Isaiah 48 Apologetics dan repost
♦ ለወሒድ ቡጭርጭር የተሰጠ ምላሽ
እስልምናን እከላከላለሁ ክርስትናን እተቻለሁ በማለት የሚጦምር ወሒድ የሚባል ሰለምቴ አለ። ይህ ልጅ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና ቋንቋዎች (ዕብራይስጥ እና ግሪክ) እንደሚያውቅ በማስመሰል ትችት ለማቅረብ በመሞከር ይታወቃል
ዛሬም በክርስትና አስተምህሮ ውስጥ ሰው በተለያዩ ሁኔታዎች አምላክ ይሆናል የሚል አስተምህሮ እንዳለ ተናግሯል። ይህ እሳቤ Deification የሚባል ሲሆን ለክርስትና ፍጹም ባዕድ ነው። እስቲ እንስማው
አብዱል፦
ፓስተር ኃይሉ እና የእግዚአብሔሮች እሳቤ
በክርስትና አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ትምህርት እንዳለ ሁሉ እንዲሁ ሰዎች አማልክት ይሆናሉ የሚል ትምህርትም አለ፥ ይህ ትምህርት “ቴኦሲስ” ይባላል። “ቴኦሲስ” θέωσις ማለት ሰው አምላክ የሚሆንበት ሶስተኛው ደረጃ”divinization” ሲሆን ይህንን ደረጃ ለማሳለፍ ሁለት ደረጃዎችን ያሳልፋል፥ አንደኛው “ካታርሲስ” θέωσις ማለትም “ንፅህና” ሲሆን ሁለተኛው “ቴኦሪዎስ” θεωρός ማለትም “መላቀቅ” ነው። ይህንን ትምህርት ከግሪክ እሳቤ ወደ ክርስትና ውስጥ የቀላቀሉት የቤተክርስቲያን አበው ኢራንየስ፣ ጀስቲን ማርቲን፣ የአሌክሳንድሪያው አትናቴዎስ፣ የአሌክሳድሪያው ክሌመንት፣ የሂፓፑ አውግስቲን፣ የአንጾኪያው ቴኦፍሎስ፣ የሮሙ ሂፓቲየስ፣ የእንዚዛዙ ጎርጎርዮስ፣ የአሌክሳንድርያው ሳውርዮስ፣ የቂሳርያው ባስሊዎስ ናቸው። “አምላክ ሰው የሆነው ሰዎች አምላክ መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት ነው”God became a man so that a man how to become God” ይሉናል።
መልስ
ይህ ጸሐፊ በመላው ጽሑፉ ውስጥ ሁለት መሰረታዊ ቅጥፈቶችን ቀጥፏል። እንደተለመደውም የቋንቋ ግድፈቶችን አስገብቷል
▶ አንደኛው ቅጥፈት divinization ምን ማለት እንደሆነ በትክክል ሳያብራራ ለመሞገት መሞከሩ ነው። ምክንያቱም divinization ምን ማለት እንደሆነ በትክክል ቢያብራራ ኖሮ ሙግቱ ተቀባይነት ያጣ ነበር
Divinization ማለት አንድ አካል (ሰው ይሁን መልአክ) የቀደመ የአገልጋይ ባህሪውን *nature* ትቶ ሙሉ በሙሉ የባህሪ አምላክ (ሮሜ 1:20) ወደ መሆን ሲለወጥ ነው። ይህንን አስተምህሮ በክርስትና ውስጥ በፍጹም አናገኘውም
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ክብሩን #ሌላ እንደማይሰጥ ይናገራልና
" ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ ስሜ ተነቅፎአልና፤ ክብሬንም #ለሌላ አልሰጥም። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 48:11)
ክብሩን ለማንም አይሰጥም ማለት፥ የትኛውንም ፍጡር ወደ ባህሪ አምላክነት ደረጃ ከፍ አያደርግም ማለት ነው።
በተጨማሪም አማኞች በትንሳኤ አካል ከተነሱ በኋላ በመንግስተ ሰማይ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም እንደሚያመልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል
" ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፥ #ሌሊትና #ቀንም በመቅደሱ #ያመልኩታል፥ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።"
(የዮሐንስ ራእይ 7:15)
ቀድሞ የነበራቸውን የአገልጋይ ባህሪ (nature of a servant) ወይም ሰውነት ትተው ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ብለው ቢሆን ኖሮ፥ አምላኪ ባልሆኑ ነበር። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን እንግዳ ትምህርት አያውቀውም
P.s ከላይ "ካተርሲስ" የሚለው ቃል በግሪክ አስቀምጣለሁ ብሎ "ቴኦሲስ/θέωσις" የሚለውን ቃል ደግሞ አስቀምጦታል። ይህ ለቋንቋው እንግዳ መሆኑን ያሳያል
▶ ሁለተኛው ቅጥፈት የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች Divinization እንዳስተማሩ መናገሩ ነው። ለዚህ ንግግሩ ምንም አይነት መረጃ አልጠቀሰም። የጠቀሰውም ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ እሱ የሚለውን divinization አይደግፍም
በክርስትና man should be like God ሲሉ፥ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል በመሆኑ ባህሪው (character) ልክ እንደ እግዚአብሔር በፍቅር፥ በቅድስና፥ በጽድቅ፥ በእውነትና እነዚህን በመሰሉ አኗኗሮች የተሞላ መሆን አለበት ማለት ነው
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 3)
----------
9፤ እርስ በርሳችሁ #ውሸት #አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥
10፤ የፈጠረውንም #ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን #አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።
በዚህ ስፍራ ሐዋሪያው ጳውሎስ ውሸትን እንዳንነጋገር ሲያዘን እንመለከታለን። ለዚህም መንስኤው አሮጌውን ሰው ጥለን፥ በምሳሌው የፈጠረውን አዲሱን ሰው በመልበሳችን ምክንያት ነው።
ይህ በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠር እውነተኛ መሆን ማለት እንደሆነ ያሳያል። እግዚአብሔር እውነት ነውና
" ዳሩ ግን። እኔ #ቅዱስ ነኝና #ቅዱሳን #ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:15-16)
በዚህም ስፍራ እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና እኛም የሱ ልጆች ቅዱሳን መሆን እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
የእግዚአብሔር ባህሪ ቅድስና ነውና፥ እኛም በእርሱ አምሳል ስለተፈጠርን ቅዱስ መሆን አለብን። እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ሁኑ ማለት ይህ ማለት ነው።
🚩 የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶችም ያስተማሩት ይህንን ነው። እንጂ ቁጭ እግዚአብሔር ቅዱስ በሆነበት ቅድስና፥ ጠቢብ በሆነበት ጥበብ አይደለም
ሀይሉ ዮሐንስ በተለያዩ የስህተት ትምህርቶች የሚታወቅ ግለሰብ ነው። በተደጋጋሚ ሰውን ወደ አምላክነት የሚያስጠጉ ንግግሮችን እና ትምህርቶችን ተናግሯል፥ አስተምሯል። በንስሃ እንዲመለስ ምኞታችን ነው
አብዱል፦
ሥላሴን እና ተሰግዎትን ያረቀቁት እንዚህ አበው ይህንን ትምህርት አርቅቀውታል። ሰዎች አማልክት ይሆናሉ ተብሎ በሞርሞን ክርስቲያኖች የሚታመንበት እሳቤ ተጠያቂዎቹ እነዚህ አበው ናቸው። ይህንን ትምህርት የምስራቋ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ፣ የምዕራቧ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ እና አግሊካን ቤተክርስቲያን ዶግማቸው ላይ አለ፥ "መላእክትና ነብያት የፀጋ አማልክት ናቸው" የሚል ትምህርት አለ።
ፓስተር ኃይሉ ዮሐንስ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሊጠየቁ ይገባል፥ አብዛኛው ፕሮቴስታንት ይህንን እሳቤ ሳያጣራ ፓስተር ኃይሉ ዮሐንስን ይዘልፋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ በአንድ ወቅት፦ "ወደ ቤተርክስቲያን የምንመጣው በምድር ላይ ትናንሽ እግዚአብሔሮች ልንሆን ነው" ብለዋል። ቪድዮውን ያድምጡ!
መልስ
የስላሴ እና የትስግዖት ትምህርት በመላው ብሉይ እና ሀዲስ ኪዳን ስር መሰረት ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው። ማንም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አልጫነውም፥ አላረቀቀውም
ነገር ግን የትኛውም የቤተክርስቲያን አባት Divinization አላረቀቀም። ለዚህ መረጃ መጥቀስ አለብህ። ይህ ፍጹም ሀሰት ነው
ምስራቃዊያን አብያተክርስቲያናት ነብያትና መላእክት የጸጋ አማልክት ናቸው ማለታቸው Divinization አያመለክትም። በነሱ አስተምህሮ የጸጋ አማልክት ማለት ከእግዚአብሔር ሰምቶ የሚናገር ወይም ከእርሱ ዘንድ ስልጣንን የተቀበለ ባለስልጣን ማለት ነው። ዘጽ 7:1 እንደ እግዚአብሔር አያመልኳቸውም፥ የባህሪ አምላክ ናቸውም አይሉም
ሞርሞኖችን እንደ ክርስቲያኖች ማቅረብህ እጅግ አስቂኝ ነው። ሞርሞኖች በአንድ አምላክ የማያምኑ polytheistis ናቸው። ክርስቲያኖች አይደሉም። ክስ እንዳጠረህ ያሳያል
የአቡነ ጴጥሮስን ንግግር ከአውዱ ገንጥለህ ያለ ምንም ጥያቄ የሚነዱትን ተከታዮችህን ማታለል ትችል ይሆናል። ነገር ግን እኛ ጋር አይሰራም
እሳቸው ቀድመው "ወደ ቤተክርስቲያን የምንመጣው ንጹሃን፥ ቅዱሳን እና