Isaiah 48 Apologetics dan repost
ጥያቄ ለሙስሊሞች
(🚩 ከዚህ በፊት በዚህ ቻናል በክርስትና ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን እንመልስ ነበር። አሁን ግን እኛም ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ተነስተናል)
እስልምና አንዱ ለሌላው ሀጢያት ምትክ መሆን አይችልም ብሎ ያስተምራልን?
ብዙ ጊዜ ሙስሊም ወገኖቻችንን "ኢየሱስ ለሃጢኣታችን ሲል ሞቷል፥ ደሙን አፍስሷል፥ ተሰቅሎልናል" ስንል አይቀበሉትም
ይህ የሆነበት ምክኒያት "ማንም ለማንም ሀጢያት መሞት አይችልም፥ ሁሉም በራሱ ሀጢያት ነው የሚጠየቀው፥ ይህ ነው ፍትሃዊነት" ስለሚሉ ነው
ነገር ግን እስልምና አንዱ ለአንዱ ሞት መሞት አይችልም ይላልን? ይህንን አስተሳሰብ ለመደገፍ የሚጠቅሱትን የቁራን ጥቅስ እንመልከት
ቁርዓን 6:164__ በላቸው "እርሱ (አላህ) የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ (ክፋን) አትሠራም። ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላይቱን ሸክም (ኃጢአት) አትሸከምም። ከዚያ መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው። ወዲያውኑ በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል
ተጓዳኝ ጥቅሶች:- ቁርዓን 17:13-15 35:18 39:7
▶ በዚህ ምዕራፍ አላህ ለመሐመድ፥ ማንም ተሸካሚ ነፍስ የሌላውን ሸክም መሸከም እንደማይችል ይነግረዋል። ሸክም የተባለውም ነገር ኃጢአት መሆኑ በቅንፍ ተቀምጧል።
ነገር ግን ይህንን ጥቅስ ከ16:22-25 ጋር ይጣረሳል፥ ምክኒያቱም እዚህ ጋር የመሐመድ መገለጦች ተረቶች ናቸው ያሉ ሰዎች የራሳቸውንም ያሳቷቸውን ሰዎች ሀጢያት ይሸከማሉ ይላልና
ቁርዓን 16:22-25 " አምላካችሁ አንድ ብቻ ነው፤ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት፣ ልቦቻቸው ከሐዲዎች ናቸው፤ እነሱም የኮሩ ናቸው፤ (አያምኑም) አላህ የሚደብቁትን የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ። ጥርጥር የለበትም፤ እርሱ ኩርዎችን አይወድም፡ ለእነርሱም ጌታችሁ (በመሐመድ ላይ) ምንን አወረደ? በተባሉ ጊዜ (እርሱ) የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦችን ተረቶች ይላሉ። (ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸው በሙሉ ከነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚገጥሟችሁ ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፤ ንቁ የሚሸከሙት ኃጢአት ምንኛ ከፋ
🚫 ቅድም ሰው የሌላውን ሸክም (ሀጢያት) አይሸከምም ብሎ አሁን አሳቾች የራሳቸውንም፥ ያሳቶቸውንም ሰዎች ሀጢያት ይሸከማሉ ይላል! የቱን እንቀበል?
▶ ጉዳዩ ግን በዚህ አላበቃም፥ ምክንያቱም ታማኝ ከሚባሉት ሀዲሳት መካከል በሆነው በሳኺህ ሙስሊም፥ መሐመድ አንድ ወገን ለሌላው ሀጢያት ተቀጥቶ ይህኛው ወገን እንደሚድን ያስተምራልና
Sahih muslim 6666
Abu Burda reported on the authority of his father that Allah's prophet said: no muslim would die but Allah would admit in his stead a jew or a christain in hell fire."
ሳኺህ ሙስሊም 6666
አቡ ቡርዳ በአባቱ ስልጣን እንደዘገበው፥ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አለ፡ የትኛውም ሙስሊም አይሞትም፥ ይልቁኑም አላህ በእሱ ቦታ አይሁድን ወይም ክርስቲያንንን ወደ ገሃነም እሳት ያስገባልና
ተጓዳኝ ጥቅሶች ሳኺህ ሙስሊም 6665 & 6668
▶ እዚህ ጋር በግልጽ አንድ አይሁድ ወይንም አንድ ክርስቲያን የአንድን ሙስሊም ቦታ ወስዶ ገሃነም እንደሚገባ ይናገራል
በሀዲስ ቁድሲ ደግሞ ክርስቲያኖች እና አይሁዶች የሙስሊሞችን ሀጢያትእንደሚሸከሙ ይናገራል
Ahadith Qudsi #8__Allah's messanger said: on the day of ressurrection, my ummah (nation) will be gathered into three groups, one sort will enter paradise without rendering an account (of their deeds). Another sort will be reckoned an easy account and admitted in to paradise. Yet another sort will come bearing on their backs heaps of sins like great mountains...Allah will ask the angels, though He knows best about them: Who are these people? They will reply: They are humble slaves of yours. He will say: Unload the sins from them and put the same-over the jews and christians: then let the humble slaves get into paradise by virtue of my mercy
🚫 እነዚህ በሙስሊም ሊቃውን ታማኝ የሚባሉ ምንጮች ሲሆኑ፥ ከቁርዓኑ በመቀጠል ተቀባይነት አላቸው
በእስልምና አንዱ የሌላውን ሀጢያት ሊሸከም እንደሚችል አይተናል። መሐመድም አላህም የተናገሩት ይህንን ነው
ታዲያ፥ ሙስሊሞች ለምንድነው ማንም የማንንም ሀጢያት አይሸከምም የሚሉት? ምናልባት መጀመሪያ የጠቀስነውን ክፍል ተመርኩዘው ሊሆን ይችላል
⚡ ነገር ግን ቁርዓኑ ማንም የማንንም ሀጢያት (ሸክም) አይሸከምም አይልም፥ ተሸካሚ የሆነ ማለትም ራሱ ሀጢያት ያለበት የሌላውን መሸከም አይችልም አለ እንጂ!
መሸከም የማይችለው፥ ራሱ ተሸካሚ የሆነ እንጂ ከሀጢአት የነጻ ወይንም ራሱ ተሸካሚ ያልሆነ መሸከም ይችላል
ስለዚህ ራሱ ተሸካሚ (ሀጢአተኛ) ያልሆነ አካል ከተገኘ፤ የሌላውን ሀጢያት የመሸከም ብቃት አለው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከክርስትና አስተምህሮ ጋር ይስማማል
በዚህ ጊዜ ይህ ሀጢአት አልባ ሰው መሐመድ ነው የሚሉ ወገኖች አይጠፋም። ነገር ግን በቁርዓን አላህ መሐመድን ንሰሃ እንዲገባ ሲነግረው እንመለከታለን።
ቁርዓን 48:2
በተጨማሪም መሐመድ በቀን ሰባ ጊዜ ንሰሃ ይገባ እንደነበር በሀዲሳት ተዘግቧል
ሳኺህ ቡኻሪ volume 8, book 75 number 39
መሐመድ ከሀጢአት ውጪ አልነበረም። እሱም እንደማንኛውም ሰው ሀጢአተኛ ነበር። ስለዚህ የሌሎች ሀጢያት መሸከም አይችልም! ተሸካሚ ነዋ!
በክርስትና ኢየሱስ ፍጹም ከሀጢአት ንጹህ ነው። ስለዚህ እሱ ሃጢአትን ለመሸከም ብቁ ነው። ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል
" እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:5)
ተጓዳኝ ጥቅስ፦ 1 ጴጥ 2:21-22
ነገር ግን የኢየሱስን ሀጢያት አልባ መሆንን ቁራንም ይመሰክራል። በእስልምና አስተምህሮ መሠረት ሰይጣን ሁሉም ሕጻናት ሲወለዱ ይነካቸዋል። መሐመድንም ሳይቀር ነክቶታል። ኢየሱስን ግን ሊነካው አልቻለም። ይህም ሊሆን የቻለው ፍጹም ሀጢአት አልባ በመሆኑ ነው!
ስለዚህ በዚህ በቁራኑ እና በሀዲሶቹ መሠረት ኢየሱስ የሌሎችን ሀጢያት መሸከም እንደሚችል አረጋግጠናል።
ሙስሊም ወገኖቻችንም ይህንን ተረድተው ወደተሰራላቸው የመስቀል ስራ እንዲመጡ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን
" በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም #ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:4)
ለራሱ ተሸካሚ ያልሆነው ኢየሱስ ሀጢአቶኦን በመስቀል ላይ ተሸክሞልዎታል!