የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!
ክፍል - 4
~
ያያያዝኩት የባህሩ ተካ ንግግር ነው። የውሸት እርከኑን በዚህ መጠን ከፍ አድርጎታል። ውሸቱን ሲለማመደው ጊዜ "አንባቢ ይታዘበኛል" የሚለውንም ትቶታል። እንዲያው አንድ ሰው መስሎት ተሳስቶ ቢናገር ይሁን። ይሄ ሐያእ የቀለለው ፍጡር ግን በምን መልኩ ሰው ላይ እንደሚዋሽ ተመልከቱ። ሳዳት ነው ወደነዚህ አካላት የሚጣራው? በሐዲሥ እንደመጣው ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ ሁለቱ ሲያወሩ መዋሸት እና በሙግት ላይ አመፀኝነት ወይም ገልብጦ መወንጀል ነው። በነዚህ አጥፊዎች ላይ ረድ መስጠት ነው ወደነሱ መጣራት ተብሎ የሚገለፀው? ጥላቻ አናቱ ላይ ወጥቶ በትክክል ማየት እንዳይችል ጋርዶታል። በረድ ስም እየዋሸ መለጠፍ ጣፋጭ ምግብ ሆኖለታል። እጅ እጅ የሚል ፅሁፉን ውሸት ጣል ሲያደርግበት ውበትና ጥንካሬ የሚጨምር ይመስለው እንደሁ አላውቅም። "የሰካራም ግጥም ሁሌ ቅዳ ቅዳ" እንዲሉ ወጥሮ የውሸት አውቶማቲክ መተኮሱን ተያይዞታል። ረድ ማለት የጠሉት ሰው ላይ የፈለጉትን መለጠፍ ሆኗል ባህሩ ዘንድ። ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ውሸትን ስራዬ ብሎ አጥብቆ ይይዛል? ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
وإِيَّاكُمْ والْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، ومَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَكْذِبُ ويَتَحَرَّى الْكَذِبَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللَّهِ كَذَّابًا
“አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡ አንድ ሰው ሲዋሽና ውሸትም ላይ ሲያተኩር አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይመዘገባል።” [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
ሳዳትን በማጠልሸት ላይ እንቅልፍ ከምታጡ ራሳችሁን ከዚህ የውሸት ሱስ አውጡ። ሳዳት እናንተን ከነ ንዝንዛችሁ እርግፍ አድርጎ ትቶ አነሰም በዛም የራሱ ስራ ላይ ነው ያለው። ደግሞም በተለይ ተራውን ህዝብ በማንቃት ላይ ባለው አስተዋፅኦ አንዳችሁ እንኳ የሚስተካከል ቀርቶ የሚቀርብ ነገር የለውም። የራሳችሁን ድርሻ ባግባቡ እንደመወጣት ሰዎች የሱን ትምህርት እንዳይከታተሉ ጥላሸት መቀባትን ጂሃድ አድርጋችሁታል። ይሄ ነው የናንተ ስኬት።
ባህሩ ተካ እንደምታዩት ወንድማችን ሳዳትን ወደ "ቲክ – ቶክ መንደር ወርዶ ወጣቱን ወደ ዮኒ ማኛና ኢክራም አውቶሞቲቭ" ይጣራል እያለ ነው።
* ሳዳት ከአጥፊዎች ነው ያስጠነቀቀው። ባህሩ ደግሞ አጥፊዎቹን ጥሎ ሳዳትን መዝለፍ ላይ ነው የተጠመደው። ከአጥፊዎች ማስጠንቀቅ ወደነሱ መጣራት ከሆነ እንዳበደ ውሻ ሁሉን የምትናከሱት እናንተ አጥፊዎች ወደምትሏቸው እየተጣራችሁ ኖሯል ለካ? መቼም በራሳችሁ ጩኸት ስለደነቆራችሁ ሂሳባችሁ ምን እንደሚሰጥ አይገባችሁም።
* ምናልባት አጥፊዎቹን ፊት ለፊት ተገኝቶ መምከሩን ከሆነ ወደነሱ መጣራት የምትለው ይሄ ምን ያህል በልብህ ያረገዝከው ጥላቻ ነገሮችን የመረዳት አቅምህንም እንዳሽመደመደው ነው የሚያሳየው። እንዲያው አቀራረቡ ላይ ሂስ አለኝ ብትል እንኳ እንዳንተ አይነቱ በቆሻሻ የብሄር ካባ ተጀቡኖ የጉራጌ ካፊ'ሮች ጋር አንድነት ስለማድረግ የሚሰብክ ሰው ሂስ የመሰንዘሩን ድፍረት እንዴት ነው የሚያገኘው? የጥላቻ ብቅል ይህን ያክል ያሰክራል ለካ! የሚገርመው በዚህ መልኩ አይኑን በጨው አጥቦ እየዋሸ "ውሸታም" ተባልኩ ብሎ ሲብሰው ማየት ነው። የእውነት ህሊና ካለህ ከመባልህ ይልቅ መሆንህ ያስጨንቅህ። ያለበለዚያ ነገሮችን እየገለበጥክ ማየትህን ትቀጥላለህ። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁላህ ምን እንደሚሉ ተመልከት:-
إياك وَالْكذب فَإِنَّهُ يفْسد عَلَيْك تصور المعلومات على مَا هِيَ عَلَيْهِ وَيفْسد عَلَيْك تصورها وَتَعْلِيمهَا للنَّاس فَإِن الْكَاذِب يصور الْمَعْدُوم مَوْجُودا وَالْمَوْجُود مَعْدُوما وَالْحق بَاطِلا وَالْبَاطِل حَقًا وَالْخَيْر شرا وَالشَّر خيرا فَيفْسد عَلَيْهِ تصَوره وَعلمه عُقُوبَة لَهُ.
"ውሸትን ተጠንቀቅ። እሱ መረጃዎችን ባሉበት ሁኔታ (በትክክለኛ ቅርፃቸው) የመረዳት አቅምህን ይበክልብሃል። በተጨባጭ መሳልና ማሳወቅንም እንዲሁ ያበላሽብሃል። ውሸታም የሌለውን እንዳለ፣ ያለውን እንደሌለ፣ እውነቱን ሃሰት፣ ሃሰቱን እውነት፣ ኸይሩን ሸር፣ ሸሩን ደግሞ ኸይር አድርጎ ገልብጦ ያቀርባል። በውሸቱ ይቅቀጣ ዘንድ የመረዳት አቅሙም እውቀቱም ይበላሽበታል።" [አልፈዋኢድ፡ 135]
ውሸትን እንደ ፅድቅ ማየት የመጣው በዚህ ምክንያት ነው። "የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይ የሰው ማገዶ ያስጨርሳል።"
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor