ሰር አሌክስ ለመጨረሻ ግዜ ያኘኳት ማስቲካ በ390 ሺህ ፓውንድ ተሽጣለች።
በ27 ዓመት የዩናይትድ ቆይታቸው በጨዋታ ወቅት ከአፋቸው ማስቲካ አለመለዬቱ የፈርጊ መገለጫ እስከ መሆን ደርሷል። ግንቦት 2013 ከዌስት ብሮም ጋር 5 እኩል በተለያዩበት ጨዋታ በአሰልጣኝነት ለመጨረሻ ግዜ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ያኘኳት ማስቲካ ዛሬ በኢቤይ የኦንላይን መገበያያ ላይ ለሽያጭ ቀርባ በ390 ሺህ ፓውንድ ወይም 14 ሚሊዮን 714 ሺህ 420 የኢትዮጵያ ብር ገደማ ተሽጣለች።
ይህ ዋጋ ቡድኑን በተረከቡ የመጀመሪያዎቹ 10 አመታት ቢሆን አንድ ተጨዋች ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይስተካከላል፥ ከአሁኑ ደግሞ የሳንቼዝን የ5 ቀን ደሞዝ መሸፈን ይችላል።
1ሺህ 500ኛ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ያኘኳት የዚ'ች ማስቲካ ሽያጭ ገቢ ለዩናይትድ ፋውንዴሽን መርጃነት እንደሚውል ተነግሯል