"ወንጀል ከሱና አያስወጣም " እየተባለ .. ውሸት ፣ ማጭበርበር እና ሌሎችም አስከፊ ወንጀሎች ዉስጥ በግዴለሽነት መነከር አሳፋሪ መባል የሚያንሰው ክፉ ና ፀያፍ ምግባር ነው .. ወቅታችን ላይ ደግሞ ይሄው ክፉ ደዌ ብዙዎችን አጥቅቷል ---- ወንጀል አይጎዳ ይመስል በቀጥታም ባይሆን ባዙሪት ቀላልነቱ ይሰበክ ይዟል - በአንዳንዶቻችን ...
ነብዩን እና ባልደረቦቻቸውን እከተላለሁ የሚል ግለሠብና ወገን ወንጀልን የሚመለከትበት አይን ኢርጃእን የተጎራበተ መሆኑ ወይም የተጎራበተ ሊሆን መቃረቡ ይሳዝናል ...
የአላህን፡ ህግጋቶች ማክበርና አግዝፎ መመልከት የተቅዋ እና የአላህን ቅጣት መጠንቀቅ መገለጫ ነው ...
وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ
የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች (ትእዛዦች ፣ ክልከላዎች ) የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦች የኾነች ጥንቃቄ ናት፡፡
ተቃራኒው እንዝላልነት የልብን መጥቆር አጉልቶ ይሳያል .....
ዓብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ሙእሚን ወንጀልን አግዝፎ እንደሚመለከት፣ ሙናፊቅ ግን እጅጉን አቅልሎና አሳንሶ እንደሚያየው ተናግረዋል .....
በወንጀሎች ላይ መዘውተር የከሃዲያን መገለጫ መሆኑንም ልንዘነጋ አይገባም ... አላህ እነሱን ሲገልፃቸው እንዲህ ይላል
وَكَانُوا يُصِرُّونَ عَلَى الْحِنثِ الْعَظِيمِ
(በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና )
ሌላው ነገር፦ ወንጀል (በተለይ የድብቅ ወንጀል ) መጨረሻን (አሟሟትን) ከሚያበላሹ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነውና የዛሬውን ሱና ላይ መሆን ብቻ ሣይሆን የወንጀል ብዛት ሊያስከትል የሚችለውን መንሸራተትና ክፉ ውጤት እናስብ... አላህን እንፍራ ... ወደሱም እንመለስ ።
ጥፋትና ወንጀል ከሁላችንም ሊመነጭ የሚችል መሆኑን አልዘነጋሁም ። ከላይ በተጠቀሰው መጠን ወንጀል ላይ ቸልተኛ መሆን ግን እጅጉን አደገኛ ነው።
አላህ፡ ይመልሰን !
ቻናሉን ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። መልእክቱን ለሌሎች በማሰራጨት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።
t.me/Muhammedsirage