Isaiah 48 Apologetics dan repost
♦ ሱራ 2:79 መጽሐፍ ቅዱስ መበረዙን ያሳያልን? (ክፍል 1)
ቁርአን ኦሪት፥ መዝሙር እና ወንጌል ፈጣሪ ለነቢያቱ የሰጣቸው መለኮታዊ ቃሎቹ መሆናቸውን ያስተምራል። ነገር ግን እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ከቁርአን ጋር መሰረታዊ የሆነ የአስተምህሮ ልየነት አላቸው። ይህ ማለት የቁርአኑ ጸሐፊ ከራሱ ዶግማ ጋር የሚቃረኑ መጻሕፍትን ነው እንደ ፈጣሪ ቃል ያጸደቀው ማለት ነው
ይህ በግልጽ እንደሚያሳየው የቁርአኑ ጸሐፊ ተውራት፥ዘቡር፥ኢንጅል ሲል የሚያወራው ስለምን እንደነበር አላወቀም። ፈጣሪ ደግሞ ሁሉን አዋቂ ስለሆነ፥ ቁርአን የፈጣሪ ቃል ሊሆን አይችልም
✒ ሙስሊም ወገኖችም ቁርአንን ከዚህ ሁኔታ ለማስመለጥ "መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል" የሚል መልስ ይሰጣሉ። ለዚህም መረጃ ይሆነናል ብለው ሱራ 2:79ን ይጠቅሳሉ። ነገር ግን ይህ አያ እንደዚያ ያስተምራልን?
▶ ዛሬ በጌታ ፍቃድ ይህ ጥቅስ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ እንደሌለበት በመረጃ እናሳያለን
" ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡ " ሱራ 2:79
1. ይህ ጥቅስ ስለ ወንጌል አይናገርም
▶ ሱራ 2:79 መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት ሊጠቀስ የማይገባበት አንዱ ምክንያት ስለ ወንጌል አለመናገሩ ነው። የሚናገረው ስለ ኦሪት ብቻ ነው። ስለዚህ መላው መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል አያስብልም። ቀጥለን እንደምንመለከተው ለኦሪቱም መረጃ አይሆንም
2. የተፍሲር ድጋፍ የለውም
እጅግ እውቅ የሆኑት ተፍሲር ኢብን ካቲር እና ተፍሲር ማውዱዲ እንደተረጎሙት፥ ይህ ጥቅስ የሚናገረው የመሐመድን ነብይነት ለማስተባበል ከኦሪት ያልሆነን ነገር በእጆቻቸው ጽፈው ከኦሪት እንደሆነ በማስመሰል አጭበርብረው ለመበልጸግ ይጥሩ ስለነበሩ የመዲና አይሁድ ነው።
▶ ነገር ግን ስለ ትክክለኛው ኦሪት #text ማለትም ስለ ኦሪት ቃላት መለወጥ ወይም መደለዝ ወይም መጥፋት በጭራሽ አይናገርም!
3. ይህ ጥቅስ የተወሰኑትን አይሁድ እንጂ መላውን የመጽሐፉን ባለቤቶች አያመለክተም
ከላይ በተፍሲሮቹም እንደተመለከትነው፥ ይህ አያ መላውን አይሁድን የሚያመለክት ሳይሆን፥ በመዲና የነበሩ የመሐመድን ነብይነት ለማስተባበል ከኦሪት ያልሆነን ነገር በእጆቻቸው ጽፈው ለመበልጸግ ስለሞከሩት የተወሰኑ አይሁድ ነው
▶ ታዲያ እነሱ ይህንን አደረጉ ማለት መላው አይሁድ በዚህ ተግባር ተሳትፏል ማለት ነው? ይህስ በአለም ዙሪያ ከሚገኘው የኦሪት text ጋር ምን ያገናኘዋል?
4. ቁርአን ኦሪትን በሚገባ የሚጠብቁ አይሁድ እንዳሉ መናገሩ
ሱራ 2:79 ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብረዛ ይናገራል ከተባለ ቁርአን እርስ በራሱ መጋጨት ይጀምራል። ምክንያቱም ኦሪትን በሚገባ የጠበቁ፥ ለገዛ ሀብታቸው ሲሉ የማያጭበረብሩ አይሁድ አሉ ይላልና
" ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለዉጡ ሲኾኑ፣ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደዉ፣ በዚያም ወደነርሱ በተወረደዉ የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ እነዚያ ለነርሱ በጌታቸዉ ዘንድ ምንዳቸዉ አላቸዉ፤ አላህ ምርመራዉ ፈጣን ነዉ። " ሱራ 3:199
▶ ያ ጥቅስ መበረዙን ካሳየ፥ ከሱራ 3:199 ጋር ግጭት ይኖራል። ቁርአን ለራሱ ባወጣው መስፈርት መሰረት ግጭት ካለበት ከፈጣሪ ቃልነት ተርታ ይወጣል (4:82) ስለዚህ 2:79 መበረዙን አያመለክትም
5. ከዚህ ጥቅስ ትንሽ ወረድ ብሎ (2:85) መላውን ኦሪትን የማይከተሉትን አይሁድ አላህ ይወቅሳል
" እርሱ (ነገሩ) እነርሱን ማውጣት በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው፡፡ በመጽሐፉ ከፊል ታምናላችሁን? በከፊሉም ትክዳላችሁን? ከእናንተም ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣት በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ " ሱራ 2:85
▶ ይህ ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው! ከላይ በቁ.79 ላይ መላው ኦሪት "እንደተበረዘ" ከተናገረ፥ አላህ ለምን አይሁዶችን ያንኑ መጽሐፍ በከፊል አመናችሁ ብሎ ይወቅሳቸዋችል? ለምንስ በመጪው አለም ውርደት አለባቸው አለ? 2:79 ኦሪት ተበርዟል ካለ 2:85 ትርጉም አይሰጥም።
🚩 ይቀጥላል