Isaiah 48 Apologetics dan repost
♦ የሱራ 109 ሀሰት!
ከክርስቶስ ትምህርት ጋር ተቃራኒ ሆኖ የሚነሳ ማንኛውም እምነት ወይንም ርዕዮተ-አለም ሀሰት ነው። ይህ ሀሰተኝነቱም በተለያየ መልኩ ይጋለጣል።
ቁርአንም የክርስቶስን ትምህርት በመቃወም ተወዳዳሪ የሌለው የክህደት መጽሐፍ ነው። በዚህም ምክንያት ሊታበሉ የማይችሉ ስህተቶችን ይዟል
ቁርአን በተለያዩ ቦታዎች እውነተኛ መሆኑን ተናግሯል። እውነተኛነት ደግሞ የፈጣሪ ቃልነት አንዱ መስፈርት ነው። ነገር ግን ቁርአን እውነተኛ አለመሆኑ ከተረጋገጠ፥ ከፈጣሪ ቃልነት ተርታ ይወጣል ማለት ነው። (ሱራ 22:54 13:1 4:170)
▶ ዛሬም በጌታ ፈቃድ አንድ የቁርአንን ሀሰት እንመለከታለን። ይኸውም የሱረቱል ካፊሩን (የከሃዲዎች ምዕራፍ) ነው። ሱራ 109
የዚህ ሱራ አስባቢል ኑዙል (የመውረዱ ምክንያት) የቁሬይሽ ሰዎች ወደ መሐመድ መጥተው "አንድ አመት ያንተን አምላክ እናምልክ፥ አንዱን አመት ደግሞ የኛን አማልክት አምልክ። ከዚያም አንተ ያመጣህልን የተሻለ ከሆነ መልካሙን እንወስዳለን፥ እኛ ያመጣነው መልካም ከሆነ መልካሙን ትወስዳለህ" ሲሉት፥ አላህ ይህንን ሱራ አወረደ
[ Wahidi - Asbab Al-Nuzul surah 109]
🚩 ይህ ሱራ የወረደው ለቁሬይሽ ሙሽሪኮን ነው። በዚህም ምክያንት ሙሉ ሱራው መታየት ያለበት በነሱ መነጽር ነው
ሲቀጥልም፥ አብዛኞቹ ኡለማዎች እንደሚስማሙት፥ ይህ ሱራ የመካ ሱራ ነው። መሐመድ "ነብይነቱን" እንደጀመረ አካባቢ የወረደ ሱራ ነው ማለት ነው
ቀጥለን እንደምንመለከተው፥ ይህንን ሱራ በእስላማዊ ምንጮች እና በታሪክ ስንመዝነው በብዙ ውሸቶች የተጠቀጠቀ ሱራ መሆኑን እናረጋግጣለን
♦ ውሸት 1
👉 እናንተም #አሁን የምግገዛውን (አምላክ አሁን) *ተገዢዎች* #አይደላችሁም (109:3)
በዚህ ስፍራ፤ አላህ መሐመድን ለቁሬይሾች "እናንተ እኔ የምገዛውን አምላክ አሁን አትገዙትም" ብሎ እንዲነግራቸው ሲያዘው እንመለከታለን። (109:1)
ነገር ግን ቁርአንን እና እስላማዊ ምንጮችን ስንመረምር የቁሬይሽ ጣዖታዊያን አላህን ይገዙት እንደነበር እንረዳለን
" «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ #የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ #ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም #አላህ ነው» #ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ " ሱራ 10:31
" ሰማያትና ምድርንም ማን ፈጠራቸው ብለህ ብትጠይቃቸው #አሸናፊው ዐዋቂው (#አላህ) በእርግጥ ፈጠራቸው #ይላሉ። " ሱራ 43:9
" ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸው፣ በእርግጥ #አላህ ነው፣ #ይላሉ።ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ። " ሱራ 43:87
" በላቸዉ #አላህን #የምትወዱ እንደሆናችሁ፣ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኅጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነዉ። " ሱራ 3:31
ቁርአን እንደሚመሰክረው፤ ቁሬይሾቹ አላህን የሚወዱ እሱን ፈጣሪ፥ ከሙታን አስነሺ፥ አስተናባሪ፥ ዐዋቂ በማለት የሚገዙት ሰዎች ነበሩ። እነርሱን ያስወቀሳቸው በእሱ ላይ ማጋራታቸው እንጂ ለእርሱ አለመገዛታቸው አልነበረም (ሱራ 16:20)
▶ እስላማዊ ምንጮችስ ስለ ቁሬይሽ አምልኮ ምን አሉ?
" ኢብን አባስ እንዲህ አለ፦ ነቢዩ ቁሬይሾች በሰጎን እንቁላል አጊጠውና በጆሮዎቻቸው የጆሮ ጌጥ አንጠልጥለው በተከበረው መስኪድ ቀጥ ብለው ለቆሙ ጣዖቶቻቸው ሲሰግዱ አዩ። እናም ስለዚህ ነቢዩ እንዲህ አሏቸው፦ እናንተ ቁሬይሾች ሆይ! ከአባቶቻችሁ ከኢብራሂምና ከኢስማኢል ሃይማኖት ሕግ ተላልፋችኋል፥ እነርሱ ሙስሊሞች ነበሩ። እነርሱም ሲመልሱ፦ ሙሐመድ ሆይ! እኛ የምናመልካቸው #ለአላህ ካለን #ፍቅር የተነሳና ወደ እርሱ ስለሚያቀርቡኝ ነው። "
[ Asbab al Nuzul Surah 3:31 ]
" የአላህ መልእክተኛ መለኮታዊ መገለጥን ከመቀበላቸው #በፊት ዛይድ ቢን አምርን ባልዳህ በተባለው ቦታ አጠገብ አገኘሁት #አሉ። የአላህ መልእክተኛ ከጣኦት አምላኪያን የተቀበሉትን ሥጋ ለዛይድ ቢን አምር አቀረቡለት። ነገር ግን አልበላም ብሎ ተቃወማቸውና እንዲህ አለ፦ እኔ ለድንጋይ አማልክቶቻችሁ የሰዋችሁትን አልበላም፥ #በአላህ_ስም ከታረደ በስተቀር #አልበላም "
[ Sahih Al Bukhari Vol 7, Book 67, Number 407 ]
" አብዱል ሙጣሊብ ጸጉሩን በጥቁር ቀለም በማቅለም የመጀመሪያ ሰው እንደሆነ ይነገራል። ምክንያቱም ጸጉሩ በፍጥነት ሸብቶ ነበር። ረመዳን በደረሰ ጊዜ ወደ ሒራ ይሔዳል፥ በዛም ወሩን በሙሉ ድኾችን ይመግባል። ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት ብቻውን ለመሆንና #የአላህን *ግርማ*፥ *ሞገሱን*፥ *ክብሩንና* *ኃይሉን* ለማሰላሰል ስለፈለገ ነው።.."
[ Mohammad Ridha, Mohammed the Messenger of Allah, translated by Dr.Mahmoud Salami, DAR al KOTOB al-ILMIYAH, Beirut-Lebanon 1998, page 15 ]
ይህ ታሪክ የተፈጸመው መሐመድ ነብይ ነኝ ብሎ ከማወጁ #በፊት መሆኑን ልብ ይሏል። ሲቀጥል አቡጣሊብ ያደርገው የነበረው ነገር በሙሉ፥ በቁርአን መሰረት ለአላህ የሚሰጥ አምልኮ ነው። ሱራ 59:22-24
እስላማዊ ምንጮች እንደሚመሰክሩት፥ ቁሬይሾቹ አላህን ያመልኩት ነበር። ያስወቀሳቸው በአላህ ላይ ማጋራታቸው እንጂ ጨርሶ ለእሱ አለመገዛቻቸው አልነበረም።
✒ ስለዚህ በ109:3 ላይ እኔ የምገዛውን አትገዙም ማለቱ #ሀሰት ነው!
🚩 ይቀጥላል