Isaiah 48 Apologetics dan repost
♦ ሱራ 2:79 መጽሐፍ ቅዱስ መበረዙን ያሳያልን? (ክፍል 2)
ባለፈው ክፍላችን እንዴት ቁርአን መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ብሎ እንደማያስተምርና፥ ሱራ 2:79 ለምን መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ እንደሌለበት ማየት ጀምረን ነበር
ዛሬም በጌታ ፈቃድ ይህ አያ ለዚህ አለማ መጠቀስ የሌለበትን ተጨማሪ ምክኒያቶች እናቀርባለን።
🚫 የዚህ ጽሑፍ አላማ፥ ቁርአን ኦሪት፥ መዝሙርና ወንጌል ተበርዘዋል ብሎ እንደማያስተምር ማሳየት ነው። በእርግጥም እንደዛ ብሎ የማያስተምር ከሆነ ከስር መሰረቱ የሚቃረኑትን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ፈጣሪ ቃል በማጽደቁ ከፈጣሪ ቃልነት ይወጣል
" ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡ "
▶ ይህ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት ምክኒያት፦
1.አላህ ቁርአን የወረደው ኦሪትን ለማረጋገጥ ነው ማለቱ
ከሱራ 2:79 ትንሽ ወረድ ብሎ አላህ ቁርአን የወረደው ኦሪትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ይናገራል
" አላህም ባወረደው (ሁሉ) ለእነርሱ «እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በኛ ላይ በተወረደው (መጽሐፍ ብቻ) እናምናለን» ይላሉ፡፡ ከርሱ ኋላ ባለው (ቁርአን) እርሱ ከነሱ ጋር ላለው (መጽሐፍ) አረጋጋጭ እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ፡፡ «አማኞች ከኾናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነቢያት ለምን ገደላችሁ?» በላቸው፡፡ " ሱራ 2:91
▶ በሱራ 2:79 ላይ ኦሪት መበረዙን አላህ "ከተናገረ" በቁ.91 ላይ ቁርአን የሚያረጋግጠው ከነሱ ጋር ያለውን ኦሪትን ነው ለምን አለ? የተበረዘውን መጽሐፍ ነው የሚያረጋግጠው?
2:79 ኦሪት ተበርዟል ካስባለ ቁርአንም ተበርዟል ማለት ነው። ምክንያቱም ቁርአን የወረደው ኦሪትን ለማረጋገጥ ነውና
2. ከ2:79 ከፍ ብሎ ቁርአን ኦሪትን አረጋጋጭ መጽሐፍ መሆኑን አላህ መናገሩ
ሱራ 2:79 መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት ምክንያት አላህ ከላይ እንዳየነው በ2:40-41 ቁርአን የኦሪት አረጋጋጭ መጽሐፍ መሆኑን መናገሩ ነው
" ከናንተ ጋር ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም (ቁርኣን) እመኑ፡፡ በርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ፡፡ በአንቀጾቼም ጥቂትን ዋጋ አትለውጡ፡፡ እኔንም ብቻ ተጠንቀቁ፡ " ሱራ 2:40-41
▶ የኦሪትን የፈጣሪ ቃልነት ከሚያረጋግጡ ጥቅሶች መካከል ያለ ጥቅስ፥ እንዴት ያ መጽሐፍ ተበርዟል ለማለት ይጠቀሳል? ይህ በቁርአን ውስጥ የማይፈታ መገጫጨትን ይፈጥራል
3. በመሐመድ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች መሐመድን በኦሪትና በወንጌል ውስጥ ተጽፎ ያገኙታል መባሉ
ሌላው እጅግ አስገራሚው ምክንያት፥ በመሐመድ ዘመን የነበሩ አይሁድ መሐመድን በኦሪት ውስጥ ተተንብዮ ያነቡታል መባሉ ነው
" ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጅል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)። " ሱራ 7:157
▶ አላህ በ2:79 የኦሪትን መበረዝ ከተናገረ፤ ለምን ለመሐመድ ነብይነት ማረጋገጫ ይጠቅሳል? የተበረዘ መጽሐፍ ነው የመሐመድ ማረጋገጫ? ነገሩ ግን 2:79 የኦሪትን መበረዝ አያሳይም
4. ቁርአን የአላህን ቃል ማንም መለወጥ እንደማይችል ይናገራል
2:79 መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት ሌላው ምክንያት ቁርአን ማንም የፈጣሪን ቃል መለወጥ እንደማይችል መናገሩ ነው
" ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ። #ለቃላቶቹ ለዋጭ #የላቸውም። ከእርሱ በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም። " ሱራ 18:27
▶ በዚህ ስፍራ በግልጽ እንደምንመለከተው የአላህን ቃል ማንም ሊለውጠው አይችልም። ከላይ እያየን እንደመጣነው ደግሞ ቁርአን የኦሪትን የፈጣሪ ቃልነት ይመሰክራል። ስለዚህ ኦሪት ሊበረዝ አይችልም
2:79 የኦሪትን መበረዝ ካሳየ በ15:27 አላህ ዋሽቷል ማለት ነው። ምክንያቱም እርሱ ያወረደው ቃል ተበርዟልና።
5. መሐመድ አይሁድና ክርስቲያኖች በእጃቸው ኦሪትና ወንጌል መኖሩኖ መናገሩ
ሱራ 2:79 ኦሪት ተበርዟል ለማለት መጠቀስ የሌለበት ምክንያት መሐመድ አይሁድ ኦሪት በእጃቸው እንዳለ መናገሩ ነው
Narrated Jubair bin Nufair:
from Abu Ad-Darda who said: "We were with the Prophet ﷺ when he raised his sight to the sky, then he said: 'This is the time when knowledge is to be taken from the people, until what remains of it shall not amount to anything." So Ziyad bin Labid Al-Ansari said: 'How will it be taken from us while we recite the Qur'an. By Allah we recite it, and our women and children recite it?' He ﷺ said: 'May you be bereaved of your mother O Ziyad! I used to consider you among the Fuqaha of the people of Al-Madinah. The Tawrah and Injil are with the Jews and Christians, but what do they avail of them?'"
(Jami at tirmihidi 2653)
▶ መሐመድ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ኦሪትና ወንጌል በእጃቸው አለ ነገር ግን አልጠቀማቸውም ሲል፥ ምንም እንኳ ታማኝ ቅዱሳት መጻሕፍት በእጅ ስለኖሩና ስለተጠቀሱ ብቻ በትክክለኛ መስመር መሆን አይደለም ማለቱ ነው።
ኦሪት ተበርዟል ብሎ ቢያስብ ኖሮ ይህ ንግግሩ ፈጽሞ የማይመስል ይሆናል። ለምን የተበረዘ መጽሐፍን እንደ ማነጻጸሪያ ይጠቀማል? ነገር ግን 2:79 ተበርዟል ስለማይል እንዲህ ሊል ቻለ
🚩 ይቀጥላል