Isaiah 48 Apologetics dan repost
✞ ሙስሊሞች በክርስትና ላይ ያነሷቸው 3 አስቂኝ ሙግቶች (objections) ✞
በተለያዩ ዘመናት በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ ሙግቶች ይነሳሉ። እነዚህ ጥያቄዎች በአይነታቸው የተለያዩ ሲሆኑ ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ ከሞላ ጎደል ተመልሰዋል
እነዚህ ሙግቶች በተለያዩ የእምነት ተቋማት የተነሱ ሲሆኑ ከእነዚህ የእምነት ተቋማት አንዱ እስልምና ነው።
ዛሬ በሙስሊም ወገኖቻችን ከተነሱት እጅግ አስቂኝና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሙግቶችን (objection) እንመለከታለን
1. እግዚአብሔር ጸጉሩን ተላጨ 😁
ሙስሊሞ ወገሞቻችን ከሚያነሷቸው አስቂኝ ሙግቶች ይህ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ይህ ሙግት የክፍሉን አውድ ያላማከለ ብቻ ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቋንቋ ያላወቀ ነው
" በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ #በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 7:20)
በመጀመሪያ የዚህ ክፍል ተደራሲ እግዚአብሔር ሳይሆን የአክዓብ ህዝብ ነው (ኢሳ 7:17) ይህን ህዝብ ነው እንደ አንድ ሰው የሚያናግረው። ህዝብን እንደ አንድ ሰው ማናገር የተለመደ ነውና (ዘዳ 18:15-16)
በቁ.20 እንዳስተዋላችሁት "የአሶር ንጉስ" እግዚአብሔር የተከራየው ምላጭ ተብሏል። "ተከራየ" የሚለው ቃል በኢንግሊዘኛው "hired" የሚል ነው። ይህም ማለት እግዚአብሔር በአሶር ንጉስ ስራውን ይሰራል ማለት ነው
እግዚአብሔር በመንግስታት አማካኝነት አላማውን መፈጸም ሲፈልግ ይህንን አይነት ቋንቋ ይጠቀማል
" አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ፤ #በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም መንግሥታትን #አጠፋለሁ፤ "
(ትንቢተ ኤርምያስ 51:20)
በባቢሎን መንግስት መንግስታትን እንዳጠፋ ሁሉ በአሶር ንጉስ አማካኝነትም (እርሱን በመጠቀም) የአክዓብን ህዝብ ጸጉር ይላጫል
▶ ጸጉሩን ይላጫል ሲል ምን ማለት ነው?
ጸጉር መላጨት ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ ከክብር ማውረድ፥ ስልጣንን ማሳጣት ማለት ነው። ለምሳሌ
" ሐኖንም የዳዊትን ባሪያዎች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ #ላጨ፥ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።"
(መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 10:4)
በዚህ ስፍራ ንጉስ ሔኖን የዳዊትን መልእክተኞች ጺም ሲላጭ እንመለከታለን። ይህ ትልቅ የማዋረድ ተግባር በመሆኑ ንጉስ ዳዊት ከዚህ ንጉስ ጋር ወደ ጦርነት ገብቷል
ይህ አይነት ቋንቋ ለሰው ልጆች ሲውል ቀጥተኛ ትርጉም የሚኖረው ሲሆን ለሀገራትን ሲሆን ተምሳሌታዊ ይሆናል። የኢሳ 7:20 ንግግር ደግሞ ለሀገር የዋለ በመሆኑ ተምሳሌታዊ ንግግር ነው
ስለዚህ በኢሳ 7:20 እግዚአብሔር በአሶር ንጉር አማካኝነት የአክዓብን ህዝብ ውርደት ላይ ይጥላል ማለት እንጂ እግዚአብሔር ጺሙን ይላጫል ማለት አይደለም
የአሶርን ንጉስ በምላጭ የመሰለውም ለዚሁ ነው። ከሚያመጣው ቅጣት ጋር ምስስሎሹ ይሄዳልና። (ይላጫል) ባቢሎንም በመዶሻ የተመሰለችው ለዚሁ ነው። (እሰብራለሁ)
መጽሐፍ ቅዱስን በቁም ነገር የሚያጠና ሰው እንዲህ ያለ ስህተት የመስራቱ እድል እጅግ ዝቅተኛ ነው።
2. እግዚአብሔር ከሴት ወለደ 😁
ሌላው በሙስሊም ወገኖቻችን ከተነሱት አስቂኝ ሙግቶች መካከል "እግዚአብሔር ከሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደ የሚል ነው
ይህ በእውነቱ ለሰሚም እንግዳ የሆነ ሀሳብ ሲሆን እጅግ ፈገግ ያሰኛል። ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስን ጽንሰ ሀሳብ ያልተገነበዘ ሀሳብ ነውና
" ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ኦሖላ #ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባ ደግሞ #ኢየሩሳሌም ናት። "
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 23:4)
በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ክፍል በሴት አንቀጽ የተገለጡት እንማን እንደሆኑ ቃል በቃል ተቀምጧል። ኢየሩሳሌምና ሰማሪያ ናቸው
ኢየሩሳሌምና ሰማሪያ የእስራኤል (የደቡቡ ክፍል) እና የይሁዳ (የሰሜኑ ክፍል) ዋና ከተሞች ናቸው። እንደሚታወቀው ከንጉስ ሰለሞን በኋላ እስራኤል ለሁለት ተከፍላ ነበር።
እነዚህን ከተሞች እግዚአብሔር ለመላው እስራኤልና ይሁዳ ህዝብ ወካይ አድርጎ እያቀረባቸው ነው።
▶ ምን ማለት ነው ልጆች ወለዱልኝ?
እግዚአብሔር ከእስራኤል ህዝብ ጋር በሲና ተራራ ስር ቃል ኪዳንን ገብቷል። የእስራኤል አምላክ እርሱ እንደሆነና ከእርሱ በቀር አምላክ እንደሌለም ነግሯቸዋል (ዘጽ 20:3)
በዚህ ቃልኪዳን ምክንያት ከዚህ ህዝብ የሚወለድ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ለእርሱ የተለየ ህዝብ ሆኗልና
"1፤2፤ እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር #ልጆች ናችሁ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔ አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አትንጩ፥ በዓይኖቻችሁም መካከል ራሳችሁን አትላጩ። "
(ኦሪት ዘዳግም 14:12)
ስለዚህ እግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለዱልኝ ሲል ከዚህ ህዝብ የተወለደውን የራሱን ህዝብ እንጂ በሰው ልጆች እንደሚደረገው ተራክቦ አይደለም
መጽሐፍ ቅዱስን በቁም ነገር የሚያነብ ግለሰብ ይህንን አይነት አስቂኝ ስህተት አይሰራም። አይደለም አንድ የእምነት ተቋም ቀርቶ
3. እግዚአብሔር አግብቷል 😁
ሌላው በሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚቀርበው አስቂኝ ሙግት እግዚአብሔር አንዲትን ሴት አገብቷል የሚል ነው
ይህም እንዲሁ እንግዳ ንግግር ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ጽንሰ ሀሳብና ቋንቋ ካለማወቅ የመነጨ ነው
" ፈጣሪሽ #ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 54:5)
በዚህ ስፍራ እንደ ሴት የተገለጠችው አንድ ሰው የሆነች ሴት ሳትሆን እስራኤል ናት። በዚህ ስፍራ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ አንዲት ሴት ያነጋግራታል።
እግዚአብሔር በእርሱና በህዝቡ መካከል ያለውን የአምላክና-የህዝብ ግንኙነት በጋብቻ መስሎ ይናገረዋል። ከእርሱም ውጪ ሌላ አምላክን ማምለክ መንፈሳዊ ምንዝርና ነው
" ከልብስሽም ወስደሽ በኮረብቶች ላይ በዝንጕርጕር ልብስ ያስጌጥሻቸውን #መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም #ገለሞትሽ፤ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም። "
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 16:16)
ባልነት የአምላክነት መገለጫ መሆኑ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቦታዎች ተጽፏል
" ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ እኔ #ባላችሁ ነኝና ተመለሱ ይላል እግዚአብሔር፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፥ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤"
(ትንቢተ ኤርምያስ 3:14)
እስራኤል በሴት መመሰሏ ይህ አገላለጽ ተምሳሌታዊ መሆኑን ያሳየናል። እንጂ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ እንደሆነ እና እስራኤልም የእርሱ ህዝብ እንደሆነ በግልጽ ተጽፏል
" ማደሪያዬም በላያቸው ላይ ይሆናል፤ እኔም #አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም #ሕዝብ ይሆኑኛል። "
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:27)
በዚህ መሠረት ፈጣሪሽ ባልሽ ነው ሲል የእስራኤል ህዝብ ፈጣሪ አምላኩ እንደሆነው እና እርሱም ህዝቡ እንደሆነ እንረዳለን እንጂ እግዚአብሔር እንደ ሰው ልጆች ከአንዲት ሴት ጋር ጋብቻን ማለት አይደለም
ይህንን አይነት ስህቱት ሰርቶ ለህዝብ የሚያስተምር አካል ራሱን ቆም ብሎ እንዲመረምር እንጠይቃለን።
ምክንያቱም ይህ ክፍል በጭራሽ መጽሐፍ ቅዱስ ለአምላክ የማይገቡ ባህሪያትን ይዟል የሚያስብል አይደለምና
ጌታ ይርዳን!