሆን ቀርቶ አፈ ጮሌ ተናጋሪና ጥሩ ፀሃፊ ተከትለህ የምትሄድ ከሆነ ሚጠብቅህ ትልቅ ኪሳራ መሄኑን አትጠራጠር።

👉 በተረፈ ምሎ ሸይኽ እንዳትሰማ አዎ እንድትሰማ እሺ! እንዳትፈራ የሚልህ ሰውዬ እሱ ነቢይ መሆን አለበት ካልሆነ በምን ሂሳብ ነው እሱን እየሰማኸው ሸይኽ እንዳትሰማ እንዳትፈራ የሚልህ?

👉 አትጠራጠር ይህንን ያለ በቂ ምክንያት ከተቀበልክ አንተ ሰው ሳትሆን ጋሪ ነህ ማለት ነው።

⏱ እንደ አስፈላጊነቱ በመርከዙ ሰዎች ላይ ሰሞኑን አሊሞችን እየተሳደቡ ባሉት አካላት ላይ የራሴን እይታ መረጃን በማጣቀስ መፃፉን እቀጥላለሁ።
ኢንሻ አላህ።

=============================

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

✔️ ጥሩ ጥሩ ት/ቶችን ለማግኘት ወደ ቻላችን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ👇👇

https://t.me/abufewuzanabduselam
✍️ አቡ ፈውዛን አብዱሰላም


Muhammed Mekonn dan repost
ግርም የሚለኝ...

የሱልጣን ኸድር ጥፋት ሲጋለጥ እንደት በአንድ ሰው ጥፋት ኢብኑ መስዑዶች ይወቀሳሉ? ይሉናል

የአዩብ ደርባቸውም ጥፋት ሲጋለጥ እንደት በአንድ ሰው ጥፋት ኢብኑ መስዑዶች ይወቀሳሉ? ይሉናል

የኢልያስ አህመድ ጥፋት ሲጋለት እንደት በአንድ ሰው ጥፋት ነሲሃ ቲቪዎች ይወቀሳሉ? ይሉናል።

እኔምለው ነሲሃ ቲቪዎችም ይሁኑ ኢብኑ መስዑዶች የነዚህ ግለሰቦች ውጤት አይደለምን?

ጥፋታቸውን እስካልተራረሙና ድረስ በጋራም አጠፉ በተናጠልም አጠፉ ጥፋታቸው ይጋለጣል። ሀቁን በደንብ ላስተዋለ ደግሞ በመደጋገፍ የተመዩዕን እንቅስቃሴ በጋራ እያራመዱ ነው።

https://t.me/AbuImranAselefy/4576


“ኢብኑ መስዑድ መርከዝ ማለት ሱኒዩም ሙብተዲዑም ልገኝበት የሚችል ዱንያዊ ተቋም እንጂ፣ አንድ አይነት ስብስብ (ሰለፊዮችን) ብቻ ልያካትት የተቋቋመ አይደለም” ይሉናል የመርከዙ ዋናዎች...

✓ ከወራት በፊት የሆነ አከባቢ በሄድኩበት ከወንድሞች ጋር ስለ መርከዙ አንስተን እያወራን፣ አንድ ወንድማችን የመርከዙ ሰዎች ያሉትን ስነግረን እንዲህ ነበር ያለን...

“ መርከዝ ኢብኑ መስዑድ ትልቅ ተቋም ስለሆነ የተለያዩ አይነት ሰዎችን የያዘ ነዉ፣ እዚህ ዉስጥ ጠንካራ አቋም ያለዉና ለዘብተኛ ሰለፊም፣ እንደዚሁም ሙብተዲዑም ልኖርበት ይችላል” ... ነበር ያለኝ... ያኔ ያሰብኩት ሰዎቹ ከመርከዙ ለመከላከል ብለዉ የሚሉት ስጠፋቸዉ የቀበጣጠሩት ንግግር ነዉ እንጂ ምንም ያክል ወርደዉ ብወርዱ በራሳቻዉ ላይ በዚህ ደረጃ የምስክር ቃል አይሰጡም ብዬ ነበር የቆየሁት። ለካ ነገሩ የምራቸዉ ነበር፣ ይሄዉ ኢልያስ አህመድ ሚዲያችን ላይ ትክክለኛ አቋም የሌለዉም ሰዉ ሊቀርብበት ይችላል እያለን ነዉ

https://t.me/Khedir_M_Abomsa/2102


ما هي قاعدة لا يلذمني؟
🎙الشيخ محمد بن هادي المدخلي حفظه الله تعالى

🔸ላየልዚሙነይ የምለው ቃዒዳ በሰለፎች ዘንድ እንዴት ይታያል?
ሙመይዓዎች እና ሙሪዶቻቸው የወደቁበት አጀንደ
ሸይኩ እንዴት አድርጎ ስያብራሩት ተመልከቱ👆
ላያልዚሙኒይ የማን ቃዒዳ እንደሆነች ይናገራሉ እናድምጥ👂
ኢልዛም ማድረግ አይቻልም ብሎ የምጮሁ ሰዎች የሰለፎችን አቋም አየቁምን?
ያ አለህ ሀቅን በሀቅናቱ አሳየን መከተልንም ወፍቀን
ባጢልን ባጢልነቱን አሳየን መራቁንም ወፍቀን
ሀቅ ላይ ፅናት ስጠን ያ ረብ🤲


https://telegram.me/Abufurayhan
https://telegram.me/Abufurayhan




#አዲስ_ሙሐደራ
✅ محاضرة جديدة


⬅️ بعنوان:-➘➘➘
↩️ جرح المبتدع الصادر من أهل العلم هل هو ملزم أم لا إلزام فيه؟!


➡️ ርዕስ፦
↪️ አንድ የሱና አሊም አንድን ግለሰብ በማስረጃ ሙብተዲእ ነው ቢል ጉዳዩ በሌሎች ላይ አስገዳጅ ነው ወይስ አይደ
ለም?

ቁጥር፦ 01

➽ በሀገራችን ላይ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ዳሰሳ ተደርጓል። በደንብ ይደመጥ!!!

🎙للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/5018

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


القناة التعليمية الرسمية لأبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي

የተለያዩ የኪታብ ደርሶች ተፍሲርናሙሀደራዎች የሚለቀቅበት ቻናል
"يا أيها السني السلفي الأثري لا تخاف في الله لومة لائم وبين الحق للناس ورد على أهل الباطل والبدع والخرافات باطلهم وبدعهم رضي من رضي وغضب من غضب "


https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha


#አዲስ_ትምህርት

🕋🕋🕋🕋
⬅️ العلاقة بين التشيع والتصوف عرض ونقد
➡️ አል አላቀቱ በይነ አት -ተሸዩኢ
ወት -ተሶውፊ

↪️ በራፊዷዎች እና በሱፍያዎች መካከል ስላለ ዝምድናና ግንኙነት

📝 تأليف فضيلة الشيخ فلاح بن إسماعيل بن أحمد مندكار أستاذ العقيدة في كلية الشريعة بجامعة الكويت رحمه الله
المتوفى سنة 1442 هجريا

📝 ፀሃፊ:- ፈዲለቱ ሸይኽ ፈላህ ቢን ኢስማኢል ረሂመሁሏህ


ኪታቡን በPDF ለማገናኘት ⬇️
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/4978
🎙للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ
🕋🕋🕋🕋🕋🕋

⬆️⬆️ ደርስ ቁጥር 05 ⬆️⬆️

@UstazAbuzarhassenAbutolha
@UstazAbuzarhassenAbutolha
@UstazAbuzarhassenAbutolha


Copy ናት። ኢንሻ አላህ በጣም ጥቃሚ ናት።


ተውሂድ አል ኡሉሂያ ፦ አሏህን በአምልኮቱ ብቸኛ ማድረግ

▪️ሰዎች በሚሰሩት አምልኮታዊ ተግባር አሏህን ብቸኛ ማድረግ ተውሂድ አል ኡሉሂያ ወይም ተውሂድ አል ዓባዳ ተብሎ ይጠራል።

➥ተውሂድ አል ኡሉሂያ ማለት፦አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከእርሱ ውጭ በእዎነት የምመለክ አምላክ የሌለ ብቸኛ እና እውነተኛ አምላክ መሆኑን ከእርሱ ውጭ የሚመለኩት ሁሉ የውሸት አሚልክት መሆናቸውን በመተናነስ እና ሙሉ በሆነ ታዛዥነት ሊመለክ የሚገባው እርሱ መሆኑን ከእርሱ ጋር ማንም ይሁን ማን በአምልኮት አንድም ተጋሪ የሌለው መሆኑን በግልፅም ይሁን በስውር ተፈፃሚ የሚሆኑ የአምልኮት ዘርፎች
➧ለምሳሌ፦ ሶላት ፣ ፆም ፣ ዘካ፣ ሀጅ ፣ዱዓ ፣ እገዛ ፣ ስለት ፣ እርድ፣ መመካት ፣ ፍርሃት ፣ ተስፋ፣ ውዴታ መተናነስ እና ሌሎች ግልፅም ይሁኑ ድበቅ የኢባዳ ዘርፎችን አሳልፎ ለሌላ መስጠት እንደማይገባ፤ በውዴታ በፍርሃት እና በተስፋ የአምልኮ አየነቶችን በጥምረት ለእርሱ እንደሚገባና አንዱን ነጥሎ በአንዱ ብቻ አሏህን መገዛት ጥመት መሆኑን በቁርጥ ማመን ማለት ነው አሏህ እንዲህ ይላል፦

قل الله تبارك وتعالى: إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ

አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
ሱረቱ ፋቲሀህ ፡ 5)

وقل تعالى: وَمَن يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِندَ رَبِّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ

ከአሏህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡
(ሱረቱ አል ሙእሚኑን ፡ 117)

➧ለአምልኮ ተውሂድ ሲባል አጋንንት እና የሰው ልጅ ተፈጥሯል። አሏህ እንዲህ ይላል፦

وقل تعالى :وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
(ሱረቱ ዛሪያት: 56)

▪️እርሱ የመጀመሪያም የመጨረሻም የውስጡም ይሁን የውጩም እምነት ነው።

እንዲሁም የመልዕክተኞች የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ጥሪ ተውሂድ አል ኡሉሂያ ብቻ ነው። ለተውሂድ አል አሉሂያ ሲባል አጠቃላይ መልዕክተኞች ተላኩ፣ መፅሐፍቶች ተወረዱ ፣ ለጂሀድ ሰይፎች ተመዘዙ ፣ አማኞች ከከሃዲዎች፤ የጀነት ባለቤቶች ከጀሀነም ባለቤቶች ተለዩ።
"ላ ኢላሃ ኢላሏህ" የሚለው ቃል ፅንስ ሀሳብም እርሱው ነው።
➥ተውሂድ አል ኡሉሂያ አጠቃላይ መልዕክተኛች ዳዕዋ ያደረጉበት የዒባዳ (የአምልኮት) አይነት ሲሆን ይህን የተውሂድ ክፍል በመቃረናቸው ያለፉ ህዝቦች መሆናቸው ይታወቃል። አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡
(ሱረቱ አል አንቢያዕ :25)


إِنْ شَاءَ ٱللّٰه ..........


#ይ_ቀ_ጥ_ላ_ል_...

=============================

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

✔️ ጥሩ ጥሩ ት/ቶችን ለማግኘት ወደ ቻላችን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ👇👇

https://t.me/abufewuzanabduselam
✍️ አቡ ፈውዛን አብዱሰላም

✍️ ابو فوزان ابدسلام


📝 ‟ተውጅሀት ሊልፈታቲአል- ሙስሊማህ‼️ Copy ናት።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
(ምክር ለሙስሊም እህቶች)

ከአቡ ሙስሊም ኡመር. አል አሩሲ

ድምጽ ፋይል የተወስደ

➡️በጊዜ መጠቀም

➡️ጊዜአችንን መጠቀም አለብን

➡️ጊዜሽን በማይሆን ነገር እንዳታቃጥይ እንዳታጠፊ
➡️በምችይው አቅም ሁሉ ጊዜሽን ተጠቀሚበት

👌የምትጠቀሚበት ደግሞ ቢያንስ. በዱኒያም በአኼራም በሚጠቅምሽ ነገር

👌 ማወቅ ያለብሽ ነገር እች የምትኖሪላት ሀያተ ዱኒያ የፈለገ ረጅም ብትመስልም እሷ አጭር ናት
👉አማኝ የሆነ ስው ደግሞ የሱ ጊዜ በጣም ውድ ነው
👉እንደት ውድ ነው የሱ ግዜ ?

👌 የሱግዜ እኮ ሂወቱ ነው። እራስ ማዶ ነው
ጊዜውን በአግባቡ ከተጠቀመ ደስተኛ ይሆናል ይድናል ።
👌ግን ጊዜውን ካቃጠለስ ይከስራል ።
➲ጊዜ አስፈላጊ ስለሆነ ነው አሏሁሱብሀናሁ ተአላ የማለበት ።
➲አሏሁ ሱብሀናሁ ተአላ በፈለገበት መማል ይችላል
▲አማኝ የሆኑ ስዎች ግን በአሏህ ሱብሀናሁ ተአላ ብቻ ነው መማል ያለባቸው።
▲በረሱልም አይማልም
▲አባቴ ከፊትህ ይነጥለኝ
▲እናቴ እንድህ ትሁን
▲በከሌ ሽህ እሚባል ነገር የለም

➡️ነብያችን ስለሏሁአለይሂ ወስለም እንድህ ብለዋል. ከናንተ ውስጥ መማል የፈለገስው በአሏሁስብሀናሁተአላ. ብቻ ይማል አው ደግሞ ዝም ይበል።

➡️ ጊዜ በጣም በእስልምና ቦታ ስላለው ነው አሏሁሱብሀናሁተአላ የማለበት

وَٱلْعَصْرِ➻

وَٱلضُّحَىٰ➻

وَٱلْفَجْرِ➻

وَٱلَّيْلِ إِذَا يَغْشَىٰ➻
↪️እነዚህ ሁሉ በቀንና በሌሊት የሚገኙ ጊዜዎች ናቸው።
↪️አሏሁ ሱብሀናሁ ተአላ በነዚህ ጊዜ የማለበት ጉዳይ አላማው
👌ይህ ጊዜ በጣም አስፈላጊና እሚያስፈልግ ነገር ስለሆነ ነው

➡️አንች እህቴ ሆይ ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚበት
➾ጊዜሽን ጥሩ ነገር ስሪበት
👌ከዚህ ጊዜ ደግሞ ወደፊት ትጠየቂያለሽ
➾ገና ከእድሜየሽ ትጠየቂያለሽ በጠቃላይ በተለይ ደግሞ በወጣትነት የስራውን ስራ ወይም ደግሞ የወጣትነት ጊዜ ትጠየቂያለሽ
👉ጊዜሽን በምነው ያሳለፍሽው የሚለው ነገር መጠየቅሽ አይቀርም

➡️አቡ በርደህ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ያስተላለፈው ሀድስ የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወስለም እንድህ አሉ
👌 የውመል ቂያማ የስዎች እግር ካለበት ቦታ ላይ አይንቀሳቀስም ይላሉ
➲እስኪ ጠይቅ እንጅ
➲ከእድሜው
➲እድሜውን በምነው ያቃጠለው የጨረስው
➲እውቀት ደግሞ ከተማረ በእውቀቱ ምንድነው የስራህበት ሳይጠየቅ ካለበት ቦታ ላይ አይንቀሳቀስም
➲ሀብቱን ደግሞ ከየት ነው ያመጣው በምንላይ ነው የለገስው የስጠው መጠየቁ አይቀርም
➲ከስውነቱም ይጠይቃል በምን ላይ እንደጨረስው

➡️ ልታምኒ ትችያለሽ ውበት ሊኖርሽ ይችላል ቁመት ሊኖርሽ ይችላል. ውፍረት ሊኖርሽ ይችላል
👌 ግን ይህን አሏህ የስጠሽን ኒእማ ለፊትና እንዳትጠቀሚበት
👌ስዎችን አዛ በማድረግ እንዳትጠቀሚበት ገና የውመል ቂያማህ አሏሁሱብሀናሁተአላ ስለሚጠይቅሽ
➾ማወቅ ያለብሽ ነገር ግን ሁላችንም እምናውቀው ዛሬ እምትተማመኝበት ይሄ ውበትሽ ውበት አደለም እምትይ ከሆነ ውበት እሚባለው በኢስላም እራሷን ሽፍና እምትኖር ነው ትክክለኛው ውበት ይህነው።
➡️ውበት ሲለካ ሂጃብ ነው ላካ ይላል ያገሬስው
➲ፊትሽ ላይ የሆነ ጠባሳ ቢኖር ኖሮ ፊትሽን ከፍተሽ አቴጅም ትሽፋፈኛለሽ
➲ስውነትሽ ላይ ትልቅ የሆነ ቁስል ቢኖርገልጠሽው አቴጅም ተሽፋፍነሽ ነው እምቴጅው
➲ግን አሏህን አትፈሪም ?
➲አሏህ ጥሩ አድርጎ ፈጥሮሽ ጥሩ ውበት ስቶሽ ለምን ትገላለጫለሽ ታዳ ይህን ውበትሽን ለምን አትሽፍኝው
↘️ገና አላህሱብሀናሁተአ ከዚህ ከአካልሽም ይጠይቅሻል
👉በሌላ ሀድስ ኢብኑ አባስ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ያስተላለፈው ሀድስ የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ውስለም
አምስት ነገር ከምጣቱ በፊት በነዚህ አምስት ነገሮች ተጠቀሙበት ይላሉ
➡️ወጣትነትህን እርጅና ከመምጣቱ በፊት ተጠቀምበት

👌አንችም ይሄን የወጣት እርሜሽን እውቀትን በመማር የሽሪአ አህካምን በመማር በማወቅ አላህን በመገዛት ማሳለፍ አለብሽ ከሀራም ነገር በመራቅ እድሜሽም መጠቀም አለብሽ

➡️ጤንነትህን በሽታ ከመምጣቱ በፊት ተጠቀምበት
👌ጤንነት በጣም ትልቅ ነገር ነው

👉በዚህ ጤንነቱ ስውየው ሶላት ካልስገደበት ፣ ዘካ ካልስጠበት ኢልም ካልተማረበት ሌሊት ቁሞ ካልስገደበት ምንም አይጠቅመውም በሽታ ይመጣል ይህን ጤንነትን መጠቀም ያስፈልጋል።
➡️ሂወትህን ደግሞ አጠቃላይ ሞት ከመምጣቱ በፊት ተጠቀምበት
👌ሞት ድንገት ነው እሚመጣው እመጣለሁ ብሉ አይናገርም ሜሴጅም አይልክም
👉የስውየው ቀጠሮ ከደረስ አጀሉ ከደረስ ከዚያ አጀል ላይ አንድ ደቂቃም አንድ ስከንድም ወደፊት ወደሁላ አይሄድም በጊዜው ይመጣል ።
➡️ለዛ ነው አሁን ያለሽበትን ሂወትሽን ተጠቀሚበት
➲ትርፍ ጊዜሽን ተጠቀሚበት
➲ቢዚ ከመሆንሽ በፊት በተለያየ ነገር ከመወጠርሽ በፊት

👌ዛሬ ጊዜካለሽ ያንን ግዜ ተጠቀሚበት ነገ ምን እንደምቶኝ ስለማታውቂ።

=============================

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

✔️ ጥሩ ጥሩ ት/ቶችን ለማግኘት ወደ ቻላችን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ👇👇

https://t.me/abufewuzanabduselam
✍️ አቡ ፈውዛን አብዱሰላም


ስለ ረመዷን ዳሰሳ
➜➜➜➜➜➜

ክፍል ሁለት

ክፍል አንድን ለማግኘት ⬇️⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/4564

✅ ተከታታይ ትምህርት ስለ ፆም ዘወትር ከቅዳሜ እስከ ሀሙስ ከአሱር ሶላት በኋላ የሚሰጥ

➽ የዛሬው ርዕስ፦
➼ የፆም ማዕዘንቶች!


🎙 أستاذ أبي جعفر محمد أمين السلفي حفظه الله
🎙በኡስታዝ አቡ ጃዕፈር ሙሐመድ
አሚን ሀፊዘሁሏህ

🕌 በሸዋሮቢት ከተማ በሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ የተሰጠ ወቅታዊ ትምህርት

https://t.me/AbuImranAselefy/4574


🟢 ውይይትና ሹቡሃት 2

✍مناظرة أهل البدع والاهواء


👉 የተወገዘው ከርክር

👉 ቁርኣን ፣ሀዲስ ፣ የሰለፎች ንግገሮች

👉 ሀቅ ተብራርቶም የሚከራከሩ እምቢተኞች



📚ከሸይኽ ሁሰይን ሙሀመድ ከቢድዐህ ባልተቤቶች ጋር ውይይት /ክርክር ስለማድረግ

🎤አቡ ሀመዊየህ

https://t.me/Menhaj_Alwadih


አፍአማኢ አፍአማኢ dan repost
ተናፋቂዋ ቀን!!
✍✍✍✍✍✍✍
ሻእባን አስራ ስድስት እለተ ቅዳሜ፤
ቀጠሮ ይዣለሁ ከሱናው ወንድሜ፤
በሱና ባንዲራ በተውሂድ ሰንሰለት፤
በማይነቃነቅ ጠንካራ ማንነት፤
ቀጠሮ ይዘናል ልንደምቅ በዛ እለት።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
በለምለሟ ደቡብ በለተሞ ምድር፤
ከድንቅ መሻይኾች በአካል ልንሰደር፤
ከድንቅ ምክራቸው ጥበብ ከሞላበት፤
እውቀትን ልንገበይ በጣፋጭ አንደበት፤
ደርሰን እስክናያት ጓጉተናል ያቺን እለት።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
የባህዳሩ ፈርጥ ኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ፤
በብእር የበጠሰ የቢድአን ገመድ፤
ታላቁ አባታችን ሸይኽ ሀሰን ገላው፤
የሙመይእ ጅራፍ ኡማውን ያነቃው፤
እንግዳችን ሆነው ዳእዋውን ሊያስውቡት፤
ቀጠሮ ይዘናል ልንደምቅ በዛች እለት።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
የደሴው ጀግናችን ኡስታዝ ኸድር አህመድ፤
ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ ሸይኽ ሁሴን መሀመድ፤
የኢልም ገበሬው ሸይኽ አብዱልሀሚድ፤
ኡስታዝ ባህር ተካ ኡስታዝ አልይ ሁሴን፤
ድንቁ መካሪያችን ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን፤
ኡስታዝ አብዱሯሂም ኡስታዝ አብዱልቃድር፤
ኡስታዝ ሰይፉዲን ደግሞም ኡስታዝ አብራር፤
ኡስታዝ ኪርማኒይ ደግሞም ኡስታዝ አንዋር፤
ሸይኹና ባህሩ ሁሉም ይጣዳሉ፤
ቢኢዝኒላህ ያኔ ደምቀው ይታያሉ።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
አብዱረህማን ኡመር ወንድም አቡ ኢምራን፤
ወንድማችን ሚስባህ አቡ ፉረይሀን፤
ከደቡብ ሰማይ ስር ከለተሞ ምድር፤
ቀምረው ቀመምው ያንን መሳጭ ምክር፤
በሶሻል ሚድያ ለአለም እንዲደርስ፤
ሽፍን ይሰጣሉ ያቺ ቀን ስትደርስ።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
የአመት ያክል ቢረዝም የሳምንቱ እድሜ፤
የወንድሞች ናፍቆት ቢዋሀድ ከደሜ፤
ደርሳ እስክትታይ ተናፍቂዋ ቀን፤
ክፉን ይያዝልን አሏህ ይጠብቀን።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አቡ ሳራህ ከሸዋ ምድር

ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል
➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/AbuSarahh
https://t.me/AbuSarahh


Muhammed Mekonn dan repost
📢 ማስታወሻ ⭕️🛑⭕️

↪️ ዛሬ በአላህ ፈቃድ በሸዋሮቢት ከተማ በፉርቃን መስጂድ እና ቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም (Telegram) ከአሱር ሶላት በኋላ ስለ ረመዳን ትምህርት ይኖረናል።

•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

🎙 أستاذ أبي جعفر محمد أمين السلفي حفظه الله
🎙 በኡስታዝ አቡ ጃዕፈር ሙሐመድ
አሚን ሀፊዘሁሏህ

✅ በአካባቢያችን ያላችሁ ወንድሞቻችን በአካል በመገኘት መከታተል ትችላላችሁ!

✅ በአካል መገኘት ለማትችሉ ደግሞ በቀጥታ ስርጭት የምናደርሳችሁ ይሆናል።

በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል
➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/joinchat/Sn62xstw8Nvq1swV


أذكـار.الـصـبـاح.والـمـسـاء.الـصـحـيـحـة.tt

1⃣ ((اللَّهمَّ أنتَ ربِّي لا إلَهَ إلَّا أنتَ ، خَلقتَني وأَنا عبدُكَ ، وأَنا على عَهْدِكَ ووعدِكَ ما استطعتُ ، أعوذُ بِكَ من شرِّ ما صنعتُ ، أبوءُ لَكَ بنعمتِكَ عليَّ ، وأبوءُ لَكَ بذنبي فاغفِر لي ، فإنَّهُ لا يغفرُ الذُّنوبَ إلَّا أنتَ)). صحيح البخاري.

2⃣ (سبحانَ اللهِ وبحمدِه) مائةَ مرةٍ. صحيح مسلم.

3⃣ (أعوذُ بكلمات الله التاماتِ من شرِّ ما خلق). صحيح مسلم.

4⃣ (اللهم فاطرَ السمواتِ والأرضِ عالمَ الغيبِ والشهادةِ ربَّ كلِّ شيءٍ ومليكَه ، أشهدُ أن لا إله إلا أنت ، أعوذُ بك من شرِّ نفسي ، وشرِّ الشيطانِ وشِرْكِه). صحَّحه الألباني.

5⃣ (اللهم إني أسألُك العافيةَ في الدنيا والآخرةِ ، اللهم إني أسألُك العفوَّ والعافيةَ في ديني ودنياي وأهلي ومالي ، اللهم استرْ عورتي وآمنْ روعاتي ، اللهم احفظْني مِن بين يديَّ ومن خلفي وعن يميني وعن شمالي ومن فوقي ، وأعوذُ بعظمتِك أن أُغتالَ مِن تحتي). صحَّحه الألباني.

6⃣ (إذا أصبح أحدُكم فلْيَقُلْ : اللهم بك أصبحْنا ، وبك أمسيْنا ، وبك نحيا ، وبك نموتُ ، وإليك النُّشورُ ، وإذا أمسى فلْيَقُلْ : اللهم بك أمسَيْنا وبك أصبحْنا ، وبك نحيا ، وبك نموتُ ، وإليك المصير). (صحيح الجامع).

7⃣ (لا إلهَ إلَّا اللهُ وحدَه لا شريكَ له ، له المُلْكُ وله الحمْدُ ، وهو على كلِّ شيءٍ قديرٌ : يومٍ مائةَ مرَّةٍ). صحيح البخاري.

8⃣ (يا حيُّ يا قيُّومُ برحمتِك أستغيثُ ، أَصلِحْ لي شأني كلَّه ، و لا تَكِلْني إلى نفسي طرفةَ عَيْنٍ). صحيح الترغيب.

9⃣ كانَ نَبِيُّ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عليه وَسَلَّمَ ، إذَا أَمْسَى قالَ : أَمْسَيْنَا وَأَمْسَى المُلْكُ لِلَّهِ ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ لا إلَهَ إلَّا اللَّهُ ، وَحْدَهُ لا شَرِيكَ له قالَ : أُرَاهُ قالَ فِيهِنَّ : له المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ وَهو علَى كُلِّ شيءٍ قَدِيرٌ ، رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ ما في هذِه اللَّيْلَةِ وَخَيْرَ ما بَعْدَهَا ، وَأَعُوذُ بكَ مِن شَرِّ ما في هذِه اللَّيْلَةِ وَشَرِّ ما بَعْدَهَا ، رَبِّ أَعُوذُ بكَ مِنَ الكَسَلِ وَسُوءِ الكِبَرِ ، رَبِّ أَعُوذُ بكَ مِن عَذَابٍ في النَّارِ وَعَذَابٍ في القَبْرِ.

وإذَا أَصْبَحَ قالَ ذلكَ أَيْضًا : أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ المُلْكُ لِلَّهِ. صحيح مسلم.

🔟 (رضيتُ باللهِ ربًّا وبالإسلامِ دينًا وبمحمَّدٍ صلَّى اللهُ عليهِ وسلَّمَ نبيًّا). ثلاث مرات. [حسَّنه الإمام ابن حجر العسقلاني].

1⃣1⃣ (قراءة سورة الإخلاص والمعوذتين ثلاث مرات). حسَّنه الألباني.

2⃣1⃣ (بسمِ اللَّهِ الَّذي لا يضرُّ معَ اسمِهِ شيءٌ في الأرضِ ولَا في السَّماءِ ، وَهوَ السَّميعُ العليمُ ثلاثَ مرَّاتٍ). حسَّنه الألباني.

3⃣1⃣ (حسبيَ اللهُ لا إلهَ إلا هو عليه توكلتُ وهو ربُّ العرشِ العظيمِ) سبعَ مراتٍ. جاء موقوفا على أبي الدرداء بإسناد جيد.

4⃣1⃣ (سبحان اللهِ وبحمدِه ، عددَ خلقِه ورضَا نفسِه وزِنَةِ عرشِه ومِدادَ كلماتِه). ثلاث مرات. رواه مسلم.

5⃣1⃣ (اللَّهمَّ عافِني في بَدَني ، اللَّهمَّ عافِني في سَمْعي ، اللَّهمَّ عافِني في بَصَري ، لا إلهَ إلَّا أنتَ ، اللَّهمَّ إنِّي أَعوذُ بكَ منَ الكُفرِ والفَقرِ ، اللَّهمَّ إنِّي أَعوذُ بِكَ مِن عَذابِ القَبرِ ، لا إلهَ إلَّا أنتَ). [ثَلاث مرات]. حَسَّنه الألباني.

=============================

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

✔️ ጥሩ ጥሩ ት/ቶችን ለማግኘት ወደ ቻላችን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ👇👇

https://t.me/+spJD1ge2_kA2MTNk
✍️ አቡ ፈውዛን አብዱሰላም


ሙፍቲ ምን እያቱ ነው⁉️

➼ ትናንት የተቀበሩትን ፓትሪያሪክ በተመለከተ "አባታችን አባታቸው ጋር በደህና በሰላም ይገናኙ እላለሁ!" በማለት የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሀጂ ዑመር ገነቴ ተናግረዋል።

ምን ማለታቸው ነው?

ጊዜ ሳገኝ እመለስበታለሁ

https://t.me/AbuImranAselefy/4572


Muhammed Mekonn dan repost
"ሙመይዓህ" የውሸት ሙግት
ወይስ በተጨባጭ ያለ አንጃ
================>


↪️ ሙመይዓህ የሚባል አንጃ የለም ለሚሉ እንዲሁም ሙመይዓህ ኢብሊሳዊ ሙግት ነው እያሉ ለሚያጭበረብሩ አካላት አጭር ምላሽ!

↪️ ሙመይዓዎች የተለያዩ ሙኻለፋዎችን [ከሰለፎቻችን መንገድ ያፈነገጡ] አካሄዶችን በሙስሊሞች ላይ ለመጫን በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ራሳቸውን መደበቅ ይፈልጋሉ። ይህ አዲስ አይደለም። ኢኽዋንዮችም ተመሳሳይ ስትራቴጂ ይከተሉ ነበር።

በሀገራችን ኢትዮጵያ ከነበሩበት ጠንካራ አቋም የቀለጡ ሰዎች ብዙ ከመሆናቸው ጋር ሙመይዓህ የሚባል አንጃ የለም እያሉ ለማጭበርበር የሚሞክሩ ግለሰቦች አሉ።

እውነታውን ለማወቅና ለመመርመር የፈለገ ሰው በጉዳዩ ላይ ተረጋግቶ ማጥናት ያስፈልጋዋል። የነብያት ወራሽ የሆኑት ታላላቅ ኡለሞቻችን ያብራሩትን መግለጫ ማስተዋል ተገቢ ይሆናል።

ለአብነት ያክል ሁለት ኪታቦችን እንመልከት፦

1ኛ በአቡ አብዲረህማን ከማል ተዘጋጅቶ በሸይኽ ሙሐመድ ብን ረምዛን ሀፊዘሁሏህ ተጠንቶ ታትሞ እንዲሰራጭ የተደረገው በሙመይዓወችና ሀዳዲያዎች ዙሪያ የሚያጠናው የሚከተለው ኪታብ አንዱ ነው።

📚 البراهين المرصعة في كشف حال الحدادية والمميعة
📚 አልበራሂኑል ሙረሶዓህ ፊከሽፊ ሀሊል ሀዳዲየቲ-ወልሙመይዓህ


በPDF ለማግኘት ⬇️⬇️⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/3789

📖 ተቅዲም ያደረጉት ሸይኽ መሐመድ ታላቅ ዓሊም ናቸው። የነኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሰይሚን፣ የነሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ የሌሎችም የሱንና ኡለሞቻችን ተማሪ ናቸው። ይህ ኪታብ ጥሩ ኪታብ ነው ታትሞ መሰራጨት አለበት ብለው ተናግረዋል።

⁉️ ጥያቄ፦ ታዲያ ይህ ታላቅ ዓሊም ስለ በሙመይዓወች ዙሪያ የተፃፈውን ኪታብ መርምረው ይሰራጭ ያሉት "ሙመይዓህ" የሚባ አንጃ ሳይኖር ነውን!? ይህ ዓሊም እየዋሹ ነውን!?

በነገራችን ላይ ኪታቡን ውዱ ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን ሀፊዘሁሏህ ሙሉውን አቅርቶታል።
001--090 ለማግኘት
➘➘➘➘➘
https://t.me/Abuzarehassenlmam/1293

በተጨማሪም ስለ ኪታቡ አስፈላጊ ማብራሪያዎችንና ተቅዲም ስላደረጉት ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ረምዛን ገለፃና ስለ ተቅዲማቸው ማብራሪያ በሸይኽ አቡ ዘር ሀፊዘሁሏህ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይከታተሉ።
➘➘➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/4569

2ኛ ሙመይዓህ የሚባል ፊርቃ የለም ለሚሉ ሰዎች ሌላ ራስ ምታት የሆነ መፅሃፍ
↩️ بعنوان ➘➘➘
📖 وجوب اتباع منهج السلف والحذر من التميع والتشدد في التعامل مع المخالفين وأهل البدع
↪️ ርዕስ፦ ➘➘➘
📖 የሰለፎችን መንሃጅ መከተል ግደታ ስለመሆኑ እንዲሁም ከሙኻሊፎችና ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር በሚኖረው ግንኙነት ከተምይዕ (ከመሟሟት) ያለቦታው ከማጥበቅ መጠንቀቅ!


✅ በዚህ ኪታብ ስለ ሙመይዓዎች ዝርዝር ማብራሪያ ተካቷል። ብቁ የሆናችሁ ሰዎች አንብቡትና 'ሙመይዓህ' የሚባል አንጃ የለም የሚሉ አካላትን ታዘቧቸው።

ኪታቡን በpdf ያገኙት ⬇️
https://t.me/AbuImranAselefy/4570


➽ ሌሎችም በሙመይዓወች ዙሪያ የተሰጡ ማብራሪያዎች በድምፅም በፅሁፍም በርካታ ሲሆኑ እንዳስፈላጊነቱ ወደፊት የምንመለከታቸው ይሆናል።

ሙመይዓህ የሚባል የለም ለሚሉ ሰዎች "ከዚህ በፊት ኢኽዋን የሚባል የለም" በማለት ሙስሊሞችን ለማታለል ሞክረው እንዳልተሳካላቸው እናንተም አይሳካላችሁም ለማለት እፈልጋለሁ።

📝 አቡ ዒምራን

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

235

obunachilar
Kanal statistikasi