Ibnu Abdellah


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan


الحق ما وافق الكتاب والسنة

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በአሏህ ላይ እውነተኛ መመካትን ተመካ

ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ:-

{አንድ ባሪያ እውነተኛ መደገፍን በአሏህ ላይ ቢደገፍ ተራራን ከቦታው ያስወግድ ነበር፣በማስወገድ ላይ ታዞ ከሆነ} መዳሪጁ ሳሊኪን(1/81)

✍ኢብኑ ዐብደሏህ
@ansarmesjidadama


كلما تمسكت بالسنة.كلما انفض الناس عنك فلا تحزن ما دمت تريد الجنة

{ሱናን አጥብቀህ በያዝክ ቁጥር፣ሰዎች ከአንተ በራቁ ቁጥር፣ጀነትን እስከፈለግክ ድረስ አትዘን}

✍ ኢብኑ ዐብደሏህ


በሶስት ነገሮች ሲቀሩ በሁሉም ነገር ላይ መረጋጋት መልካም ነው። እነርሱም

① ሰሏትን በጊዜዋ በመስገድ
②የሞተን ሰው በመቅበር
③ ተውበት በማድረግ

በእነዚህ ሶስት ነገር ላይ ችኩል ሁን

@ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

بسم الله الرحمن الرحيم

ቢድዐ ④

البدع ٤

ኡለሞች ከቢድዐ ሰዎች ና ከእነርሱ ጋር አብሮ በመቀማመጥ ዙሪያ ያላቸው አቋም

موقف العلماء من أهل البدع ومجالستهم

ኢማሙ በይሀቂይ ስለ ኢማሙ ሻፊዒይ ሲናገር እንዲህ ይላሉ:-

{ኢማሙ ሻፊዒይ በክህደት ና በቢድዐ ሰዎች ላይ ብርቱ ነበር፣እነርሱን በመጥላት ና ከእነርሱ በመራቅ ግልፅ አድራጊም ነበር} መናቂቡ ሻፊዒይ [1/469]

ኢማሙ አህመድ እንዲህ ይላሉ:-

{አንድ ሰው ቢድዐ ለሚሰራ ሰው ሰላምታ ካቀረበለት፣ይህን ግለሰብ ይወደዋል ማለት ነው} ጠበቃቱ አልሀናቢላ [1/196]

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል:-

{ቢድዐ የሚሰራን ሰው የወደደ አሏህ ስራውን ያበላሽበታል፣ከልብ ውስጥ የእስልምናን ብርሀን ያወጣበታል} ሸርሁ ሱና ሊልበርበሀሪ [138]

ኢማም ኢስማዒል አስ ሳቡኒ የአህሉ ሱናዎችን እምነት ከዘረዘሩ ቡሀላ እንዲህ ይላሉ:-

{ከዚህም በተጨማሪ አህሉ ሱናዎች የቢድዐ ሰዎችን በማዋረድ፣በማሳነስ፣በማራቅ፣በማገድ፣ከእነርሱም በመራቅ፣ባልደረባ ከመሆን ፣አብሮ ከመኗኗር በመራቅ፣እነርሱን በማኩረፍ ና በመራቅ ወደ አሏህ በመቃረብ ላይ ተስማምተዋል} አቂደቱ ሰለፍ [123]

ኢማም አል በገዊ እንዲህ ይላሉ:-

{ሰሀቦች፣ታቢዒዮች ና የእነርሱ ተከታዮች እንዲሁም የሱና ዑለሞች በዚህ ጉዳይ {የቢድዐ ሰዎችን መራቅ ና መጥላት} ላይ ተስማምተው አልፈዋል} ሸርሁ ሱና [226]

ስለ ቢድዐ ዙሪያ በዚሁ አቆማለሁ ርዕሱ ሰፋ ያለ ቢሆንም ካለችኝ ጥቂት እውቀት አንፃር ይበቃኛል

ወሏሁ አዕለም
@ansarmesjidadama


ሚዛኑ ቁርዐን ና ሀዲስ ነው።

{إذا رأيتم الرجل يمشي على الماء
ويطير في الهواء فلا تغتروا به حتى تعرضوا أمره على الكتاب والسنة } الشافعي

{አንድ ሰው በውሀ ላይ ሲሄድ፣አየር ላይ ሲበር ብታዩት ነገሩን ቁርዐን ና ሀዲስ ላይ እስታቀርቡት ድረስ እንዳትሸወዱ} ኢማሙ ሻፊዒይ

@ansarmesjidadama


يا أخي في الله لا تعرف الحق بالرجال ولكن اعرف الحق تعرف أهله
√{ወንድሜ ሀቅ በሰዎች አትታወቅም፣ነገር ግን ሀቅን እወቅ የሀቅ ሰዎችን ታውቃለህና}

✍ ኢብኑ ዐብደሏህ


ወንድሜ ትዳር ያዝ አትፍራ

ታላቁ ታቢዒይ ኢብራሂም አን ነኸዒ ለአንድ ግለሰብ እንዲህ አለው:-

{ሚስት አግባ፣ያ እርሷን በቤቱ እያለች የሚመመግባት ጌታህ አንተንም እርሷንም በአንተ ቤት ይመግባችሇል} ታሪኹ ኢብኑ ሙሀረዝ 105

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

بسم الله الرحمن الرحيم

ቢድዐ ክፍል ③

البدع

ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች ስለ ቢድዐ ውስን ነጥቦችን ተመልክተናል ስንቀጥል

ታላላቅ ዑለሞች ከቢድዐ ስለመራቅ ና ሱናን በመከተል ዙሪያ ምን አሉ?

أقوال أئمة الدين في إتباع السنة والنهي عن الإبتداع

ታላቁ ሰሀባ ሙዐዝ ኢብኑ ጀበል እንዲህ ይላል:-

{እናንተ ሰዎች ሆይ እውቀት ከመነሳቱ በፊት በእውቀት ላይ አደራ፣አዋጅ የእውቀት መነሳት ማለት የእውቀት ባለቤቶች መሞታቸው ነው።ከፈጠራ፣ፈጠራን ከመፍጠር ና ድንበር ከማለፍ ተጠንቀቁ፣በጥንቱ ነገር ላይ አደራ} ኢብኑ ወዳህ

የጥንቱ ነገር ሲል ነቢዪ የነበሩበት ዘመን ማለቱ ነው።

ታላቁ ሰሀባ ሁዘይፋ (ረዲየሏሁዐንሁ) እንዲህ ይላል:-

{ማነኛውም የነቢዩ ባልደረቦች አሏህን ያልተገዙበት ዒባዳ እናንተም እንዳትገዙበት፣የመጀመሪያው ትውልድ ለመጨረሻው ትውልድ ክፍት ቦታ አላስቀረም፣ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን መንገድ ተከተሉ} አል ኢባና

አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁዐንሁ) እንዲህ ይላሉ:-

{[ሱናን] ተከተሉ፣ፈጠራን አትፍጠሩ በእርግጥም ተበቅታችሇል} አዳሪሚይ ፊ ሱነን

አብደሏህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁዐንሁ) እንዲህ ይላሉ:-

{ሁሉም ፈጠራ ጥሜት ናት፣ሰዎች መልካም ነች ቢሉም} አላ-ለካዒይ

ኢማሙ አል አውዛዒ(ረሂመሁሏሁ) እንዲህ ይላሉ:-

{አደራህን የቀደምቶችን ፈና በመከተል ላይ ሰዎች ቢተዉክ እንኳን፣ተጠንቀቅ የሰዎችን አስተሳሰብ በንግግር ቢያሸበርቁልህ እንኳን፣ጉዳዩ ይገለፃል አንተ ቀጥተኛው መንገድ ላይ እስከሆንክ} ኽጢብ አል በግዳዲ

ሶፍያን አስ ሰውሪ [ረሂመሁሏሁ] እንዲህ ይላሉ:-

{ቢድዐ(ፈጠራ) ሸይጧን ዘንድ ከወንጀል የበለጠ ተወዳጅ ናት፣ከወንጀል ተውበት ይደረጋል፣ቢድዐ ግን ከእርሷ አትመለስም} አል በገዊ ፊ ሸርህ አስ ሱና

ከቢድዐ አትመለስም ሲባል አንድ ሰው ከቢድዐ የመመለሱ ተስፋ እጅግ በጣም የመነመነ ነው።ምክንያቱም ቢድዐን ዲን ነው ብሎ ስለሚያስብ ከወንጀል በተቃራኒ ወንጀል የሚሰራ ሰው ወንጀል መሆኑን ያምናል።

ኢማሙ ማሊክ {ረሂመሁሏሁ} እንዲህ ይላሉ:-

{ሱና የኑህ መርከብ ናት፣የተሳፈረባት ይድናል።ከእርሷ ወደ ሇላ ያለ ይሰምጣል} ሚፍታሁ አልጀና ሊሱዩጢይ

ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው
بسم الله الرحمن الرحيم
ቢድዐ ②
البدع

ባለፈው ስለ ቢድዐ የተወሰኑ ነጥቦችን አይተን ነበር ስንቀጥል

ቢድዐ ይከፋፈላልን??
هل البدعة تنقسم؟

በዲን ላይ የሚፈጠር ፈጠራን(ቢድዐን) ወደ ተለያዩ ክፍሎች ለመከፋፈል መሞከር ትልቅ ስህተት ና ጥፋት ነው።ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሉም(كل)በሚለው ሁሉንም ጠቅላይ በሆነ ቃል ተናግረው ሲያበቁ ቢድዐን ለመከፋፈል መሯሯጥ ከንቱ ተግባር ነው።

ኢብኑ ሀጀር አርበዒንን ባብራሩበት ኪታባቸው ውስጥ {ሁሉም ፈጠራዎች ጥሜት} ነው የሚለውን የነቢዩን ንግግር ሲያብራራ እንዲህ ይላል

[ ይህ ንግግር ሁሉን ጠቅላይ ከሆኑ ንግግሮች ውስጥ ነው፣ከእርሱ ምንም ተነጥሎ አይወጣም፣ይህ ሀዲስ ከዲን መሰረት ውስጥ ትልቁ መሰረት ነው] ጃሚዕ 223

ቢድዐ የሚያከፋፍሉ ሰዎች ቢድዐን ለመከፋፈል እንደመረጃነት የሚጠቀሙት የዑመርን(ረዲየሏሁዐንሁ) በተራዊህ ሰሏት ዙሪያ {ምን ያማረች ቢድዐ ነች} የሚለው ንግግር ነው።

ለዚህ ማምታቻ መልስ

① ዑመር (ምን ያመረች ቢድዐ ነች) ሲል የፈለገበት ቋንቋዊ ትርጉሙን ነው።ምክንያቱም ተራዊህን ሰሏትን ነቢዩ በጀመዐ ለተወሰነ ጊዜ አሰግደው በኛ ላይ ግዴታ እንዳይሆንብን ሰግተው ተዉት ስለዚህ በሸሪዐችን መሰረት አለው ማለት ነው።በሸሪዐ መሰረት ያለው ነገር ደግሞ ቢድዐ አይሆንም።

②ሰሀቦችም ሰላተ ተራዊህን ለየብቻ በመሆን የዑመር የመንግስትነት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ሰግደዋል ዑመር መንግስት በሆኑ ሰዐት ሰዎችን ነቢዩ መጀመሪያ በጀመዐ እንዳሰገዱት እርሱም ለሰዎች የሚያሰግዳቸው ኢማም በመመረጥ በጀመዐ እንዲሰግዱ አደረገ፣ምክንያቱም ነቢዩ በመሞታቸው ምክንያት ከአሏህ ዘንድ የሚወርደው ራዕይ የተቋረጠ በመሆኑ ሰላተ ተራዊህ ግዴታ ትሆናለች የሚለው ስጋት ተወግዷል ማለት ነው።

③ዑመር ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱናቸውን እንድንከተል ካዘዙን ቅን መሪዎች አንዱ በመሆናቸው እነርሱ የሚሰሩትን ስራ መስራት የነቢዩን ሱና እንደመስራት ይቆጠራል።

ሌላኛው ማምታቻ

{ከነቢዩ ህልፈት ቡሀላ ቁርዐን በአንድ መፅሀፍ መፃፉ፣የነቢዩ ሀዲስ መመዝገቡ፣ ሌሎችም የተሰሩ ፈጠራዎች አሉና መልካም የሆነ ቢድዐ በኢስላም አለ}

መልስ

① እነዚህ ነገሮች ከመዳረሻ(ወሳዒል) ውስጥ የሚመደቡ ናቸው።

②በነቢዩ ዘመን እነዚህን ነገሮች ከመስራት ያገዳቸው ነገር ወህይ እየወረደ ስለነበረ ቁርዐን ና ሀዲስ እንዳይደባለቁ ሲባል ነው።

③በነቢዩም ዘመን ሀዲስም ሆነ ቁርዐን ይመዘገብ ነበር ነገር ግን በአንድ መዝገብ አልነበረም የሚመዘገበው ስለሆነም ለመመዝገቡ በሸሪዐ መሰረት ያለው እስከሆነ ድረስ ከቢድዐ ውስጥ አይመደብም።

ይቀጥላል, ,,,,,,,,,,,,

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

بسم الله الرحمن الرحيم

ጥምቀት (baptism)

المعمودية

ምስጋና ለዛ በተፈጥሮ ጥምቀት ለጠመቀኝ ጌታዬ አሏህ ምስጋና ይገባው።የአሏህ ሰላም ና ረድኤት የተጠማቂዎች ሁሉ አለቃ በኾኑት በነቢዩ ሙሀመድ ላይ ይስፈን

ወንድሞቼ ቁርዐን የወረደው ሁሉን ነገር ለማብራራት፣ሰዎችን ከጥሜት አውጥቶ ወደ ምሪት ሊያቀና፣ከድቅድቅ ጨለማ ሊያወጣ፣እውነትን እንደ ፀሀይ ፍንትው ሊያረግ ነው።

እናም እስኪ ወንድሞቼ ቁርዐን ስለ ጥምቀት ምን አለ?

ሁላችንም እንደምናውቀው ማነኛውም ሰው ሲፈጠር ተፈጥሮዐዊ በሆነው ብቸኛ ሀይማኖት ኢስላም ላይ ነው።ከተወለደ ቡሀሏ ወላጆቹ አይሁድ ያረጉታል፣ከርስቲያን ያረጉታል፣እሳት አምላኪ ያደርጉታል።

قال النبي (كل مولود يولد على الفطرة.فأبواه يهودانه.أو ينصرانه.أو يمجسانه.كمثل البهيمة تنتج البهيمة هل ترى فيها جدعان) البخاري ١٣٨٥

(ሁሉም የሚወለድ ሰው በተፈጥሮ(በኢስላም ላይ) ነው የሚወለደው፣ወላጆቹ የሁዳ፣ክርስቲያን፣እሳት አምላኪ ያረጉታል እንጂ፣ልክ እንስሳ እንስሳን እንደምትወልደው፣በተወለደችው እንስሳ ላይ ከሰውነት ክፍሏ የተቆረጥ አካል ታያለህን?) ቡዃሪ 1385

ከዚህ ሀዲስ ምንረዳው አንዲት እንስሳ አንዲትን እንስሳ ምንም ዐይነት ጉድለት ሳይኖራት እንደምትወልደው የሰው ልጆችም ምንም ዐይነት የእምነት ጉድለት ሳይኖርባቸው በኢስላም ተነክረው ተጠምቀው ይፈጠራሉ ማለት ነው።

قال الله تعلى (صبغة الله ومن أحسن من الله صبغة ونحن له عبدون) البقرة ١٣٨

(የአሏህን (ተፈጥሮዐዊ) ጥምቀትን(መነከርን) ያዙ፣በመጥመቅም ከአሏህ ይበልጥ ያማረ ማነው?፣እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢ ነን በሉ) አል በቀራ 138

በቃ ስትወለድ በትክክለኛው እምነት ላይ ከተጠመቅክ ምን ያስፈልግሀል? የውሀ መጠመቅ? በጭራሽ!!!! የውሀ መጠመቅ ውጫዊ ቆሻሻን እንጂ ውስጣዊ ቆሻሻን አያፀዳም።

በዚህች የቁርዐን አንቀፅ ዙሪያ ኢማም ኢብኑል ጀውዚ የሰጡትን ማብራሪያ ላስፍር

قال(( سبب نزولها أن النصارى كانوا إذا ولد لأحدهم ولد فأتى عليه سبعة أيام صبغوه في ماء لهم.يقال له المعبودية ليطهروه بذلك

ይህች አንቀፅ የወረደችበት ምክንያት:- ከክርስቲያኖች ለአንዳቸው ልጅ በተወለደለት ጊዜ ከተወለደ ሰባት ቀን ካስቆጠረ ቡሀላ መጠመቂያ ተብሎ በሚጠራው ውሀ ላይ እንዲፀዳ ሲሉ ይነክሩት ነበር

يقولون هذا طهور مكان الختان.

ይህ የተገረዘበት ቦታ ንፅህና ነው ይላሉ

فإذا فعلوا ذلك قالوا صار نصرانيا حقا. فنزلت هذه الأية قاله ابن عباس

ይህን በፈፀሙ ጊዜ እንዲህ ይላሉ:- አሁን እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ በዚህም ምክንያት ይህች አንቀፅ ወረደች ይህን ያለው ኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁዐንሁ) ነው።

قال ابن مسعود وابن عباس وأبو العالية ومجاهد والنخعي وابن زيد (صبغة الله) دينه.

ኢብኑ መስዑድ፣ኢብኑ ዐባስ፣አቡል አሊያ፣ሙጃሂድ፣አን ነከዒይ፣ኢብኑ ዘይድን ጨምሮ (የአሏህ መጠመቅ) የሚለውን የአሏህ ሀይማኖት የሆነው ኢስላም ነው ብለውታል።

إنما سمي الدين صبغة لبيان أثره على الإنسان كظهور الصبغ على الثوب

በቁርዐን ውስጥ ዲንን መጠመቅ ተብሎ የተሰየመው ዲን በሰው ላይ በሚያደርገው ተፅዕኖ ነው።ልክ ልብስ ውሀ ውስጥ ሲነከር እርጥበቱ በልብሱ ላይ በሚያደርገው ተፅዕኖ ግልፅ እንደሚሆነው)) (ዛዱል ሙየሰር)

ሙስሊሙ ወንድሜ ሆይ:-

—ጥምቀት ተብዬውን በዐል እንዳታከብር

—እንኳን አደረሳችሁም አትበል

ምክንያቱም አንተ ስትፈጠር በኢማን ባህር ውስጥ ተጠምቀሀልና

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على نبينا محمد وآله وصحبه أجمعين. أما بعد

አሏህ ለኛ ይህን ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነውን የኢስላምን ፀጋ መርጦ ሲለግሰን ጎደሎ ነገር አይደለም ለኛ የመረጠልን የተሟላ ና ሁሉን ነገር የሚያጠቃልል አድርጎ ሰጥቶን ሲያበቃ ሙሉ ከተደረገልን ነገር መጨመርም ሆነ መቀነስ በፍፁም ተገቢ አይደለም።

ቢድዐ በቁርዐንም በሀዲስም የተወቀሰ ተግባር ነው።ቢድዐ በሙሉ ጥሜት ሲሆን ጥሜት በሙሉ ወደ እሳት ይመራል።

قال الله تعلى( وما ءآتكم الرسول فخذوه وما نهكم عنه فانتهوا) الحشر ٧

(መልዕክተኛውም የሰጣችሁን (ማነኛውንም) ነገር ያዙት፣ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከለከሉ) አል ሀሽር 7

ስለዚህ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያላዘዙበትን ነገር መፈፀም የተከለከለ ና ፈጠራ ይሆናል ማለት ነው።

قال النبي( وإياكم ومحدثات الأمور.فإن كل محدثة بدعة وكل بدعة ضلالة) أخرجه أحمد

{አደራችሁን አዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ፣አዲስ መጤ ነገር በሙሉ ፈጠራ ነው፣ፈጠር በአጠቃላይ ጥሜት ነው} አህመድ

ከፈጠራ በሙሉ ለመራቅ ና ለመጠንቀቅ ጤነኛ አዕምሮ ላለው ሰው ይህ ሀዲስ ብቻ በቂ ነበር

ቢድዐ(ፈጠራ) ምንድ ነው?

ما هو البدعة؟

البدعة في اللغة هو الإختراع على غير مثال سابق

ቢድዐ በቋንቋ ደረጃ : ቀዳሚ ምሳሌ የሌለው ፍልሰፋ ፈጠራ ነው።

البدعة في الشريعة: الأمر المحدث في الدين الذي لم يكن في عهد النبي ولا في عهد خلفائه الراشدين المهديين

ቢድዐ በሸሪዐ ደረጃ: በነቢዩ ና በቅን ተተኪዎቻቸው(ኹለፋዎች) ክፍለ ዘመን ያልነበረ (በዲን ላይ የተፈጠረ)አዲስ የተፈጠረ ነገር ነው።

ኹለፋዎች ማለት እነ አቡበከር አስ ሲዲቅ፣ዑመር ኢብኑ ኸጧብ፣ዑስማን ኢብኑ ዐፋን፣ዐሊይ ቢን አቡ ጧሊብ ናቸው።

ማሳሰቢያ!!

(በዲን ላይ የተፈጠረ) የሚለው አባባል አንድ ቁም ነገር ያስጨብጠናል።እርሱም ሰዎች ዛሬ ስለ ቢድዐ ሲነገር ቢድዐ ማለት አዲስ ነገር ነው በሚባሉ ሰዐት እንደዛ ከሆነማ ኮብልስቶን፣ማይክሮፎን እናም የመሳሰሉትን ቢድዐ ናቸው ይላሉ

①በቋንቋ ደረጃ ከሆነ እነዚህም ነገሮች ቢድዐ ናቸው ምክንያቱም በፊት አልነበሩምና
②ቢድዐ ስንል በዲን ላይ የተጨመረ አዲስ ፈጠራ ነው እንጂ በዱንያዊ ጉዳይ ላይ አይደለም እያልን ያለነው

وابتداع في الدين محرم لأن الأصل فيه التوقيف

በዲን ላይ አዲስ ፈጠራ መፍጠር የተወገዘ ና የተከለከለ ነው።ምክንያቱም ዲን በቁርዐን ና በሀዲስ መረጃ የተገደበ ስለሆነ

البدعة في الدين نوعان:

በዲን ላይ አዲስ ፈጠራ መፍጠር በሁለት ተካፍሎ ይታያል

الأول: بدعة قولية اعتقادية

አንደኛው: ንግግራዊ ና ዕምነታዊ ፈጠራ ሲሆን ጀህሚዮች፣ሙዕተዚላዎች፣አህባሾች የሚናገሯቸው ፈጠራዊ በነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሆነ በኾለፋዎች ዘመን ያልነበረ ንግግርን ይመስል።

الثاني: بدعة في العبادات.وهي أقسام

ሁለተኛው: በአምልኮ ዙሪያ የሚፈጠሩ ፈጠራዎች ሲሆኑ በብዙ ይከፈላሉ

الأول: ما يكون في أصل العبادة.

አንደኛ: በመሰረተ አምልኮ(ዒባዳ) የሚፈጠር ፈጠራ

ምሳሌ: በሸሪዐ ያልተደነገገ ና በሸሪዐ መሰረት የሌለውን አምልኮ አዲስ ሰሏትን ማምጣት፣አዲስ ፆምን መፍጠር እንደ መውሊድ የመሰሉ በዐሎችን መፈፀምን ይመስል።

እነዚህ እንግዲህ በሸሪዐ መሰረት የሌላቸው አምልኮዎች ናቸው።

الثاني:ما يكون من الزيادة في العبادة المشروعة

ሁለተኛ: የተደነገገ በኾነ አምልኮ ላይ የሚደረግ ጭማሪ ነው።

ምሳሌ:- አንድ ሰው ዙህር ሰሏትን ወይም ዐስርን አምስት ረከዐ ቢያደርግ ፈጠራ ይሆንበታል ምክንያቱም ዙህር ሰሏት ና ዐስር በሸሪዐ የተደነገጉ ከመሆናቸው ጋር ግን ሸሪዐ ካስቀመጠው አራት ረከዐ ገደብ ጭማሪ አለውና

ይህ እንግዲህ መሰረቱ የተደነገገ በኾነ አምልኮ ላይ በሚደረግ ጭማሪ የሚከሰት ፈጠራ(ቢድዐ) ነው።

الثالث:ما يكون في صفة أداء العبادة المشروعة

ሶስተኛ:የተደነገገ አምልኮ አፈፃፀም ሁናቴ ላይ የሚሆን ነው።

ምሳሌ:- ሰዎች ዛሬ የሚተገብሩት ተሰባስበው በቡድን ሆነው ዚክር ማድረግን ይመስል ዚክር የተደነገገ አምልኮ ከመሆኑም ግን የአፈፃፀም ሁኔታው ግን አልተደነገገም።

ስለዚህ ማነኛውንም አምልኮ በምንፈፅምበት ሰዐት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምን ሁኔታ ነበር የፈፀሙት የሚለውን መጠየቅ ግድ ይለናል።

الرابع: ما يكون بتخصيص وقت للعبادة المشروعة.لم يخصصه الشرع

አራተኛው:-የተደነገገ ዒባዳ ሆኖ ሸሪዐ ያልገደበው ጊዜ በመገደብ የሚሆን ነው።

ምሳሌ:- የሻዕባን ወርን ከ15 ቀን ቡሀላ በፆም ና ለይል ሰሏትን በመስገድ መነጠልን ይመስል ፆም ና የለሊት ሰሏት የተደነገጉ ቢሆኑም ነገር ግን በጊዜ ለመገደብ መረጃ ያስፈልጋል።

ይቀጥላል ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በሆነው

بسم الله الرحمن الرحيم

الحمدلله رب العالمين والصلاة والسلام على نبينا محمد وآله وصحبه أجمعين أما بعد

የጫት መዘዞች

نتيجة و أضرار القات

የጫት ቅጠል ቀይ ባህር ዳርቻ ና ምስራቃዊው የአፍሪካ ክፍሎች በስፋት የሚበቅል ጎጂ የእጽ አይነት ነው።

ኢትዮዺያ፣ኬንያ፣ሶማሊያ፣ሱዳን፣ደቡብ አፍሪካ፣ማዳካስጋር እና የመን በስፋት ከሚበቅልባቸው ሀገራት መሀል ዋነኞቹ ናቸው።

የጫት ቅጠል ጎጂ ና አደንዛዥ ከሆኑ የእጽ ዐይነት ለመሆኑ ሁለት አካሎች እንኳን የማይጨቃጨቁበት ጉዳይ ነው።

እንደ ኢስላም ጎጂ ነገሮች በጥቅሉ የተወገዙ ሲሆኑ በዚህም ዙሪያ የቁርዐን አንቀፆች በስፋት ሰፍረው ይገኛሉ።

قال الله تعلى{ ولا تلقوا بأيديكم إلى التهلكة} البقرة ١٩٥

{በእጆቻችሁም(ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ} አል በቀራ 195

ዑለሞች ጫት የተወገዘ ና የተከለከለ ለመሆኑ ካጣቀሷቸው የቁርዐን ጥቅሶች አንዱ ይህ ሲሆን ጫትን ማመንዠግ ወደ ተለያዩ የጥፋት መንገድ የሚወስድ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

قال النبي{كل مسكر حرام كل ما أسكر عن الصلاة فهو حرام أنهى عن كل مسكر أسكر عن الصلاة} المحلى ٧/٤٨٢

ነቡዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ{ ሁሉም አስካሪ ነገር የተከለከሉ ናቸው፣ሁሉም ሰላት ከመስገድ ያሰከረ ነገር የተከለከሉ ናቸው፣ከሁሉም ሰላትን ከመስገድ ያሰከረ ከሆነ አስካሪ እከለክላለሁ}

በአረብኛ ቋንቋ (سكر) የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከማወቅ ና ከማሰብ አዕምሮን የጋረደ ነገርን በሙሉ ያካትታል።

አንድ ሰው ጫትን ከማመንዠጉ በፊት ና ቡሇላ ያለው ፀባይ ሰማይ ና ምድር እንደሚራራቁት ይለያያል።

እነዚህ ጥቅሶች ለመጥቀስ ያክል እንጂከባህር ላይ በኩባያ እንደመጭለፍ ነው። ስለሆነም መረጃዎችን በሙሉ በዚህች አጭር ፁሁፍ ለማቅረብ ብንሞክር ሰዐቱ ይጠበን ነበር

የጫት ጉዳቶች

በጤናችን ዙሪያ ያለው ጉዳት

①የጥርስ መበስበስ
② የምግብ ፍላጎት መቀነስ
③ የስሜት መረበሽ
④ ከፍተኛ የድካም ስሜት
⑤ ስንፈተ ወሲብ
⑥ የአዕምሮ ህመሞች
⑦ የሆድ ድርቀት

በሀብታችን ዙሪያ ያለው ጉዳት

①የገንዘብ መባከን
②የጊዜ መባከን
③ባል ና ሚስትን ያፋታል
④ ወደ ሌብነት ይወስዳል

በዲናችን ዙሪያ ያለው ጉዳት

①ከኢባዳ መዘናጋት
②ወደ ዝሙት ይወስዳል
③ ሀሜት መናገር
④ ከሰላት መዘናጋት በተለይ የዐስር ና የኢሻ ሰላትን
⑤የወላጆችን ሀቅ አለመጠበቅ

እነዚህ ከጉዳቶቹ ጥቂቶቹ ናቸው።አዕምሮ ያለው ሰው መቼም ይህን ሁሉ ጉዳት እየተነገረው ጫት አመነዥጋለሁ ይላል ብሎ ለመገመት ይከብዳል።

ጫት አመንዣጊ ወንድሜ ሆይ

አሏህን ፍራ ዱዐ አብዛ ከዚህ አደንዛዥ ቅጠል ራስህን አርቅ ወደ እዚህ ከሚገፋፉ ጓደኞች ራቅ ቁርጠኛ ሁን ጊዜህን ሀብትህን፣አካልህን ተንከባከብ ከቻልክ ይህ ቅጠል ከሚኖርበት ና ከሚበዛበት ስፍራ ሽሽ

አሏህ ይወፍቅህ

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

بسم الله الرحمن الرحيم

ኢስላማዊ ሕክምና (ሩቃ)

الرقية

ክፍል ②

ከዚህ በፊት በነበረን ትምህርት የሩቃን ምንነትና ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶችን አይተናል። ከዚህ ስንቀጥል: -

هل يجوز للإنسان أن يطلب من غيره أن يرقيه؟

አንድ ሰው ከርሱ ውጪ ካሉ ሰዎች ሩቃ እንዲያረጉለት መጠየቅ ይቻልለታልን?

ሩቃ ማድረግ በመሠረቱ የተፈቀደ ቢሆንም ከሌሎች መፈለጉ ግን በአሏህ ባለህ መደገፍ(التوكل) ሙሉነት ላይ ጉድለት ነው።

ምክንያቱም ቡኻሪ ና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነገ የትንሳዔ ቀን ሰባ ሺ ያለ ምርመራ ና ያለ ቅጣት ጀነት ከሚገቡ ሰዎች አንዱ ባህሪያቸው ኢስቲርቃ የማያደርጉ ናቸው።

(هم الذين لا يسترقون) متفق عليه يعني لا يطلبون الرقية

ኢስቲርቃ ማለት ከሌላ ሰው ሩቃ ሊደረግላቸው የማይፈልጉ ማለት ነው።

እራሱን በራሱ በሩቃ ማከም የሚችል ሰው የትኛውም አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ በሽታ ሲገጥመው ወደ ሌላ ቦታዎች ከመሄዱ በፊት እራሱን በሩቃ ሊያክም ይገባዋል።

قال الله تعلى{ وننزل من القرءان ما هو شفاء ورحمة للمؤمنين} الإسراء ٨٢
(ከቁርዐንም ለምዕመናን መድሀኒት ና እዝነት የኾነን እናወርዳለን) አል ኢስራዕ 82

አንድ ሙስሊም ከቁርዐን ማነኛውንም አንቀፅ በማንበብ እራሱን ማከም ይችላል።ነገር ግን ሱረቱል ኢኽላስን፣ሱረቱል ፈለቅን፣ሱረቱ አንናስን ደጋግሞ በመቅራት እራሱን ቢያክም የተሻለ ነው።

ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸውን በነዚህ ሶስት የቀርዐን ምዕራፎች እራሳቸውን የሚያክሙ እንደነበሩና እነዚህ የቁርዐን ምዕራፎች መጠበቂያዎች በማለት እንደሰየሟቸው በሀዲስ ተዘግቧል

{فما تعوذ متعوذ بمثليهما} رواه مسلم

(በነዚህ ምዕራፎች እንደሚጠበቅ አምሳያ አንድ ተጠባቂ አልተጠበቀም) ሙስሊም

እንዲሁ ድግምት ቢሰራበት ትዕግስት በማድረግ እራሱን ሱረቱል በቀራ፣አያተል ኩርሲይን እናም ሌሎችንም የቁርዐን ምዕራፎች በራሱ ላይ እየቀራ ራሱን ማከም ይኖርበታል።

በአንድም ሰው ላይ ልቡን ሊያጠለጥል አይገባውም።እከሌ የሚያደረገው ሩቃ ፈውስ አለው ብሎ ራሱን ሊያታልል በፍፁም አይገባም።ማነኛውም ሩቃ የሚያረግ ሰው እርሱ ዘንድ ቁርዐንን ና ዚክሮችን ከመቅራት ያለፈ የተለየ ነገር የለም ፣እርሱ ዘንድ ያለው ሁላችንም ጋር አለ።

የሚገርም ነገር!!

አብዛሀኛው ሰው ውሀ ና የተለያዩ ቅባቶች በእቃ እያረጉ ሩቃ ለሚያደርግ ሰው ይልካሉ ለምን? አንተ ከእርሱ በምን ታንሳለህ?

ውሀውን አቅርበህ ፋቲሀን፣አያተል ኩርሲይን፣ሙዐዪዘተይኖችን እራስህ በውሀ ላይ እየቀራህ የምራቅህን ቱፍታ በመትፋት ለምን አታረግም?

የእርሱ ምራቅ ካንተ የተለየ በረካ አለውን? በጭራሽ!! ምንም የለውም ነገር ግን እራስህ ስተህ የወደቅክ ከሆነ ሌላው ሰው ሩቃ ቢያረግብህ ችግር የለውም።

ስለዚህ እራሳችንም ሆነ ቤተሰቦቻችን ሲታመሙ ወደ ሩቃ ቤቶች ከመሮጥ ይልቅ እራሳችን ማድረጋችን የተሻለ ነው።

ማሳሰቢያ !!! ይህን ታውቃለህን??

በዲነል ኢስላም ውስጥ ሸሪዐዊ ሩቃ አድራጊ የሚባል እንደ አንድ የስራ ዘርፍ የሚቆጠር ነገር የለም። ለምን በለኛ??

የትኛውም የነቢዩ ሰሀባ የሂይወት ታሪኩ ሲፃፍ ስራው ነበር ተብሎ የተነገረ ነገር የለም ይህ ነገር መልካም ቢሆን ኖሮ ሰሀቦች በቀደሙን ነበር

ማነኛውም ሙስሊም ቁርዐን መቅራት የሚችል ከሆነ እርሱ ሩቃ አድራጊ ነው።

በዚህን ጊዜ በሩቃ አድራጊነት ስም ንግድ ተስፋፍቷል ሩቃ ያደርጋል ገንዘብ ሊቀበል ሲል ሱብሀነሏህ በውሀ ላይ ወይም በተለያዩ ቅባቶች ላይ ቁርዐን እየቀራ በውድ ገንዘብ ይሸጣል ይህ ሁሉ ዲን ላይ ከመጫወት ውስጥ ይመደባል።

ሩቃ አድራጊውም ቢሆን የሰዎችን ልብ በእርሱ ላይ እንዲንጠለጠል ማድረግ የለበትም።እኔው ጋር ተመለስ ሌላ ቦታ መሄድ የለብህም መድሀኒቱ እኔ ጋር ብቻ ነው የሚገኘው ምናምን ማለት የለበትም።

ምክር ለሩቃ አድራጊዎች

አሏህን ፍሩ የሰዎችን ልብ በአሏህ ላይ እንዲንጠለጠል አርጉ ሰዎች እናንተ ዘንድ በሚመጡበት ሰዐት ቁርዐን እንዲቀሩ፣የጠዋት ና የማታ ዚክር እንዲያረጉ መምከር አለባችሁ እናንተ ዘንድ የሚገኘው ውሀ ሌላው ሰው ከሚቀራበት ውሀ የተሻለ ና የተለየ አለመሆኑን ለሰዎች አስተምሩ

በሩቃ ዙሪያ ልናውቀው ግድ ከሚለን ነገር አንዱ ሙከራዎች ማብዛት የለብንም።ለእያንዳንዱ ሩቃ አድራጊ በቴሌቭዥን መስኮት ፕሮግራም ኖሮት ሲያበቃ

አንዱ ይመጣና መኖሪያ ቤትህ ውስጥ ውሀ በጨው በጥብጠህ በግርጊዳ ዙሪያ ድፋ የሆነ ተንቀሳቃሽ ነገር ካየህ ድግምት የተሰራበት ቦታ እርሱ ነው ይላል።

አንዱ ደግሞ ስትተኛ በትራስህ ስር ቢላዋ አስቀምጥ ይላል።

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!! ኹራፋትን ደግመን በአዲስ መልኩ ለማሳደስ ነው ይህን ምናረገው??

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በህመምተኛ ላይ ሩቃ በሚያደርጉ ጊዜ ታማሚውን ደረቱን መታ መታ በማድረግ እንዲህ ይሉ ነበር

{اخرج عدوالله} ابن ماجه
(የአሏህ ጠላት ውጣ) ነበር የሚሉት

አንዳንዱ ጭራሽ ቁርዐን የተቀራበትን ውሀ በታማሚው ላይ እየደፋ እንዲህ የሚለውን የአሏህ ቃል ያነባል።

(በራሶቻቸው በላይ የፈላ ውሀ ይምቧቧባቸዋል) አል ሀጅ 19

ይህን ማድረግ ተገቢ አይደለም።

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

بسم الله الرحمن الرحيم

ምክር ለሙስሊሟ እህቴ

وصية لأختي المسلمة

الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين أما بعد:

ሴት ልጅ አሏህ ከፈጠራቸው ፍጡሮች ውብ ና ድንቅ ፍጡሮች መሀከል ዋነኛዋ ነች

በኢስላም ውስጥ ትልቅ ደረጃ ና ቦታ ያላት ስትሆን ነቢዩ ሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለእርሷ ነፃነት ማግኘት ሰፊውን ድርሻ ይይዛሉ

እናም ውዷ እህቴ ዛሬ ምዕራባዊያን ላንቺ ነፃነት እንሰጣለን፣ኢስላም ሴትን ልጅ ይበድላል በሚል ሙግት የኢማን ልብስሽን፣ጨዋነትሽን፣ዐይነአፋርነትሽን ነጭ ልብስ በሳሙና ሲታጠብ ቆሻሻው እንደሚወገደው ሙልጭ አድርገው አሯቅተውሻል።

በዚህ ርዕስ ዙሪያ ሌላ ጊዜ የምመለስበት ሲሆን ወደ ዛሬው ነጥቤ ስመለስ ላንቺ ካለኝ ከውስጥ የመነጨ ውዴታ ምክሬን ልለግስሽ ወደድኩ ከልብሽ አድምጪኝ

ቡኻሪ 5249 የሀዲስ ቁጥር ላይ እንዳሰፈሩት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሴቶችን ለብቻቸው ይመክሯቸው ነበር

ከዚህ ሀዲስ በመነሳት እኔም አንቺን ለብቻሽ ልምከርሽ

أولا: عليك أن تعلمي علم اليقين أن أحسن الأحكام وأقومها وأكملها وأجملها أحكام رب العالمين وخالق الخلق أجمعين.

አንደኛ: ከፍርዶች ሁሉ መልካም፣ትክክለኛ፣ሙሉ የሆነ፣ያማረ ፍርድ የዐለማት ጌታ የፍጡሮች ሁሉ ፈጣሪ የሆነው የአሏህ ፍርድ መሆኑን ከልብሽ ማወቅ አለብሽ

قال الله تعلى{ ومن أحسن من الله حكما لقوم يوقينون} المائدة ٥٠

{ለሚያረጋግጡ ሰዎች ከአሏህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው} ማዒዳህ 50

እናም ውድ እህቴ አሏህ በቁርዐን ውስጥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ በሀዲሳቸው ላንቺ የፈረዱልሽ ፍርድ በአጠቃላይ ላንቺ የሚጠቅም ቢሆን እንጂ የብናኝ ያህል እንኳ ጉዳት የለውም።

الثاني:عليك أن تدركي أن سعادتك وكرامتك مرتبطة تمام الإرتباط بهذا الدين وبالطاعة لرب العالمين والتزام أحكامه وشرعه.

ሁለተኛ: ያንቺ እደለኝነትሽ ና ክብርሽ ከዲኑ፣ለዐለማቱ ጌታ ከመታዘዝ፣የእርሱን ፍርድ ና ድንጋጌ አጥብቆ ከመያዝ ጋር ሙሉ ለሙሉ ቁርኝት እንዳለው ልታውቂ ይገባል።

وأن حظك ونصيبك من السعادة بحسب حظك ونصيبك من الطاعة والتزام.

የዕድለኝነትሽ ልኬት ና ድርሻ ለጌታሽ ባለሽ መታዘዝ እና በትዕዛዙ ባለሽ ጥብቁነት ድርሻ ና ልኬት ነው።

الثالث: عليك التنبه-وفقك الله- إلى أن المسلمة لها في هذه الحياة أعداء كثر يسعون للإطاحة بكرامتها وخلخلة سبيل عزها وفلاحها وسعادتها وإيقاعها في حمأة الرذيلة والفساد.

ሶስተኛ: ውዷ እህቴ - አሏህ ለመልካም ነገር ይግጠምሽና -ሙስሊም እንስት በዚህች ሕይወት ውስጥ ለእርሷ ከክብሯ ዝቅ ሊያደርጓት፣የበላይነቷን፣ነፃነቷን፣ዕድለኝነቷን ምታገኝበት መንገድ ላይ መዋኘት የሚፈልጉ፣እንዲሁም ወደ ውርደት ና ብልሹነት ጉድጓድ ሊጥሏት የሚሹ ብዙ ጠላቶች እንዳሉብሽ ልታውቅ ይገባል።

ويقدمون في سبيل ذلك كل ما يستطعون. ويأتي في مقدمة هؤلاء الأعداء الشيطان عدو الله وعدو الدين وعدو عباد المؤمنين

በዚህ መንገድ ላይ የሚችሉትን ነገር ሁሉ ይመፀውታሉ። ከጠላቶች ሁሉ የመጀመሪያው የአሏህ ጠላት፣የዲን ጠላት፣የሙዕሚኖች ጠላት የሆነው ሸይጧን በመጀመሪያነት ይገኝበታል።

ስለዚህ ውድ እህቴ ነቃ ልትይ ና ከእንቅልፍሽ ልትባንኚ ይገባሻል።ጠላት ያለበት ሰው ተኝቶ አያድርምና

الرابع: عليك أن تؤمني إيمانا جازما أن التوفيق والصلاح والإستقامة وتحقق الخير والكرامة بيد الله

አራተኛ: ለመልካም መገጠም፣የነገራቶች መስተካከል፣ፅናት ማግኘት እንዲሁም መልካም ነገር ና ክብር መጎናፀፍ በአሏህ እጅ መሆኑን ቁርጠኛ እምነት ልታምኚ ይገባሻል።


ውድ ሙስሊም እህቴ እነዚህ ምክሮች ላንቺ ካለኝ ክብር ና ውዴታ የመነጩ ሲሆኑ ካንቺ የምፈልገው አንዳቺ ጥቅም የለም አንብበሽ ተግባራዊ ከማድረግ ውጪ

t.me/ansarmesjidadama


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በኾነው

ኢስላማዊ ሕክምና(ሩቃ)

الرقية

بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين أما بعد:

በዚህ ነጥብ ዙሪያ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ነገር

አንደኛ: በሩቃ ስም የሚከፈቱ በውስጡ ሽርክ፣ዝሙት፣ የሚፈፀምባቸው ቤቶች በመብዛታቸው።

ሁለተኛ: አብዛኞቻችን ሩቃ እናረጋለን ነገር ግን ውጤቱ እምብዛም መሆኑ

ሶስተኛው: ሙስሊሞች በተለይ ሴቶች ና ወደ ገጠር አካባቢ ያለው ማህበረሰብ በሩቃ ስም ገንዘቡን ፣ ንብረቱን ለሼኽ ተብዬዎች እየገበረ መሆኑ ነው።

አሏህ ሱብሀነሁ ወተዐላ ሰዎችንም ጂኖችንም ሲፈጥር እርሱን ብቻ እንዲገዙ ና ከእርሱ ውጭ ያሉትን ጣኦት የተባለን ነገር በሙሉ እንዲርቁ ነው። ይህ የተፈጠርንለት ዐላማ ሲሆን ይህን የተፈጠርንለትን ዐላማ ለመፈፀም ስንጥር መንገዱ ሁሉ ወርቅ በወርቅ አይሆንም፣እውነተኞች መሆናችንን ለማረጋገጥ ሲባል በሂይወታችን ውስጥ ብዙ መከራዎች ና ፈተናዎች ይገጥሙናል።ፈተናውን በትዕግስት ያለፈ ሰው ቀሪውን የሂይወት ዘመኑን ደስተኛ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን በፈተናው የወደቀ ሰው ቀሪውን የሂይወት ዘመኑን በቁጭት ያሳልፋል።

ከሚገጥሙን ፈተናዎች አንዱ የተለያዩ በሽታዎች ናቸው።እነዚህ ፈተናዎች ወንጀሎቻችንን ለማበስ፣ደረጃዎቻችንን ከፍ ለማድረግ፣ወደ አሏህ እንድንመለስ ሲባል ነው።

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደነገሩን ማነኛውንም በሽታ አሏህ አያመጣም ለዚህ በሽታ መድሀኒት ያወረደለት ቢሆን እንጂ፣ያወቀው አውቆታል፣ያላወቀው አላወቀውም ብለዋል

ለዛሬ ላስቃኛችሁ የፈለኩት (ሩቃ) በመባል የሚታወቀውን ኢስላማዊ ሕክምና ነው።

ሩቃ ምንድ ነው?

ما هي الرقية؟

ሩቃ ማለት:ህመምተኛ እንዲፈወስ፣በሽታዎች እንዲወገዱ አሏህን መለመን ነው።

ሩቃ አሏህ ላይ ማጋራት (ሽርክ) የሌለበት እስከሆነ ድረስ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፈቅደዋሉ።

{اعرضوا علي رقاكم. لا بأس بالرقى ما لم يكن فيه شرك} مسلم

ነቢዩ ለሰሀቦቻቸው እንዲህ ይላሉ:{ የምታደርጉትን ሩቃ እኔ ዘንድ አቅርቡ፣በውስጡ አሏህ ላይ ማጋራት(ሽርክ) የሌለበት ሩቃ (በመደረጉ)ችግር የለውም} ሙስሊም 2200

ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ራሳቸው በሩቃ ይታከሙ እንደነበረ ከሰሀቦች ተዘግቧል።

ሩቃ ለፈውስ ሰበብ ይሆን ዘንድ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ምንድ ናቸው?

ما هي شروط الرقية ؟

الأول: أن لا تتضمن شركا. كدعاء الأولياء وغيرها

አንደኛ መስፈርት: በውስጧ በአሏህ ላይ ማጋራትን(ሽርክ) አቅፋ የያዘች መሆን የለባትም።ከአሏህ ውጪ ወሊዮችን መጣራት ይመስል።

الثاني:أن تكون بكلام الله سبحانه وتعلى. أو بأسمائه وصفاته.أو بما ورد في الأحاديث النبي صلى الله عليه وسلم

ሁለተኛው መስፈርት:በአሏህ ንግግር(በቁርዐን)፣በአሏህ ስሞች ና ባህሪያቶች መሆኑ ና ከነቢዩ ንግግር(ሀዲስ) በመጣበት መሆን አለበት።

الثالث:أن تكون مفهومة المعنى. بأن لا تكون عبارة عن كلمات غير مفهومة كالتميمة وغيرها.

ሶስተኛው መስፈርት: የሚነበበው ነገር ትርጉሙ የሚታወቅ መሆን አለበት።ሂርዝ ና ሌሎችም ትርጉም አልባ የሆኑ ቃላቶች መሆን የለባቸውም።

الرابع: أن لا يعتقد أنها مؤثرة بذاتها.فالقى هي من باب فعل الأسباب. فالأسباب لا تؤثر بذاتها.

አራተኛው መስፈርት:ሩቃዋ በራሷ ተፅዕኖ ማድረግ ትችላለች ብሎ ላያምን ነው።ሩቃ ሰበብ እንደማድረስ ሲሆን ሰበብ ደግሞ በራሷ ተፅዕኖ ማድረግ አትችልም።

ሰበቡን ያደርጋል መፈወስ ግን በአሏህ እጅ ነው።ልክ ነቢዩሏሂ ኢብራሒም ዐለይሂሰላም እንዳሉት

قال الله تعلى (وإذا مرضت فهو يشفين) الشعراء ٨٠

{በታመምኩም ጊዜ እርሱ(አሏህ) ያሽረኛል) አሽ ሹዐራዕ 80

በአሏህ ፍቃድ እነዚህ መስፈርቶች የተሟሉ ከሆነ ሩቃ ለፈውስ ሰበብ ይሆናል።

ለዛሬ በዚህ እናቁም፣በቀጣይ ክፍል በዚህ ርዕስ ዙሪያ የተለያዩ ነጥቦችን የምናይ ይሆናል። ኢንሻ አሏህ


በአሏህ ስም በጣም ሩህሩህ እና አዛኝ በሆነው

بسم الله الرحمن الرحيم

በወሊዮች ና በሷሊሆች( ደጋጎች)የአሏህ ባሮች ተወሱል የማድረግ ፍርዱ

حكم التوسل بالأولياء والصالحين

ክፍል ሁለት

ባለፈው ትምህርታችን እንዳሳለፍነው የተወሱልን ምንነት፣በስንት እንደሚከፈል፣ከእርሱም ውስጥ የሚፈቀደውን የተወሱል ዐይነት ተምረን ነበር ከዛው ስንቀጥል

ሁለተኛው ከተወሱል ዐይነት በሸሪዐ ያልተፈቀደ፣ያልተደነገገ የሆነ ነው።

القسم الثاني: توسل غير مشروع

በመጀመሪያው ክፍል ከዘረዘርናቸው ውጭ ያሉት በአጠቃላይ ከሞተ ሰው ምልጃን ና ዱዐን መፈለግ፣በነቢዩ ክብር(جاه) መለመን፣ ሌሎችንም ጨምሮ ካልተፈቀደው እና ከሚከለከለው የተወሱል ዐይነት ስር የሚመደቡ ናቸው።

በዝርዝር ስንመለከታቸው

አንደኛው: ከሞተ ሰው ምልጃን ና ዱዐን መፈለግ አይቻልም።

الأول: طلب الدعاء والشفاعة من الأموات لا يجوز

ምክንያቱም የሞተ ሰው ከሶስት ስራዎች ውጭ ስራው በአጠቃላይ ተቋርጧል።በሂይወት እያለ ዱዐ ማድረግ እንደሚችለው ከሞተ ቡሀሏ ግን ማድረግ አይችልም እንደውም ዱዐ ሊያረግልን ቀርቶ እኛ ነን ለእርሱ ዱዐ የምናደርግለት ዱዐ አርጉልን ብለን ብንጠራቸው እንኳን ጥሪያችንን አይሰሙም ይሰማሉ ቢባል እንኳን መልስ አይሰጡንም።

{ ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም።ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም።በትንሳኤ ቀን{እነርሱን በአሏህ ማጋራታችሁን} ይክዳሉ።እንደ ውስጥ አዋቂው ማንም አይነግርህም} አል ፋጢር 14

አዎ ወሏሂ ከውስጥ አዋቂው አሏህ ውጪ ማን ሊነግረን!!!

ሁለተኛው:በረሱል ክብር(جاه) ና በሌሎችም ክብር ይሁንብህ ብሎ ተወሱል ማድረግ አይቻልም።

الثاني: التوسل بجاه النبي أو بجاه غيره لا يجوز

በዚህ ነጥብ ዙሪያ ሰዎች ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ብለዋል ብለው የሚጠቀሙት የተቀጠፈ ሀዲስ አለ።

እርሱም {አሏህን በጠየቃችሁ ጊዜ በኔ ክብር ጠይቁት፣የኔ ክብር አሏህ ዘንድ ትልቅ ደረጃ አለውና}

ይህ ሀዲስ የተዋሸ ና በነቢዩ ላይ የተቀጠፈ ሲሆን በየትኛውም ትክክለኛ በኾኑ የሙስሊሞች መዛግብት አልሰፈረም። ሀዲሱ ትክክል አለመሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ለመረጃነት መጠቀም አይቻልም።

ሶስተኛው:በሰዎች በአካላቸው ይሁንብህ ብሎ ተወሱል ማድረግ አይቻልም።

الثالث: التوسل بذوات المخلوقين لا يجوز

በዚህ አባባል(بذوات) ውስጥ ያለችው (ب) ባ ፊደል ለመሐላ ከሆነች በአሏህ ላይ በፍጡሮች መማል ነው። ወይም ደግሞ መሐሏው በፍጡሮች ከሆነ ከአሏህ ውጭ በፍጡር መማል በሀዲስ እንደመጣው ትንሹ ሽርክ ነው። ከአሏህ ውጭ በፍጡሮች መማል ሽርክ ከሆነ በአሏህ ላይ በፍጡሮች መማል ምን ሊሆን ነው? ከባድ ነው።

ወይም ደግሞ በዚህ አባባል (بذوات) ውስጥ ያለችው (ب) ባ ፊደል ምክንያትነትን (ሰበቢያነትን) የምታመለክት ከሆነ አሏህ እርሱን ልንጠይቀውም ሆነ ልንለምነው በፍጡሮች ተወሱል ማድረግን ሰበብ አላደረገልንም።

አራተኛው፣ በፍጡሮች መብት (ሀቅ) በአሏህ ተወሱል ማድረግ ለሁለት ነገሮች ሲባል አይቻልም።

الرابع: التوسل بحق المخلوقين لا يجوز لأمرين

አንደኛ: አሏህ ለባሪያዎቹ ከትሩፋቱ ይለግሳቸው እንጂ አሏህ ላይ የማንም መብት (ሀቅ) የለበትም።

ሁለተኛው:ይህ አሏህ ለባሪያዎች ከትሩፋቱ የለገሳቸው መብት(ሀቅ) ለአሏህ ብቻ የተገባ ነው፣ሌሎች መብት የላቸውም። መብት በሌላቸውን ሰዎች ይሁንብህ ብሎ ተወሱል ማድረግ ምንም ጥቅም የሌለው ውሀ ወቀጣ ነው።

አሁንም በዚህ ነጥብ ዙሪያ ሰዎች ነቢዩ ብለዋል ብለው የሚጠቅሱት ቅጥፈት አለ።

ይሀውም { በጠያቂዎች ሀቅ (መብት) እጠይቅሀለሁ} የሚል ሲሆን ይህ ሀዲስ ውድቅ ነው፣ምክንያቱም ይህን ሀዲስ ከዘገቡት ሰዎች መሀከል ዐጢየቱል ዐውፊ የሚባል የሀዲስ ሊቃውንቶች ሀዲስን በማስተላለፍ ደካማ በመሆኑ የተስማሙበት ግለሰብ በውስጡ ስላለ ነው።

የሶስተኛ ና የአራተኛው ልዩነቱ ሶስተኛው በፍጡሮች በዛታቸው(አካላቸው) ተወሱል ማድረግ ሲሆን አራተኛው ደግሞ ለፍጡሮች ባላቸው መብት ይሁንብህ ማለት ሲሆን ሁለቱም የተከለከሉ ናቸው።

በዚህ ርዕስ ዙሪያ ባለችኝ ጥቂት እውቀት ላቀርብላችሁ የወደድኩት የእስካሁኑ ሲሆን ያልገባችሁ ነገር ፣ የተሳሳትኩት ነገር ካለ ብትጦቅሙኝ ደስ ይለኛል።


ወሏሁ አዕለም


በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ ና አዛኝ በሆነው

በነሺዳ ጥሪ (ዳዕዋ) ማድረግ ይፈቀዳልን??

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ : -

ጥያቄ: ትላልቅ ወንጀሎችን ሰውን መግደል፣መዝረፍ፣መጠጥ መጠጣት፣ ሌሎችንም ከባባድ ወንጀሎችን ለመስራት አላማ አድርገው የሚሰባሰቡ ሰዎች አሉ

እናም አንድ በመልካምነት ና ሱናን በመከተል የሚታወቅ ሸይኽ እነዚህን ሰዎች ከዚህ ተግባራቸው ሊያቅባቸው አሰበ

ነገር ግን እነዚህን ሰዎች ከዚህ ድርጊታቸው ለማቀብ ያለው አማራጭ አንድ ና አንድ ብቻ ነው።

እርሱም: - እነዚህን ሰዎች በመሰብሰብ በዲቤ እየመታ የተለያዩ ግጥሞች(ነሺዳዎችን) ማሰማት ነው። እናም ሸይኹ ይህን ባደረገ ጊዜ አብዛኞቹ ወደ አሏህ በመመለስ የማይሰግደው፣ንብረትን የሚዘርፍ የነበረው ሰው አሏህን መፍራት ና ከሀራም(የተከለከሉ) ነገሮች መራቅ ጀመር

ስለዚህ በዚህ አካሄድ ጥቅም ስላለው እንዲሁም እነዚህን ሰዎች ለመጥራት ከዚህ መንገድ ውጭ ሌላ አማራጭ የሌለ ከመሆኑ ጋር ለዚህ ሸይኽ ሰዎችን በዚህ መንገድ መጣራት ይፈቀድለታልን??


ሸይኹል ኢስላም(ረሂመሁሏህ) እንዲህ ሲሉ መለሱ: ይህ በጥያቄው ውስጥ የተወሳው ሸይኽ ሰዎች ከከባባድ ወንጀሎች እንዲታቀቡ አስቧል።ይህን ለማድረግ ደግሞ በዚህች ፈጠራ (ቢድዒይ) በሆነ መንገድ ቢሆን እንጂ አልቻለም።ይህም የሚያመለክተው ይህ ሸይኽ ወንጀለኞችን ወደ አሏህ እንዲመለሱ ማድረጊያ መንገድን አላዋቂ ወይም ደካማ መሆኑን ነው።ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ና ሰሀቦች እንዲሁም ታቢዒዮች ከነዚህ ሰዎች የከፉ ከሀዲያንን፣ፈሲቆችን፣ከባባድ ወንጀል ይፈፅሙ የነበሩ ሰዎችን ከፈጠራዊ (ቢድዒይ) ከሆነው መንገድ የተብቃቁ እንዲሆኑ በማደረጋቸው ሸሪዐዊ መንገድ ጥሪ(ዳዕዋ) ያደርጉ ነበር ። መጅሙዕ አልፈታዋ 11/620


{እውነተኛ ገጠመኝ}



ከአንድ ዳቦ ጋጋሪ ጋር ያደረኩት ቆይታ

እንደ አጋጣሚ እኔ በቡሉቱዝ የጀግናውን ሳዳት ከማል< የተቃጠሉት መስጂዶች> የሚለውን ሙሀደራ ከፍቼ ነበር

እናም ሳዳት ከንግግሩ መሀከል አንድን ታሪክ አንስቶ ነበር እርሱም አንዲት ሴት አንድ ልጅ ወልዳ ከዛ ቡሀላ መውለድ አልቻለችም ና ደውላ ያኡስታዝ ሰዎች የሆነ ሰው አለ አታዪውም፣አይነካሽም፣አዳዲስ 500 ብር ብቻ ከሰጠሽው መድሀኒት ይሰጥሻል። እናም እርሱ ጋር እንሂድ ብለውኛል,,,,,,,,,,,,)

ዳቦ ጋጋሪው እንዲህ አለኝ: ይህን የሚሰራው ሙስሊም ነው?

እኔም: አዎ ሙስሊም ነው

ዳቦ ጋጋሪው: ከእነርሱ እኔ እሻላለሁ ምክንያቱም እኔ ሰላት አልሰገድኩም እንጂ እንደዚህ ዐይነት ሽርክ አልሰራም፣አሏህ ሲያገራልኝ እሰግዳለሁ

እኔም: አዎ ትክክል ነህ፣ነገር ግን ሰላትንም ሆነ ሌሎችን አሏህ ያዘዘውን ነገር ብትሰራ ያምርብሀል አልኩት

ተመልከቱ ንፁህ አዕምሮ ነፃ ሆኖ ሲፈርድ፣ተውሒድ ደግሞ በተፈጥሮ የተሞረከዝ መሆኑን ታውቃለህ

እስኪ አሏህ ያግራልህ ብላቹ ዱዐ አርጉለት


አቂዳ ማለት ምን ማለት ነው??

አቂዳ ማለት:- በአሏህ፣በመላዒኮች፣በመፅሀፎች፣በመልዕክተኞች፣በትንሳዔ(ቂያማ) ቀን ፣በቀደር(በአሏህ ውሳኔ) በመልካሙም በክፉም ማመን ሲሆን አርካኑል ኢማን በማለት ይሰየማል።


ኢባዳ(አምልኮ) በሁለት ይከፈላል እነርሱም: -

አንደኛው: ተግባራዊ አምልኮ ሲሆን በሰውነት አካሎቻችን የምፈፅማቸው ድርቶች ናቸው ከእነርሱም ውስጥ ሰሏት፣ሀጅ፣ፆም የመሳሰሉት ሲሆኑ በልብ ከሚቋጠሩት እምነታዊ ከሆኑት አምኮቶች አንፃር ቅርጫፍ በመባል ይሰየማል።

ሁለተኛው: እምነታዊ (በልብ የሚቋጠሩ) አምልኮ ሲሆኑ ይህ ማለት አሏህ የሁሉም ፍጡሮች ጌታ መሆኑን፣አምልኮ የተባሉ ተግባሮች በአጠቃላይ ለእርሱ የተገቡ መሆናቸው ማመን እና በተጨማሪም አርካኑል ኢማን ተብለው የሚጠሩትን ማመን በመሆኑ ከተግባራዊ አምልኮ አንፃር መሰረት (አስል) በመባል ይሰየማል።ምክንያቱም የስራዎች ትክክለኝነት ና ብሉሹነት በልብ ውስጥ ባለው እምነት የሚለካ ና የሚገነባ በመሆኑ ነው።

ትክክለኛዋ አቂዳ ዲኑ በሙሉ የሚገነባበት መሰረት ነች፣እንዲሁም ስራዎችም ትክክለኛ የሚሆኑባት ነች

አሏህ በቀርዐኑ እንዳለው: ቁርዐን 18/110

እንዲህም ይላል:> ቁርዐን 39/65

እንዲህም ይላል: >ቁርዐን 39/2

እነዚህና ሌሎችም ብዛት ያላቸው የቁርዐን አንቀፆች አምልኮ የተባለ በአጠቃላይ ከሽርክ የፀዳ ካልሆነ ተቀባይነት እንደሌለው ያመላክታሉ።ለዚህም ሲባል ነበር መልዕክተኞች በአጠቃላይ ለዚህ ርዕስ ትኩረት ና የመጀመሪያነት በመስጠት ህዝቦቻቸው ከምንም በፊት አቂዳን ወደ ማፅዳት የተጣሩት የመጀመሪያ ጥሪያቸው አሏህን ተገዙ ከእርሱ ውጪ ያሉትን በአጠቃላይ አትገዙ ነበር የሚሉት

አሏህም እንዲህ ይላል: - ቁርዐን 16/36

ሁሉም መልዕከተኛ መጀመሪያ የህዝቦቹን ጆሮ የሚቆረቁርበት ነገር > ቁርዐን 7/59 ኑህ፣ሁድ፣ሷሊህ፣ሹዐይብ፣ሌሎችም በአጠቃላይ ይህን ነበር የሚሉት

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከነቢይነታቸው ቡሀላ አስራ ሶስት አመታትን ወደ ተውሂድ በመጣራት ና አቂዳን በማስተካከል ብቻ መካ ላይ ተቀምጠዋል ምክንያቱ የዚህ ዲን መሰረት በመሆኑ ነው።

ከዛም ቡሃላ ትክክለኛ ዱዐቶች፣ሷሊሆች፣የመጀመሪያ ስራቸው ወደ ተውሒድ መጣራት ና አቂዳን ወደ ማስተካከል ነበር

እኛም ቢሆን የነቢያቶችን ና የሷሊሆችን ፋና በመከተል የመጀመሪያ ስራችን ሊሆን የሚገባው ወደ ተውሂድ መጣራት ና አቂዳን ወደ ማስተካከል ሊሆን ይገባል።ዑመተል ኢስላም ዛሬ ባለንበት ጊዜ በብዙ የሽርክ ተግባሮች ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛልና


بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله والصلاة والسلام على من لا نبي بعده، وبعد :

حكم التوسل بالاولياء والصالحين

በወሊዮች እና በሷሊሆች(በደጋግ) ሰዎች ተወሱል የማድረግ ፍርዱ

ይህን ርዕስ ለመንሳት ያስገደደኝ ነገር ሰሞኑን አህባሾች ና ሱፍዮች ዘንድ ከየመን ሐቢብ ዑመር የሚባል ግለሰብ መምጣቱን አስከትሎ በዚህ ግለሰብ ላይ ድንበር ሲያልፉበት በመመልከቴ ሲሆን እነርሱ እንግዲህ ይህን ግለሰብ ወልይ ነው ብለው ስለሚገምቱ ነው።በዚህ ግለሰብ ላይ ድንበር ካለፉበት ነገሮች መሀከል ተወሱል የሚባለውን ታላቅ ዒባዳ አሳልፈው ሲሰጡና ሌሎችንም ሙስሊሞች ወደዚህ ተግባር ጥሪ ሲያረጉ ነበር።

ይህን አስመልክቶ አንዳንድ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እያታለሉ ይገኛሉ። እስኪ ይህን ርዕስ በሸሪዐ ሚዛን ጠለቅ ብለን እንመልከተው።

በመጀመሪያ ተወሱል(التوسل) ማለት ምን ማለት ነው?

التوسل: هو التقرب إلى الشيئ والتوصل إليه

ተወሱል ማለት: ወደ ማነኛውም ነገር መቃረብ ና መዳረስ ነው።

التوسل قسمان
ተወሱል በሁለት ይካፈላል

القسم الأول: توسل مشروع.وهو أنواع
የመጀመሪያው የተወሱል ዐይነት: የተፈቀደ ተወሱል ሲሆን እርሱም ብዙ ዐይነት ነው።

النوع الأول: التوسل إلى الله تعلى بأسمائه وصفاته

አንደኛው: በአሏህ ስሞች ና ባህሪያቶች ተወሱል ማድረግ ነው።

አሏህ እንዲህ ይላል: { ለአሏህም መልካም ስሞች አሉት፣በእርሷም ጥሩት} አል አዕራፍ 180

በዚህ የቁርዐን አንቀፅ መሠረት የአሏህን ስሞች ና ባህሪዎችን በመጥቀስ ወደ አሏህ ማድረግ እንደሚቻል ይጦቅመናል።

النوع الثاني: التوسل إلى الله تعلى بالإيمان والأعمال الصالحة التى قام بها المتوسل

ሁለተኛው: ተወሱል የሚያረገው ግለሰብ በኢማኑ እና በሰራቸው መልካም ስራዎች ወደ አሏህ መቃረብ ነው።

አሏህ እንዲህ ይላል: { ጌታችን ሆይ: እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን:አመንም፣ጌታችን ሆን ሀጢያቶቻችንን ለኛ ማር፣ክፉ ስራዎቻችንንም ከኛ አብስ፣ከመልካሞችም ሰዎች ጋር ግደለን} አል ዒምራን 193

ቡኻሪ ና ሙስሊም ከኢብኑ ዑመር ከዘገቡት ሀዲስም እነዚያ ሶስት ሰዎች በጉዞ ላይ ሳሉ መሽቶባቸው ለማረፍ ወደ ዋሻ ገብተው ቋጥኝ ተንከባሎ መውጫ መንገድ ዘግቶባቸው ሶስቱም ለአሏህ ብለው የሰሯቸውን መልካም ስራ በመጥቀስ ወደ አሏህ ተወሱል በማድረግ ከነበሩበት ጭንቀት ወጥተው ጉዟቸውን ቀጥለዋል

ይህ የሚያመለክተን በመልካም ስራዎች ተወሱል ማድረግ እንደሚቻል ነው።

النوع الثالث:التوسل إلى الله تعلى بتوحيده

ሶስተኛው: በተውሂድ (ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ)የሌለ መሆኑን በመመስከር ወደ አሏህ ተወሱል ማድረግ ነው።

አሏህ የነቢዩሏሂ ዩኑስን ዐሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሆነው ተወሱል ሲያረጉ እንዲህ ይላል:{ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም፣ጥራት ይገባህ፣እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ በማለት ተጣራ) አል አንቢያ 87

ከዚህ ምንረዳው አንድ ሰው አሏህን በተውሂድ ነጥሎ መገዛቱን እየነገረ ችግሮቹ እንዲቀረፉለት ወደ አሏህ ተወሱል ማድረግ ይችላል።

النوع الرابع:التوسل إلى الله تعلى بإظهار الضعف والحاجة والإفتقار إلى الله

አራተኛው: ድክመትህን፣ወደ አሏህ ፈላጊነትህን፣እንደዚሁም ወደ አሏህ ከጃይ መሆንህን እየገለፅክ ወደ አሏህ ተወሱል ማድረግ ነው።

አሏህ የነቢዩሏሂ አዩብ ዐለይሂ ሰላም ታሪክ ሲያወሳ እንዲህ ይለናል:{ አዩብንም ጌታውን ሲል በተጣራ ጊዜ አስታውስ} አንቢያ 83

ነቢዩሏሂ አዩብ ዐለይሂሰላም ችግራቸውን በመጥቀስ ወደ አሏህ ተወሱል አርገዋል።

النوع الخامس: التوسل إلى الله تعلى بدعاء الصالحين الأحياء

አምስተኛው: በሂይወት ባሉ ደጋግ የአሏህ ባሮች በዱዐቸው ተወሱል ማድረግ ነው።

ልክ ሰሀቦች ነቢዩ ዘንድ እየመጡ ችግራቸው እየነገሯቸው ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ችግራቸውን አሏህ እንዲያስወግድላቸው ዱዐ ያረጉ ነበር።ከነቢዩም ህልፈት ቡሀላ ሰሀቦች ወደ ነቢዩ ቀብር ሳይሆን የሄዱት ወደ ታላቁ ሰሀባ ዐባስ ረዲየሏሁዐንሁ ጋር በመምጣት አሏህን እንዲለምኑላቸው ይጠይቋቸው ነበር።

እነዚህ እንግዲህ ከሚፈቀደው የተወሱል ዐይነት የሚመደቡ ሲሆን በቀጣይ የሚከለከለውን የተወሱል ዐይነት በዝርዝር እናያለን

ወሏሁ አዕለም

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

78

obunachilar
Kanal statistikasi